Gezahegn Abebe Norway Lena
ግንቦት ሃያ የጥቂት የአረመኔዎችና ሆዳሞች የደስታ ቀን ሲሆን የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ደግም የሃዘን እና የጭቆና ቀን ነው!
ወያኔ ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን በሀይል መግዛት ሕዝብን በአፈናና በእንግልት ማሰቃየት ከጀመረ ሀያ ሶስተኛ አመት የሆነው ሲሆን ይህንንም ወያኔዎች የድል ቀን ብለው የሚጠሩት ለመላው ኢትዮጵያ ደግም የሃዘንና የጭቆና ቀን የሆነው ግንቦት ሃያን ቀን ለሃያ ሶስተኛ ጊዜ ለማክበር ሽር ጉድ እያሉ ሲሆን ግንቦት ሃያ በመጣ ጊዜ ወያኔዎቸ በየአመቱ የሚያደርጉት የተለያዩ አይን ያወጣ የሀሰት ፕሮፓጋንዳዎችን ዘንድሮም ተያይዘውት በኢትዮጵያ ሕዝብ አይምሮ ላይ እየቀለዱ በወያኔ የግፍ ጅራፍ እየተገረፈ ያለውን ሕዝብ ይበልጥኑ እያቆሰሉት ይገኛሉ : :በዚህ የወያኔ ግንቦት ሃያ ኢህአዲግ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አሰገኛውላቸው የሚላቸውን ጥቅሞችንና ያላፉት ሃያ ሁለት አመታቶች ወደ ኋላ ዞር ብለን በምናይበት ጊዜ ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ምንም ያስገኙለት ጥቅም የለም ብል ድፍረት አይሆንብኝም ::ይልቁንም የኢትዮጵያን ሕዝ ለአስቸጋሪና ከባድ ችግር እንዲዳረግ አደረገው እንጂ:: በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ አለም ዓቀፍ ጥናቶች እና ሐሀዞች ሳይቀር እንደሚያሳዩት ወያኔ በስልጣን በቆየባቸው በእነዚህ ዓመታቶች በአገሪቷ ላይ አስከፊ ድህነት እንደሰፈነ ፣ የስራ አጥ ቁጥር እንዳሻቀበ ፣ ሰበዓዊ እና ፣ ዲሞክራሳዊ መብቶች ክብር አልባ ሆነው ፣ የገአሪቷ ዜጕች የኖሮ ደረጃ ከቀነ ወደ ቀን እንዳሽቆለቆለ ነው:: ስለሆነም ግንቦት ሃያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይዞለት የመጣው ነገር ቢኖር እስራት፣ ግድያ፣ መከራና ሃዘን ፣ ድህነት፣ችግር፣ ፣ስቃይና ስደትን ብቻ ነው::በጣም የሚገርማችው ወያኔዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ ድልን አስገኘለት ብለው በሚያምኑበትን ቀን ዳንኪራ በመምታት ሊያከብሩት ሽር ጉድ በሚሉበት በዚህ የግንቦት ሃያ ዋዜማ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያኖች የወያኔ ስርዓት በፈጠረው የኑሮም ሆነ የፖለቲካ ጫና በመሸሽ አገራቸውን ትተው ለስደት እና ለመከራ ሲዳረጉ አብዛኞቹም ያሰቡበት ሳይደርሱ ሕይወታቸው እንደዋዛ አልፉል ::
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የኢትዮጵያ ሕዝብ ከቀን ወደ ቀን በብዛት አገሪቷን በመተው ባገኘው አጋጣሚ ወደተለያዩ አገሮች በመሰደድ ላይ ሲሆን በአለም ላይ ዜጓቻቸው ከሚሰደዱባቸው አገራት ተርታ ኢትዮጵያ በቀዳሚዎች ውስጥ እንደምትመደብ ነው:: ስርአቱም በፈጠረው የኑሮ ፣ቀውስ ምክንያት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎቻችን ሀገሪቷን በመልቀቅ ወደ ተለያዩ ሀገራት ለስደት ሲዳረጉ አንዳንዶቹም ለተለያየ ስቃይና ህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል:: በተለይም ወደ ተለያዩ አረብ ሀገራት የተሰደዱ ወገኖቻችን ለከፋ ችግር እየተዳረጉ እንዳለ ይታወቃል::
ወያኔ ኢሕአዴግ ሕዝብን ለማታለል በስልጣን በቆየባቸው አመታቶች በሀገሪቷ ላይ አመርቂ ውጤት እንዳስመዘገበና እያስመዘገበ እንደል ይለፍልፍ እንጂ አሁንም እየታየ ያለው ሀቁ ግን እንደሚያሳየው በአገሪቷ ላይ የአንድ ብሔር የበላይነት ብቻ የሚነጸባረቀበት መሪዎች የፖለቲካ ስልጣንን ለግል ጥቅም ማካበቻ የሚጠቀሙበት ዘረኛ እና ጨቆኝ ስርዓት የነገሰባት ሀገር አንዷ ኢትዮጵያ እንደሆነች ነው:: ይህንንም ብልሹ እና አስከፊ ስርዓት የሚቃወሙ እና የሚተቹ ሰዎች በማን አለብኝነት በየእስር ቤቱ እየተወረወሩ ሲሆን ከሰማንያ ሺህ በላይ የሚሆኑ ንጹህ ኢትዮጵያን ዜጎቻችን በፖለቲካ አቋሟቸው ብቻ ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው በወያኔ እስር ቤት ውስጥ የተለያዩ ስቃዮችና በደሎች እየደረሰባቸው በመማቀቅ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል :: በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ አንዳንዱችም በእስር ላይ እንዳሉ እዛው እስር ቤት ውስጥ እንዳሉ ህይወታቸው እያለፈ ሲሆን ከእነዚህ እስረኞች መካከል ስድሳ ከመቶው የሚሆኑት አእምሮቸውን ስተው እንደሚገኙ በቅርቡ ከውጭ የተገኘ ምንጮጭ ያስረዳሉ:: ይህ እንዲህ ባለበት ሁኔታ ነው እንግዲህ የኢትዮጵያኖች መብት የተከበረበት ቀን የሚባልለት ግንቦት ሃያ በየአመቱ በኢትዮጵያ የሚከበረው::
ወያኔዎች እንደሚሉት ግንቦት ሃያ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች አንድነታቸውን ያጠናከሩበት ቀን እንደሆነ ነው እኔ አኮ የማይገባኝ ነገር ኢህአዲግ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የቱ ላይ ነው ብሔር ብሔረሰቦች አንድነታቸው የጠነከረው በየቦታው የምናየውና የምንሰማው እርስ በእርስ መጣላት፣ እንደ ጠላት መተያየትና ፣መገዳደል ካልሆነ በቀር:: ወያኔ እንደሚያወራው ሳይሆን እውነታውና ሀቁ ግን ይኼ ግንቦት ሃያ ኢትዮጵያ አንድነቷ የፈረሰበትና ሕዝቡም አንድነቱን በማጣት በዘር፣ በጓሳ፣ በሃይማኖት የተከፋፈለበት ዘረኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባበት የጨለማ ቀን ነው::ታሪክ እንደሚያሳየን ከወያኔ መንግስት በፊት ኢትዮጵያን ሲመሩ የነበሩ መንግስታቶች ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ስለዜጎችም እኩልነት የቆሙና ይሰብኩ የነበሩ መንግስታቶች እንደነበሩ ታሪክ ምስክር ነው:: ነገር ግን አሁን ላይ እንደምናየው በኢትዮጵያ በመቼውም ጊዜ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሕዝቡ አንድነቱን ያጣበት በዘር የተከፋፈለበት ጊዜ ነው:: የወያኔ መንግስት በሀይል ወደ ስልጣን ከመጣባቸው ጊዜያቶች ጀምሮ ማለትም በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች ግንቦት ሃያ ካፈራቸው ፍሬዎች አንዱ ዘረኝነት ሲሆን ይህ የግንቦት ሃያ የዘረኝነት መዘዝ በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች በስፋት በኢትዮጵያ ተንሰራፍቶ ብዙዎች ኢትዮጵያኖች ዘረኝነት ባመጣው መዘዝ ሕይወታቸው እንዲያልፍ ምክንያት ሆኖል::
በመጀሪያም ማወቅ ያለብን ነገር ወያኔዎች ከዛሬ ሃያ ሁለት አመት በፊት በግንቦት ሃያ ወደ ስልጣን ሲመጡ ቀደምት እንደነበሩ መሪዎች የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነትንና ኢትዮጵያዊነትን እየሰበኩን ሳይሆን አንዱን ብሔር እያዋረዱና እየረገጡ ሌላውን ብሔር ከፍ እያደረጉና ተጠቃሚ እያደረጉ ሲሆን ይህንንም እስከዛሬ በኢትዮጵያ በየቦታው በስፋት ተንሰራፍቶ እየተተገበረ የምናየው የግንቦት ሃያ ፍሬ እውነታ ነው::
ሌላው በግንቦት ሃያ ወያኔ ሕዝብን አቀዳጀውት የሚለው ቴሌፎን፣ መንገድ፣ንጹህ መጠጥ ውሃ፣የጤና፣የትምህረትና ሌሎችም መሰረተ ልማት ከተሞችን አልፎ ገጠር ቀበሌ ድረስ በሰፊው መስፋፋት ሲሆን እዚህ ላይ ከእውነት የራቀ የወያኔን አይን ያወጣ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እንመለከታለን::በእነዚህ ሃያ ሶስት አመታቶች ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ ብዙ ለውጦች እንዳመጣ እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወደ ተሻለ የእድገት ደረጀ እያመራ እንዳለ የሕዝቡም የኖሩ አቀጣጫ እንደተለወጠ አፋቸውን ሞልተው ሲናገሩ እየሰማን ነው ወያኔ ኢሕአዴግ የፖለቲካ ስልጣኑን ለማስረዘመ ይህንን ይበል እንጂ ሀቁና እውነታው ግን ይህ አይደለም::የተለያዩ ጥናቶችና ሪፖርቶ እንደሚያሳዩት አገሪቷ ከታች ካሉ የደሃ አገሮች ግንባር ቀደም እንደሆነች እና አገሪቷ ወደ መጥፎ አቅጣጫ እያመራች እንዳለ ነው:: የኢትዮጵያ ህዝብ የኑሮን ፈተና መወጣት ባልቻለበት በአሁኑ ወቅት የግንቦት ሃያ ድልን ሳይሆን እያሰበ ያለው የግንቦት ሃያ ቀን በመርገም ከዚህ ከአስከፊው የወያኔ ስርአት እንዲት እንደሚላቀቅ በማሰብ ከመከራና ከባርነት ነጻ የሚወጣበትን ቀናቶች በመናፈቅ እንደሆነ ግልጽ ነው :: ይህንንም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ ጊዚያቷች ከሚያሰማው ሮሮ ማወቅ ይቻላል ::
በርግጥ በአሁን ሰአት ወያኔዎችና ጥቂት ሆዳሞ የወያኔ ካድሬዎች የስርአቱ ተጠቃሚ ከመሆናቸው የተነሳ ግንቦት ሃያ ይዞላቸው የመጣውን ጥቅም በማየት በደስታ የግንቦት ሃያ ቀንን ለማክበር ሽር ጉድ እያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ሕዝብንም የግንቦት ሃያ ተጠቃሚ ለማስመሰል ወያኔ ግንቦት ሃያ በመጣ ቁጥር በሕዝቡ ላይ የተለያዩ ድራማዎችን እየሰራ እንዳለ ይታወቃል:: ከእነዚህም መካከል የገጠሩን ነዋሪ በሀይል እያስፈራሩ በግድ ስለ ስርአቱ ጥሩ ነገር እንደስገኘለትና ያንን በማሰብ ግንቦት ሃያን ደስ እያለው እንደሚያከብር በግዳጅ እንዲናገር ማድረግ እንዲሁም በገጠርም በከተማም የሚኖረውን ሕዝብ ከየቀበሌው፣ ከየህድሩ፣ ከየመስሪ ቤቱ፣ ተማሪው፣ ገበሬው፣ ነጋዴው በተለያዮ ጥቃጥቅሞች በማታለልና እንዲሆም በማስፈራራት በግዳጅ ሰለፍ እንዲወጣ በማድረግ በየአመቱ ይህን ተግባር እንደሚፈጽም የሚታወቅ ሲሆን ከአንዳንድ ሰዎች እንዳገኘውት መረጃ ዘንድሮም በየመስሪያ ቤቱ የግንቦት ሃያ ቀን ሰልፍ ላይ እንዲገኙና ሕዝቡ ከኢህአዲግ ጋር እንዳለ ለማስመሰል ግዳጃዊ ትህዛዝ እንደተላለፈላቸው ለማወቅ ችያለው የዛሬ ሁለት አመት አስታውሳለው አንድ በጣም የማውቀው ሰው በአንድ ትልቅ የመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ የሚሰራና ነገር ግን በሚሰራበት መስሪያ ቤት ከሚያየው የዘር መጠቃቀምና ወያኔ ሕዝቡ ላይ እያደረሰ ካለው በደሎች የተነሳ ስርአቱን ክፎኛ የሚጠላና የሚቃወም ሰው ስለሆነ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ሁሉ በግንቦት ሃያ ቀን ሰልፍ ላይ እንዲገኙ ሲነገራቸው በሰልፉ ላይ እንደማይገኝ በመናገሩና ባለመገኘቱ በተለያየ ነገሮች በማሳበብ ከስራ መባረሩን አውቃለው:: አሁን ላይም ሁላችንም ኢትዮጵያኖች ስርአቱ ይዞብን የመጣውን ዘረኝነት፣ ድህነት፣ ስደትና ጭቆና ባለመቀበል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምኑም ላልሆነው ግንቦት ሃያ ማድመቂያ የወያኔ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እንዳንሆን እንጠንቀቅ ለማለት እወዳለው::
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
[email protected]
ግንቦት ሃያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምኑ ነው………..? (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌ ሌና)
Latest from Blog
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም
ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ
የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ
ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ አንድ አባውራ ምንነቱ ያልታወቀ እህል ከገበያ ገዝቶ ለሚስቱ አምጥቶ ሰጣት አሉ፡፡ ከሰጣትም በኋላ ሚስቱ ያንን እህል ፈጭታ ቂጣ ላርግህ ብትለው፣ እንጀራ ላርግህ ብትለው፣ ገንፎ ላርግህ ብትለው … ምን አለፋህ
ወሰንየለሽ ኦሮሙማዊ ዕብደት!!
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን
የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ
ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?
የቀጠለው ውጊያና የፋኖ ድሎች / የግብፅ ፣ሶማሊያ ፣ኤርትራና ሱዳን ውሳኔ / “የህወሓት መከፋፈል ገደለን “|EN
የቀጠለው ውጊያና የፋኖ ድሎች / የግብፅ ፣ሶማሊያ ፣ኤርትራና ሱዳን ውሳኔ / “የህወሓት መከፋፈል ገደለን “|EN
ከሃይለገብርኤል አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ
የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’
ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም January 10, 2025 በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና
በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ሀገሪቱ እኮ የለችም…. የጄነራሎቹ ጉድ…. የአብይ አህመድ ነገር…
ዓለም ሁሉ ያስደነቀው ሚልዮኖች የተመለከቱት አስደናቂው ቪድዮ| Ethiopian Orthodox Mezmur