ለምን የሳሙኤል ዘሚካኤል ጉዳይ ያን ያህል ያስደንቀናል? (በትረ ያዕቆብ)

ከበትረ ያዕቆብ

በትረ ያዕቆብ

ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፆች አካባቢ የህዝብን ቀልብ መሳብ የቻለና አሁንም ዋና መወያያ አጀንዳ ሆኖ የቀጠለ ጉዳይ ተከስቷል፡ የሳሙኤልዘሚካኤልየሀሰትዶክተር እናኢንጂነርነት፡፡ ጉዳዩ ብዙዎችን አጃኢብ አስብሏል ፤ አሁን በርካቶች ብስጭታቸዉን እና ቁጣቸዉን በተለያየ መንገድ እየገለፁ ይገኛል፡፡ ብዙ ሰዎች በአንድ ወቅት የስኬት ምልክታቸዉ እስከ መሆን የደረሰና አድናቆታቸዉን ያጎረፉለት ሰዉ ድንገት የሀሰት ሆኖ ሲያገኙት መደናገጣቸዉ አልቀረም፡፡

እርግጥ ነዉ ነገሩ ትንሽ የሚያስገርም ነዉ፡፡ ወጣቱ የሄደበት እርቀት ግራ የሚያጋባና ድፍረቱ የሚያስገርም ነዉ፡፡ ሌላዉን ትተን በሀገር ዉስጥ የሚገኙትን ዩንቨርሲቲዎች ስም ደጋግሞ እያነሳ ይህንን ሸለሙኝ ፣ ይህንን ሰጡኝ ፣ የረዳት ፐሮፌሰርነት ማዕረግ ተበረከተልኝ ወዘተ ማለቱ በእርግጥም ከማሰገረም አልፎ ብዙ ያስብላል፡፡ ያም ሆኖ ግን እኔን ይበልጥ ያስገረመኝ ጉዳዩ የዚያን ያልህ  እንደ ተዓምር የመታየቱ ነገር ነዉ፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ እየተደረገ ያለዉን ዉይይት ስመለከት እንዴ ነዉ ነገሩ ብየ መደነቄ አልቀረም፡፡

በዚህ ወጣት የተፈፀመዉ አሳፋሪ ተግባር ዛሬ የተከሰተ አዲስ ክስተት አይደለም ፤ የነበረና አሁንም  እየተፈፀመ ያለ ነገር ነዉ፡፡  እዉነቱን መነጋገር ካለብን መሰል ማጭበርበር ቤተ-መንግስት አካባቢ በጣም የተለመደ እና  ብዙዎች የተጨማለቁበት ተግባር ነዉ፡፡ ይታያችሁ ፣ ቤተ-መንግስት ነዉ ያልኩት፡፡ ይህንን ስናይ ወጣቱ የፈፀመዉ ተግባር የሚደንቅ አይመስለኝም፡፡ እንዴትስ ያስደንቃል፡፡

ዛሬ ሳሙኤልዘሚካኤልእድል ጥሎት ሁሉም ተረባረበበት እንጅ የኢህአዴግ ባለስልጣናት የትምህርት ማስረጃ ቢመረመር ስንት ከሱ የባሰ ጉድ ይገኝ ነበር፡፡ እንግዲህ ሀገርን ያህል ትልቅ ነገር እንመራለን የሚሉ  ግለሰቦች መሰል ተግባር በሚፈፅሙበት አገር የዚያ ወጣት ተግባር ጉድ የሚያስብልበት ምክንያት አይታየኝም፤፤ እንዴትስ ሊያስብል ይችላል፡፡ ከዚህ ይልቅ ቤተ-መንግስት ተቀምጠዉ አገርን የሚዘዉሩ ግለሰቦች ፣ በያንዳንዳችን እጣ ፈናታ ላይ የመወሰን ስልጣን በጉልበት የጨበጡ ባለስላጣናት የሀሰት ማስረጃ ሊያስደንቀን ፣ ሊያበሳጨን ፣ ሊያስደነግጠን ይገባ ነበር፡፡

ዛሬ በርካታ የኢህአዴግ/ህወሀት ጉምቱ ባለስልጣናት እንከዋን ትምህርት ቤት ገብተዉ ሊማሩ በበሩ እንኳን ሳይልፉ ባለሁለተኛ እና ሶስተኛ ድግሪ የመሆናቸዉ ጉዳይ ለብዙዎቻችን ሚስጥር አይመስለኝም፡፡ ዛሬ የአዲስ አበባ ዩንቨርሲት ድግሪና ማስትሬት በቀጭን ትእዛዝ እንዳሻቸዉ የሚሰበስቡት ተራ ነገር ነዉ፡፡ ሲያሻቸዉም ከዉጭ በገንዘብ ይሸምቱታል፡፡ ሲልም እድሜ በሙያዉ ለተካኑ የቻይና እና የህንድ ዜጎች እንደፈለጉት አሳምረዉ አዘጋጅተዉ ኮንግራ ይሏቸዋል፡፡ከዛም ከለታት አንድ ቀን ብቅ ብለዉ ይህ አለን ይላሉ፡፡ ይህ ነዉ ለኔ አሳፋሪዉ ፣ አስደንጋጩ፡፡

በእንዲህ አይነት መልኩ በርካታ ትልልቅ ባለስልጣናት የሀሰት የክብር ካባ ለመደረብ ሞክረዋል፡፡ አሁንም ብዙዎች ይህንን መንገድ ቀጥለዉበታል፡፡ ከብዙ ወራት በፊት አንድ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ዉስጥ የሚሰራ ወዳጄ ሲያጫዉተኝ “ዩንቨርስቲዉ በካድሬ መመራት ከጀመረበት እለት አንስቶ በርካታ የኢህአዴግ መኳንንቶችን በማዕረግ” አመርቋል” ነበር ያለኝ፡፡ ይታያችሁ እርሱ ያለዉ “በማዕረግ” ነዉ፡፡ ይህ ማለት ሳይማሩ ፣ ሳያጠኑ ፣ ሳይፈተኑ ኤ በ ኤ ይሆናሉ ማለት፡፡ ለኔ ይሄ ነዉ አስደንጋጩ ጉዳችን፡፡ ይህ ወዳጄ እንደነገረኝ አልፎ አልፎም በዉጭ ዩኒቨርስቲ መማር የሚፈልጉ ከተገኙም የሚፈልጉትን የትምህርት መስክ መርጠዉ የመዓረግ ተመራቂ ተብሎና ሁሉም ነገር ተሟልቶለት ይሰጣቸዋል፡፡ እኒህ ሰዎች ናቸዉ ዛሬ ሀገሪቱን የሚመሩት ፤ ከእኛ በላይ አዋቂ የለም የሚሉን ፣ የጭቆና ቀምበር ጭነዉ ፍዳችንን የሚያሳዩን፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሁለት ግለሰቦች ማንሳት እዉዳለሁ፡፡ ይህ ለምሳሌ ያህል ብቻ ነዉ፡፡ የመጀመሪያዉ በአንድ ወቅት እንደ ምሁር ለመፈላሰፍ ሲቃጣዉ የነበረዉ የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ነዉ፡፡ ሰዉየዉ ትምህርቱን ከዩንቨርሲቲ አቋርጦ በረሀ እንደ ወረደ እና ከ17 አመት የትጥቅ ትግል በኋላ በለስ ቀንቶት ቤተ-መንግስት እንደገባ ነዉ ነበር የምናዉቀዉ፡፡ ሆኖም ከእለታት በአንዱ ቀን አቶ ምን ይሳነዋል ባለሁተኛ ድግሪ ምሁር ነዉ ሲባል ሰማን ፣ ያም አልበቃ ብሎ ሌላም እንዳከሉበት የቀብሩ እለት ተነገረን፡፡ የአቶ ሳሞራ የኑስም ታሪክ ተመሳሳይ ነዉ፡፡ 11ኛ ክፍል አቅርጠዉ በረሀ ገብተዉ እንደታገሉ እንጅ ሌላ የምናዉቀዉ ነገር አልነበረም፡፡ ሆኖም  እርሳቸዉ ከ11 ክፍል በአቋራጭ ከፈለጉት ቦታ ላይ ጉብ አሉ፡፡ በሀዉልታቸዉ ላይም ባለ ሁለተኛ ድግር ምሁራ ናቸዉ ተብሎ ተፃፈ፡፡ እንዴት ብሎ የጠየቀም አልነበረም፡፡ እስከማዉቀዉ ድረስ በጉዳዮ ላይ ጥያቄ ያነሳ ብቸኛ ሰዉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ብቻ ነዉ፡፡ ዛሬ “ለእዉነት ቆሜያለሁ” የሚለዉ ሬድዮ ፋናም ያኔ አዳች ነገር ትንፍስ አላለም ነበር፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በቅርቡ ብዙ አፍሪካዊ ጋዜጠኞች  የተሳለቁበት በሀሰት የትምህርት ማሰረጃ በመንግስት ሴራ የአፍሪካ ህብረት አካል በሆነ ድርጅት ዉስጥ ትልቅ ስልጣን እስከመጨበጥ የበቃዉ የኢህአዴግ ካድሬም በምሳሌነት ሊጠቀስ ይችላል፡፡

እንግዲህ ይታያችሁ እነዚህ ሰዎች ሀገር መሪ ነን ይላሉ፡፡ እነዚህ ናቸዉ የሀገሪቱን ፖሊሲና እስትራቴጅ ቀራፂያን ፣ እነዚህ ናቸዉ ሀገሪቱ እና እኛን ወክለዉ ከሌሎች ጋር የሚደራደሩት ፣ እነዚህ ናቸዉ ዛሬ በእያንዳንዳችን ህልዉን ላይ ወሳኝ ሆነዉን የሚገኙት፡፡ ይህ ነዉ እኔን ይበልጥ የሚያሳፍረኝ ፣ የሚያሰገርመኝ፡፡ ይህ ነዉ ለኔ ትልቁ ጉድ፡፡ እንዴት ነዉ እንዲህ አይነት የሀገር መሪዎች ባሉበት ሀገር አንድ ከደሀ ቤተሰብ የወጣ ልጅ የፈፀመዉ የማጭበርበር ተግባር የሚደንቀዉ፡፡ ነዉ ወይስ አላዉቅም ልንል ነዉ፡፡

ከባለስላጣናቶቻችን እና ከእኛ ዜጎች አልፎ ተርፎ እንኳ በየዩንቨርስቲዉ በዶክተር እና ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ስም የሚያጭበረብሩት የዉጭ ዜጎች በርካታ አይደሉም? የመጀመሪያ ድግሪ ይዘዉ በዶክተር ስም የነገ ሀገር ተረካቢ በሆኑ ወጣት ልጆች ላይ ሲቀልዱ አላየንም ፣ አልሰማንም ? ለምሳሌ እንኳን በቅርቡ ወደ አንድ የዉጭ ዩንቨርስቲ  ሁለተኛ ድግሪዉን ለመማር ያቀና ወጣት ዶክተር ነኝ ብሎ ካስተማረዉ የዩንቨርሲቲ መምህሩ ጋር በአንድ ክፍል ዉስጥ ለትምህርት እንደተገናኙ ሲተረክ ሰምተናል፡፡

በጥቅሉ እንነጋገር ከተባለ በርካታ ጉድ በዙሪያችን አለ፡፡ ዘርዝረን አንጨርሰዉም፡፡ በመሀከላችን በርካታ የቀበሮ ባህታዊያን እንዳሉ ልብ ልንል ያገባል፡፡ ይህ እየሆነ ባለበት አገር የሳሙኤልተግባር ለኔ ብዙ የሚያስደንቅ ነዉ ብየ አላስብም፡፡ እንዴዉም በአንድ ግለሰብ የማጭበርብር ተግባር ላይ ብቻ ማፍጠጡ ችግሩ እንደሌለ ያስመስለዋል ፤ ወደ መፍትሄም አይወስድም፡፡ ስለዚህም ችግሩን ሰፋ አድርጎ ማየትና አፍረጥርጦ መነጋገር ተገቢ ነዉ እላለሁ፡፡ ሬድዮ ፋናም ቢሆን “ለእዉነት ቆሜያለሁ” የሚል ከሆነ በአንድ ግለሰብ ተግባር ላይ ብቻ ከማንባረቅ በዘለለ የሌሎችንም በተለይም ሀገር እንመራለን በሚሉ የኢህአዴግ/ህወሀት አምባገነን ባለስልጣናት እየተፈፀሙ ያሉ ማጭበርበሮችን ሊያጋልጥ ይገባል፡፡ እርግጥ ኢህአዴግ አምጦ ከወለደዉ ተቋም ይህን መጠበቅ ሞኝነት ነዉ፡፡ ለሁሉም ቸር እንሰንብት !

10 Comments

 1. The nation itself is becoming all about lie, cheating and immoral activities. Though things still should be presented with a more in depth research than what your friend say or whoever, cheating and stealing has become something anyone do and never feel a tiny shame about it.

  This nation has start giving trophy for those who steal the most.

 2. It is obvious that most if not all TPLF officials are ignorant, but all of them holds at least a masters degree. What can we do? as their move is violent we have to simply wach them until that day comes

 3. R u shure? Where is ur evidence? U r not write brevity but not a concrete evidence! Can u put it? Otherwise ur article is a gosip. Can u tell me about the samora deth? He is dead? I don’t think so

 4. You are right. This laughable woyane rebel group, they did so many tricks and cheatings in these innocent people. We shouldn’t blame only on the so called Samuel, we have many gov’t officials leading us with fake certificates. Alfa University college hold the lead of giving these forged credentials, diploma, degree and even MA to the EPRDF cadres, still they couldn’t write and read English. Azeb mesfin she was under 5th grade when woyane migrated to Addis and now she hold her MA, kiiikiiiikiii, Siye Abreha, Melese Zenawi, Shiferaw Jarso are among the few who purchased their certificates from abroad, these people they don’t have 1st degree and they posted their MA through short cut. <Edme tsega new gena bizu yasayenal, yasemanal. BZW Samuel was also a member of Woyane and they used him up to the level they need and when the tooth brush is finished, they just throw him away like garbage. Where were they before he did all these chaos for the last five years? He was channeling their stolen coffee to abroad….shame to Woyane & its supporters, how can you live with lies, cheating, smuggling, ignorance, stupidity…Million shames, asafariwoch. Our days will come soon and will put you into fire as you suffered our peoples.

 5. You are right. This laughable woyane rebel group, they did so many tricks and cheatings in these innocent people. We shouldn’t blame only on the so called Samuel, we have many gov’t officials leading us with fake certificates. Alfa University college hold the lead of giving these forged credentials, diploma, degree and even MA to the EPRDF cadres, still they couldn’t write and read English. Azeb mesfin she was under 5th grade when woyane migrated to Addis and now she hold her MA, kiiikiiiikiii, Siye Abreha, Melese Zenawi, Shiferaw Jarso are among the few who purchased their certificates from abroad, these people they don’t have 1st degree and they posted their MA through short cut. <Edme tsega new gena bizu yasayenal, yasemanal. BZW Samuel was also a member of Woyane and they used him up to the level they need and when the tooth brush is finished, they just throw him away like garbage. Where were they before he did all these chaos for the last five years? He was channeling their stolen coffee to abroad….shame to Woyane & its supporters, how can you live with lies, cheating, smuggling, ignorance, stupidity…Million shames, asafariwoch. Our days will come soon and will put you into fire as you suffered our peoples.

 6. Beye adebabayu degre alen, masters alen, etc silu alsemanin. Is this what u want to talk about? Please don’t mix politics with this case.

 7. ጽሁፉ በጣም ጥሩ አቀራረቡም መልካም ነበር:: ችግሩ “የሚያስብል” ምን ማለት ነው? የሚያሰኝ; ያሰኛል የሚለው ምን ጎድሎት ነው እንዲህ ዓይነት አጉራ ዘለል አስቀያሚ ቃል የተተካበት:: አማርኛችን ቅጡን እያጣ ነው:: እንዳመልጥ ረዳኝ; አተረፈኝ ማለት አቅቶአቸው ጠዋትና ማታ አስመለጠኝ ሲሉ ሰምቺ መታገስ አቅቶኝ ነበር::

 8. A day before yesterday I saw a news from Sudan tribune which states UN chief Ban Ki-moon Tuesday appointed the Ethiopian Lt Gen. Yohannes Gebremeskel Tesfamariam as the Force Commander for the United Nations Mission in South Sudan (UNMISS). According to the news Lieutenant-General Tesfamariam who is from Tigry region has a master’s degree in peace and security from Addis Ababa University. Look this people how they cheat international communities, leave alone our people, AAU doesn’t have MA program on peace & security. The guy even didn’t finish his secondary education. may be he purchased it from AAU as his boss did. Shame to Woyane and its supporters.

 9. >>< ሳሙናው ዘሚካኤል! ይህ እብደትም ስሕተትም አደለም። ይህ በተማረ መሰል ደረጃ፣ ከታጋይ በታች፣ ከካድሬ በላይ የሆነው እንደ ታጋይ አዜብ አባባል አድርባይ! መሆኑ ነው ለዚያውም ታማኝ ምሁር አድርባይ…አንዳንድ ሰዎች የፀሐዩ መንግስታችን ሲሉ…ልማት ለግላቸው፣ ሀብት ለብቻቸው፣ ሰላምና መረጋጋት፣ ብልጽግና፣ ደብል ድጅት፣ በኪራይ ሰብሳቢነት፣ በሙስናና በማጭበርበር፣ስኬታማ የሆኑ የጥንት መደብ ላይ ተወላጆች፣ የዛሬ የራሳቸው ክልልና የሥራ መደብ በነፃ የተፈቀደላቸው ሁሉ በእነሱ ያለእነሱ ምንም የማይሆን ባለራዕይ..ቦንብ ሳይጥሉ፣ የበረሃ ቁር፣ ሐሩር ሳይበላቸው፣ ውሃ ጥም፣ ውጣ ውረድ፣ ሳይገጥማቸው በአፋቸው ወሬ እየቆሉ፣ የሚመፃደቁ፣ ለህወአት አባላት ተቆርቋሪ ቦንም አምካኝ፣ ሆነው ከፊት ተሰልፈው ቂጣቸውን እተገረፉ እየለፈለፉ የሚኖሩ ሆድአደር፣ አውርቶ-አደር፣ ከሁሉም ብሄር ውስጥ መኖራቸውን ማስረጃው "ድንቁርና ዘሚካኤል" ማለት ይህ ነው።

  **እነኝህ ይህ መንግስት ቢፈርስ መጥፋታቸው የገባቸው..ተቃዋሚና ተፎካካሪ ሥርዓቱን ቢለውጥ ቦታ አልባ መሐል ሰፋሪ ሆነው ማቀው እነደሚሞቱ የሚያምኑ ይህ መንግስት ዘለዓለማዊ አንዲሆን ጉሮሮአቸው አስኪደርቅ ስለልማትና ዕድገት አጋንንትና ጋኔል እንደሰፈረባቸው የሚቀሳፍቱ፣ ትውልዱ እዳይጠይቅ፣ እንዳይናገር፣ አንዳያስብ፣ እንዲመክንና እንዲባክን ግዜውን በወሬ፣ ኑሮውን በሳቅ በዋዛ፣ ባህልና ሃይማኖቱን በቀልድ፣ሀገሩን በፍቃደኝነት እንዲያጠፋ የሚሰብኩ የዚሁ ሥርዓት ታማኝ ቅጥረኖች እንጂ…የዚህን ሥርዓት ተቀናቃኝና እውነተኛ ፀሐፊና ጋዜጠኛ የድሃ ልጆችማ ደረታቸው ለጥይት፣ እግራቸው ለቃሊቲ፣ እጃቸው ለእሥር ሰንሰለት፣ መዳረጋቸውን አይተናል።

  -**አሁንም አሳዛኙና አሳሳቢው የሀገር ጉዳይ ይህ ትውልድ እየተጭበረበረ፣ እየተጥበረበረበትና እየጨፈረ የሚሞተው ለመሆኑ እነ ሽፈራው ሽጉጤ ት/ሚ ሲሸጎጡ ፴፪ ዩኒቨርስቲ የተከፈተው አፍ ከፍቶ ለማጨብጨብ ነው ማለት ነው! ?ወይንስ ትውልዱ በቁሙ የሞተ ተብሎ ተፈርጇል? ነባርና ሽማግሌ ምሁራንን እግሩን እያነሳ የሚሳደበው የኢህአዴግ አባላትና ወጠጤ ካድሬ "ሳሙናው ዘሚካኤልን" በማዳነቅ፣በመጃጃልና አፍ መክፈት የድንቁርና መስፋፋት አደለምን!?

  ***ወይንስ እውነተኛ ትምህርት የሚማሩት የሥልጣን የዱላ ቅብብል እስከ ሶስተኛው ትውልድ ፣ለማድረግ በውጭው ዓለም ከሀገር በተዘረፈ ገንዘብ የሚንፈላሰሱት የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ልጆችና ቤተዘመዶች ብቻ ናቸው!?በእርግጥ ይህ ትውልድ ተምሯል ወይስ ተማሯል!? ለማናቸውም የኢህአዴግ የተበላሸ ሥርዓት ተመልሶ ሊፀዳና ሊስተካካል ቢያንስ ፵ዓመት ይፈልጋል።ይህ ትውልድ ልክ ሲሞት ነፃ ይወጣል!!

Comments are closed.

self addis 2
Previous Story

(ሰበር ዜና) ከ1000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ቤታችን ፈረሰ በሚል ኢሰመኩ ደጃፍ ተቃውሞ ወጡ

Next Story

‹‹የኢትዮጵያን ወጣቶች የጨፈጨፉትን በህግ የምንበቀልበት ጊዜ ይመጣል›› – ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop