የትግራይ ህዝብ የወያኔ ስርአት ተጠቃሚነው! (አንዷለም አስራት )

ከአንዷለም አስራት Andasr1983@gmail.com

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ በቅርቡ የማከብራቸውና የሶስት አፋኝ መንግስታትን ጭቆና ከህዝብ ጫንቃ ላይ ለማንሳት እየታገሉ ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም እና የአረና ትግራይ አባል የሆነው አብርሃ ደስታ የትግራይ ህዝብ የወያኔ አገዛዝ ተጠቃሚ እንዳልሆነ ለማስረዳት የሞከሩት ስህተት መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡

የትግራይ ህዝብ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ አገልግሎት፣ በመሰረተ ልማትና በልማት ባለፉት 23 አመታት በአንጻራዊነት ከሌሎች ክልሎች በተሻለ ሁኔታ ተጠቃሚ እንደሆነ ለማስረዳት እሞክራለሁ። ይህን ስል የትግራይ ህዝብ አልፎለታል ፤ በልጽጓል፤ ከድህነት ወጥቷል እያልኩ ሳይሆን ህዋሃት በሚያደርገው በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አድልኦ ምክንያት ከሌሎች ክልሎች የተሻለ የስራ እድል ተፈጥሯል ፤ የተሻሉ የአገልግሎት ተቋማት አሉ፤ እንዲሁም ከፍ ያለ የገንዘብ ፍሰት አለ ይህም የሆነው የሌሎችን ክልሎች ጥቅም በሚጎዳ መልኩ ነው የሚለውን ለማስረዳት ነው። ከመጀመሪያው ማስረገጥ የምፈልገው ግን ለወያኔ ወንጀሎች የትግራይ ህዝብ ተጠያቂ ሊሆን አይችልም።

1. በፖለቲካ

ወያኔ በትግራይ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት አለው ፣ የወያኔን ዓላማ የማይደግፍ ትግረኛ ተናጋሪ በጣም ጥቂት እንደሆኑ ይታዎቃል፡፡ አብዛኛዎቹ ትግርኛ ተናጋሪ የህዋሃት ተቃዋሚዎች አላማውን ሳይሆን ግለሰቦቹን የሚጠሉ መሆናቸው የታዎቀ ነው፡፡ እነ ገብሩ አስራት ፣ ስየ አብርሃ ፣አረጋዊ በርሄ የመሳሰሉት ከወያኔ የተለዩት አላማውን ጠልተው ሳይሆን መለስ ዜናዊና መሰል አምባገነኖችን በመጥላት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ አንጋፋው ገብረ መድህን አርአያ ግን የወያኔን አላማ የማይቀበል እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ሁኖም የሁሉንም ትግርኛ ተናጋሪዎች የፖለቲካ አቋም አውቃለሁ ብየ አልታበይም ሌሎችም የወያኔን እኩይ ተግባር የማይደግፉ ይኖሩ ይሆናል ግን አብዛኛው ደጋፊ መሆኑ አሊ አይባልም።

ስለዚህም ወያኔ የትግርኛ ተናጋሪ ምሁራንን ሙሉ አቅም በሁሉም የስራ መስኮች ይጠቀማል፣ ኢትዮጵያ እንደ አዲስ በክልል ከተዋቀረችበት ጊዜ ጀምሮ የትግራይ የተለያዩ ቢሮዎች በአንጋፋና የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው የቢሮ ሃላፊዎች ሲመሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚሁ ምሁራንም የውስጥ ነጻነታቸው የተጠበቀ በመሆኑ በሙሉ አቅም ይሰራሉ፡፡ በተቃራኒው የሌሎች ክልሎች ተዎላጅ የሆኑ አብዛኛዎቹ ምሁራን የወያኔን አላማ ከመጀመሪያው የተጸየፉ በመሆናቸውና ወያኔም ገና ከጅምሩ በጣላቻና በጥርጣሬ ስላያቼውና እንዲጠጉ ስላልፈለገ በተለጣፊ ድርጅቶች መዋቅሮቹ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ በዚህም ምክንያት በሌሎች ክልሎች ከክልል አስተዳዳሪዎች ጀምሮ ትምህርትም ፣ብቃትም፣ ልምድም የሌላቼውና ጠርናፊ ወያኔዎች ሲጠሩዋቸው አቤት ሲልኳቸው ወዴት የሚሉ ፣ ታማኝነታቼውንም ለማሳየት የተሻለ ነገር ከመስራት ይልቅ በሚገዙት ህዝብ ላይ ቀንበር የሚያጠቡ ደካሞች ክዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ ስልጣን ተሰግስገውበታል፡፡ ለዚህ አለምነው መኮንን አይነቶችን እንደምሳሌ ማየት ይቻላል፣ አለምነው መኮንን መለስ ዜናዊን ያመልክ እንደነበር ይነገራል ፣አለቆቹ የመለስን ራእይ ማስቀጠል ሲሉ ሰምቶ እሱም ራሱን ጭምር አይሰድቡ ስድብ ሰደበ፡፡

ስለዚህም ትግራይ የተሻለ ትምህርት፣ ልምድ፣ ብቃት፣ ዝግጁነት እና ሙሉ ስልጣን ባላቸው ሰዎች የሚተዳደር ክልል እና ህዝብ በመሆኑ ተጠቃሚ ነው፡፡

በአንጻራዊነት መልካም አስተዳደርም አለ ማለት ይቻላል፤ ፖለቲካውን እስካልነካ ድረስ ማንኛውም ትግራዊ በትግራይ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ክልሎችም አቅሙ የፈቀደውን ይሰራል። አሁን ያለው የፖለቲካ ስርአት ቢቀየር የትግራይ ህዝብ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ምናልባት አምልካከታቸውን ቀይረው ዲሞክራቶች ይሆናሉ ብለን እናስብ እንደሆነ እንጅ የተለዩ ሰዎች ያገኛል ብየ አላስብም ፤ ምክንያቱም የአረናና የህዋሃት ልዩነት የግለስቦች ጸብ ብቻ ነው ብየ አስባለሁ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሌባ ዓይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ - ሰማነህ ታምራት ጀመረ፤ ኦታዋ፤ ካናዳ

በኢኮኖሚ

ሀ. በኢትዮጵያ በጣም ሀብታሙ ድርጅት ኢፈርት ነው፣ ኢፈርትም ትግራይ ውስጥ ከሃያ በላይ ግዙፍ ድርጅቶች አሉት፣ የነዚህ ድርጅቶች ክፍተኛ ገቢ የት እንደሚገባ መረጃው ባይኖረኝም እነዚህ ድርጅቶች ግን በጣም ብዙ የስራ እድል ትግራይ ውስጥ ከፍተዋል፣ ብዙ የትግራይ ወጣቶች በትግራይ ውስጥም ሆነ ከትግራይ ውጭ የዚህ ህገውጥ ድርጅት ተቀጣሪ በመሆን የሌሎች ክልሎች ወጣቶች ያላገኙትን እድል አግኝተዋል፡፡ በነገራችን ላይ የኢፈርት የገንዘብ ምንጭ በጦርነቱ ወቅት ከወሎ፣ ከጎንደር፣ ከጎጃምና ከወለጋ አካባቢዎች የተዘረፈ ገንዘብና እንዲሁም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ልማት ባንክ በትእዛዝ የተወሰደና ከጊዜ በኋላ እንዲሰረዝ የተደረገ ብድር ነው፡፡ በሌሎች ክልሎች የሌሉ በርካታና ብዙ ቢሊዮን ብር ኢንቭስት ያደረጉ ድርጅቶች የስራ እድል ሲፈጥሩ የክልሉ ህዝብ አልተጠቀመም ማለት አይቻልም።

ለ. ህወሃት በጠባብ አላማው ከጎንደርና ከወሎ በጣም ሰፊ ለም የእርሻ መሬት ዘርፏል፣ ይህንንም የእርሻ መሬት ለአባላቱና ሌሎችም የትግራይ ተዎላጆች ብቻ አከፋፍሏል፣ እንዲሁም በርካታ የትግራይ ገበሬዎች በነዚህ ለም መሬቶች ሰፍረዋል፣ እነዚህ መሬቶች ቀደም ሲል በሌሎች ሰዎች የተያዙና የሁመራ አካባቢ ደግሞ የመንግስት እርሻ የነበረ ነው፡፡ ይህንኑ የዘረፈውን መሬት ህጋዊነት ለማረጋገጥ ይመስላል ወያኔ በተለይ በወልቃይት አካባቢ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካሂዷል፣ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፣ ታፍነው ተወስደው የደረሱበት አይታዎቅም፡፡ በነዚህ መሬቶች መወሰድ ምክንያት በርካታ የጎንደር ስዎች ተፈናቅለዋል፤ ተጎድተዋል፡ የትግራይ ሰዎች ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቅመዋል።

ከዚህ ጋር የተያያዙ በተለይ በሁመራ አካባቢ የተደረጉ ሶስት ነገሮችን ልጥቀስ፤

በተፈጥሮ በተራቆቱ የጎንደርና የወሎ አካባቢዎች የሚኖሩ ገበሬዎች በቂ የእርሻ መሬት ስለሌላቸውና በለም አካባቢዎችም መስፈር ስለማይፈቀደላቸው ወደሁመራ አካባቢ እየሄዱ በቀን ሰራተኛነት ህወሃትን ያገለግላሉ፣ እነዚሁ ድሆች ከደጋው አካባቢ የመጡ፡በመሆናቸው ለወባና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎች በቀላሉ ይጋለጣሉ፣ መጀመሪያም እንደሰው የማይቆጥሯቸው የትግራይ ባለሃብቶችም ሲታመሙ አውጥተው ይዎረውሯቸዋል በርካቶችም በዚህ ሁኔታ ይሞታሉ፡፡ ይህን ሪፖርት ያደረገው በጊዜው በቦታው እርዳታ ይሰጥ የነበር የ MSF ሰራተኛ ፈረንጅ ነው። በጊዜው ሰው እንዴት በሰው ላይ እንደዚያ እንደሚጨክን በግርምት ያውራ ነበር። እንደዚህ አይነት ሰዎች ወደሁመራ ለስራ መሄድ በደርግ ጊዜም የነበረ ሲሆን በዚያን ጊዜ ግን በቂም ባይሆን እንደሰው ህክምና የማግኘት እድል ነበራቸው፡፡

ሌላው ባለፈው አመት በሚድያ እንደተነገረው በህዋሃት ካድሬዎች ደባ የቀን ሰራተኞቹ የወሎና የጎንደር በሚል በቡድን ተከፋፍለው ለሳምንታት ሲጨራረሱ የአካባቢው ፖሊስም ሆነ የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ግጭቱን ለማስቆም አጥጋቢ እርምጃ አልወሰዱም፡፡

ሶስተኛውና ከአመት በፊት ከስፍራው ከመጣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረ ወጣት የተገለጸው የቀን ሰራተኞቹ የሰሩበት ደመዎዝ ተከፍሏቸው ከወያኔ እርሻዎች ሲወጡ በቅርብ ርቀት በሽፍቶች በተደጋጋሚ መዘረፋቸው ነው፣ በኋላ የቀን ሰራተኛ የነበረው ይህ ወጣት ያረጋገጠው ነገር ቢኖር ግን በሽፍታ መልክ መልሰው የሚዘርፉትም ቀደም ሲል ደመወዝ ከፋይ የነበሩት የእርሻዎቹ ባለቤቶች የሆኑት የህዋሃት ካድሬዎች ናቸው፡፡

በሶስቱም መንገድ የህዋሃት ካድሬዎች በነጻ ጉልበት ስራቸውን ያሰራሉ፡፡ ድሆቹ ገበሬዎች ደግሞ ወደቤተሰባቸው የመመለስ እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ ብዙዎቹ በበሽታና በእርስ በርስ ድብድብ ያልቃሉ ቀሪዎቹም በተደጋጋሚ የሰሩበት በቀጣሪዎቹ ስለሚዘረፍ ወያኔ ያዘጋጀላቸውን የባርነት ኑሮ ይቅጥላሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  አክራሪነት በኢትዮጵያ - ጥያቄዎች ለሃጂ ናጂብ

ሐ. በኢትዮጵያ የወታደራዊ (90% በላይ የኢትዮጵያ ጀኔራሎቹ ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው)፣ የደህንነት፣ የጉምሩክ፣ የኢምባሲ፣ የቴሌ፣ የመብራት ሃይል፣ የአዲስ አበባ መስተዳድር በተለይ በክፍለ ከተማና በወረዳ (አብዛኛዎቹ የአዲስ አበባ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ትግርኛ ተናጋሪዎች ናቸው) ፣የአየር መንገድ፣ የፖስታ ቤት፣ የስኳር ፋብሪካዎችና ሌሎችም በፌደራል መንግስት ስር የሚተዳደሩ መስሪያ ቤቶች ቁልፍ ቦታዎች በአብዛኛው የተያዙት በትግርኛ ተናጋሪዎች ነው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የእርዳታ ድርጅቶች የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ትግርኛ ተናጋሪዎችን በብዛት እንዲቀጥሩ እየተደረገ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሰዎች የሚመጡት ከትግራይ ነው ስለዚህም ትግርኛ ተናጋሪዎች ከሌላው ክልል ተወላጆች የበለጠ የስራእድል አላቸው ማለት ነው፡፡ እነዚህ አዲስ አበባን የሰማይ ጠቀስ ፎቆች ባለቤት ያደረጓት ጀኔራሎች ትግራይ ውስጥ ምንም ኢንቭስት አያደርጉም አይባልም፡፡ የየመስሪያቤቶቹን ቁንጮ ስልጣን የያዙት ትግረኛ ተናጋሪዎች በክልላቸው ኢንቨስት አያደርጉም ማለት ዘበት ነው። በአንድ ወቅት “አዲ በግዲ” ተብሎ ሁሉም ከትግራይ ውጭ የሚኖር የክልሉ ተዎላጅ በትግራይ ከተሞች ቤት እንዲሰራ ተደርጎ እና በርካታ ቤቶች ተሰርተው ተከራይ ጠፍቶ እንደነበር ይታዎሳል።

መ. የትግራይ ተወላጆች በፈደራል መንግስትና በሌሎችም ቦታዎች ባላቸው ስልጣን ተጽኖ በማድረግ በርካታ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ትግራይ ውስጥ ፕሮጄክት እንዲኖራቸው ይታዘዛሉ አንዳንዶችም ፕሮጄክቶቻቼው በቀና መንገድ እንዲሄዱላችው ቀድመው ትግራይን ይመርጣሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ትግራይ ውስጥ ቅርንጫፍ የሌለው፡የውጭም፡ሆነ የአገር በቀል ድርጅት ጥቂት ነው ብል ማጋነን አይሆንም፡፡ ትግራይ ውስጥ ደግሞ ማንም የውጭ ሆነ የአገር ውስጥ ድርጅት የሌላ ክልል ተወላጅ መቅጠር አይታሰብም ቋንቋ እንደምክንያት ይቆጠራል፤ በተቃራኒው የትግራይ ተዎላጆች በሌሎች ክልሎች ውስጥ በብዛት ይሰራሉ።

2. በማህበራዊ አገልግሎት

የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲወዳደር የተሻለ የትምህርትና የጤና አገልግሎት ያገኛል፣ በምሳሌ ላስረዳ ወያኔ ብዙ ያዎራለትን የጤና አገልግሎት ብናይ በ2000 አ. ም እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሪፖርት በትግራይ ለሚኖር 4.5 ሚሊዮን ህዝብ 15 ሆስፒታሎችና 123 ጤና ጣቢያዎች ይህም ለ304333 ህዝብ አንድ ሆስፒታልና ለ37113 ህዝብ አንድ ጤና ጣቢያ ሲሆን በአማራ ደግሞ ለ20.1ሚሊዮን ህዝብ 20 ሆሰፒታሎችና 183 ጤና ጣቢያዎች ይገኛሉ፡ ይሕም አንድ ሆስፒታል ለ1ሚሊዮን ህዝብ እና አንድ ጤና ጣቢያ ለ110636 ህዝብ ይደርሳል፡፡ ይህ ቁጥርን በሚመለከት ሲሆን በአማራ ክልል ያሉት ሆሲፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በመስፈርቱ መሰረት የተሟላ አገልግሎት የሚሰጡ ሳይሆኑ የተሾሙ ናቸው [የተሾሙ ማለትም በወያኔ ሹመት ብቃት ስለማይጠይቅ ያለብቃታቸው ለፖለቲካ ጠቀሜታ የተሰየሙት ጤና ድርጅቶችና ትምህርት ቤቶች የተሾሙ ይባላሉ]በዚህ በወያኔ ዘመን የሚአርጉ ድርጅቶችም እንዳሉ ስነግራችሁ የቀልድ ይመስላችሁ ይሆናል፣ የአረጉ ማለት ያልተሰሩ ግን እንደተሰሩ ተደርገው ሪፖርት የሚደረጉና እንደተሰሩ ተደርጎ የወጣው ገንዘብም በየደረጃው የሚወራረድ ማለት ነው፡፡ ከጥቅሙ ተካፋይ ያልነበረ ተቆጣጣሪ ሲመጣ ድርጅቱ ማረጉ ይነገረዋል፡፡

3. በመሰረተ ልማት

ትግራይ በመሰረተ ልማት ማለትም በመንገድ ፣ በቴሌኮሙኔኬሽን ፣ በመብራት ከሌሎቹ ክልሎች በተሻለ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በቅርቡ ሪፖርተር የሚገርም ዜና አውጥቷል አንድ ትግራይ ውስጥ ለሚሰራ መንገድ ሱር ኮንስትራክሽን የ2ቢሊዮን ብር ውል ፈረመ የመንገዱ ርዝመት 53ኪሚር ሲሆን ለአንድ ኪሎ ሜትር 40ሚሊዮን ብር ይከፈለዋል፡፡ እስካሁን በአገሪቱ ለኮንትራክተር የተሰጡ መንገዶች በኪሎሜትር ከ20ሚሊዮን አይበልጥም ነበር ይላል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሁሉም ነገር ወደ ትግራይ! (ዳግማዊ ጉዱ ካሣ)

4. በልማት

ባለፉት 23 አመታት ትግራይ ውስጥ በአድዋ፣ አዲግራት ፣ መቀሌ ፣ ማይጨው በርካታ ፋብሪካዎችና የአገልግሎት ሰጭ ትቋማት ተሰርተዋል እነዚህም ድርጅቶች ለብዙ ሰዎች የስራ እድል ፈጥረዋል፡፡

ከዚህ በላይ የቀረቡት መረጃዎች የሚያሳዩት ትግራይ ውስጥ የተሻለ መሰረተ ልማት ፣ ማህበራዊ አገልግሎትና በጣም የተሻለ የሰራ እድል መኖሩን ነው፡፡ ወያኔ ማእከላዊ መንግስቱን በመቆጣጠሩ ለወጣበት ክልል ልጆች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡ ወያኔ ለትግራይ ወጣቶች ያመጣላቼው ግን የተሻለ የስራ እድልና ገንዘብ ብቻ አይደለም፤ በየሄዱበት በጥርጣሬ መታየትን በአንዳንድ ቦታም መጠላትን ጭምር እንጅ።

ይህ የወያኔ አንድን ክልል ለብቻው ሌሎችን ክልሎች በሚጎዳ መልኩ ለማሳደግ የሚደረግ ጥረት ፍሬ እያፈራ ነውን? የሚል ጥያቄ መጠይቃችን አይቀርም። መልሱ አዎ የትግራይ ህዝብ የተሻለ የትምህርት ደረጃ ፤ ዝቅተኛ የስራ አጥ ቁጥርና በተለይ በህጻናት ሞት ዝቅተኛ መጠን አስመዝግቧል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2011 በአሜሪካ የእርዳታ ድርጅትና በማእከላዊ ስታቲስቲክስ ድርጅት በተደረገ የህዝብና የጤና ጥናት (Demographic and health survey) መሰረት ክጥናቱ በፊት ባሉት 12 ወራት ውስጥ ምንም ስራ ያልሰሩ ወይም ያልተቀጠሩ ሴቶች በመቶ ሲለካ በትግራይ 24.8%፣ በአማራ 38.4%፤ በኦሮሚያ 43.9% ና በደቡብ ህዝቦች 44.8% ነበር። በተመሳሳይ ጥናት መሰረት በእርግዝናቸው ጊዜ በሰለጠነ ባለሙያ ምርመራ የተደረገላቸው እርጉዞች በመቶ የሚከተለውን ይመስል ነበር፤ ትግራይ 50.1% ፤ አማራ 33.6% ፤ ኦሮሚያ 31.5% ፤ የደቡብ ህዝቦች 27%. ከዚህ ላይ የትግራይም ሽፋን ቢሆን በቂ ነው ማለት አይደለም ግን ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲውዳደር ከፍተኛ ነው።

በተመሳሳይ ጥናት መሰረት ክትባት የተከተቡ ህጻናት በመቶ ትግራይ 73.4%፤ አማራ 38.4%፤ ኦሮሚያ 26.8% ና ድቡብ ህዝቦች 38.1% ነበር።

በዚሁ ጥናት መሰረት ከአንድ አመት በታች የሆኑ ህጻናት ሞትና (IMR) ከአምስት አመታት በታች ባሉ ህጻናት የሞት መጠን በሚቀጥለው ሰነጠረዥ ቀርቧል

ከዚህ በላይ እንደሚታየው ትግራይ በሁሉም መለኪያዎች የተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛል። ትግራይ በ 2005 የደረሰበት ደረጃ ሌሎቹ ክልሎች በ2011 ማለትም ከ5 አመታት በኋላም አልደረሱም ፤ በሌላ አነጋገር ሌሎቹ ክልሎች ትግራይ የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ከ7-8 አመታት ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው።

በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ውስጥ አንድ ቀልድ አለ እሱም ቀደም ሲል አንድ ወጣት ስታድግ ምን መሆን ትፈልጋለህ? ሲባል ፓይለት ፤ ዶክተር ማለት የተለምደ ነበር፤ ያሁኑ ወጣቶች ግን ምን መሆን ትፈልጋለህ ሲባሉ ቶሎ ብለው “ትግሬ” ይላሉ። አሁን ባቋራጭ ሀብታም የሚያደርገው ፓይለትነት ወይም ዶክተር መሆን ሳይሆን ከገዥ ጎሳ መወለድ በመሆኑ ነው።

ለማጠቃለል ያህል በሁሉም መስፈርቶች የትግራይ ክልልም ሆነ ግለሰብ ትግርኛ ተናጋሪዎች የወያኔ ከፋፍለህ ግዛ ስርአት ተጠቃሚዎች እየሆኑ ነው ይህም እንዲቀጥል ወያኔ ሌሎች ክልሎች ብቃት ባላቸው ሰዎች እንዳይተዳደሩና ለእድገት ጥረት እንዳያደርጉ ሌሊት ከቀን ተግቶ ይሰራል። የክልል ፕሬዘዳንቶችን ይሽራል፤ ይሾማል፤ ይቆጣጠራል። ህዝብን ከህዝብ ያጋጫል ፤ ያፈናቅላል። ሲፈልግ አመጽ ያስነሳል፤ አመጹን ልቆጣጠር በማለት ይገድላል ፤ ያስራል፤ ከስራም ያፈናቅላል።

የዚህ ሁሉ ግፍ ቁናው ሞልቶ ዶክተር መረራ በተደጋጋሚ እንደሚሉት የሚበላው ያጣ ህዝብ መሪዎቹን ሳይበላ ሊታሰበብት ይጋባል እላለሁ።

ቸር ይግጠመን።

7 Comments

  1. Dear Andualem,
    Your article is less emotional but fair, investigative as well as analytical. As you clearly has indicated almost all Tigres including members of arena are beneficiaries as well as supporters of the system.

    I hope Professor Mesfin will read your analytical thesis and come back to his mind.

  2. the writer is either a stupid arrogant MORON who has no clue about the reality except being driven by emotion or a weyane servant who wants to expand the gap between tigrians & non-tigrians…regardless of his long echo and regardless of some stupid arrogant morons irritional comment, the truth is that weyane doesnt represent tigrians as millions of tigrienas are dying everyday with starvation while million of tigrians are being killed, harassed and abused as same as non-tigrians ethiopians, and the only solution is instead of sitting behind a computer and flooding with irrelevant echo ….lets us work together and united to remove the weyane cancer …in fact those who are irrationally saying that tigrians are benifeciers from weyane are not diffrent from those who are saying that Amahra was benfeciery in derg and hailesellasie…lets stop this stupid type argument and wake up from our dream to focus on weyane

  3. I agree with the author. Although i dislike such argumentation, on the other hand we have to be bold enough to face truth. Woyane didnot represent the great Tigiray people this must be underlined. But as the author said, these people benefited more in relation to other nations and nationalities in Ethiopia.

    let me add few points

    1. Come and see in Gambela, Benishangul, and even in some places in south Omo zone, most investors who won huge ha of land are Tigries. That means, these investors who unfairly owned land in most cases displacing locals and pushing out existing older investors, have their families in Tigray. Their families are benefiting hugely from such illegal investments. Donot undermine the number of these illegal investors, they are many.
    2. Today, it is more than simple thing for a tigiray youths and man to come to addis and other cities, simply get land, loan, and start up business, while its is almost impossible for others. Many youth from other nations who even presented a very clear proposal to get loan and land were not given. for instance, go and see all the licurative businesses from Megenagna to Hayat. All the shops that sale construction materials, cement, steel—wood products, water works are owned by tigire. It is only hardly possible to get Gurage, amhara or oromo doing these type of business in these areas. See all cement, gravel, sand distributors, they are all tigres. That means they are doing huge money and hence their families are benefiting.

    3. Who can re-post the list of the 400 or so people whose bank account was temporarley off last time by government. Over 90% of them are tigries. wedia wedeh malet asayfeligem.

    4. who own most of the effective business companies in all cities including hotels, shoping moles? mots of them are owned by tigire. One has to not simply drop what dr merera last time said. —amara 100 amet yegataten hager 20 amet enkua sanibela mikegna bezaben—-i am not sure if amhara did that. In case they did they have to be blamed, but it is unfair to say we should repeat what amhara did sometimes ago.
    5. most posts in government institutions including NGOs are occupied by tigire. The government stretch hand up to distant far to make sure the best posts will be given to tigire. this is true.

    My friends, just go out see and see around bole, and or megenagna, so that you will see the clear boundry/difference between tigire children and the children of other nations. It is more than clear and visible! Just go to a restorant and you will see a young tigire boy just investing 10 of 1000s on spot, while millions go hungry.

    It is obvious tigires are beneficail compared to others.

    meweshashetu bezum riket aysedenim

  4. @አንዷለም አስራት You spoke my mind. የኢትጵያን ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታ በትክክል ተረድተኸዋል፡፡ አንተ እንዳልከው ሌሎች ክልሎች በቂ የትምህርት ዝግጅት፤ ልምድ እና ብቃት በሌላቸው ሰዎች እየተዳደሩ ነው፡፡ በራስ መተማመን የሌላቸው እና አሁን ካሉበት የመንግስት ስልጣን ውጭ ሌላ ቦታ መስራት ስለማይችሉ ወያኔ ከሚያዛቸው ውጭ ዝንፍ አይሉም፡፡ ወያኔ ሆን ብሎ የሚነገራቸውን ብቻ ወደታች የሚያስተላልፍ ካድሬዎችን በየክልሉ የሰገሰገው፡፡ አሁን ኦሮሚያ ክልል ከነ ሙክታር ከድር፤ አስቴር ማሞ፤ ዳባ ደበሌ ወዘተረፈ የተሻለ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሰዎች የሉትም?
    ተላላኪዎቹም ለወገናቸው የሚቆረቆሩ ከሆኑ ስም ይለጠፍባቸዋል፡፡ አንድ የአማራ ክልል ባለስልጣን ስለክልሉ ልማት ወደ ኃላ መቅረት ካነሳ ትምክተኛ ተብሎ ከስራ ይባረራል፡፡ የኦሮሚያው ጠባብ ተብሎ ይባረራል፡፡ የትግራይ ክልል ባለስልጣን እንዲህ ካለ ሀገር ወዳድ ተብሎ ስልጣን ይጨመርለታል፡፡
    ሌላው መጨመር የምፈልገው የመከላከያ ኮንስትራክሽን የሚባለው እና በብዙ ቢልዮን የሚቆጠር የሀገሪቱን ገንዘብ የሚያንቀሳቅሰው ተቋም የወያኔ የግል ንብረት ነው ማለት ይቀላል፡፡ ይሄ ተቋም በሚሰራቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ውስጥ ለተደራጁ የትግራይ ተወላጆች ያለምንም ውድድር የብዙ ሚሊዮን ስራ ሰብ ኮንትራት ይሰጣቸዋል፡፡ ሌላ ምሳሌ ደግሞ የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌምንኬሽን ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም ከ አንድ ሺ የማያንሱ በተለያዩ ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ተማሪዎችን ቀጥሮ ነበር፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ግን የተቀጠሩት በተለመደው አሰራር ማስታወቂያ በሰው ኃይል አስተዳደር በጋዜጣ ወጥቶ ሳይሆን ማንም የኮርፖሬሽኑ ማኔጅመንት ሳያውቅ እና ሳይወስን በጊዜው የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ በነበረው ደብረጽዮን ደብረሚካኤል ቀጭን ትዕዛዝ ነው፡፡ እነዚህ የተቀጠሩት ሁሉም በዩንቨርሲቲ ቆይታቸው ቀንደኛ የኢህአዴግ አባላት የነበሩ ናቸው፡፡ ከነዚህ አንድ ሺ ውስጥ ሰባት መቶ የሚሆኑት ትግሬዎች ናቸው፡፡ በ 2007 እ.ኤ.አ በተደረገው የህዝብ እና የቤት ቆጠራ ከአጠቃላይ 73,750,932 የኢትዮጵያ ህዝብ የትግራይ ክልል ድርሻ 4,483,892 ነው፡፡ ያም 6.07% ነው፡፡ የቴሌን እንደ ምሳሌ ስንወስድ 6.07% የህዝብ ድርሻ ያለው ህዝብ 70% የሚሆነውን የመንግስት ስራ ያገኛል፡፡ ቀሪው 93.93% ህዝብ 30% የሚሆነውን የመንግስት ስራ ያገኛል ማለት ነው፡፡ ያኔ የተቀጠሩት አሁን ወደ ከፍተኛ ማኔጅመንት የገቡ አሉ፡፡ ይሄንን መረጃ በ2000 ዓ.ም የቴሌ ሰራተኛ የነበረ ማንኛውም ሰው የሚያውቀው ነው፡፡ ይህንን የምታነቡ ሁሉ የዚህን መረጃ ትክክለኝነት በጊዜው የቴሌ ተቀጣሪ የነበረን ሰራተኛ ጠይቃችሁ ማረጋገጥ ትችላላችው፡፡
    የትግራይ ህዝብ አሁን ካለው ስርዓት በአስተዳደር እና ኢኮኖሚ ከሌሎች የሀገራችን ህዝቦች በብዙ እጥፍ በበለጠ ተጠቃሚ መሆኑ ግልፅና አከራካሪም አይደለም፡፡

  5. This is a good analysis and I agree 100% with the writer. This short analysis is only the tip of the iceberg. As we dig deeper and deeper in the data, we are going to see a lot of surprising and utterly unfair balance of poltico – socio – economic data in the future.

  6. It is amazingly analysed. I think Abreha Desta, professor Mesfin and others who claim that, the people of Tigray has not benefitted from the brutal regime of weyane needs to think twice before they suggest such kinds of unacceptable idea. Certainly, supporter of this racist regime has tried to convince the Ethiopian people as if the people of Tigray has not benefitted from the vicious regime of weyane. These people still they are trying and will also try to misinform the people of Ethiopia to divert from the reality. However, regardless of their effort to deceive the people of Ethiopia, the fact of the matter is they can’t hide the truth from the people of Ethiopia. It is better for them to stop their extreme selfish ambition to rob Ethiopia in order to build their region and also they need to repent for the evil deed they committed in the past and now before it is too late. Even though the dictator weyane tried to benefit its region, they have made the people of Tigray hated by the rest of Ethiopian people. They made the people of Tigray to live uncomfortable life among others. Soon or later the almighty God will bring Justice in Ethiopia. God bless Ethiopia.

  7. አንዱአለም ልጅ ይውጣልህ! ብዙዎቻችን እያልን ያለነዉ ይህንን ነዉ:: ማለባበስ ይቅር ነዉ የምንለዉ:: ትግሬ ሆነዉ በዚህ ስርአት የተጎዱ አሉ? አዎ አሉ:: የተጠቀሙስ? እንደጥያቄ እንኩዋን ሊነሳ አይገባዉም _ በጣም ግልፅ ስለሆነ:: የተጎዱና የሚጎዱ ትግሬዎች አእምሮኣቸዉን መጠቀም የፈለጉ ብቻ ናቸዉ:: ሌላዉና አብዛኛዉ ኢትዮዽያንና ህዝቡዋን በማጥፋቱ ወንጀል ከግር እስከራሱ ተነክሮበታል:: መጨረሻዉ ግን የእቶን እሳት ነዉ:: እናያለን ብዙ_ታገሱ!
    አቤል የተባለዉ አስተያየተኛ ሌላ ሳይሆን ራሱ ወያኔ ነዉ:: ወያኔ በሚዮን የሚቆጠሩ ተጋሩ በጥይት ሲፈጅ; በርሀብ ሲገድል; በችግር ሲኮደኩድ … ይታያችሁ:: በዚህ አይነት እንደአቤል ከሆነ በወያኔዉ ስርአት አንድም ትግራዋይ አልደላዉም ማለት እኮ ነዉ:: ዉሸታም!!
    አንዱአለም አሁንም ልጅ ይዉጣልህ!
    አንድ በጣም በቅርብ የማዉቀዉ ወያኔያዊ ጉድ ላስታዉስ:: ትንሽ ተደነቁ::
    በምኖርበት ቀበሌ አንድ ትግሬ ካድሬ አንድ ዲግሪ ያለዉ ሰዉ መርጦ ለአንድ ከፍ ያለ የሺሞት ቦታ(የሹመት) እንዲልክ ከበላዮቹ(ትግሬዎች) ይነገረዋል:: ያ ካድሬ የትግሬ ባለድግሪ በቀበሌዉ ፅ/ቤት ቢሮዎች ቢፈልግ ቢያስፈልግ ያጣል:: ይህን የሰማ አንድ አማራ ባለድግሪ አይኑን በጨዉ አጥቦ ወደካድሬዉ ቢሮ ይሄድና ‘ለምን እኔን አትልከኝም?’ ይለዋል:: ብልግና’ቸ ‘ዉንና ትእቢታዊ እዉርነታቸዉን እዩልኝ እንግዲህ:: ካድሬዉ በማላገጥ ‘ያንተን ድግሪ ለሽንት ቤት ተጠቀምበት!’ ነዉ ያለዉ:: የላከዉ ታዲያ የተጠየቀዉን መስፈርት አጣሁ በሚል ዲፕሎማ ያለዉ ትግሬ ነዉ:: ይህ አስጠሊታ ዘመን ማለፉ አይቀርምና ሲያልፍ የምናወራዉ ብዙ ታሪክ አለ:: ግን ግን እንዳይዘነጋ በደንብ ይመዝገብ:: ለማንኛዉም ለሁላችንም አቅል ጀባ:: ቀኒቱ ቀርባለች!! ያኔ ወዩ መግቢያሽን እንጃ::

Comments are closed.

Share