ራስዎን በሁለት ቦታ የማስገኘት ጥበብ

ከሊሊ ሞገስ

ፈረንጆቹ (በይበልጥ የስነ ልቦና ተመራማሪዎች) ‹‹ቴሌፓርቴሽን›› በማለት ይጠሩታል፤ ስለተመኙ ወይም ስላሰቡ ብቻ የፈለጉት ቦታ የመገኘት ታላቅ ጥበብ ነው፡፡ ደግሞ አስደናቂው ጉዞ የሚከናወነው ከብርሃን ፍጥነት በመጠቀ ቅፅበት እንደመሆኑ መጠን እልህ አስጨራሽ የኤምባሲዎችን የቪዛ ቢሮክራሲ ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የሚችል መሆኑ በጣም አስደሳች ነገር ሆኖ ሳለ፤ ዘመድ አዝማድ ሳይሰናበቱ እንደው በድንገት የሚከናወን ምኞት በቅፅበት ነጥቆ እሩቅ ሀገር መውሰዱ ምናልባት መጠነኛ የሆነ ቅሬታ ሊፈጥር ይችላል፡፡

እንዲያውም ሆኖ ግን የብዙዎች ‹‹ባህር ናፋቂ›› ልቦች ምኞት ከምኞትነት አልዘለለም፣ በተፈጥሯዊው የቴሌፓርቴሽን ጥበብ የታደለ ሆኖ መገኘት ማለት ከባህር ውስጥ መርፌ የመፈለግ ያህል የማይመስል (Rare) ነገር ነው፡፡

በቅርቡ እየተሰሙ ያሉት ሌሎች ግኝቶች ደግሞ ለሰሚ ጆሮዎች አግራሞትም ድንጋጤም ሊፈጥሩ የሚችሉ ናቸው፡፡ ጉዳዩ እንደ ቴሌፓርቴሽን ለሳይንስ ገና ሊታይ ያልቻለ ‹‹ተዓምር›› አይደለም፤ ጉዳዩ የሳይንስ ውጤት ነው፡፡ ሆኖም እንኳን ሳይንስን እንደ ፖለቲካ ለምናገል ብዙሃን ቀርቶ በዘርፉ ተሰማርተው ለሚገኙ ተመራማሪዎችም ግኝቱ ግራ መጋባትን መፍጠሩን መፅሔቱ ዘግቧል፡፡ ይህ አዲስ ፈጠራ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ በእምቡጥ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኝ ቢሆንም ከዚህ በኋላ የሚመጣውን ዘመን አኗኗር ግን በከፊል ወይም በሙሉ ሊቀይር (አሊያም ሊያናጋ) ይችላል ተብሎ ከወዲሁ ተተንብዮለታል፡፡

ነገሩ ወዲህ ነው፤ ወደ ቴክኖሎጂያዊ ፈጠራው ውስጠ ምስጢርና ሐተታ ዘው ብለን በደረቱ ከመዝለቃችን በፊት ቴክኖሎጂው ስለሚያስገኛቸው መልካም ትሩፋቶች በጥቂቱ ጀባ እንበላችሁ፡-

ምሳሌ 1፡- ለስራም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ከሚኖሩበት ሞቅ ያለ ከተማ ርቀው ስልጣኔ ወዳልዳሰሰው አካባቢ ተጉዘዋል እንበል፤ ታዲያ ቀድሞ ይከሰታል ብለው ያላሳቡት የጤና ችግር ይፈጠርና ችግር ላይ ይወድቃሉ፡፡ ደሞ አጣዳፊ በሽታ ነው፤ ግን ሐኪም እንደሰማይ ርቆዎታል፡፡ ሆኖም ብዙ ጊዜ ከኪስዎ የያዝዋትን የሞባይል ስልክ በመጠቀም ወደ ሐኪምዎ የያዝዋትን የሞባይል ስልክ በመጠቀም ወደ ሐኪምዎ ጥሪ ያደርሳሉ፡፡ ከዚያም ስልኳ ላይ ያሉትን አንዳንድ ቁልፎች ጫን ጫን ሲያደርጉ በሚያስገርም ሁኔታ መዳፍ የማትሞላው ሞባይል ወደ ዶክተርነት ትቀየራለች፡፡ ዶክተሩ እዚያው ባሉበት አገላብጦ ይመረምርዎታል፤ ያክምዎታልም፡፡

እዚህ ላይ ግን ሞባይልዎ የተለወጠችው ስጋ ወደ ተላበሰ ዶክተር አለመሆኑን አስረግጠው ይወቁ፡፡ ሞባይሏ የተቀየረችው ወደ አርቴፊሺያል ዶክተርነት ነው፡፡ ዶክተሩ ደግሞ ከየትም የመጣ ሳይሆን በሩቅ ትተውት ከመጡት የመኖሪያ ከተማዋ ዘወትር ክሊኒኩ ውስጥ ተቀምጦ በሽተኞቹን የሚያስተናግደው ወዳጅዎ ነው፡፡ በሽቦ አልባው መስመር በአየር ላይ ረዥም ጉዞ ተጉዞ እርስዎ ጋ ይደርስና ሞባይልዎ ውስጥ ዘው ብሎ ገባ፣ በዚያው ቅፅበትም ሞባይልዎ ወደ ‹‹እሱነት›› ተቀየረች፣ ተመረመሩ፣ ተገቢው ህክምናም ተደረገልዎት!

ምሳሌ 2፡- መቼም ‹‹ቪዲዮ ኮንፍረንሲንግ›› የሚባለው የስብሰባ ‹‹ፋሽን›› ሀገራችን ውስጥም ሳይቀር በመስፋፋት ላይ ነው ያለው፡፡ እንግዲህ ቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ በቦታ ተራርቀው የሚገኙ ተሰብሳቢዎች በቪዲዮ ስክሪን አማካኝነት የተለያዩ እሰጥ አገባቸውን የሚያጧጡፉበት ዘዴ ሲሆን ርቆ የሚጓዘው ምስላቸው ብቻ ነው፡፡ በመጪው ዘመን ዓመታት ግን ለተሰብሳቢዎች የሚልኩት በቪዲዮ የተቀረፀ ምስልና ድምፅዎን ብቻ ሳይሆን ተንቀሳቃሽ ሐውልት የመሰለውን ባለሶስት ዳይሜንሽን (3-D) አካልዎን ከነአስተሳሰብዎ ጭምር ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ መንግስት ቻይና አሰርቶ ያስገባው የጸረ ኤችአይቪ መድሃኒት ከፍቱንነት ይልቅ አቁስሎ እየገደለ ነው ተባለ

እርስዎ ‹‹እርስዎነትዎን›› ለወዲያኛው ጫፍ በመላክ መልካም ተሳትፎ እንዳደረጉ ሁሉ ከዚያኛው ጫፍ ላይ ያለው አጋርዎም በሽቦ አልባው መገናኛ አማካኝነት ‹‹እሱነቱን›› ይልክልዎታል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታም ሌሎች ተሳታፊዎች ካሉም ተመሳሳይ ሂደት ያከናውኑና ስብሰባው በይፋ ይጀመራል፡፡
ለምሳሌ እርስዎ መቀመጫዎት እዚህ መዲናችን ውስጥ ቢሆን፣ ሁለተኛው ተሳታፊ ናይሮቢ፣ ሶስተኛው ጆሃንስበርግ፣ አራተኛው ቦነስ አይረስ፣ አምስተኛው ኒውዮርክ፣ ስድስተኛው ለንደን፣ ሰባተኛው ሲዲኒ፣ ስምንተኛው ዱባይ፣ ዘጠነኛው ቤይጂንግ እንዲሁም አስረኛው ደግሞ ሚላን ቢሆን፣ በአስሩም የተራራቁ ከተሞች ውስጥ ለስራችሁም ጠረጴዛ ከባችሁ ትቀመጣላችሁ፣ አልፎ አልፎ እንደሚታየው በመካከላችሁ ጠና ያለ አለመግባባት ከተፈጠረም እንዳስፈላጊነቱ እርስ በርስ መቧቀስ ትችላላችሁ!

ምሳሌ 3፡- የጤናን ጉዳይ አሁንም እናንሳና (አያድርስብዎትና) በሆድ ውስጥ ህመም ታመው በኦፕራሲዮን ጠረጴዛ ላይ በማደንዘዣ ደንዝዘው የቀዶ ጥገናው ሂደት እየተከናወነብዎት ነው እንበል፡፡ ታዲያ ደዌው የመሸገበት የሆድ ውስጥ ብልትም መጠኑ በጣም አነስተኛ ሆነው ሐኪሞቹ የት ቦታ መቁረጥ እንዳለባቸው ተቸገሩ እንበል፤ ነገር ግን ሐኪሞቹ የመጪው ዘመን ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ነበሩና የምስር ፍሬ የምታክለውን ብልት ወደ ግዙፍና ተመሳሳይ ግን አርቴፊሻል ብልት ቀይሯት፤ ደዌው ያለበትን ጥግም ተመለከቱ ከዚያም ይህን ወሳኝ መረጃ በመጠቀም ጥንጥየዋን ብልት ኦፕራሲዮን ለማድረግ ቻሉ!

እነዚህን ሁሉ እውነተኛ ተአምሮች እንካችሁ ብሎ የሚሰጠን ‹‹Claytronics›› ተብሎ የተሰየመው ጥበብ ነው፡፡ ጥበቡ ከቴሌፓርቴሽን ጥበብ የሚለየው በቴሌፖርቴሽን አንድ ሰው ካለበት ቦታ ተነስቶ ሌላ ስፍራ ላይ ሲያርፍ በቦታው የሚገኘው የተፈጥሮ አካሉ ነው፡፡ በክሌይትሮኒክስ ጥበብ ግን በሌላኛው ላይ የሚገኘው ስጋ የለበሰው ተፈጥሯዊው አካል ሳይሆን የእርሱ ሙሉ ቅጂ ነው፡፡ ቅጂው በመልክ፣ በቁመና እንዲሁም በአሰተሳሰብ ከኦርጅናሉ ሰው ጋር ፍፁም ተመሳሳይ ከመሆኑም በተጨማሪ ህይወት በውስጡ ያለ ይመስል የተንቀሳቃሽ አካል ባለቤት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ኦርጂናሉ ሲናገር በሩቅ ያለው ቅጂውም ተመሳሳይ ንግግር ይናገራል፤ ኦርጅናሉ የሚያከናውናቸውን ማናቸውንም እንቅስቃሴዎች በቅጂው ‹‹ይቀዳሉ››፡፡

ስለዚህም የክሌይትሮኒክስ ጥበብ ከተአምራዊው የቴሌፓርቴሽን ጥበብ የተሻለ ጥቅም የሚያስገኝ ነው ተብሎለታል፡፡ በቴሌፓርቴሽን ጥበብ አንድ ሰው በሁለት የተለያዩ ስፍራዎች ላይ መገኘት አይቻለውም፤ ይህ ሁኔታ ግን ለክሌይትሮኒክስ የሚሳነው አይደለም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም፣ የቴሌፓርቴሽን ጥበብ ‹‹የሚታደሉት እንጂ የማይታገሉት›› ሲሆን ክሌይትሮኒክስ ግን እደማንኛውም የቴክኖሎጂ ውጤት ለፈላጊ ተጠቃሚው የሚሸጥ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health: ጤናማ ሆኖ ለመቆየት 6ቱ ምርጥ ጥቆማዎች

ግና ለመሆኑ ‹‹ክሌይትሮኒክስ›› ምን የሚሉት ጥበብ ነው? የመሳሪያው መሰረታዊ አካላት ‹‹Catoms›› በመባል የሚታወቁ ሲሆኑ፤ እያንዳንዱ ካቶም መጠኑ የፀጉርን አንድ ሚሊዮንና የደቀቀ መጠን ያላቸው አነስተኛ ኮምፒውተሮች ናቸው፡፡ በዘርፉ ጠበብት ‹‹ናኖ ኮምፒውትርስ›› በማለት ይጠሯቸዋል፡፡

ናኖኮምፒውተር (የአምስት ሣንቲም አስር ሚሊዮንኛ መጠን ያላቸው ኮምፒውተሮች) ለዘመናችን አዲስ የሚባሉ አይደሉም፡፡ ካተሞች (Catoms) ግን ከሌሎቹ ናኖኮምፒውተሮች በብዙ መልኩ የተለየ ባህሪይ ነው ያላቸው፡፡ ካተሞች እርስ በርስ የመገጣጠም ልዩ ፀባይ አላቸው፡፡ እንደ አስፈላጊነቱም አንዴ ሞባይል ስልክ፣ አንዴ ብዕር፣ አንዴ መነፅር ወይም ሌላ ጊዜ የሰው ቅርፅ መያዝ ይችላሉ፡፡ የተለያየ ቅርፅ እንዲይዙ የሚያስችላቸው ደግሞ የተቀመሩበት ሶፍትዌር (ፕሮግራሚንግ) መሆኑን የቴክኖሎጂው ፈጣሪ ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡

የክሎይትሮንክስ አመጣጥ

በታዋቂው የቴሌኮሙኒኬሽን መሳሪያዎች አምራች ኩባንያ ‹‹ኢንቴል›› የምርመራ ላብራቶሪ ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሁለት ሰዎች ማለትም ቶድ ሞሪ እና ሴት ጎልድስታይን የተባሉት ሳይንቲስቶች ናቸው፡፡ ከመጀመሪያው ሐሳቡን በማመንጨት በቀጣይነት ወደ ምርምሩ የገቡት፡፡ ጠቢባኑ ‹‹ክሌይትሮኒክስ›› የሚባለው ሃሳብ ጭንቅላታቸው ውስጥ ብልጭ ያለባቸው የዛሬ ስምንት ዓመት ገደማ በተከሰተ አንድ አጋጣሚ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ያኔ ቨርጂኒያ ውስጥ በተዘጋጀ አንድ ኮንፈረንስ ውስጥ እንድንሳተፍ ለሁለታችንም ጥሪ ቀረበልን፡፡ ታዲያ ስብሰባው የሚካሄደው በቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ አማካኝነት ነበርና ቨርጂኒያ ድረስ መጓዝ አላስፈለገንም፡፡ ይህ ሁኔታ በጣም ስላደሰተንም ነበር ለቀጣይ ምርምር የጋበዘን፡፡ ከቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ የተሻለ ነገር ለምን አንፈጥርም? ተባባልን፡፡ ምርምሩ ተጀመረ፣ እናም አሁን ያለንበት ደረጃ ላይ ደረስን በማለት ነበር የገለፁት፡፡
አነስተኛ መጠን ያላት መሳሪያ ነች፡፡ ቁመቷ 3.4 ሴ.ሜ፣ የዙሪያ ዲያሜትሯ ደግሞ 4.4 ሴ.ሜ የሆነችና የባትሪ ድንጋይ ቅርፅ ያላት ስትሆን ወደ አስር አይነት የተለያዩ ቅርፆች መቀየር ትችላለች፡፡ ቅርፆቿን የሚቀይረው አብሮ የተገጠመላት ኮምፒውተር ሲሆን በሽቦ አልባው መገናኛ አማካኝነት ራቅ ካለ ስፍራ ላይ ባለ ሰው መታዘዝ ትችላለች፡፡ ስሪቷ ከካተምስ የሆነችና የክሌይትሮኒክስ ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ ውጤት ነች፡፡ ምርምሩ ግን በአስገራሚ ፍጥነት ቀጥሏል፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥም የታለመለትን ግብ ይመታል ተብሎ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ በተለይም አንድ ሰው በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ሁለት የተለያዩ ስፍራ ሊገኝ የሚችልበት ጥበብ መሆኑ ታላቁ የኢንቴል ኩባንያ ምርምሩን ስፖንሰር እንዲያደርግ አስገድዶታል፡፡

በእርግጥ አንድ ሰው በክሌይትሮኒክስ ወደ ሌላ ስፍራ እንዲጓዝ የአካሉ ቅርፅ በቪዲዮ ተቀርፆ በሽቦ አልባ መገናኛ ወደ ሌላኛው ጫፍ የሚተላለፍበት ሁኔታ መኖር አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም ሲባል ኦርጂናል አካል ባለበት ስፍራ ሆኖ በቪዲዮ ይቀረፃል፡፡ ቪዲዮ የሚቀርፀው መሳሪያ በአይነቱ ለየት ያለና የሰውየውን አካል በ360 ዲግሪ ከሁሉም አቅጣጫ እየቀረፀ በየሰከንዱ የሚያስተላልፍ ነው፡፡ በሌላኛው መሳሪያም ይህን የተሟላ መረጃ በመመርኮዝ የሰውየውን ተመሳሳይ ቅጂ (ኮፒ) ይሰራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health: አስም ትናንት፣ ዛሬና ነገ - የአስም ህክምናዎችና መድሃኒቶች በቀድሞዎቹ እና በአዳዲስ ጥናቶች ውስጥ

የክሎይትሮኒክስ ቴክኖሎጂ በጣም ወሳኝ የሚባሉ በጎ ጠቀሜታዎች ኖረውት ሳለ ምናልባት ለጥፋት ተግባር ሊውል ይችላል የሚል ፍራቻ ገና ከአሁኑ እየተንፀባረቀ ነው፡፡

ለምሳሌ ቅጂ ወታደሮችን ለጦርነት በመጠቀም ምንም ሳይጎዱ ሌላውን ብቻ መጉዳት፣ ከዚህም በተጨማሪ ለዝርፊያ ተግባር እና ለመሳሰሉት ወንጀሎች ቢውል የወንጀለኛው ዱካ ወይም አሻራ ሊገኝ በማይችልበት ሁኔታ ከበድ ያሉ የወንጀል ተግባራት ሊፈፀሙ ይችላሉ፡፡ ያም ሆነ ይህ መቼም መጠቀም ካለ ጉዳት መኖሩ አይቀርምና ገና ለገና ለጥፋት ዓላማ ሊውል ይችላል በሚል ፍራቻ ተመራማሪዎች ከምርምራቸው አልቦዘኑም፡፡ እንደማንኛውም አዲስ ቴክኖሎጂ ክሌይትሮኒክስም በወደፊት ህይወታችን ላይ የሚያስከትለውን ለውጥ ከወዲሁ በትክክል ለመገመት ያስቸግራል፡፡ ወይ ያለማናል፣ አሊያም ያጠፋናል፣ ለውጡ ግን አይቀርልንም፡፡

ናኖቴክኖሎጂና ቴሌፓርቲሽን ሌሎቹ አማራጮች

በክሌይትሮኒክስ በአንድነት ሁለትነት፣ ሁለትም በአንድነት መከሰቱ ላልተመቻቸው ደግሞ ሌላ አማራጭ አለ፡፡ ምን ጠፍቶ፣ የጊዜው መርዘም ካልሆነ በቀር ሁሉ በእጃችን ሁሉም በደጃችን ነው፡፡
ናኖሮቦቲክስ ሁለተኛው አማራጭ ነው፡፡ ይህ ድንቅ ጥበብ የሚያተኩረው ደግሞ በአይን ለማየት እጅግ በሚከብዱና ጥቃቅን በሆኑ ሮቦቶች የሚመራ ቴክኖሎጂ ማስታቀፍም ይከተላል፡፡ ሽሉም የዘጠኝ ወር እድገቱን ጨርሶ እነሆ ይወለዳል፡፡ ሰውዬውም የድሮ ህፃናንቱን ክሎን በተደረገው ህፃን ውስጥ መመልከት ይችላል፡፡ ልጅም ሲያድግ ቁርጥ አባቱን፡፡ በእርግጥ ሴቷ አርግዛ ትውለድ እንጂ የልጁ ባዮሎጂካዊ (የዘር) እናትና አባት የሚባለው ሰውየው ነው፡፡ አባትና እናት ይባልም እንጂ ልጁ ልጅ ብቻ ሳይሆን ቁርጥ የሰውየው መንትያ ወንድም ነው፡፡ የሚበላለጡት በዕድሜ ብቻ!
ይህን ሁሉ ዕድል ይቅርብኝ ላለ ሰው ደግሞ የመጨረሻ ሌላ ዕድል አለ፡፡ ኳንተም ቴሌፓርቴሽን መቼም የእያንዳንዱ ሰው ሴል የተሰራው ከአተሞች ነው፡፡ እያንዳንዱ አተምም የተሰራው ከፓርቲክሎች ነው (ኤሌክትሮን፣ ፕሩቶንና ኒውትሮን)፡፡ እያንዳንዱም ፓርቲክል የኳንትም ባህሪ ያለው በመሆኑ በአንዴ ሁለት ቦታ ይከሰታል፡፡ እያንዳንዱም ፓርቲክል የኳንትም ባህሪ ያለው በመሆኑ በአንዴ ሁለት ቦታ ይከሰታል፡፡ እያንዳንዱም ሰው የኳንትም ባህሪ ካላቸው አተሞች ተገንብቷልና ይሄው በአንዴ በሁለት ቦታ የመከሰት ዕድሉ አይነፈገውም፡፡ ነገር ግን እነዚህን በሁለት ቦታ የመከሰት ዕድል ያላቸውን ፓርቲክሎች ተቀብሎ ልክ እንደ ኦርጂናሉ አይነት ሰው ለመፍጠር ልዩ የሆነ ተቀባይ መሳሪያ ያስፈልጋል፡፡ ይህ መሳሪያ ‹‹ግሪድ›› እየተባለ የሚጠራ ሲሆን በሞገድ መልክ የተከሰቱትን ፓርቲክሎች ሰብስቦ ወደ ፍፁም ሰውነት ይቀይራቸዋል፡፡ ልክ በአየር ላይ የተለቀቀን ድምፅና ምስል ሰብስቦ እንደሚያሳየን ቴሌቪዥን ይሆንና ግሪዱን ግን ለየት የሚያደርገው የሰውየውን አምሳል በስክሪን መልክ ብቻ ሳይሆን ገሃዳዊ ሰው አድርጎ ነው የሚተፋው፡፡ ይህ ሰውም ከኦርጂናሉ ሰው የሚለየው አንዳችም ነገር አይኖርም፡፡ ፍፁም ተመሳሳይ፡፡ ለመሆኑ እርስዎ የቱን ይመርጣሉ?…

1 Comment

  1. አንተም ይህን ስትጽፍ የሰይጣን ስራ መሆኑን ጠንቅቀህ ታውቀዋለህ.ስለዝህ ወደ እግ/ር ብትመለስ ነው የምያዋጣህ.

Comments are closed.

Share