የኢትዮጵያ የቀድሞ ዘመናዊ የጦር ሰራዊትን ታሪክ ሳንዘክር ስለ ኢትዮጵያ ማውራት አንችልም

የኢትዮጵያ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት መሰረቱ በዳግማዊ ምንሊክ ዘመን ይጣል እንጂ በተደራጀ መልክ የተመሰረተው ከፋሽሽት ኢጣልያ መባረር በኃላ መሆኑን በርካታ ድርሳናት ያስረዱናል።ዛሬ ቀና ብለን ስለ ኢትዮጵያ መናገር የቻልነው በጥንት አባቶቻችን ተጋድሎ ብቻ አይደለም።የቀድሞ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት ገድልም ትልቅ አስተዋፆ አለበት።ሱማልያ ”ቁርስ ድሬዳዋ ምሳ አዲስ አበባ” በሚል መፈክር በ1969 ዓም በከፈተችብን ጦርነት ከሞቃዲሾ በምታስተላልፈው የአማርኛ ራድዮ ፕሮግራም ፎክራብን ነበር።ምስራቃዊውን የሀገራችንን ክፍል ይዛ ነበር።
በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሚሊሻ ከመደበኛ ሰራዊት ጋር እልህ አስጨራሽ ውግያ አድርጎ ነፃነታችንን እና የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ያስከበረው የቀድሞ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት ነው።ኢትዮጵያውያን ብዙ ያልገቡን፣ክብር መስጠት ሲገባን ክብር ያልሰጠናቸው ክቡራን አሉን።
ክብር ለቀድሞ ዘመናዊ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት! የኢትዮጵያ የቀድሞ ዘመናዊ የ ጦር ሰራዊትን ታሪክ ሳንዘክር ስለ ኢትዮጵያ ማውራት አንችልም።

Source: ጉዳያችን GUDAYACHN BLOG

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማለዳ ወግ...ለአሚራና ቤተሰቦቿ የጎደለው ፍትህ ... !

1 Comment

  1. ያለተደፈረ እውነት። የዛሬያዋ ኢትዮጵያ መቆዬቷ በኢትዮጵያ ሠራዊትና በመሪው ነበር። ቢመርም መዋጥ ያለበት ሃቅ ነው። ትጥቅ አስፈቺ ዘማቸው ሰፊ ነበር። ኢትዮጵያ ግን በልጆቿ ክብሯን አስከብራለች! ወደፊትም! ትናንትም ዛሬም ወደፊትም በቀድሞ የእግርኛ፤ የባህርና የአዬር ኃይላችን ጀግኖቼ እኮራለሁ። በህይወት ያላችሁትን እግዚአብሄር ይጠብቅልኝ። ህይወታችሁ ያለፉትም የክብር ሞት ስለሆነ ነፍሳቸውን አርያመ ገነት ያስገባልኝ። አምላኬ! አሜን!

    የጀግና ጀግንነት ወርቅ ነው። ይነጥራል ይፈልቃልም!
    ለሱማሌ ያለስገዛችሁኝ ጀግኖቼ ናችሁ!

Comments are closed.

Share