(ዘ-ሐበሻ) በሳንሆሴና ሳንፍራንሲስኮ ቤይ ኤርያ ለ31ኛ ጊዜ በሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት ፌስቲቫል ላይ የሚገኙ ድምጻውያን ከወዲሁ ታወቁ።
ላለፉት 31 ዓመታት ኢትዮጵያውያንን በሰሜን አሜሪካ ሲያገናኝ የቆየው ይኸው የስፖርት ፌስቲቫል ከጁን 29 እስከ ጁላይ 5 ድረስ የሚቆይ ሲሆን ሆቴሎችም ከወዲሁ እየሞሉ እንደሚገኙ ከስፖርት ፌዴሬሽኑ ድረገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በዘንድሮው ኳስ ጨዋታ ወቅት የተለያዩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች የሚደረጉ ሲሆን ከነዚህም መካከል ቴዲ አፍሮ፣ ጃኪ ጎሲ፣ ሸዋንዳኝ ሃይሉና ሚካኤል በላይነህ የሚያቀርቧቸው ኮንሰርቶች ከወዲሁ የሕዝብን ቀልብ ስበዋል።
ሐሙስ ጁላይ 3 ቀን 2013 ቴዲ አፍሮ፣ አርብ ጁላይ 4 ቀን 2014 ጃኪ ጎሲ፣ ቅዳሜ ጁላይ 5 ሚካኤል በላይነህ እና ሸዋንዳኝ ኃይሉ የሙዚቃ ኮንሰርታቸውን በሳንሆዜ ያቀርባሉ።