የነፃነት ትግል ሁሉንም መራራ መከራ ለመቀበል መፍቀድ ነው። (ሥርጉተ ሥላሴ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 01.07.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ

የነፃነት ትግል መከራን ለመቀብል ተፈቅዶና ተወዶ የሚወሰድ እርምጃ ነው። የነፃነት ትግል የጫጉላ ጊዜ ሽርሽር አይደለም። ሊሆንም ከቶውንም አይችልም። ስለዚህ ዛሬ በግንቦት 7 ጸሐፊ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የደረሰው እግታ ከትግል መስምር አንዱ በመሆኑ ሊያደናግጥ የሚገባው የዓለም ፍጻሜ አይደለም። ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን እራሳቸውን ሰጥተው ነው ኢትዮጵያ ሀገራችን ከክብሯ ጋር ያቆዩን። ኢትዮጵያ በቀደሙት ጠላቶቿ ላይ ድልን በድል አነባብረው ነጻነትን ዘምን ከዘመን የቀለቡት – ለትውልዱ። ዐፄ ቴውድሮስ እራሳቸውን በሽጉጥ የገደሉት በመሬታቸው ነበር። ሌላ መሬት ሄደው አልነበረም። ይህ ለነፃነት የሚሰጥ የከበረ ስጦታ ነው። ዛሬ በወያኔ እስር ቤት የሚገኙት ጀግኖቻችንም ዬትም ሄደው አይደለም በመሬታቸው ላይ ነው ስቃያቸውን የሚያዩት። ዘርአይ ደረስ ደግሞ ገድሉ ዕጹብ ነው። አብዲሳ አጋ፤ ሞገስ አስገዶም፤ አብርሃም ደቦጭ ሁሎችም የተፈቀደላቸውን ጀግንነት የከወኑት በተሰጣቸው ቦታና በተፈቀደላቸው ጸጋ ነበር።  ለጀግና ሁሉ ቦታ የድርጊት መስኩ ነው። ሁሉ አጋጣሚ መሪውና መርሁ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌም ለድሎት ሄደው አይደለም የታገዱት። ለምንመኛት አንዲት ኢትዮጵያ፤ ለውዱ  – ለክብሩ  – ለፍቅሩ ኢትዮጵያዊነት እንጂ። ይህ የትውልዱን አደራ በድርጊት ያዘከረ ሰማዕትነት ነው – ለእኔ ለሥርጉተ።

ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ ስንት ጀግኖች በመሬታቸው መሥራትን፤ መኖርን፤ መተንፈስን፤ ማደግን፤ ታግደው ለእስር ለሞት፤ ለስደት፤ ለፍርሃትና ለስጋት፤ ለባይተዋርነትና ለሞት ተጋልጠዋል። ስለዚህ አንድ እራሱን ቆርጦ ለነፃነት ትግል ለሰጠ ጀግና የቃሉ መፈፀሚያ ውሉ ወርቅ ቀለበቱ ስለሆነ ጀግንነቱን ቢያፈልቀው እንጂ ፈጽሞ አያደበዝዘውም። ለወያኔ ሻ/ አጣናው ዋሴን ሱዳን አሳልፋ ከሰጠች በኋላ ገድሏቸዋል። ይህ ደም የጠማው አረመኔ የለመደበት ነው። መክለፍለፉ ሆነ አጋጣሚ ጠብቆ ማጥቃት መቻሉ የሚጠበቅ ነው። ቋሳ እኮ ለወያኔ የተፈጠረበት የተፈለፈለበት እጭነቱ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የመርህ  አልባነት ፖለቲካችንና አስከፊ ውጤቱ - ጠገናው ጎሹ

ወያኔ ፍጥረተ ነገሩን ሲመረመር በቀል ነው። ደሙ ትንፋሹ አካላቱ በሙሉ በጎሰኝነት የሰመጠ እንደ አራዊት የሚያስብና የሚኖር ሆኖ አብዛኞቻችን ግን የጠላታችን ማንነት ለመግለጽ ተሸማቀን ወያኔ ለማለት ድፈረት አንሶን ኢህአድግ እያልን እናቆለባብሰዋለን። እነሱ ያላፈሩበትን። ደፈረው የሚናገሩትን። ቁስለት!

የወያኔ ሃርነት ትግራይ እያፈረሰን እንዲቀጥል የፈቀድንለት እኛ እንጂ እሱ አቅም ኖሮት ፈጽሞ አይደለም። ካለ አቅምና ወርዱ የተሸከመው ህዝባዊ ሃላፊነት ስላልቻለው እንዲህ ነገን ፈርቶ ዙሪያ ገባውን በእሾኽ አጥሮ አልፎ ተርፎ ባህርማዶ ተሻግሮ በቀሉን ለማሳካት የሚንፈራፈረው። ስንት የማይታወቁ ኢትዮጵውያንን ሱዳን፤ ጁቡቲ፤ ኬኒያ፤ በመላ አረብ ሀገር ላይ እዬታፈኑ እጅግ በሚዘገንን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው ታሪክና ነገ የሚያወጡት ሃቅ ይሆናል።

ለዚህም ነው ጠላታችን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ስለመሆኑ ጠንቅቅን በሚገባ ማወቅ የሚገባን። አሁንም ትግሉ ተጠናክሮ መከራው አስተቃቅፎን፤ ፈተናው ውስጣችነን አገናኝቶት፤ ጥቃቱ እልህን አመንጭቶ እንዲመራን መፍቀድ ከእያንዳንዱ በግል ከሁሉም በጋራ የሚጠበቅ ግዴታ ይመስለኛል።

የዛን ብልህ ጀግና አበራ ሀይለመድህን ጥበብ ማንበብ – መተርጎም – ማመሳጠር የሚገባውም ከዚህ አንፃር ነው። ጀግናው የጠላቱን ብልቱን አገኘው። ድሉን በእጁ አስገባ። ስለምን ጣሊያን ወይንም ወደ ጀርምን ሄዶ እጁን አልሰጠም እያሉ ሲሞግቱኝ ለነበሩት የፋሽስቱ አስትንፋስ ዬት ድረስ ሊያካልል እንደሚችል ማመዛዘን የሚያስችል  ይመስለኛል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለእኔ አሁንም ጀግናዬ ናቸው። ጀግንነታቸው ላመኑበት ፍላጎት እራሳቸውን በመስጠት መቁረጣቸው ብቻ ሳይሆን ማናቸውንም መከራ ፈቅደው በመቀበላቸውም ነው። ተፈጥሯቸውም ለድርጅታዊ ተግባር ፍጹም የሰጠና ብቁ ነውና።

በተረፈ ግንቦት 7 እንደ ድርጅትነቱ፤ አባላቱ እንደ አባልነታቸው በመሰምራቸው የሚሰጣቸውን ግዳጅ ሊከውኑ ይችላሉ። ወይንም መመሪያ ሊጠብቁ ይቸላሉ።  ሌሎቻችን ግን በጠገግ ከግንቦት 7 መመሪያና መርህ ለማንጠብቀው የጠራ አቋም ይዘን በድፍረት ፊት ለፊት ወጥተን ድርጊቱን ማውገዝ አለብን። እንደ ተለመደው ትግላችን በግል እንቅስቃሴ ለማድረግ የፈቀድነው በጀመርነው መስመር መረጃውን መላክ አሁኑን ያስፈልገናል። ፍጥነት ድል ነው። ለዚህም መዳህኒቱ ኢጎን መታገልና ማሸነፍ –  ከውስጥ። በወያኔ እርር ድብን አደረገን እንላለን። ግን የእውነት ነውን?! ከሆነ — ቁስሉ የወያኔ ማሸንፍን እንዳያውጅ በአንድነት መነሳት ነው። እኔ ከዬትኛውም ድርጅት አመራር አልጠብቅም። ስለምን የራሴ መሪ እራሴ ነንኝና። ቁስለቴ ይመራኛል። እህህን ታቅፌ አልተኛም። የሚጋፉኝን እዬተጋፋሁ ሰላቢዎችን ሊጎትቱኝ የሚፈልጉትን እዬገፈተርኩ ከራሴ ጋር ታርቄ ለህሊናዬ አድራለሁ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትናንት ዱቄት ያሉን ዛሬ አለት ለሚሉን !

ዛሬ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የደረሰው ነገር በማናቸውም የነፃነት ትግሉ ቤተሰቦች በአነሰ – በበዛ ሊከሰት የሚችል ስለሚሆን ጠንቃቃነት ጠረናችን ሊሆን ይገባል። ችግሩን ቋያውን አብሮ ለመጋፈጥ መወሰን መቁረጥ መገኘት።  የፋመ ግፊት – የፋመ ድርጊት በፍጥነት! እርግጥ ነው ጉዳዩ ባለቤት አለው። ይህ መልካሙ ነገር ነው። ነገር ግን „ ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው።“ ዕድል ያላቸውም ወገኖች ይኖራሉ። ሊደመጡ የሚችሉ። ቀንም ዕድል አለው። ቦታም ዕድል አለው። ስለዚህ ሁሉም በመክሊቱ የተሰጠውን ለመከወን ይተጋ ዘንድ ዝቅ ብዬ እኔ ሎሌያችሁ አሳሰብኩኝ።

 

እርገት። በተረፈ አሁን ወደ ኋላና ፊት እዬሄዱ፤ የፖለቲካ ትንተና የሚሰጥበት ክፍለ ጊዜ ሳይሆን፤ እኔ – ለእኔ፤ ለራሴ ላደርግ የሚገባውን መከላከል ስጀምረው ሀገሬ ኢትዮጵያን አድብቶ እያጠቃት ካለ ባንዳ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጥቃት ትድናለች። ማልቀስን ለማስቆም በሁለት እግር ቆሞ ጠላትን በማናቸውም ሁኔታ መመከት። አቅምን አክብሮ – በአቅም በአግባቡ ለመጠቀም ጥሩ አደራጅና ጥሩ መሪ መሆን። ቅንንት። መጀመሪያ ግን እራስን ማደራጀት።

 

ኢትዮጵያዊነትን የሚጠብቅ አምላክ ጀግኖቻችን ይጠብቅ! አሜን!

 

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

3 Comments

  1. This could be a blessing in disguise the consequences of which can change the equation. Ginbot 7 had promised to take the struggle to the next level this year. The detention and perhaps extradition of ato Andargachew to Ethiopia should give his group incentive to act decisively with urgency because time is of the essence. It is time to activate sleeper cells and unleash hit squads and mean business. This is going to be a test for the group to see what it is made of and find out whether or not they are hostages of Esayas as some people claim. It is time to walk the talk!!!

    FREE ALL POLITICAL PRISONERS IN ETHIOPIA!!!
    LONG LIVE ETHIOPIA!!!!

  2. እጝዚአብሔር ይስትስህ የኒኮንጆ ትክክል አባባል ነው

  3. ስርጉት ወንዱ ሰቱ እንዳንች ልብ ቢያገኝ ምንኝኣ በታደለ. እንዳንች እውነት ተናግሮ የመስበት ማደር ነው. በታም ኮራሁብስ እህት አለም.

Comments are closed.

Share