የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት የአራተኛ መደበኛ ስብሰባ የአቋም መግለጫ

በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ተቃዋሚነት ጎራ የተሰለፉ ኃይሎች በቅድሚያ ትግላቸውን በብሔራዊ ነፃነት ዙሪያ ያድርጉ!

እኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት ከሰኔ ፲፬ – ፲፭ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. (June 21 – 22, 2014) አራተኛ መደበኛ ስብሰባችንን በተሣካ ሁኔታ አካሂደናል። በሁለት ቀናት ጉባኤያችን የሥራ አስፈጻሚ እንዲሁም የቁጥጥርና ፍተሻ ኮሚቴዎች ያቀረቧቸውን የ፮(ስድስት) ወራት የድርጅቱን የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርቶችን አዳምጠን ጠቃሚ ውይይት አድርገናል። ድርጅቱ ያከናወናቸው መልካም ተግባሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በአፈፃፀም የታዩ ድክመቶች እንዲታረሙ በማስገንዘብ፣ ለድርጅቱ ዓላማ ዳር መድረስ የሚያግዙ የሚከተሉትን አቋሞች ወስደናል።
፩ኛ) የኢትዮጵያውያን ሉዓላዊነት፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም መከበር እና የግዛታዊ አንድነት መጠበቅን በተመለከተ፦

በዘረኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሉዐላዊ መብቱን የተነጠቀ፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅምም ለባዕዳን ተላልፎ የተሸጠና የአገሪቱ ግዛታዊ አንድነት ፈጽሞ ያልተጠበቀ መሆኑን ከቀረቡት ተጨባጭ ማስረጃዎች ተገንዝበናል። የአገሪቱን የባሕር በር ወያኔ ተገዶ ሣይሆን ወዶ እና ፈቅዶ ለሻዕቢያ ከሸጠው ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ የተነሣም ኢትዮጵያ መተናፈሻ የሌላት ዝግ መሬት ሆናለች። ስለዚህ ኢትዮጵያ የወጪ እና የገቢ ንግዷን ጂቡቲን በመሣሰሉ ትናንሽ አገሮች መልካም ፈቃድ ላይ እንዲመሠረት በማድረጉ በዕድገቷ ላይ ከፍተኛ መሠናክል ሆኗል። «ወደብ ለሌለው አገር ስለ ዕድገት አይታሰብም» ማለት ባይቻልም እንኳን፣ የዕድገት ግስጋሴው ግን ወደብ ካላቸው ጋር ፈጽሞ ሊወዳደር አይችልም።

ከዚህ በተጨማሪ በመሬት ስፋት አንፃር ከአየርላንድ ሪፑብሊክ ግዛት የሚበልጥ ከ፰(ስምንት) ሚሊዮን ሄክታር በላይ የሆነ የአገሪቱ ለም እና ድንግል መሬት ለ፺፱(ዘጠና ዘጠኝ) ዓመታት ለሕንድ፣ ለቻይና፣ ለፓኪስታን፣ ለግብፅ፣ ለጅቡቲ እና ለሌሎችም አገሮች ባለኃብቶች በጣም በርካሽ ገንዘብ ተሸጦ ገበሬው ጦም አዳሪ እና አገር-የለሽ ሆኗል።

ከምዕራባዊ የአገሪቱ ድንበር በቁመት ከሰሜን ወደ ደቡብ ፩ሺህ፮፻(አንድ ሺህ ስድስት መቶ) ኪ.ሜ.፣ በወርድ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ከ፶(ሃምሣ) እስከ ፷(ስድሣ) ኪ.ሜ. ጥልቀት ያለው ለሙ እና ድንግሉ መሬት ለሱዳን በገጸ-በረከትነት ተሰጥቷል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጲያ፣ ሃይማኖት እና ብሄር ካለፈው እና ከአሁኑ ታሪካችን ተምረን ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እንታገል

በቋንቋ ላይ የተመሠረተው የፌደራል አገዛዝ አደረጃጀት የሕዝቡን ነባር የአንድነት እና የአብሮነት ስሜት ንዶታል። ይህንንም ወያኔ ሆን ብሎ ኃይልን በአካተተ ፕሮፓጋንዳ ጭምር በመታገዝ የሕዝቡን የአንድነት እና የኢትዮጵያዊነት ስሜት በእጅጉ እንዲሸረሸር አድርጓል።

በዛሬዋ ኢትዮጵያ ከዐማራ የጸዱ ክልሎች ለመመሥረት በተያዘው ዘር የማጽዳት እና ዘር የማጥፋት ዘመቻ ዐማራው የማይኖርባቸው ክልሎች ተፈጥረዋል።

ይህ አጠቃላይ ሁኔታ ተዳምሮ ሲታይ የሕዝቡ ሉዓላዊነት፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም እና ግዛታዊ አንድነት ያልተጠበቀ እና ያልተከበረ መሆኑን ለመገንዘብ አይከብድም። በመሆኑም ዛሬ በትግሬ-ወያኔ ተቃዋሚነት ጎራ የተሰለፉት ኃይሎች የትግል ሥልታቸውን ዳግም ሊመረምሩ ይገባል። በአንድ አገር ላይ ሰላም፣ ዕኩልነት፣ ዲሞክራሲ እና ፍትኅ የሚሠፍኑት በቅድሚያ አገሪቱ ኅልውናዋ ሲጠበቅ ነው። ስለሆነም «በቅድሚያ የመቀመጫዬን» ነውና፣ የተቃዋሚ ድርጅቶች የትግሉን አቅጣጫ በቅድሚያ በብሔራዊ ነፃነት ዙሪያ እንዲያደርጉት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።

፪ኛ) በዐማራው ላይ የሚካሄደውን ሁለንተናዊ ጥቃት በተመለከተ፦

ባለፉት ፶(ሃምሣ) እና ፷(ስድሣ) ዓመታት ብቻ ሣይሆን፣ ከዚያም ቀደም ሲል ጀምሮ፣ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሱ የውጭ እና የውስጥ አጥፊ ኃይሎች የመጀመሪያው የጥቃት ዒላማቸው የሚያደርጉት «ዐማራ» የተሰኘውን ነገድ መሆኑ ይታወቃል። ለዚህም የረዥም ዘመናት ታሪካችን አሻራዎቻችንም ሆነ ዛሬ በዐማራው ነገድ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ አጉልተው ያሣያሉ። ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ዐማራው በኢትዮጵያ ምድር የመኖር መብቱን ተገፍፏል፤ በአገሩ ውስጥ ተንቀሳቅሶ በፈለገው እና ባሻው የሥራ መስክ ተሠማርቶ የመሥራት የዜግነት መብቱን ተነጥቋል፤ በነገዱ ማንነት ብቻ ኢ-ሰብአዊ በሆነ መንገድ በጅምላ ተሠልቧል፣ ጭፍጨፋ እና ግድያ ተፈጽሞበታል፤ እህቶቻችን እና እናቶቻችን ጡታቸው ተቆርጧል፤ ዐማራው ኃብት እና ንብረቱን ተነጥቆ፣ በአገሩ እንደ ባይተዋር ተቆጥሮ በግፍ ከመኖሪያው ተባርሯል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለቂም በቀል ያልታጨ ማንነት - በቀለ         

ለአብነት ያህል ባለፉት የ፮ ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ካድሬዎች እና በተላላኪዎቻቸው ከተፈፀሙት ግፎች መካከል፦
· በመጋቢት ወር ሁለተኛ ሣምንት መጀመሪያ በአምቦ ከተማ አካባቢ፣ ዳኖ ወረዳ (ከምዕራብ ሸዋ) በመቶዎች የሚቆጠሩ የዐማራ ተወላጆች በኦሕዴድ ካድሬዎች አማካይነት «አገራችሁ አይደለም እና ውጡ» ተብለው ተባርረዋል፤ ፳፮(ሃያ ስድስት) ዐማሮች በአሠቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በተለይ አቶ ጌጡ ክብረት የተባሉት የዐማራ ተወላጅ በአሠቃቂ ሁኔታ በገጀራ ተቆራርጠው መገደላቸው ተዘግቧል።

· በግንቦት ወር «የአዲስ አበባን ከተማ መስፋፋት እንቃወማለን» በሚሉ አክራሪ የኦሮሞ ብሔረተኞች በሚመራው እንቅስቃሴ ተሣታፊዎች፦ በአምቦ፣ በዓለማያ፣ በነቀምት እና በሮቤ (መዳወላቡ) ዩኒቨርስቲዎች በሚማሩ የዐማራ ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እና አልፎ ተርፎም ኢሠብአዊ ግድያ ፈፅመዋል። በተለይም በነቀምት ዩኒቨርስቲ ይማሩ የነበሩ ፯ ተማሪዎች በትግሬ-ወያኔ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ተገድለዋል። በመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ትማር የነበረችዋን የዐማራ ተወላጅ ከፎቅ ፈጥፍጠው ገድለዋታል። ግንቦት ፲፭ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. በቅፅ ፪፣ ቁጥር ፳፩ ባወጣነው መግለጫችን በይበልጥ እንደተብራራው፣ በጊምቢ ከተማ እና አካባቢው (ምዕራብ ወለጋ) ከሚኖሩት ዐማሮች መካከል በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩት ቤት፣ ንብረታቸውን ተነጥቀው እንዲፈናቀሉ ሆኗል። በአጠቃላይ በጊምቢ ከተማ እና በአካባቢው ይኖሩ ከነበሩት ዐማሮች የንብረት ይዞታ ውስጥ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል። ከዚህ በተጨማሪም በግንቦት ፮ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. የአካባቢው የኦሕዴድ ካድሬዎች በዐማራ ተወላጆች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ፈፅመዋል። ከስቡ ስሪ ወረዳ (ምሥራቅ ወለጋ) ፪መቶ ዐማሮች ‹‹ይህ አገር የእናንተ አይደለም፣ አገራችሁ ግቡ፤›› ተብለው ኃብት፣ ንብረታቸውን ተነጥቀው ተባርረዋል። በወለጋ በአክራሪ ኦሮሞዎች እና በኦሕዴድ ካድሬዎች አማካይነት በዐማሮች ላይ በስፋት የሚፈፀመው ግፍ አሁንም ያልተገታ መሆኑን የመገናኛ ብዙሃን እስካለፈው ሣምንት መጨረሻ ድረስ የዘገቡት ጉዳይ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:    በአገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ  ውሳኔ መወሰን ያለበት ማነው?  - ኤፍሬም ማዴቦ

· በዘንድሮው ዓመት በ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ብቻ የትግሬ-ወያኔ ካድሬዎች «ሕገ-ወጥ ግንባታ አካሂዳችኋል» እና «ቦታችሁ ለልማት ይፈለጋል» የሚሉ ሠንካላ ምክንያቶችን በመደርደር፦ በአዲስ አበባ፣ በጎንደር፣ በባህርዳር፣ በደብረማርቆስ፣ በደሴ፣ በሐረር እና በሌሎችም ከተሞች በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን በግሬደር እና በሰው ኃይል አፍርሰዋል። የትግሬ-ወያኔዎች በየዓመቱ ይህን አረመኔያዊ ድርጊት የሚፈፅሙት ሆን ብለው የክረምትን ወቅት ጠብቀው ነው። የዚህ ድርጊት ቀዳሚ ተጠቂዎች ደግሞ ዐማሮች መሆናቸው ይታወቃል።

በአንድ ቃል በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ዐማራው በየዕለቱ የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈፀምበት፤ ቀኑ የጨለመበት፤ ድምፁ ሰሚ ያጣበት፤ ግፉን ተመልካች ያላስተዋለለት ሆኗል።

ሐ) በዐማራው ላይ በሚደርሰው ግፍ እና በደል የተቃዋሚ ድርጅቶች እርምጃ፦

በሚያሣዝን ሁኔታ «በኢትዮጵያዊነት» ስም የተደራጁት የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች እንኳን ስለዐማራው ችግር ተቆርቁረው የሚያደርጉት ረብ ያለው ሥራ የለም። በዐማራው ላይ የሚፈፀሙትን ግፎች እና በደሎች «በዐማርኛ ተናጋሪዎች ላይ የደረሰ» እየተባሉ የሚሰጡት መግለጫዎች ዛሬ የዐማራውን ኅልውና ሆን ብለው የሚክዱ መሆኑን እና ለችግሩም የሚሠጡትን ዝቅተኛ ግምት በገሃድ ያሣያል።

መ) ዐማራው ኢትዮጵያዊነቱን ሣይለቅ በዐማራነቱ የመደራጀቱ አስፈላጊነት፦

አሁን ያለውን «የዐማራውን ጉዳይ ሆን ብሎ የማጣጣል» ሁኔታ መለወጥ የሚችለው፣ የዐማራው ልጆች ተደራጅተው «አለንልህ» ሲሉት እና ከጠላቶቹ አንፃር አቻ ወይም ጉቢ ኃይል ሲፈጥሩ ብቻ እንደሆነ የምክር ቤቱ አባላት ባደረጉት ሠፊ ውይይት ሙሉ በሙሉ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። ስለሆነም ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የጀመረውን ዐማራን የማደራጀት ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል፤ አባላት እና አካላትም ሳይሰለቹ እና ሳይታክቱ የእያንዳንዱን ዐማራ በራፍ በማንኳኳት የድርጅቱ አባል እንዲሆን፤ ድርጅቱንም በዕውቀት፣ በገንዘብ፣ በመረጃና በመሳሰሉት እንዲደግፍ እንዲያደርጉ ጥሪውን ያስተላልፋል።

 

ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!

ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!

ኢትዮጵያ በጀግና እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

 

8 Comments

  1. The suffering of Amharas have traversed boarder into neighboring countries where they have been subjected to inexplicable suffering because of their ethnic background. In the country, where I have been living for the past 12 years, i.e., Kenya, Amharas have been subjected to inexplicable suffering at the hands of EPRDF/TPLF agents who are operating in kenya above the law. I am among them.

  2. ድርጅቱ የጅመረው ስራ እንዳለ ሆ ኖ አሁንም መግለጫ ከማውጣት ያለፈ ስራ መስራት የቻለ አይመስልም:: በአማራው ላይ የዘር ማጥፋቱ ስራ በሕወሀት, በኦህዴድና ኦነግ ወዘተ. ብሶበት ባለባት ኢትዮጵያ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ዛሬ በአውሮፓና አሜሪካ እንዲሁም አውስትራሊያ ውንጀለኛ የወያኔ, ኦህዴድና ኦነግ ካድሬዎች ማለትም በስማቸው የሚታወቁ ጥገኛ ሆነው የሚኖሩት ላይ በፍርድ ቤት ክስ መክፈት ሞረሽ ያቃተው ምክንያቱ ምንድ ነው?
    አንድና ሁለት ግለሰቦች በቀይሽብር ወንጀለኛ ላይ በዴንቨር ያገኙትንና ያሳዩትን ሕጋዊ ርምጃ ውጤት ስንመለከት ድርጅቱ “የወረቀት ላይ ነብር” ብቻ ሆኖ አግኝተነዋል:: ሞረሽ ለአማራው እታደጋለሁ ካለ በተጨማሪም አማራውን በዙሪያው ማንቀሳቀስ ከፈለገ በተግባር ስራ ሰርቶ ማሳየት አለበት, ሌሎች ቡድኖችን መውቀሱ ጊዜ ከማማባከን በቀር ሌላ ጥቅም የለውም:: ምክንያቱም ሌሎች ድርጅቶች አማራውን እንታደጋለን ብለው የተመሰረቱ አይደሉም:: በአማራው ላይ የሚደርሱትን ወንጀሎች Human Rights Watch ወዘተ. እውቅና እንዲሰጡት ማድረግ ያልቻለ ድርጅት ሆኖ አግኝቼዋለሁ:: ለመሆኑ ሞረሽ ከመጣ ወዲህ አንድም አለም አቀፋዊ የመብት ተቆርቕሪ ድርጅት አማራውን አስመልክቶ ያወጡት መግለጫ አለ? የለም:: በዚህ ጉዳይ ሞረሽ ምን ይላል? የኦጋዴን, ኦርሞና ጋምቤላ ጉዳዮች አለም አቀፋዊ ዜና ሲሆኑ የአማራው ችግር ተዳፍኖ ያለበት ምክንያት አማራ ነን የሚሉ ምሁሮች ጉዳዬ አይደለም በማለትስቸውና ሞረሽ ደካማ መሆኑን አምኖና ተቀብሎ ወደ አዲስና የሚያዋጣ ስልት ራስን ማስተካከል ከምሁሩም ሆነ ክድርጅቱ ይተበቃል የሚል ሂስ ለመስጠት ተገድጃለሁ::

  3. To all Amharas,

    This is a call for unity and solidarity called upon by the worst times as this. Get yourself organised and muster up your energy and resources. To organize ourselves and fight discrimination under one organization is not a compromise to Ethiopian brotherhood and unity. Rather it is a call for self-defence and redemption of our people from the untold miseries. The Amhara have been subjects of genocide since times immemorial for no reason, but because they have been unionists, with a strong conviction in Ethiopian integrity and freedom of its people. For nothing but for their staunch struggle against colonialism, and divisive policies of the greedy west. Fascist Italians decimated a considerable population of the Amhara, the wars on Ethiopia and its freedom earlier this time have also targeted mainly the Amharas. The conspiracy of the Dergue corrupt officials have taken many Amhara, Oromo, and southern peoples young generation into the valley of death. The present divide and rule policy has ensnared the Amharas and has to date been working in ethnic cleansing of the Amharas. Other peoples of Ethiopia have fallen victims of short-sight and victims of the venoms of EPRDF.
    Get into one organization and rise up for your rights. Rise up as one people before falling victim in individual feeble attempts. ዝምታ ለበግም አልበጃት…..
    Rise up in unison and the termite hills will be washed out!!!

  4. thanks MORESH, and many thanks for mr TEKLE YESHAW the only courageous AMHARA who dare to speak on behalf of the voiceless AMHARAS who are being killed and displaced from every part of Ethiopia being used as a scape goat by extremists OLF and TPLF cadres and pseudo scholars

    Mr TEKLE Yishaw we are behind you and your organization and we will remember you for standing up for us and our people while AMAHRA ELITES are watching the killing and displacement of AMHARAS silently evenThese stupid AMHARA elites have no courage to write the true History of Amharas and Menilik while OLFites and TPLFites writing HATE HISTORY that is taking the country in to civil war

    we will not remember only the brutality of OLFites and TPLFites we will also remember the silence of AMHARA ELITES

  5. ሞረሽን እንዴት እንርዳው? ጎበዝ ከማለቃችን በፊት መላ ማለት ያስፈልገናል:: ቲዎዶር ሄርዝል የሚባል ሰው በአንድ ወቅት አይሁዶች የራሳቸው ሀገር ከሌላቸው ህልውናቸው አደጋ ላይ እንዳለ ሲናገር ብዙም ሰሚ አላገኘም ነበር ይሁን እንጂ በናዚ ሲጨፈጨፉ ያኔ ነበር አብዛኛው ህዝብ የባነነው:: ብልህ ከሰው ተሞክሮ ይማራል እናም ከተከፈተብን አደገኛ የዘር ማጥፋት ህዝባችንን ለመታደግ በተግባር ለተደገፈ ትግል አደራጁን:: ከማንም ያላነሰ ሪሶርስ እንዳለን ይሰማኛል ግን አቅምን ወደ አንድ አቅጣጫ ካላሰባሰብከው ትርጉም የለውም:: ጎበዝ የአደጋው ግዝፈት ሊያሳስበን የሚገባው ወቅት ላይ እንዳለን ይሰማኛል::

  6. MORESH is another racist few amahra people organization that are based in diaspora of course who are a bunch of silver retiree worthless walfare abusers who can not do anything except insltuing around cyber….and members of MORESH are not diffrent from weyane as they are racist like weyane members and Jawar first oromo few racist members…..NO MORE RACIST GROUP

  7. Although tigre people liberation front has focused on destroying the amhara, its eventual aim is to dismantle Ethiopia and to create a weak and ethnically divided enclaves south of the would be tigre republic.

  8. ለሞረሽ መልክት አለኝ_____ የአማራውን መፈናቀል በመንግስት የተሾሙ ካድሬዎች ባጀትና አስፈላጊው የሰው ሀይል ተመድቦላቸው የሚያስፈጽሙት____ 1ኛ/ አዲሱ ለገሰ (የፌደራል ልዩ እገዛ ቦርድ ሀላፊ) 2ኛ/ ካሳ ተ/ብርሀን (የፌዴሬሽን ም/ቤት ሊቀመነበር) 3ኛ/ ሻንቆ ደሳለኝ (በፌደራል ጉዳዮች ሚ/ር ከፍተኛ አማካሪ) ናቸው::

Comments are closed.

Share