ሕዝበ ክርስቲያን በጰራቅሊጦስ መንገድ ሲሄዱ፤ ፓትርያርክ፤ ሊቃነ ጳጳሳት፤ መነኮሳትና ቀሳውስት በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ (ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ!

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
nigatuasteraye@gmail.com
ሰኔ ፳፻፮ ዓ.ም.

ማሳሰቢያ፦
ቀሲስ አስተርዕየየዚህች ክታብ አላማ ነገረ መለኮት ለማስተማር አይደለም። ሆኖም አብዛኛዎቻችን ኢትዮጵያውያን እምነታችሁ ምንድነው ስንባል መልሳችን ክርስቲያን ነና! ነው። እንዲያውም ብዙዎቻችን በኩራት በልበ ሙሉነት ከዘመኑ ክርስትና በፊት በነበረችው በኦርቶዶክስ ተጠምቄ ያደኩ ነኝ እንላለን። በተለይም በአውደ ምህረት ላይ ቆመን እግዚአብሄር ይባርክ ለማለት ተክነናል የምንል ሰዎች፤ ስንጠየቅ ለክርስትናየ ደግሞ ምን ጥያቄ አለው! እንዲውም ባይደንቅህ ልብሴን ተመልከት! የጨበጥኩትንም መስቀል እይ! በደረቴ ያንዘረገኳቸውን ክርስቲያን ነክ ጌጣ ጌጦች ተመልከት የዚህች ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ቄስ፤ መነኩሴ፤ (ጉዳችን አያልቅምና በአቡነ ጳዎሎስ ዘመን የተለቀቀ ቆሞስ)፤ ጳጳስ ነኛ! እንላለን። በእምነት በታሪክ በባህል መኩራት ተገቢ ነገር ነው። የሚኮሩበትን ሳይጠበቁ መኩራራት ብቻ ግን ዝናብ የለሽ ባዶ ደመና መሆን ነው።

መጠበቅ መቻላችን የሚመዘንበት ጰራቅሊጦስ ነው። በሱ እየተመዘን ፤ እሱ ከሚጠላቸው ከዝሙት፤ ከሀሰት፤ ከስርቆት፤ ከስስት፤ ከክህደት ተጠብቀናል፤ ህዝቡንም፤ ጰራቅሊጦስ ከማይወዳቸው ነገሮች ሁሉ ራቁ እያልን፤ ራሳችንን ምሳሌ አድርገን እናስተምራለን። እግዚአብሄርን እንቀድሳለን፤ ህዝቡንም እናስቀድሳለን ቄስ፤ ቆሞስ ( መረን የተለቀቀ)፤ ጳጳስ ነን የምንል፤ በወያኔ ዘመን ያለን ካህናት፤ ከምን ላይ እንዳለን ማሳየት እችል ዘንድ፤ የጰራቅሊጦስን ሚዛንነት ለመግለጽ ወደ ነገረ መለኮቱ ገባ ብየ ለመውጣት እገደዳለሁና ለትእግስታችሁ ይቅርታ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምርጫ የዴሞክራሲያዊ ስርአት መገለጫ ብቻ ሳይሆን የሰላማዊ ትግል ስልት አካል ጭምር ነው!

2 Comments

  1. Great piece as usual! I think God has sent Kesis Asteraye to rebuke and straighten us and the whole Ethiopian Orthodox followers.

    EOTC Priests, monks, bishops, and the Patriarch, please open your heart to listen to the word of God and His rebuke that is coming through His servant Asteryae so that you can save yourself from the coming hell and condemnation. Your fate will be much worse than that of Abune Paulos and the weyane PM; the duo are dead on earth and in heaven.

  2. ለመሆኑ አንተ ማነህና ሰውን ትተቻለህ ሰውን ከመተቸት ይልቅ በመልካም ስራህ በመልካም አንደበት ሰውን ለማስተማር ሞክር ለአንተ አይነቱ ፕለቲከና ጽሁፍህ መልካም ነው መቻም ከዝንብ ማር አይከጀል አንተ ከወያኒ በምን ትለያለህ አመድ በዱቁት ይስቃል ትክክለና ካህን ከሆንክ ክነትህን በአግባብ በስራ አውል ማስተዋሉን ያድልህ::

Comments are closed.

Share