የወያኔ ጥላቻ ፍሬ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

መስፍን ወልደ ማርያም

ሚያዝያ 2006

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ወያኔ ለትግራይ ሕዝብ ሀብትንና ብልጽግናን አመጣ ብለው የሚያምኑ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ወያኔ የሥልጣን ወንበሩ ላይ በመውጣቱ ትግሬዎች ሁሉ አልፎላቸዋል ተብሎ ይታመናል፤ በተለይ በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ ላይ የጠነከረ እምነት አላቸው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ብዙ ውይይትም ይሁን ንትርክ ይደረጋል፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተፈራ ርእስ ነው፤ ውስጥ-ውስጡን እንጂ አደባባይ አይወጣም፤ ይህንን ጉዳይ በኢትዮጵያ ውስጥ አደባባይ ለማውጣት ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል፤ አረጋዊ በርሄ፣ ገብረ መድኅን አርአያ፣ አስገደ ገብረ ሥላሴ፣ አብርሃ ደስታ (አሥር ቢሞሉልኝ ደስ ይለኝ ነበር!) እየደጋገሙ ቢያነሡትም ሌሎች በቁም-ነገር የተቀበሉት አይመስልም፤ ሕዝቡ ግን በራሱ መንገድ እየተናገረና ምስክርነቱን እየሰጠ ነው፤ በመቀሌ የተሠራውን የመኳንንት መንደር ሕዝቡ አፓርቴይድ ብሎ ሲሰይመው፣ በአዲስ አበባ የተሠራውን መንደር መቀሌ ብሎ ሲሰይመው እየመሰከረ ነው፤ ‹‹የለሁበትም!›› እያለ ነው።

የትግራይ ሕዝብ መደህየቱ አልበቃ ብሎት ሲለምንም እየተሳቀቀ ነው፤ የሚለምነው ትግሬ ለብዙ ሰዎች ትግሬና ወያኔ አንድ መስሎ እንደሚታየው ያውቃል፤ አብዛኛው ሰው በወያኔ ላይ ያለውን ስሜት ያውቃል፤ ስለዚህም ሲለምን ሰዎች በወያኔ ላይ ያላቸውን ስሜት ስለሚያራግፉበት እየተሸማቀቀ ነው፤ አንድ የትግራይ ቄስ ከአርሲ ነኝ አሉኝና ለምን እውነቱን አይናገሩም ስላቸው እውነቱን ስናገር የማገኘው ስድብ ብቻ ነው አሉኝ፤ እኒህ ሰው ምን በወጣቸው የወያኔን ኃጢአት ተሸካሚ ይሆናሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በትግሬነቱ የተጠቀመ አለ፤ እኔ የማውቀው የደርግ ወታደር የነበረ ትግሬ ቆስሎ ከውትድርና ወጣና በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት የጥበቃ ሥራ ላይ ነበር፤ በጣም ይቸግረው ነበር፤ ሚስቱ ሕመምተኛ ነበረች፤ የቤት ኪራይ መክፈል ይቸገር ነበር፤ ዛሬ ግን የሚለብሰው ልብስ ሌላ ነው፤ ከኑሮውም ተርፎ ለሲጃራና ለጫት እያወጣ ነው፤ ወይም ሌሎች እያወጡለት ነው፤ ትግሬነታቸው ብቻ እንዲህ የደላቸው በጣም፣ በጣም ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህም በወያኔ አገዛዝ ትግሬ ሁሉ ተጠቅሞአል ማለት ከጉልሁ እውነት ጋር የሚጋጭ ስሕተት ነው፤ አብርሃ ሰዎች ትግሬ ሁሉ ተጠቃሚ ሆኗል ሲሉ ‹‹ያመኛል›› ማለቱ ይገባኛል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ውሸት! ውሸት! ውሸት! ውሸት! ውሸት! - የዋሾ መንግስት ጩኸት

ወያኔ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ትግሬ ሁሉ ዕዳ አለበት ማለት እንደወያኔ ማሰብ ነው፤ ወንጀል በዘር አይተላለፍም፤ እያንዳንዱ ሰው ለሠራው ሥራ ሁሉ ኃላፊነትን ይወስዳል፤ ጊዜው ሲደርስ ውጤቱንም ለመቀበል ይገደዳል፤ ይህ የሚሆነው ሰው ሁሉ በመንፈሳዊ ኃይል በጎ መንፈስ አድሮበት፣ አእምሮው በትምህርት ተገርቶ በትክክል ማሰብ ሲችል ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን በአለበት ሁኔታ በጎ መንፈስ የራቀው ይመስላል፤ አእምሮም ጭራሹኑ በእኩይ መንፈስና በጥላቻ እየዛገ ነው፤ ስለዚህ ያስፈራል፤ በደቡብ ሱዳን ሁለት መቶ ሰዎች በዘር ተለይተው ታረዱ ሲባል ያስፈራል፤ በናይጂርያ፣ በኮንጎ የሚካሄደውን የዘርና የሃይማኖት እልቂት ስንሰማ ያስፈራል፤ በ1997 ዓ.ም. መለስ ዜናዊና አዲሱ ለገሰ እንዳስታወሱን የሩዋንዳ የጎሣ እልቂት በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ አለ፤ የቅርብ ተኳሽ የሆነው የአግዓዚ ጦርም አድፍጦ መጠበቅ ያስፈራል፤ ሌላውም ይህንን አውቆ አድፍጦ መጠበቁ ያስፈራል፤ ሰማይ ጠቀስ የሠሩት፣ የሥልጣን ኃላፊነትን ችላ ብለው በሥልጣን የሚነግዱና የሚከብሩት፣ የማይኖሩበትን ሕንጻ የሚክቡት፣ ከሕዝብ ጋር ያላቸው የአይጥና የድመት ኑሮ ያስፈራል፤ አቶ አስገደ ወያኔ መደንገጡን ይነግረናል፤ መደንገጥ የማይቆጣጠሩት ፍርሃት ነውና አደጋ ያመጣል፤ አደጋው አደጋን ይጠራል፤ ይህም ያስፈራል።

በትግራይ ዙሪያ ያለው ምንድን ነው? የትግራይ ሕዝብ በየትኛው አቅጣጫ ነው አንደልቡ እየተዘዋወረ ለመሥራትና ለመኖር የሚችለው? ወያኔ የትግራይን ሕዝብ ከሰሜን ከወገኑ ከኤርትራ ሕዝብ ጋር ደም አቃብቶታል፤ በደቡብ-ምሥራቅ ከወሎ መሬት ቆርሶ የወሎን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ በደቡብ-ምዕራብ ከጎንደር መሬት ቆርሶ የጎንደርን ሕዝብ ቂም አስቋጥሯል፤ የራስን ወገኖች አስቀይሞ ሱዳንን በመሬት ለመደለል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ፋይዳ የለውም፤ ሱዳን ለራሱም ያልበጀ አገር መሆኑ እየታየ ነው፤ ወደፊት ደግሞ ይበልጥ ይታያል፤ በትግራይ ውስጥ ደግሞ ወያኔ የፈጠረው አፓርቴይድ የወያኔን የኑሮ ደረጃ ወደሰማይ ሲያስጠጋው፣ የቀረውን ወደአንጦርጦስ የደሀነት ገደል ውስጥ ከቶታል፤ በዚህም ምክንያት በአዲስ አበባ ከተማ ከነልጆቻቸው እየተዘዋወሩ የሚለምኑ ሞልተዋል፤ ይህ ልመናም ለወያኔ ለመገበር ነው፤ ብዙዎቹ እንደሚናገሩት የሚለምኑት የማዳበሪያ ዕዳቸውን ለወያኔ ለመክፈል ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሕወሐት ኢሕአዴግ መንግስት በልጆቼ ለምን ዘመተ? (ከኣስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል)

ወያኔ ከሀያ ዓመታት በላይ አፍንጫ እየያዘ ያስከፈለውን የሚመልስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ ጥያቄው ወያኔ እንዲመልስ የሚገደደው እንዴት ነው? የሚል ነው፤ጥላቻ ወደንዴት፣ ንዴት ወደቁጣ ተለውጦ ሲገነፍል ምጽዓት ደረሰ ማለት ነው፤ ሁሉም ሰው ራቁቱን ይሆናል፤ አንደአውሬ ከጥፍሩና ከጥርሱ በቀር ሌላ መሣሪያ አይኖረውም፤ ሰው ሁሉ በክፋት ወደአውሬነት ይለወጣል፤ ጠመንጃና ቦምብ አያገለግሉም፤ ሕንጻው ምሽግ አይሆንም፤ መኪናው፣ ባቡሩ፣ ታንኩ ከቆመበት አይነቃነቅም፤ የትም አያደርስም፤ ጭፍራ ሁሉ በየራሱ ፍዳ ታንቆ እንኳን ለሌላ ሊተርፍ ለራሱም የማይበቃ ይሆናል፤ ለነገሩ ጌታና ሎሌም የለም፤ ሁሉም በአውሬ እኩልነት የተፋጠጠ ነው፤ ርኅራኄ ተሟጦ፣ መግል ያዘለ ልብ ፈርጦ፣ ውይይትና ክርክር አብቅቶ፣ ጥርሱን ያገጠጠና ጥፍሩን የሳለ መንጋ በደም የሚራጭበት ሁኔታ ነው።

ሌላ አገር እንዲህ አልሆነም፤ እዚያ አገር እንዲህ አልሆነም፤ የሚባል ነገር የለም፤ እኛ ዘንድ ሌላ ነው፤ የኢትዮጵያ ደሀዎች እንባ የእግዚአብሔርን ሰማይ አጨቀየው!

ክፋት እንደእሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደዓምድ ይወጣል፤ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቁጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ አይራራም፤ ሰው በቀኙ በኩል ይነቅላል፤ ይራብማል፤ በግራም በኩል ይበላል፤ አይጠግብምም፤ እያንዳንዱም የክንዱን ሥጋ ይበላል፤ ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤… ኢሳይያስ 9/18-21

ትንቢተ ኢሳይያስ ለሩዋንዳውያን ብቻ አይደለም፤ ጥላቻና ክፋት በተዘራበት ቦታ ሁሉ ውጤቱ ጥፋት ነው፤ ምናሴ ኤፍሬምን በልቶ አይቀርም፤ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላዋል።

19 Comments

  1. @professor,
    I don’t think the burning issue is trying to define the landscape for the silent majority of Tigrai people by trying to draw a line between them and the TPLF junta and high level officials of TPLF’s satellite organizations who live a life which no single Ethiopian can dream of these days. Let first the Tigrai silent majority first speak out against this junta before jumping on defending them. They did not official make a demarcation between the Junta and themselves as you even could not count more than three individuals from the elites of Tigrai. Many people can sense the reason for your writing this article at this particular time. The burning issue is now about the massacred people for simply asking the junta to stop its injustice and a program of pushing a certain group of people further off the cliff from economic progress and further uprooting them from their qualified right place, if you are genuine about rights of all people in the country. But those who are freshly killed by the junta are not of your concern as “human right activist”.
    The people who are honestly fighting back the marginalization of their people by this TPLF government are more matured than you expect. They don’t touch any person who is honestly doing his/her business within their area. BUT people who are dying for their right have a justifiable reason to fight back those who are siding with the killing army by providing information to the security force or against those who speak out derogatory statement about the people they are living in among in the cities and villages.

  2. good oservation Prof. I do not think die hard TPLF JUNTA will listen your advice. d Junta’s end is so close, but we need to be carefull about WOYANE TIMEBOMB of TRIBALIZM.

  3. ወያኔ ህዝባችን በየጎሳው መለያየት ብቻ ሳይሆን እሳትም እያቀበለ አንድ ሌላውን እንዲያጠቃው ያመቻቻል። ሲመቸው ይገድላል፤ ያስራ፤ ይሰውራል፤ ከሃገር ውጭ ድረስ ተከትሎ ይገድላል። በሃገራችን ታሪክ እንደወያኔ ያለ አፍራሽ ድርጅት ተፈጥሮ አያውቅም። ጥቅም የሚያካፍለው ለድርጅቱ መሰሪዎች ብቻ ነው። ለምሳሌ – እንደ አምባሳደር ብርሃኔ ያሉት ሌቦች በኤምባሲ ስም በመዘበሩት ነው ቤት የሰሩት። ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባል የወያኔ ሰዎች በውጭ ሃገር የባንክ ቁጥር በሚሊዪን የሚቆጠር ገንዘብ አካብተዋል። ዘመድ አዝማድ ልጅ የልጅ ልጅ በውጭ ሃገር በሥራ በትምህርት በማሳበብ ለቅመው አሰልፈዋቸዋል።
    ወያኔ ለትግራይ ህዝብ አይገደውም። ገዶትም አያውቅም። በስሙ ግን ይነግዳል። ዶሮ የማይነጋ መስሎት ከቆጥ ላይ ምን አለች ይባላል። ወያኔ አወዳደቁ የሮም አወዳደቅ ነው የሚሆነው። ጊዜ እያለ ያበላሽቱን ለማስተካከል እንደመጣር ዛሬም እንደ ትላንቱ ወሬአቸውና ሥራቸው ሁሉ እሾህ ነው። የወያኔ መፈራረስ ጊዜው ሩቅ አደለም፡፡ የሚያስፈራኝ ግን ያቀጣጠሉት የጎሳ የዘር እሳት ሁሉንም እንዳይበላ ነው። ፈጣሪ ያውቃል!

  4. Egziabhere ewnet mayet yemichlu bale birhan aynoch ayasatan. Hone bilen yewistachinin ye ewnet chuhet alsemam blen le tilacha dimtsoch jorowochachin yetekefetutin lib yisten.

  5. yemisema goro yalew yesema enem yehenenu yemelew tenberkek kemchoh lelea minm madereg alchelm geta ayenochachennen yekefet
    thankyou

  6. Dedeb amara anten belo professor keamara docter mehayim tigre yebeltal yehem betegbar teregagtual megnotehin new yemtsefew yesawdi negestat 700 amet geztewal egna tegrewoch degmo anten becha sayhon yelij lijochehinm engezalen. 20 amet temegneh eyetemegneh temotaleh.
    In fact this is not political analysis it’s the dedeb amara fake professor wish lists.

  7. @ Zehabesha,
    If you are genuine to be independent to entertain different views on any posted article on this website, please don’t hold genuine responses to postings. I did comment on this article. But my comment is not posted in 36 hours. That is not expected from the website which advocate for freedom of speech and for the release of journalists and bloggers who are imprisoned by Wayane just because of their writings and/or comments freely on actions and reactions of the dictatorial government of TPLF.

  8. The EPRDF/TPLF wild beasts didn’t realize the unintended consequences of what they have been doing for the past 23 years as the Professor clearly explained it in this weekly commentary.I am echoing the voice of the professor to tell them[ the wild beasts] that to stop and think the unintended consequences, otherwise the consequence is dire.
    I take off my hat to Professor Mesfin Woldmariam.

  9. Prof. If you are belive and meant what you write is correct you are mistaken.

    Alem

  10. yehe sewye hule ‘ndasferaran new. balefew gize egypt ltatefan endemtchl sisebken nebere. ahun demo chrash basebet. ho ho…fetari meche new yemigelaglen kezi metetam sewye

  11. ህይ ጽሁፍ ከ15ዓመት በፊት ተጽፎ ቢሆን ወያኔ እስካሁን ኣይቆይም ነበር። ኢህኣፓ እንካን ሳይቀር እንዴት ትግሬዎች ይገዛሉ በማለቱ ኣብዛኞቹ ኣባላቱን ኣጥተዋል። ኣዎ ጥቂጦች የወያኔ ኣሽከሮች ናቸው፣ ጥቂቶችም ከነሱ የተሻለ ኣይመጣም የሚሉ ኣሉ፣ ጥቂቶችም ካለፈው ኣስከፊ ስርዓቶች ገና ኣእምሮኣቸው ያላጸዱ ኣሉ፣ ኣብዛኛው የትግራይ ህዝብ ግን በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ሰላም ፈላጊ ነው፣ ይህ ማገናዘብ የተሳናቸው ደግሞ ከወያኔ ጋር ይደባልቃቸዋል፣ ለትግሉ እንቅፈት የሆኑ እነዚህ ትምክህተኞች ናቸው። ኣዲስ ኣበባ ነጻነት የሌለ እንዴት ትግራይ ነጻነት ይኖራል። በስለላ ተከቦ። ነጻ ጋዜጣ የሌለው። ነጻ ፍርድ ቤት የሌለ። ስንቶች በእስር ቤት ተዳርገው። ወያኔዎችና ደጋፈዎቻቸው ደልተዋቸው ገበሬው በመዳበርያ እዳ ኣስረውት ለዚህ ተግባር ኖርወይ ለመለስ ሽልማት ስትሰጠው። ስለዚህ እብዝሔር ይስጥዎት ፕሮፊሰር ኣስራት፣ ሌሎቻቹሁም ለተጎዳ ህዝብ ተነሱ ከራሳችሁ የሰብኣዊ ርህራሄ፤ ኣራዊት እንካን እርስ በርሳቸው ኣይጨካከኑም እንድያውም ትግራይ መነሻችን ለሁላችን የሆነችው።
    ገብረስላሰ

  12. Thank you Professor Asrat; others from Tigray, Amhara, Oromo, etc show us your unity!
    To the other a few commentators: In the Derg time, no one was opposing him in Addis Abeba or other cities; but we don’t blame the Amhara people. You have no clue how TPLF is holding in a cage and torturing the people of Tigray. They don’t even trust their own children because they are brain washed by TPLF security, even though, thanks to Arena and to the death of Meles; change is coming. 17 opposition parties who held a conference in Paris back 1993called Paris Conference; we know who the main obstacle was. 15 opposition parties who held in Washington, DC and formed Hibret or UEDF back in 2009; we know who was the main obstacle. So instead of blaming Tigray people whom are under TPLF military and security guards like the other people all over the country, stand up and be honest to yourself and know who the main obstacles to throughout TPLF/EPRDF are and speak out against them; don’t hide them because they are from your birth area; we know them very well.
    Laikun

  13. Apologetic!
    You can’t hid the fact that TPLF is an apartheid government that stands for all Tigreans! Tigreans are the queen and kings in present Ethiopia. Don’t run around the bush. Tell it like it is.

  14. Professor it is a good message to those of whom want to listen. The ruling elites like the TPLF always use ethnicity politics to advance their political and economic interests. As a people we need to understand their divisive tactics and learn not to hate our fellow human being. All ethiopians have the same wishes and desires for themselves and their families which is to eradicate poverty and live in peace and harmony. As the professor said the ruling TPLF elites use the Tigrian people as a cover to advance their own individual interests by creating artificial conflicts with other ethnic groups in various parts of the country. As a people we should learn not to hate each other and avoid the divisive political tactics of our elite politicians.

  15. This is for the admin of this web site –
    What exactly is your goal to let through vile and stupid comments from so called readers?

  16. ፕሮፌሰር መስፍን በቅርብ ባላውቅዎትም በሁለት ምክንያት አደንቅዎታለሁ አንደኛው ነገሮችን የመተንተን ብቃትዎ እና እጥር ምጥን ያለ ፅሁፍ የማቅረብ ችሎታዎ ሁለተኛ በዚህ ዕድሜዎ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሶሻል ሚድያ ሳይቀር እየተከታተሉ ለአገርና ህዝብ ይጠቅማል የሚሉትን ለሌሎች ለማካፈል ሲተጉ ሳይ ያልዎትን ተፈጥራዊ ጥንካሬ ግርም ይለኛል በዚህ ፅሁፍዎ ላይ ትግሬዎች ተጠቅመዋል ለማለት ያቀረቡት የወታደሩ ምሳሌ ግን ምን ነካቸው ፕሮፌሰር ለማለት አስገድዶኛል በአንድ በኩል ለዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍልም ያልዎትን ቅርበት እያደነቅኩ ኢህአዴግ ከገባ ይሄው 23 ድፍን ዓመታት ሊሞላው ቀናት ብቻ ናቸው የቀሩት በዚህ ጊዜ ውስጥ የማንም ብሄር ተወላጅ ገቢ የሚያስገኝ ስራ ከሰራ ልብስ እና ጫት ከመግዛት ያለፈም ሃብት ሊያፈራ ይችላል ብዬ አምናለሁ ሁሉም ሃብት ያከማቸ የትግራይ ተወላጅ ነው የሚለው አባባል ደግሞ ዓይናችን እነሱን ብቻ እንዲያይ ካልተጋረደ በስተቀር ትክክል አይደለም ስም መጥቀስ አስፈላጊ ባይሆንም አንቱ የተባሉ ቱጃሮች ከሌላም ብሄር እንዳሉ ፀሃይ የሞቀው ሃቅ ነው በተለይ እኛ በደርግ ጊዜ የነበርን ሰዎች አንድ ሃብታም ምን ያህል ካፒታል እንዲኖረው በህግ ተደንግጎ እንደነበር ስለምናውቀው ማን በ23 ዓመታት ለውጥ እንዳመጣ ለማወቅ አንቸገርም ስለዚህ አንድ ግለሰብ ለምን ልብስ ቀየረ ተብሎ ሳይሆን መቅረብ የነበረበት ይህን ለማድረግ የተጠቀመበት ህገ ወጥ አካሄድ ከነበረ ማለትም የትግራይ ተወላጅ በመሆኑ ብቻ ሳይሰራ ያገኘው መሆኑን በማስረጃ አስደግፈው ቢያቀርቡት የተሻለ ነበር እላለሁ ረዥም ዕድሜ ለፕሮፌሰር!!

Comments are closed.

Share