የሠሞኑ የአክራሪ ኦሮሞዎች እንቅስቃሴ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የነደፈውን የአዲስ አበባ ከተማን የማስፋፋት ዕቅድ ለመቃወም ሣይሆን ዐማራን ከምድረ-ገፅ ማጥፋት መሆኑን ያረጋግጣል።
ሠሞኑን በዓለማያ፣ በአምቦ፣ በነቀምት እና በሮቤ (መዳወላቡ) ዩኒቨርስቲዎች በሚማሩ የዐማራ ተማሪዎች ላይ በአክራሪ የኦሮሞ ተማሪዎች እና በኦሕዴድ ካድሬዎች ትብብር ዘርን መነሻ እና መድረሻ አድርጎ የሚፈጸመው ጥቃት፣ ማቆሚያ የሌለው እና የዐማራን ነገድ ከምድረ-ገፅ ለማጥፋት በትግሬ-ወያኔዎች እና በተባባሪዎቻቸው አማካይነት የተከፈተው የዕልቂት ዘመቻ አካል መሆኑን ያረጋገጠ ሃቅ ነው። ይህንን ኢሰብአዊነት የተሞላው ናዚያዊ ድርጊት የዐማራው ነገድ ልጆች ብቻ ሳይሆኑ፣ ማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር ሊያወግዘው እና አጥፊዎቹን ለፍርድ ለማቅረብ ተባብሮ ሊንቀሳቀስ ይገባዋል። ባለፉት ሁለት ሣምንታት ብቻ በጊምቢ ከተማ እና በአካባቢው (ወለጋ) ነዋሪ በሆኑ አያሌ ዐማሮች ላይ የከፋ ጭፍጨፋ ተፈጽሟል። ከእነዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ ድርጊቶች መካከል ለአብነት ለመጥቀስ ያህል፦ በግንቦት ፪ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ላይ ትውልዳቸው ከጎንደር የሆኑ የቤተሰብ ኃላፊ በገጀራና በአካፋ ተጨፍጭፈው ተገድለዋል፤ ወይዘሮ አበባ ጌቱ የተባሉ፣ ኑሯቸውን በጠላ ሽያጭ የሚመሩ ሴት፣ ዐማራ በመሆናቸው ብቻ ጭንቅላታቸው በአካፋ ተፈልጧል፤ አቶ አጥናፍ ምሕረቱ የተባሉትን ግለሰብ አሰቃይተው ከመደብደባቸውም በላይ፣ ፲፬ (አሥራ አራት) ቋሚ እና ፴፪ (ሠላሣ ሁለት) ጊዜያዊ ሠራተኞችን ያስተዳድሩበት የነበረው ድርጅታቸው ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውም ሙሉ በሙሉ እንዲወድም ተደርጓል። የአቶ ዘሪሁን ካሤ ንብረት በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲወድም ተደርጓል። አቶ ፍሬው አያሌው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል። ፲፫(አሥራ ሦሥት) ሰዎች በድብደባ ከፍተኛ የሆነ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከ፪ሺህ፻(ሁለት ሺህ አንድ መቶ) በላይ ዐማሮች ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው እንዲፈናቀሉ ሆኗል። በአጠቃላይ በጊምቢ ከተማ እና በአካባቢው ይኖሩ ከነበሩት ዐማሮች የንብረት ይዞታ ውስጥ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፤ ፴፪(ሰላሣ ሁለት) ቤቶች በእሳት ተቃጥለዋል፤ ፻፷፪(አንድ መቶ ስድሣ ሁለት) የዐማራ ቤቶች መስኮቶቻችው እና በሮቻቸው ወላልቆ ወድመዋል። ከዚህ በተጨማሪም በግንቦት ፮ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. በነቀምት ዩኒቨርስቲ ይማሩ የነበሩ ፯ ተማሪዎች በትግሬ-ወያኔ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ተገድለዋል። ለመሆኑ አክራሪ የኦሮሞ ነገድ ተወላጆች በዐማሮች ላይ ይህንን ሁሉ ናዚያዊ ጭፍጨፋ የሚፈጽሙት በእርግጥ በትግሬ-ወያኔ የተነደፈውን የአዲስ አበባ ከተማን የማስፋፋት ዕቅድን ለመቃወም ነው?
የአዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮጵያ ከተሞች መካከል በቆዳ ስፋት፣ በሕዝብ ብዛት እና ስብጥር እንዲሁም በዘመናዊነቷ የምትታወቅ የአገሪቱ እና የአፍሪቃ አኅጉር መዲና ናት። እቴጌ ጣይቱ እና ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ከተማዋን ከቆረቆሯት ፻፳፯ (አንድ መቶ ሃያ ሰባት) ዓመታት አስቆጥራለች። ሆኖም ከተማዋ እንደ ዕድሜዋ ብዛት የመሠረተ ልማት አውታሮቿ እና የአገልግሎት ተቋሞቿ ዘመናዊነትን የተላበሱ አይደሉም። ይህንን የከተማዋን ያልተመጣጠነ የዕድገት አቅጣጫ ለማሻሻል ከተቆረቆረችበት ዘመን ጀምሮ በተከታታይ ኢትዮጵያን በመሯት እና በገዟት ገዢዎች ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ምንም እንኳን የትግሬ-ወያኔ ለአዲስ አበባ ከተማም ሆነ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ጥፋትን እንጂ ልማትን ለማምጣት ዓላማው ባይሆንም፣ ለከተማዋ መስፋፋት ዕቅድ መነደፉ በራሱ የተቃውሞ መንስኤ ሊሆን የሚገባው አይደለም። ሆኖም ይህንን ዕቅድ መቃወምም መብት ነው። ከዚህ አጠቃላይ መንደርደሪያ በመነሣት በየዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የኦሮሞ ተማሪዎች በትግሬ-ወያኔ ዕቅድ ላይ ያስነሱት እና የመሩት ይህ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በመርህ ደረጃ ስህተት የለውም። ነገር ግን የእኒህ ተማሪዎች የጥቃት ዒላማ ያነጣጠረው፣ ዕቅዱን በአቀዱት እና ለማስፈጸም በተዘጋጁት፣ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት አውራ ጠላቶች በሆኑት በትግሬ-ወያኔ እና ወያኔ-ወለድ በሆኑት የጠባብ ብሔርተኛ ድርጅቶች አባላት ላይ አይደለም። «አህያውን ፈርቶ ዳውላውን» እንደሚባለው፣ እኒህ አክራሪ የኦሮሞ ብሔረተኞች ጅምላ የጭፍጨፋ ዘመቻቸውን ያወጁት «ኢትዮጵያዊ ነኝ» ብሎ፣ ኢትዮጵያን እምነቱ አድርጎ በሚኖረው፣ ራሱን በቋንቋ ማንነት ላይ አደራጅቶ እና ሌሎችን በጠላትነት ፈርጆ በማያውቀው በዐማራ ነገድ ተወላጆች ላይ ነው። ለመሆኑ እኒህ አክራሪ የኦሮሞ ተማሪዎቹ አብረዋቸው በአንድ ክፍል የትምህርት ገበታ ዕውቀት የሚቀስሙትን፤ በአንድ ማዕድ ቁርስ፣ ምሣ እና እራት አብረዋቸው የሚመገቡትን፤ «ኢትዮጵያ አገሬ ናት፣ ኢትዮጵያዊው ሁሉ ወገኔ ነው» ብለው በንጹሕ ኅሊና የሚያምኑትን፣ ቀና ልቦና ያላቸውን፣ ወደው ወይም መርጠው ሳይሆን በተፈጥሮ ሕግ ከዐማራ ነገድ የተወለዱትን ዐማራ ተማሪዎች እየመረጡ የአረመኔያዊ ጥቃታቸው ሠለባዎች ሲያደርጓቸው ምን ይሰማቸዋል? የሚደንቀው እንቆቅልሽ ደግሞ ከዛሬ ፻፶(አንድ መቶ ሃምሣ) ዓመታት በፊት «የእናቶቻችን እና የእህቶቻችን ጡት ተቆርጧል» ብለው የሚቆጩ እና ለዚያም ማስታዎሻ ሐውልት የገነቡ ሰዎች ልጆች መሆናቸው ነው። እነርሱ ድሮ ያልተፈጸመውን በውሸት ልብ ወለድ ተክተው፣ እንደ ዕውነተኛ ሃቅ አድርገው በመቀበል፣ «ያኔ ተፈፅሟል» ያሉትን ክፉ ተግባር ዛሬ እነርሱው የዐማራ ሴቶችን ጡት ሲቆርጡ ማዬት የሚያረጋግጠው በተቃራኒው እኒህ አክራሪ የኦሮሞ ተማሪዎች በ፳፩ኛው ክፍለ-ዘመን አስተሣሰብ የሚመሩ ያለመሆናቸውን ነው። ይህ ድርጊታቸው አልፎ ተርፎም «ያኔ በዳግማዊ ምኒልክ የአገር መገንባት እንቅስቃሴ ወቅት የኦሮሞ እናቶች ጡት ተቆርጦ ይሆናል» ብለው ለሚሞግቱ ነሆለሎች ከበቂ በላይ ማፍረሻ ምክንያት ይሆናል። ስለሆነም ይህንን ናዚያዊ ድርጊት ለመቃወም ዐማራ መሆን አያሻም። እንደሰው የሚያስብና ሰብአዊነት የሚሰማው ማንኛውም ሰው፣ ድርጊቱን በግልፅ በአደባባይ ከመቃወም አልፎ፣ ከተጠቂዎቹ ጎን በመቆም የጥፋቱን መንገድ ሊዘጋ ይገባዋል። ከሁሉም በላይ የጥቃቱ ሠለባ የሆንነው የዐማራው ነገድ አባሎች ሊቆጨን እና ጥፋቱን ፈጽሞ ለማስቆም በአንድነት ኃይላችንን አስተባብረን መቆም እንዳለብን ማወላወል አያሻም።
በትግሬ-ወያኔ እና በተባባሪዎቹ የተከፈተውን ዐማራን ነጥሎ የማጥፋት ዘመቻ ማስቆም የሚቻለው እንደጅል በሚያስቆጥር «አድሮ እንዬው» በሚሉት ትዕግሥት አይደለም። ወይም ደግሞ ስሟ ብቻ ስለቀረ እና ስለሌለች ኢትዮጵያ በመስበክ አይደለም። ጥቃቱ እና ጥፋቱ የሚቆመው እያንዳንዱ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የዐማራው ነገድ አባል፣ «ከዚህ ወዲያ ምን ይመጣል?» ብሎ ራሱን በመጠየቅ ሲነሣ ብቻ ነው። የጥፋቱ መግቻ ብቸኛ መንገድ ዐማራው «ከዚህም ቤት እሳት አለ» ብሎ በአንድነት ሲነሳ ብቻ ነው። እሾህ በሾህ እንደሚወጣ ሁሉ፣ ይህንን አጥፊ ዘረኛ ቡድን ከጥፋት ጉዞው ማስቆም የሚቻለው በሚገባው ቋንቋ በማነጋገር ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል፤ ከሁሉም በላይ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የዐማራ ነገድ ተወላጅ ሁሉ በአስመሳይ ቡድኖች ከንቱ ስብከት ሳይወናበድ ራሱን በማንነቱ ዙሪያ አደራጅቶ በጠላቶቹ ላይ ክንዱን የሚያነሳበት ወቅት ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው። ውርደት እና ስደት፣ በእኛ ትውልድ ላይ ሊቆም ይገባል። አልቃሽነታችንን ከአንድ ቦታ ላይ ልናቆመው ይገባል። በማንነታችን ልንኮራ እና ልንመካ ይገባል። ዐማራነት ማለት፥ ነፃነት፣ ዕኩልነት፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ጀግንነት እንጂ፥ ተዋራጅነት፣ ፈሪነት፣ ስደተኛነት፣ ተሸናፊነት ማለት ያለመሆኑን በተጨባጭ ማስመስከር ይገባናል። እንደ ጀግኖች አባቶቻችን እና እናቶቻችን ገድለን ለመሞት እንጂ፣ በፍርሃት ሽሽተን የማይቀረውን ሞት ለመሞት መጠበቅ ወይም በቁማችን በየዕለቱ መሞት የለብንም። የወገኖቻችንን የ«ድረሱልን» ጥሪ ልንሰማ ይገባናል። የአባቶቻችንን እና እናቶቻችንን አደራ ልንወጣ እና ልንጠብቅ ይገባል። ዛሬ ተዋርደናል፤ ስማችን ጎድፏል፤ ጠላቶቻችን ይህም አልበቃ ብሏቸው የእህቶቻችን ጡት እየቆረጡ፤ የነፍሰጡር እናቶቻችን ሆድ ተቀዶ ሽል እየተሰለበ፤ «ኢትዮጵያ አገራችሁ አይደለችም» ተብለን እንደባይተዋር እየተባረርን፤ «ዕብድ ውሻ እና ዐማራ ልብ የለውም» እየተባልን፤ መጤዎቹ እና ወራሪዎቹ ነባሮቹን እና ተወራሪዎቹን «ወራሪዎች ናችሁ» እያሉን እስከመቼ እንዘልቃለን? ለመሆኑ በትግሬ-ወያኔ የአገዛዝ ዘመን ለዐማራ ያልተሰጠ ምን መጥፎ ስም እና ተግባር አለ? ከዚህ ወዲያ ምን እንጠብቃለን? ምንስ እንዲደረግ እንሻለን? ከዚህስ የባሰ ምን ይመጣል ብለን እናስባለን? ስለሆነም ሰብአዊነት እና ኢትዮያዊነት ይሰማኛል የሚል፣ ከሁሉም በላይ የዐማራው ነገድ አባል፣ ጥቃቱን እንዳመጣጡ ለመመከት እና ለመመለስ ራሱን በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ዙሪያ በማሰባሰብ ለወገኖቻችን አለኝታችን እንድናረጋግጥ ድርጅታችን የነፍስ አድን ጥሪውን ያቀርባል።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃል -ኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በሚያምኗት እና በሚወዷት ልጆቿ መስዋዕትነት ኮርታ እና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!
––[PDF ሙሉውንለማንበብእዚህይጫኑ]–