ተረግመሻል ይሆን????!!

..<< ተረግመሻል ይሆን????!! >>..

ከድር አብዱ

ሰማይሽ ቢቋጥር፣ ደመናሽ ቢያጠላ፤
ወንዞችሽ ቢንቧቡ፣ ኩሬሽ ምን ቢሞላ፤

የ13 ወር ፀሀይ፣ገፅሽን ቢያሞቀው፤
የተፈጥሮሽ ፀጋ፣ግርማሽን ቢያገዝፈው፤

በደጋጎች ልሳን፣በድሆች አንደበት፤
በቅጥርሽ በምድርሽ፣ሰላም ላይወርድበት፤
የነፃነት ሰንደቅ፣ ፍትህ ላይፀናበት፤

ተይዘሽስ እንደው!!

በሰራሽው ስራ፣ እጅሽ ባስቀደመው
ሞገስሽ ተረስቶ፣ክብርሽ የነጠፈው

የተጣባሽ መጥኔ፣ ክፉሽ የመብዛቱ፤
የጠፍሩ ሲሄድ፣ የልጓም መምጣቱ፤

(ጠፈር በሊታ ሲሄድ ልጓም በሊታ መጣ ) ነው ተረቱ

መች ይሆን ትንሳኤሽ…..እማማ ኢትዮጵያዬ

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአቶ መለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation)! ክፍል ሁለት - ከግርማ ሞገስ

3 Comments

  1. ለከድር አብዱ ባለህበት:: አንተ እና መሰሎችህ ወጥሮ የያዛችሁ ጭፍን ጥላቻ የሀገሬን ክብርና ምርጥነት አየቀንሰውም:: ሀገሬ ኢትዮጵያ የተረገመች ሳይሆን ያንን ሁሉ የዘሮችን ዘመን አልፋ ዛሬ በብረሃን ዘመን ላይ ትገኛለች:: በረሃኑ ለተጭፈነ እና ከስልታን ሌላ ነገር ማየት ለማይፈልግ ሰው አየታይም:: የጨለመባችሁ የተረገማችሁ እናንተ ዉሸታሞቹ ስልጥን ፈላጊዎቹ ናችሁ::

  2. ሶሎሞን መ ሬት ላይ የወደቀው ደሃ ተማሪ ነው ተምሬ ያልፍልኛል ብሎ ነው፣ግጥሙም ቢሆን በሀገራችን ያለውን ሁኔታ የሚገልጽ ብሶትና ምሬት አዘል ነው፣ለአንተ እና ለመስሎችህ እንዲህ አይነት እውነት መስማት አይጥምህም፣ የአንተው አይነት ሞክሼ ሰለሞን ተካልኝ ለእዛ ብኩን የዘፈነለትን ቅንድቡን ጋብዔሃለሁ፣አትጠራጠር የኢትዮጵያ ትንሳኤ በቅርብ ነው

Comments are closed.

Share