ልማታዊ ፓትርያርክ (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ)

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
nigatuasteraye@gmail.com
ግንቦት ፳፻፮ ዓ.ም.

መግቢያ

ይህችን ክታብ በዚህ ርእስ እንዳዘጋጅ ያነሳሳችኝ “ልማታዊ መንግስት-እንደ ቻይና፤ ነገሩስ ባልከፋ” በሚል ርእስ ዶ/ር ደስታው አንዳርጌ ግንቦት ፲ ቀን ፪ሺ፮ ዓ.ም ያቀረቡልን ክታብ ናት።  ከ’ሀ’ እስከ ‘ሠ’ ተዘርዝራ የቀረበችውን ይህችን ክታብ ሳነብ፤ እንደኔ ያለውን እንቅልፋም ተማሪ ቀስቃሽ ምሁር፤ በክታባቸው አማካይነት ጣቴን ይዘው ወደ ጠቀሷቸው አገሮች ወደ እስያ፤ ቻይና፤ ታይዋንና ጃፓን በመንፈስ ወሰዱኝ።

ተመልከት! ልማታዊ መንግስት ይሉሀል:: ሰላም በምድራቸው፤ በጎ ፈቃድ በዜጎቻቸው አዕምሮ እና ስነ ልቡና ላይ ልማትን የመሰረቱ እነዚህ የቻይና የጃፓንና የታይዋን መንግስታት ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት የዘረጋው የልማት ግን፤ በጅብና በአህያ፤ በተኩላና በበግ፤ በጃርትና በዱባ መካከል የተዘረጋ የልማት ተቃራኒ ጥፋት ነው።” እያሉ በማነጻጸር ያስጎበኙኝ መሰለኝ።

ቀጥለውም፤ “የኢትዮጵያን ግማሽ ህዝብ ያቀፈችውን ኢትዮጵያዊቷን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን እመራለሁ ብለው ፓትርያርክ ነኝ የሚሉት “ካዲስ አበባ ወጥቼ በየገጠሩ ስዘዋወር ዓለም ያደነቀው ልማት ሲጣደፍ አየሁ” እያሉ ሲናገሩ ሰምተሀል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በዘረጉት ያብነት ጉባዔ ተሳትፌያለሁ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ትክክለኛ ቄስ ነኝ የምትል ከሆነ፤ ያስጎበኘሁህን አይተህ፤ የነገርኩህን ሰምተህና ተረድተህ፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መምህራን ካስተማሩህ የልማት ዘይቤ ጋራ አነጻጽረህ፡ በክህነታዊ ሀለፊነትህ የምትለው ለማለት አትፍራ” ያሉኝም መሰለኝ።

በዚህ ስሜት ላይ ሆኘ ክታቧን ለመጨረስ ቀጥየ ሳነብ፤ በተራ ዝርዝር ሐ ላይ “የአገር ፍቅርና የሃላፊነት ስሜት” በምትለው አንቀጽ ስር፤ እኛ ኢትዮጵያውያን የተሰለፍንበት መስክ የሚጠይቀንን ሀላፊነት መውሰድ የማንችል ደካሞች መሆናችንን ለማሳየት፡ እኒሁ የተከበሩ መምህራችን ብዙ ምሳሌዎችን ከጠቀሱ በኋል፤ “ለበጎውም ለክፉውም ተጠያቂው ሁልጊዜ ሌላ ነው። . . . . . . . ራስን መጠየቅ፤ እውነትን መጋፈጥ መንፈሳዊ ወኔ ይጠይቃላ።” ካሏት እንደ ጦር ፍላጽ ከምትናደፈው ቃለ አጋኖ ላይ ደረስኩ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰልፍ ወጥተን ይሄን ሰውዬ ሀይ ማለት አለብን - በቀለ ገብርኤል

 [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

3 Comments

  1. kesis Asteray, Thank u for your understanding. I really agreed on your detail analysis of why people think themselves, It will be a solution for a current problem of our country political conflict. be thought our selves don’t eco for others.
    thank you a gain Mr. Asteray.

  2. You modern debtera, when the Wlqayit Tsegade farmers are evicted and the land is grabbed by Tigrians it is a crime ,and you bark like a doog, but when farmers are evicted from districts around Finfinne it is city development and opposing that is a crime and narrow nationalism according to your cognition. You people do your mind work properly?????

  3. I completely agree with the Father. He called the spade spade. What do we expect from the wayne Church leader. If my memory serve me right he used to be the mouth piece of the Derge leader Mengistu. They said he was very effictive in his speech and community activities. So by the same token Ato Tsehaye the ring leader who is manipulating the Orthodox Church is using the so called leader to spin this endless development. The sad thing is the people are dieing of hunger, diseases and untold suferring from harsh weather to being eaten by wild animals. The is occupied by lucifer and his helpers. God children must pray to God the Father to rescue Ethiopia from the jaws of these criminals and unblievers.

Comments are closed.

Share