‹‹የሚገሥጹንን ሁሉ መቅጣት የለብንም›› (ከዳንኤል ክብረት)

ዳንኤል ክብረት

ብጹዕ አቡነ ዮሐንስ በሊቅነታቸው፣ በቆራጥነታቸው፣ ለየት ባለ አስተሳሰባቸውና ለነገሮች በሚሰጡት አስደናቂ ምላሽ የሚታወቁ የትግራይ ሊቀ ጳጳስ ነበሩ፡፡ እስካሁንም እርሳቸውን በተመለከተ የሚተረኩ እጅግ አስገራሚ ታሪኮች አሏቸው፡፡ አንዱ እንዲህ ይላል፡፡ አቡነ ዮሐንስ በዓላትን በተመለከተ የነበራቸው አስተሳሰብ ከብዙው ሰው ለየት ያለ ነበር፡፡ ‹‹በዓል መከበር ያለበት በሥራ ነው›› ብለው ያምኑ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት እንዲያውም በቀዳሚት ሰንበት ሥራ ሲሠሩ ያያቸው ሰው ‹‹እንዴት ጌታ ባረፈበት ቀን ይሠራሉ›› ቢላቸው ‹‹እርሱኮ ያረፈው ሥራውን ጨርሶ ነው፡፡ እኔ መች ሥራዬን ጨረስኩ ብለህ ነው›› ብለው መመለሳቸው ይነገራል፡፡

‹‹የበዓላትን ቀናት ለበዓሉ የሚስማማ ሥራ በመሥራት እንጂ እጅና እግርን አጣጥፎ በመቀመጥ፣ መጠጥ ቤትና ጭፈራ ቤት በመዋል ማክበር ከማክበር አይቆጠርም፡፡ ሰው ምንጊዜም መቦዘን የለበትም፡፡ በየዕለቱ ለዕለቱ ተስማሚ የሆነ ሥራ መሥራት አለበት›› ብለው ያም ይህንንም ያስተምሩ ነበር፡፡

 

ታድያ በአንድ ወቅት በበዓል ቀን ቤተ ክርስቲያን ሲያሠሩ ውለው ለጉዳይ ወደ ሌላ ቦታ ይሄዳሉ፡፡ ለአቤቱታ ወደ እርሳቸው ዘንድ ከገጠር የመጣ አንድ ካህን እርሳቸውን ፍለጋ ወደሚያሠሩት ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ይመጣል፡፡ ሲመጣ እርሳቸው የሉም ነገር ግን ሠራተኞቹ በሥራ ተጠምደዋል፡፡ ተገረመም፣ ተናደደም፡፡ ‹‹እንዴት በበዓሉ ቀን ትሠራላችሁ›› ሲል ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ያዘዟቸው አቡነ ዮሐንስ መሆናቸውን ነገሩት፡፡ እርሱ ግን አልተቀበለውም፡፡ ከኖረበትና ከተማረው ውጭ የሆነ ነገር ሲፈጸም እያየ ዝም ማለቱን ኅሊናው አልተቀበለውም፡፡ በርግጥ ያዘዙት ሊቀ ጳጳሱ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሊቀ ጳጳሱም ቢሆኑ ሊሳሳቱ ይችላሉ አለና አሰበ፡፡

አስቦም አልቀረ ወደ ሠራተኞቹ ሄደና ‹‹በሉ ሥራችሁን አቁሙ›› አላቸው፡፡ እነርሱ ግን ሊቀ ጳጳሱ ያዘዙትን እንደማያቆሙ ነገሩት፡፡ በዚህ ጊዜ መስቀሉን አወጣና አወገዛቸው፡፡ ያን ጊዜም ሠራተኞቹ ሥራቸውን አቆሙና ቁጭ አሉ፡፡ እርሱም ሊቀ ጳጳሱን ፍለጋ ሄደ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማለዳ ወግ ...አምላክ ሆይ ! የአዲሱ አመት ተስፋና ምኞታችን አሳካው !

አቡነ ዮሐንስ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲመጡ ሠራተኞቹ ሁሉ ቁጭ ብለዋል፡፡ ‹‹ለምን ሥራ ፈትታችሁ ተቀመጣችሁ?›› አሏቸው፡፡ ‹‹አንድ ካህን መጥቶ አወገዘን›› አሉና መለሱላቸው፡፡ ካህኑ ይጠራ ተባለና ተፈልጎ መጣ፡፡ ‹‹አንተ ነህ ወይ ያወገዝካቸው›› አሉት፡፡ ‹‹አዎ›› አለ፡፡ ‹‹ለምን?›› ሲሉ መልሰው ጠየቁት፡፡ ‹‹አባቶቻችን ያቆዩትን ሥርዓት ጥሰው ለምን በዓል ይሽራሉ ብዬ‹‹ አላቸው፡፡ ‹‹ያዘዝኳቸውኮ እኔ ነኝ›› አሉት፡፡ ‹‹ቢሆኑም ስሕተት ነው፡፡ ስሕተቱን እያየሁ ዝም ማለትም ሌላ ስሕተት ነው›› አላቸው፡፡

አቡነ ዮሐንስ ተገረሙ፡፡ ካህኑን በመኪናቸው አሳፈሩና ወደ ቤታቸው ወሰዱት፡፡ ‹‹በል ያንተን ጉዳይ በጉባኤ ነው የማየው፤ እስከዚያ እዚሁ እኔ ቤት እየበላህ እየጠጣህ ተቀመጥ›› አሉት፡፡ አቡነ ዮሐንስ ለጉዳይ የሚመጣ የገጠር ሰው ከገጠማቸው ከተቻለ ጉዳዩን ዕለቱኑ ይፈጽሙለታል፡፡ ካልተቻለ ደግሞ እዚያው ራሳቸው ቤት አስቀምጠው ጉዳዩ እስኪያልቅ ያስተናግዱታል፡፡ ክሱ የሚቀርበው በእርሳቸው ላይ ቢሆንም ሰውዬው በቤታቸው መስተናገዱ ግን አይቀርም፡፡

ቀን ተቀጠረና በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ ጉዳዩ ታየ፡፡ የመቀሌ ከተማ ሕዝብ፣ ካህናትና ሊቃውንት ተሰበሰቡ፡፡ አቡነ ዮሐንስ በሚሰጡት ለየት ያለ ፍርድ፣ በሚናገሩት ዘመን ተሻጋሪ ንግግር ይታወቃሉ፡፡ በአንድ ወቅት ወደ እርሳቸው የመጣ ሰው ‹‹ተማር›› ቢሉት ‹‹ምን እየበላሁ ልማር›› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹‹ታድያ የደነቆርከው ምን እየበላህ ነው›› ብለው ጠይቀውታል ይባላል፡፡

ያ ካህን ቀረበ፡፡ ‹‹ለምንድን ነው ሠራተኞቹን የገዘትካቸው?›› ተብሎ ተጠየቀ፡፡ ‹‹አባቶቻችን ባቆዩን ሥርዓት በበዓል እንዲህ ያለ ሥራ መሠራት የለበትም ብዬ ነው›› አላቸው፡፡ ‹‹ያዘዝኩት እኔ ነኝ፣ አንተ ይህንን ስታደርግ ሊቀ ጳጳሱ ይቀጡኛል፣ ከሥራ ያባርሩኛል፣ ክህነቴን ይይዙብኛል ብለህ አላሰብክም›› አሉት፡፡ ‹‹ቢያባርሩኝም፣ ክህነቴን ቢይዙብኝም መቀበል ነው እንጂ ምን ይደረጋል፡፡ ስሕተት እያየሁ ግን እንዴት አልፈዋለሁ፡፡›› አላቸው፡፡ ‹‹እና የሚመጣብህን ሁሉ ለመቀበል ተዘጋጅተሃል›› አሉት ‹‹ከመጣ ምን ይደረጋል›› አለ ካህኑ፡፡ ‹‹ከምቀጣህ ለምን ግዝትህን አታነሣም›› አሉት፡፡ ‹‹እርሱማ አቋም ነው፡፡ እምነቴ ነው፡፡ ቃሌ ነው፡፡ ይኼማ ከእርስዎ የባሰ ስሕተት መሥራት ነው›› አላቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምጧ የተራዘመባት- ኢትዮጵያ! – ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

ያን ጊዜ አቡነ ዮሐንስ ተነሡ፡፡ ሕዝቡም ምን ሊፈርዱበት ይሆን? እያለ በጉጉት ጠበቀ፡፡ ግማሹ እንዲያ ግማሹም እንዲህ አሰበ፡፡ አቡነ ዮሐንስም የመጣበትን አውራጃ ጠየቁት፡፡ ነገራቸው፡፡ አሁን ሕዝቡ የቅጣቱ ደብዳቤ ለአውራጃው እንደሚጻፍ አረጋገጠ፡፡ አቡነ ዮሐንስም አውራጃውን ከሰሙ በኋላ ‹‹እገሌ የተባለው የዚህ አውራጃ ሊቀ ካህናት እንዲህ ወደተባለ አውራጃ ተዛውሯል›› አሉ፡፡ ያን ጊዜ ሕዝቡ ‹‹የኃጥኡ ዳፋ ጻድቁን ያዳፋ›› ብሎ ተረተ፡፡ በዚህ ካህን ዕዳ ሊቀ ካህናቱ በመቀጣቱ አዘነ፡፡ አቡነ ዮሐንስም ቀጠሉ፡፡ ‹‹የዚህ አውራጃ ሊቀ ካህናት ግን ይህ ቄስ ይሆናል›› ሲሉ ሕዝቡ በአግራሞት አጨበጨበ፡፡ካህኑም ግራ ገባው፡፡ የጠበቀውና ያገኘውም ተለያየበት፡፡ ሕዝቡም በጥያቄ ተወጠረ፡፡ ለምን?

‹‹አያችሁ ወገኖቼ›› አሉ አቡነ ዮሐንስ፡፡ ይህ ሰው ሊቀ ጳጳሱን አወገዘ፡፡ እንደ ሥርዓታችን ልክ አልነበረም፡፡ ቢያንስ ለምን እንደዚያ እንዳደረግን እንኳን መጠየቅ ነበረበት፡፡ ነገር ግን በአቋሙ ትክክል ነው፡፡ ሰው ማለት፤ ጀግና ማለት፣ ጎበዝ ማለት አቋም ያለው ሰው ነው፡፡ የበላዩን የማይፈራ፤ ፈጣሪውን ብቻ የሚፈራ፡፡ ላመነበት እውነት የሚቆም፡፡ በአቋሙ ምክንያት የሚመጣበትን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ የሆነ፡፡ አሁን እኔ ሥልጣኑን ልይዝበት፣ ከሥራ ላግደው፣ ጨርሶም ላወግዘው እንደምችል ያውቃል፡፡ ይህንን ሁሉ እያወቀ ግን ላመነበት እውነት መጽናቱ ጀግና ያደርገዋል፡፡ ማክበር ያለብን የሚፈሩንን፣ ቅዱስ ቅዱስ የሚሉንን፣ የሠራነውንም ያልሠራነውም የሚያደንቁልንን፣ የሚያወድሱንን ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ይህማ የማንም ሰው ጠባይ ነው፡፤ አክባሪውን የማይወድ ማን አለ፡፡ እኛም ጀግና የምንሆነው የሚገሥፁንን፣ የሚቆጡንን፣ ስሕተታችንን በድፍረት የሚናገሩንን፣ ሥልጣናችንን ሳይፈሩ ያመኑበትን እውነት የሚመሰክሩልንን ጭምር መውደድና ማክበር አለብን፡፡

እናንተ እንደምቀጣው ነው የጠበቃችሁት፡፡ የሚገሥጹንን ሁሉ ግን መቅጣት የለብንም፡፡ ያመኑበትን ስሕተታችንን የሚነግሩንን፣ በአቋም የሚሞግቱንን ሁሉ መቅጣት የለብንም፡፡ እንዲያውም መሸለም አለብን፡፡ ለዚህ ካህን ክህነቱን የሰጠሁት እኔ ነኝ፡፡ ስሰጠውም ‹ደኻ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ በል› ያልኩት እኔ ነኝ፡፡ ያን የሰጠሁትን እኔ ላይ ሲፈጽመው መናደድ የለብኝም፡፡ ፍርደ ገምድል መሆንም የለብኝም፡፡ እንዲያውም እንዲህ ያለ ልጅ በማድረሴ ልኮራ ይገባል፡፡ ሞኞች የሚገሥጽዋቸውን አይወዱም፡፡ ግን ቢሆንም እየመረረን እንኳን መቀበል አለብን፡፡ አሠራሩ ስሕተት ቢሆንም አቋሙ ግን ልክ ነው፡፡ ቆራጥነቱ ግን ልክ ነው፡፡ ማንንም አለመፍራቱ፣ ላመነው እውነት ብቻ መቆሙ፣ የሚመጣበትን ለመቀበል መዘጋጀቱ ግን ልክ ነው፡፡ ስለዚህ ሸልሜዋለሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢሬቻው ማን ተጠቀመ? ማንስ ተጎዳ? - አሊጋዝ ይመር

አዳራሹ በጭብጨባ ተሞላ፡፡ ካህኑም መሬት ወድቆ እጅ ነሣ፡፡ ታሪክም ለእኛ እንዲህ ሲል አቆየን፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ላይ የወጣ ነው

8 Comments

  1. Hey buddy. We have too too much of you. Get lost. Are you a politician or a religious guy? Who do you call yourself? We are not here to read your fancies dude. Write it in your diary and sleep on it. Don’t wash your dirty clothes on our website chap! Even your picture is so disgusting to look at. Throw yourself into the sea for you are no more useful this way unless you get back into some business like writing a well researched book. Do not wa ssh team your time waiting for ads to appear on your web. Take ear to my advice. Otherwise you will be writing sheet expecting the air to drop and you lose your purpose in life. Alright. Get move yourself that way, or get out of the way.

    • Take it easy friend. You know exactly what he is talking about, that is why you got irritated. you hate him but kept on visiting his web site. What really push you to visit such sites??

  2. አይ የኛ መምህር ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በጨካኞች መዳፍ ገብታ በችግር ላይ ባለችበት በዚኸ ሰዓት እንደዚህ ዓይነት የልጆች ተረት አርቲ ቡርቲ ነገር ትፅፋለህ እጅግ ያሳዝናል የእግዚዓብሄር ቃል ለተጠማ ምእመን ካንተ እንደዚህ አይጠበቅም ይህን እንደ መርኸ ካየህው በትልቁ አሰርተኸ እመኝታ ቤትህ ግድግዳ ላይ ለጥፈው ፤ ኦሮማይ።

  3. Mehayiman !! Le Ahiya Mar Aytimatim Nachihu. Dani you are simply AMAZING Keep it coming.May God blees you with more.

  4. በጣም አከበርኩህ ወንድሜ !!! ፈጣሪ በረከቱን ይሰጥህ፡ልቦናው በክፋት እና በጥላቻ ለታወረበት የሰወዘር በሙሉ ብረሃን የሚያሳይ በጥበብ የተሞላ ታላቅ ትምህርት ነው።ምንም እንኩአን ለአንዳንዱ (cyber cadres) ጋኔሉን አሰነሰቶበ ፈጥኖ ከላይ እንደፃፈው ቢያሰለፈልፈውም.

  5. Fess yalebet ziilaay aychilim
    you are going to get hurt for ever in your own by your own for the rest of your life.
    It was your choice, to push away poor christians.
    Blame no one1

  6. Araya kkkkk you are almost crying like a little girl kkkk I think this smart guy hurt you a lot even before he call WOYANE by name

    Deacon Daniel what a wise and smart guy to convey your message in a creative manner but your advise would fall on a deaf ear as our leaders are not out there to serve the nation and the people rather they are out there to loot the people and maintain the Aparthaid regime they created to benefit only Tigray and Tigrians at the expense of Ethiopians

    Daniel I hope you say something one day about the persecution of Amharas in OROMIYA region by OLF Oromos and teach them what they doing to Amharas will one dY lead to a catastrophic civil war

  7. ዳኒ ጽሁፍህ ወቅቱን የተከተለ አይመስለንም ምክንያቱም በአሁኑ ሰአት ከአገር የተሰደደው ህዝብ ከፍተአና አህዝ ያለው ፕሎቲካንና ሀይማኖትን መለየት አቅቶት በመደናበር ባለበት ወቅት ገደል አፋፍ ላይ ያለን ወደገደል መገፍተር ነው መጀመሪያ ሀሁ ከዝያ አቦጊዳ ሁሉም በስረአቱ ሲሆን መልካም ነው በአሁን ግዛ መቅደስሱን ፕሎቲካ ካልቀደሳችው በማለት ባስቸገሩበት ወቅት የአባቶችን ድምጽ መስማት በተውበት ሰአት ጽሁፍህ ለጀማሪ አይሆን መጀመሪያ ያየናቸውን አባቶች ችግር ያለባቸው ቢሆን ልንጸልይላቸው ሲገባ አባቶቻችንን በአደባባይ በመናቅ ነው የያዝነው ስለዝህ አስብበትና ወቅቱን የሚመለከት ጽሁፍ ብታቀርብ ሰውን ልታስተምር ትችላለህ ያአባቶች አምላክ ይክበር ይመስገን::

Comments are closed.

Share