በሬየን አልሸጥም – አጭር ወግ – በሄኖክ የሺጥላ*

አዲሱን (የነበረውን ግን ሰሞኑን የሾረውን) የ “ኦሮሞ ወጣቶች ” ግድያ። በነገራችን ላይ ለምንድን ነው “የኢትዮጵያ ወጣቶች ” የማንለው? ማለት ስለማንፈልግ? ወይስ ብንል ባንል ምን ይጠቅማል ( ምንስ ይጎዳል በሚል ሃሳብ?) ሁለቱንም ያዙልንና እንቀጥል።

ሰሞኑን አምቦ ላይ የተፈጸመውን ግድያ  ተከትሎ ወዳጆች ” ልጅ ሄኖክ በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር በል እንጂ “ጠላቶች ደሞ ” አንተ ምንትስ አማራ አሁን አማራ ቢሆን ኖሮ ይሄ ሁሉ መከራ የደረሰበት አምሳ ገጽ ጽፈህ ፣ ነገሩን ለውጠሕና ለጥጠህ ባቀረብከው ነበር ” የሚሉ መልዕክቶችን አስቀምጠውልኛል። እኔም እንደ ለገዳዲ ሬዲዮ ” ጦማሪዎችች ሆይ ምልእክታችሁ  ደርሶኛል ለሁሉም እንደነገሩ ለመመለስ እንሆ–”

በነገራችን ላይ አማራ ስለመሆኔ እኔ በበኩሌ እርግጠኛ አይደለሁም ፣ ቢያንስ እርግጠኛ እስክሆን ብትታገሱኝ ምን ነበረበት ( ስለ-ኔ ከኔ በተሻለ መልኩ የምታውቀው እናቴ እንኩዋ እንዲህ በሙሉ አፍዋ “አንተ አማራ!”  ብላኝ  አታውቅም። ታዲያ የምታውቀው ነገር ቢኖራትም አይደል ? አለበለዚያ ማኛና ሰርገኛ በሚል ማህበረስብ ውስጥ አድጋ እኔን በደም ስሜ መጥራት ባልዳገታት ” እስኪ ለናቴ ጊዜ እንደሰጠሁዋት እናንተም ለኔ ጊዜ ስጡኝ ” ደሞ ለዘር ፣ እድሜ ለወያኔ እንኩዋን የሰው  የንብ ሰፈር እንኩዋ በታወቀበት ዘመን የምን መንገብገብ ነው!) ።  አቦ እናት ለዘላለም ትኑር ! ቀጣዩን ሃሳብ በሚቀጥለው መስመር ላይ ያንብቡት።

መልስ አንድ:  ለሞቱት ስንገጥም

 

ሲረግጡን ታግሰን

ሲሰድቡን ታግሰን

ይሄን ሁሉ ዘመን ብሶት ተንተርሰን

ሃዘን አኮራምቶን

መላ ቅጡ ጠፍቶን

ሁሉም ግራ ሆኖ

በሃሳብ ተውጠን

ከሥጋ ስማችን

ያፈሩ ከበደን ።

 

እና አይሆንም አልን

ሕጉ ይስተካከል

ይሞረድ ይቦረሽ ባለ ጥርሱ መድብል

ድንበሬን መልሱ ክብሬን እንዳሻችሁ

ነጻነቴን ቀሙኝ ስሜን እባካችሁ።

 

አልጻፍ አልናገር

አልሰለፍ ይቅር

ባልበላም ግድ የለም ዘመን ጾሜን ባድር

አይከፋኝም ከቶ ብሰደድ በገፋ

ሃገሬ ቢቆረጥ ታሪኬ ቢጠፋ

 

አይሞቅ አይበርደንም እኛ ግድ የለንም

ሰው ቢፈናቀል ቢራቆት ቢራብም

 

ወደብ አልባ ብሆን ወይም ወኔ አልባ

እሱ አይደልም ለኔ ከቁብ የሚገባ

 

እያልኩ ልቀጥል አሰብኩና ተውኩት።  እውነት እውነት እላችሁዋለሁ ሰው እንዳይከፋው እያሰቡ ለመጻፍ ከማሰብ የበለጠ  የሚከብድ ነገር ዕኔ በበኩሌ አላጋጠመኝም። ስለ መፈናቀል ጽፈ ሳልጨርስ ስለ አፈናቃዮች መጻፍ በጣም ይከብዳል፣ ስለ ዘረኛ ስርዓት ጽፈ ሳልጨርስ ስለ ዘረኛ ተጨቁዋኝ መጻፍ አሁንም ይከብዳል። ስለ ኢትዮጵያ ተናግሬ ሳልጨርስ ስለ መንዝ ወይም ስለ ኦሮሚያ መጻፍ ይደብታል። ስለ ትግሬ አምባገነን ተናግሬ ሳልጨርስ ስለ አማራ ወይም እሮሞ ታዳጊ አምባገነን ወግኖ መናገር ይከብዳል ።  የነገሩን ውስብስብነት ተረዱልኝ። በደላቸው፣  ስቃያቸው፣ መታሰር መገደላቸው፣ ሁሉም እውነትነት አለው። ግን   ሀሳባቸው ከደረሰባቸው በደል ያንሳል ፣ ስሜታቸው ካሳለፉት መከራ አንጻር ኢምንት ( ታልኢት) ነው፣ ጉልበታቸውን የማያውቁ በትንሽ ነገር የተጠመዱ ታጋዮች ሆኑብኝ፣ ወንድሞቻቸውን የሰዉለትና የምሰዉለት አላማ ከማንነታቸው ይደቃል፣ ጉዋዶች የተሻል ጥያቄ አለ ( ፍንጭ ልስጣችሁ አይደልም ኦሮሚያ  ኢትዮጵያ የኔ ነች የሚል )።   እስኪ አንድ ወደ ሁዋላ እንመለስና እናስብ። ስናስብ ደሞ በርጋታ እናስብ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ከብሔረሰብ በዓል ወደ ለታላቁ ሩጫ! - በእውቀቱ ስዩም

አንድ ወደ ሁ-ዋላ

በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ክፍላተ ሃገራት እንዴት ይካለሉ እንደነበር እናስብ ( ስለ ደርግ ጠቅላይ ግዛት አሰያየም  ብዙ ማውራት አልፈልግም፣ ማወቅ የፈለገ ያንብብ )  ፣ ከዚያ ” የዘመናት ብሶት የወረሰው ጀግናው የ ትግራይ ሰራዊት ( ስሙን ቀይሮ የ ኢህአዲግ የተባለው ) አዲስ አበባ ገባና ዔርትራን ለማስገንጠል የሚመች ሕግ አወጣ፣  በዚህም ሕጉ ኤርትራን  ብ ቻ ሳትሆን የልጅነት ( የእቃቃ ፍቅረኛዬም ) ከነ ኮካ ኮላ ኮርክያችን ( ጥሪታችን) ጋ አብራ ተገነጠለች (የሚገርመው ኮርኪ ሰለሆነ ነው መሰለኝ ይዘሽ መወጣት አትችይም አልተባለችም )። በመቀጠልም 70 ምናምን  ሺ  ሰው የጨረሰውና ያስጨረሰውን   ጦርነት አካሄአዱ ( በቴዲ አፍሮ ቁዋንቁዋ ” ሁለቱ ዝሆኖች”) በኔ ቁዋንቁዋ ዘ-ለቱ  እባብስ።

ያ ጦርነት አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ ለሰራው ሥራ የማህተም ማድረቂያ ካሳ ነበር።  ከዛ የመሃል ሀገር ሰው ጨዋተው የተጀመረ መስሎት በደስታ ፓርላማ ውስጥ ጨፈረ ( አንዳንዱ ኮፍያውና ሽርጡ እስከሚወልቅ ድረስ ) እና በየቤቱ የዘሩን ቆዳ የስል ጀመር። ጀግናው የኢህአዲግ ሰራዊት ግን ልጅነት ደጎሰ ጨዋታ ፈረሰ አለ ። ድሮስ እግዚአብሔር ሰጠ እግዚሀብሄር ነሳ እንዳለው እዮብ ወያኔ ሰጠ ወያኔ ነሳ ሆነ  ( ስለዚህም ይህ የዘመን ብሶተኛ  ለኤርትራ በደም ለተቀረው ሕዝብ ደሞ በቾክ  ያሰመረውን ሕግ መርገጥ ጀመረ ) እና ከተሜ እንዴት ተደርጎ አለ። እኛ ስንት ነገር ስናስብ የምን ዘሎ መቀላቀል አይነት ነገርም አንዳንዶች ሲናገሩ ሰማናቸው። አንዳንዶቹ ልጆቻቸው በበሽታና በድንቁርና ከማለቃቸው የበለጠ የልጆቻቸው አማርኛ መማር አሳሰባቸው፣ በ 2006  መሬታቸውን ከቀማቸው ይልቅ ከመቶ ዓመት በፊት ቸፍጭፎናል የሚሉትን ሚኒልክን  መውቀስ ቀለላችው፣ የብሔር ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል በሚለው ይጠደሰጡት ፣ የአንድን ግለሰብ ሃሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱን ተቃወሙ እና በታንክ እና በ መትረይስ ከሚደበድባቸው ወያኔ ይበልጥ የቴዲ አፍሮ ዘፈን አመማቸው እና በጠራራ ጸሓይ እየተገደሉ  ወያኔ ይሙት ይላሉ ስል ” ቴዲ አፍሮ ይታሰርልን አሉ” ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ። ለዚያ ነው እየከፈሉት ያለው መስዋትነት ከያዙት ሃሳብ ይበልጣል ያልኩት ።  ነብሳቸውን አይማረውና የጎሳ ማይክሮ ባይሎጅስቱ ( መለስ )  ይህንን  ቆመው ቢያዩ ምን ይሉ ይሆን ? እንደኔ እንደኔ ” አዋ ይሄኛው ባክቴሪያ ልክ እንደታሰበው ነው ሪ- አክት እያደረገ ያለው፣ ያኛው አሁንም ቢሆን ትንሽ ራይቦሶማል ትራይባል ሴንስ ኢንሰርት ሊደረግበት ያስፈልገዋል ” የሚሉ አይመስላችሁም? አይ እሳቸው ! አይ እኛ !

ተጨማሪ ያንብቡ:  የማለዳ ወግ ... 83 ኛው የሳውዲ አረቢያ ብሔራዊ በአል ምልከታየ !

አንድ ወደ-ፊት 

የትግል ስያሜ ያላማ ግብር ይሆናል ማለት ዘበት ነው። ለምሳሌ ( የትግራይ ነጻ አውጪን እንመልከት)። በመጀመሪያ ትግራይ ማለት ከየት እስከየት ነው ? የመሃል ሃገሩን ትግራይ ይጨምር ነበር ? እንደዚያ ከሆነ የትግራይ ሕዝብ ሳይሆን የትግራይ ኑዋሪዎች ነጻ አውጪ ነበር መባል የነበረበት። ምክናይቱም ትግሬ ትግራይ ውስጥ ብቻ አይደልምና  የሚኖረው። ለምሳሌ የኛ ጎረቤት የነበሩት እማማ ሐዳስ ( እድሜ ለ ወያኔ የተንጣለለ ቤት ሰርተው ወደ ሳር ቤት ገቡ እንጂ ትግሬ ነበሩ። ግን ነጻ ስለመውጣታቸው እርግጠኛ አይደለሁም።

አሁንም ወደ ነገሬ ልመለስ ( ማንሽ አንቺ በዛሁ የጠፋሁ እንደሁ መልሽን )። ይሄ በተያያዘ ሃሳብ የመጥፋት ችግር አለብኝ ”

አሁንም የስያሜ ጦርነትን የሚቀድም ነገር ያለ ይመስለኛል ( እንዲሁ ሳስበው ፣ አያርገውና የኦሮሞ ሕዝብ ምናምን የሚባል ድርጅት አዲስ አበባን ” ፍንፍኔን በሸዋኛ ” ወይም ” ፊንፍኔ በኦሮምኛ” እዚህ ጋ ቶሎሳ እና ተሎሳ ብለው ሲጣሉ ስላየሁ ጥንቃቄ ቀድሜ ባረግ ብዬ ነው፣ ለማስመልስ ባደረጉት ጥረት ወያኔን ሳያስቡት ገለበጡት እንበል ( ልክ ወያኔ ሳያስበው አዲስ አበባ እንደደረሰ ) ከዛ ምን የሚሆን ይመስላችሁዋል ? እናንተ ለመመለስ ትፈሩ ይሆናል ሌኔ ግን የሞተው መለስ  በኦሮሞ ልጆች ስም; በኦሮሞ ልጆች ደም ፣ በኦሮሞ ልጆች አፈር ብቅ የሚል ይመስለኛል። ከስያሜ ማንነት ይቀድማል። ማንነታችንን ሳናስከብር ስለ ምንነታችን መናገር አንችልም ( ” መ ስፍን ወ/ማርያም እንዳሉት)።  መቼ ነው የነሱን ጨዋታ መጫወት የምናቆመው ? መቼ ?

 

ወግ

አንድ ገበሬ እጅግ የሚወደው በሬውን ሊሸጥ ገበያ ይዞ ይወጣና ሳይሸጥ  ይዞ ይመለሳል።

ዘመድ “ምነው ጃል በሬህን የሚገዛ ሰው አጣህ?”

ተጨማሪ ያንብቡ:   ዝ ክ ረ   ዓ   ደ   ዋ  ! - መኮንን ሻውል  ወልደጊዮርጊስ

ገበሬ ” አይ በሬዬን  ሊገዙ ከመጡት ሰዎች መሃል አንዳቸውም  ለበሬው የሚሆን ድርቆሽ ( መኖ ወይም ሳር ) አልነበራቸውም፣ ስለዚህ በሬየን ሽጬ በረሀብ ከምገልው ብዬ ነው ሳልሽጥ  ይዤው የተመለስኩ ”

እኔም እንዲህ ነው የሚታየኝ።  ወያኔ መውደቅ ስላለበት ተብሎ በሬዬን በርሃብ ለሚገል ገበያተኛ ነጻነቴን አልሸጥም። እንሱም (ወያኔዎችም) ቢሆን  ሲጠነሰሱ እርሾዋቸው ዘረኝነት ነበረና። በሬዬን ልተገዛ ከፈለክ መጀመሪያ ሳር ይኑርህ ፣ መጀመሪያ የሚገዛ ሃሳብ ይኑርህ፣ መጀመሪያ ስለ በሬ እወቅ።  አስራ ስምንት ሚሊዮን ጭቁን፣  አስራ ስድስት ሚሊዮን ጭቁን ቢጠላ ጥላቻው  ወተት አይወጣውም እሱንም የሚጠላውንም  ይዞ ይጠፋል እንጂ።  ብሬ መግዛቱ አይደልም ቁም ነገሩ ፣ ቁም ነገሩ እስክታርደው ድረስም በሬነቱን መገንዘብ ነው።

ገበያ ወጥቶ ሸማች መሆን አይደለም ቁም ነገሩ፣ ቀም ነገሩ ቢያንስ የሸማች ባህሪ ይዞ መገኘት ነው።

በአንድነት ለመቆም አንድ አይነት አመለካከት የግድ ሊኖር ይገባል በሚለው ሃሳብ ብስማማም በይበልጥ የሚያስማማኝ አንድ አይነት አላማ ሊኖር ይገባል የሚለው ነው።

እስከሚገባኝ የታጋይ ሃሳብ የጨቆኑትን ከማሸነፍ፣ የገደሉትን ከማንበርከክ፣ የበደሉትን ከመበደልም የራቀና የላቀ መሆን አለበት ብዬ አስባለው። በታጋይና በበቀልተኛ መሃከል ያለው ልዩነት ይሄም ይመስለኛል። ታጋይ አንድን ስርዓት ሲቃወም ወይም ሲታገል፣ ስርዓቱ ማድረግ የነበረበት ግን ያላደረገውን ነገር ለመለወጥ ይመስለኛል፣ አንድ ታጋይ አንድን ስርዓት ለመለወጥ ሲነሳ ፣ ኢ-ፍትሃውነትንም ሆነ የአስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እውቀቱና ብቃቱ እንዳለው አምኖ ያ እውቀቱና ብቃቱ ስልጣን ላይ ባለው ስራዓት ( ስርዓቱ በሚፈቅደው መንገድ ታግሎ ) እውቅናን ሲነፈግ ፣ ያ የሚያልመውን ለውጥ ለማምጣት እምቢ ያለ አካል ነው ብዬም አስባለሁ። በቀልተኛ ግን የድሮ ቁስሉንና ብሶቱን ከማሰብ እና ብድሩን እንዴት እንደሚመልስ ከማውተንተን ያለፈ ሕልም የለውም፣ ለሱ የሥርዓት ለውጥ ማለት የበደሉትን ( ወይም በድለውኛል በሎ የሚያምነውን) ማህበረሰብ መበደል ነው፣ ለሱ ትግል ቂሙን የሚወጣበት ፣ እልሁንና ቁጭቱን የሚገልጽበት አጋጣሚ መፈለግ ነው። ወያኔ የተፈጠረው በዚህ መንገድ ነው፣ ሌላውም በዚህ መንገድ መሄድ ይፈልጋል ፣ እንደ ዜጋ የተሻለ ሃሳብ ከሌለህ፣ ከቂመኛነት ወደ ታጋይነት፣ ከባለ አረርንት ወደ ባለ ር-አይነት መለወጥ ካልቻልክ በሬየን አልሸጥም።

ቸር ይግጠመን

 

 

 

* ገጣሚው

 

16 Comments

  1. what an insightful thought and analysis of the politics and apprciative way of saying it! Keep it up. That is why I think the TPLF will continue to rule….till we start to learn how to behave as a reponsible heir of this diverse country!

    God Bless you!

  2. wey gud henok yeshitela.

    amaranet, amharization, ethiopianization. bedem bicha aydelem yemiweresew.

  3. ሔኖክ ጹሑፍህን በአንድ ትንፋሽ አነበብኩት ግን ስመዝነው የክፍለ ዘመኑ አስነዋሪ ጹሑፍ መሆኑን ስነግርህ በግጥሞችህ የማደንቅህ ሰው ስለሆንክ ቅር እያለኝ ነው። ሔኖክ የሚገርመው ነገር ፈጽሞ ሰባዊነት የሚባል ነገር የፈጠረብህ አይምስልም ነገሮችን በአንድ አቅጣጫ ብቻ አይተህ አንድ አላማ ስለለለኝ ቢያልቁ ግድ የለኝም ነው የጹሑፍህ መንፈስ እኔን ሲገባኝ። አንተ እንዴት አድርገህ ነው ለእነ እስክንድር ነጋና ርዮት አለሙ የምትገጥመው(ጥያቄ ምልክት) ማንስ ይሰማሀል (ጥ.ም) አንድ ስንኝ በአንተ ቁዋንቁዋ ልጠቀምና ለሞቱት ኢትዮጵያዊያን መጻፍ ተሳነህ። ለምን መሰለህ የኦሮሞ ተማሪዎች ናቸው የምንለው ፤ አየህ ተቃውሞውን የተቃወሙት እነርሱ ስለሆኑ ነው ያም ማለት ሁሉም ብሔረሰብ ባለበት ት/ቤት (ዩኒቨርሲቲ) ውስጥ የወገናቸው መፈናቀል የተሰማቸው ኦሮሞዎች ብቻ ስለሆኑ ነው። ቆይ እንጂ ወዳጄ አንድ ነገር ልበልህ እነዚህ ተማሪዎች አንተን የሚያሰጋህ ጥያቄ ይዘው ቢሰለፉም እኮ መብታቸው ነው። ምን ታስባለህ ብሎ የሚጠይቅ ሀገር ስለሆነ እንጂ እኔና አንተ በምንኖርበት የምዕራቡ ሀገር ሰው ሰለሚያሰብው ነገር ተፈጥሮአዊ መብት እኮ ነው። የነዚህ ተማሪዎች ጥያቄ ግን ግልጽና አጭር ነበር መንግስት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ነዳው እንጂ። እንደዚህ አይነት ቅጥ ያጣ ዘረኝነት ግን እውነት ነው የምልህ በዘረኝነት በምንታማው ዘንድ እንኩዋን አይገኝም። በቅርብ አንድ ግጥምህን ለኢትዮጵያዊው ፓይለት የገጠምከውን ጹሑፍ ስታነብ ሰምቼ በጣም ስሜቴን ነክተሐው ነበር ነገር ግን ያን ግጥም ያፈለቀው አህምሮ እንደዚህ አይነት አስነዋሪ ጹሁፍ ጽፎ ሳይ ጩሐታችሁ የውሸት ነው ወደ ሚል ድምዳሜ አመጣህኝ ያስጮሀህ ከኢትዮጵያዊነቱ ይልቅ አማራነቱ ነው ወደ ሚል ድምዳሜ አድርሶኛል። ሔኖክ ሰለተፈራ የሚቀር ስለ ተደፈረም የሚመጣ ነገር የለም ነገሮች በእኔና በአንተ እጅ ናቸው ወይ ተጋግዘን ልናጠፋት ወይ ደግሞ ልንገነባት ምርጫው በእናንተ እጅ ላይ ነው። ይህንን ጹሑፍ ከማንበቤ ከደቂቃዎች በፊት የእስክንድርን ጹሑፍ አይቼ ነበር በዛው ብወጣ ኑሮ ደስ ባለኝ ነበር ምክንያቱም ከምወድልህ ግጥሞች ጋር ፊት ለፊት ባልተጋጨው ነበርና። ግን እንደ አለመታደል ሆኖ ጹሑፍህን አነበብኩት ግጥሞችህንም ጠላዋቸው። በል ወዳጄ ቸር ይግጠምህ

  4. Zarem inde ayatochih teret teret taweraleh? Awo min tihonale?…yeminilik chifchefa, ye mayim azmari torinetin ‘kidus’ bilo yemitera (asafari, yezemenu mirt mayim), …lemas tarek minim bitizebarik indante mayim kalhone beker yemisemah yelem. Gena oromia wust yalewun amhara kitun iyewegan wede limena inasemarawalen (wede tikikilegnaw siraw). Teretihin awura.

  5. kemehal ende zare tnsh wezgebgeb alkebegn. ezina eza regetk yhone begedemdame malef yefelkew neger ale ena tedebesebesk. tsehufeh ena re’esu bizu algenagn alugn.

    gin bechilotah terter yelegnim akbarih negn. endew welem zelem alshebegn zare. minm teyake yelewem teyakiyachew minamin ayasegnign begif tegelewal tegelwal arat niteb yelu nebr nebs yemar ena egna melata::

  6. ማቅ ይሞቃል ሻሽ ይደምቃል ጉዳቱን ባለቤቱ ያውቃል ቢባልና ሔኖክ የፃፈው ፅዩፍ እራሱን ለመጥቀም አደረገው ብንልና ጥቂጥ አንባቢያኑን አስከፍቶ ከሆነ እንዴትና ለምን አስከፋ ?የተፃፈውን ፅሁፍ ከነግጥሙ አነበብኩት ;;; እርግጥ ነው ስለ ጎጥ ማንጎጥ እያሰብን ወያኔ የፃፈውን መፈከር አፍ ቀይረን እየዘመርን የራሳችን ጠፋን ይላል።እረግጥ ነው ስሙ ሔኖክ ነው ግን የዚ ሰፈር (ብሔር) ነኝ አላለም ።በጉርድ ፎቶ ቁመናን ማሳየት ሩቅ ላለ ሰው ያስቸገራልና ሙሉን ለመነሳት ግዜውም አሁን ነው አቅሙም አለን ነው ያለው ።(እጆሌ አሮሞ ማል ታተኔ)እርግጥ ነው ስራ ቤለው ቀኑ ብቻ ስለሐገሩ ለሚያስብ ሰው የዛሬ 100 አመቱ የዛሬ አመት ያህል ይቆጥረውና ይቆጨዋል። አውነት ነው ተደርጎ ከሆነ እጅግ አሳዛኝ ታሪክ ነው የሚሆነው (በሚኒሊክ የተፈፀመው። ማንም የሚቀበለው አደለም ።ግን እኮ ወያኔ ሚኒልክ እንዲህ አደረጋችሁ ሲል እና ሲሻንን አደረገን ብለው ጣሊያን ኢንባሲ ፊት ለፊት ሰላመዊ ሰልፍ የወጡትን አስሮአል ።ጣሊያን ደሞ ያልገደለው ያልጨፈጨፈው የለም ። ግን ማንም የኦሮሞ ልጅ የሚኒልክን ያህል አልተቆጣበትም። ቦታም አልሰጠውም።ምነው ታዲያ ህወዋት የደገመውን ውዳሴ እኛ አፍ ቀይረን ማንበባችን ?አረ ረ ግዴለም አንድ እንሁን በእኛ ይብቃን።ምነው ለ ኢትዮጲያ አገም እሽክ ሆንባት ።ወይ ቆርጦ ወጠወቶ መታገል እና የሚመኙትን መሆን ወይም ማድረግ አልያም …..ብቻ ጥሩ ዝምታም የብሩቱ ትግል ያህል ነው ።ዥም ያለ ሰውና የረጋ ውሃ ጉዳቱ ከጉዳት በላይ ይወጣዋልና።

  7. aweksh aweksh seluat. . . . . yelu neber abatochachn
    Yemtawerawun kalawek zem malet yeshaleh neber.

  8. 1) Why was Ambo University calm and steady when Amhara were displaced from Benishangul, Wldiba Monastry was demolished and Amhara women were defertilized, or when Assefa Maru was killed or when TPLF interferes in Islamic matters?
    2) Please those who have no words to condemn the recent killings of innocent African young university students in Ethiopia, nor have no words to condemn other attrocities committed by this regime, the last regime, etc, have no words to speak against the hero of Adwa, the Mastermind of African Liberty, His highness, Minilik. Because, Italians have killed more black race in this land and no one is saying anything about it, because it might compromise diplomatic relations between the two nations. But speeches against minilik are already compromising unity among Ethiopians right now.

  9. i think such idea is very important for future Ethiopia. I am very very sad for Ethiopian students who killed by TPLF and may God give stregnething for thier family. We have to think bigger please try to think as one Ethiopian. That is the logica and a natural way, but who you think opposite of this, you will never move an inch. የዛሬ ሰዎች እንሁን፤ ሆድ ውስጥ ሁነን፤ጨጓራ፤ኩላሊት፤ጣፊያ ባንቆራርጥ ጥሩ ነው። ህመሙ የራሳችን ነውና። ሁላችሁንም እወዳችኋለሁኝ።

  10. አመለካከትህን አልወድኩትም መቃወምም መብት ነው።ይሁንና ኢትዮጵያዊነት በራሱ ተዥጎርጉሮ ተከባብሮ አብሮ መኖር ነው አሁን ግን በአንተ ፅሁፍ የምመለከተው ይሄን ብላችሁሃልና እኔ የ ምወደውን አልወደዳችሁምና ሞት ወይም ግርፋት ይገባችሁዋል ነው። ቴዲ ዘፈነ ለገንዘብ : በአሁኑ ሰአት የተጠየቀው ጥያቄ የነፃነት ጥያቄ አይደለም ከአዲስ አበባ ዙሪያ የሚነሱ ወይም የሚያርሱት መሬት የሚወሰድባቸውን ገበሬዎች ምን ውስጥ ልትጥሉአቸው ነው ተገቢ የሆነ የለት ጉርስአቸውን ማግኛ የሚሆን ተመጣጣኝ ካሳ ይሰጣቸው ብሎ መጠየቅ ይሄን ያህል አንተን በብእሬ እናገራለሁ ወይም ችግር ሳይ አልወድም ባዩን አሰደሳች ወይም ይበላችሁ የሚያሰኝ አልመሰለኝም ።ነገር ግን ያንተን ቂመኛነት አሳየኽ እንጂ ለጥያቄው ከጠያቂው በቀር የተራ አሉባልተኞችን ድጋፍ የሚፈልግ አይደለም ።አንድ አባባል አለ መታመሙን ታመም ነገ ትድናለህ፣መታሰሩንም ታሰር ነገ ትፈታለህ ፣ወዳጅ ጠላትህን ትለይበታለህ እና ነውና ነገሩ እራስህን አወጣህበት ለማንኛውም የራሳችሁ ጉዳይ ነው ብሎ ዝም ማለት ይቻል ነበር ሌላ ቁስል ለመጨመር ባትሞክር ምን አለበት ።የታወቀ ጉዳይ እኮ ነው አሁንም በሃገሪቱ ጫንቃ ለይ የተቀመጠው አካል ያለው እኔ ብቻ ነኝ ለእናንተ የማውቀው ነው አንተና ያንተ ወፈፌ ግብዝ ደጋፊዎች ደግሞ የዛሬ መቶ አመት የተፈፀመውን ጉዳይ ሰለአስታወሳችሁ ልትሞቱ ይገባል ።አይ ኢትዮጵያ መቼ ይሆን ጉዳትህ ጉዳቴ የምንባባለው ደግሞ ሰለ ባቡር ሃዲድ ሰለ መብራት ሰለ መንገድ ማውራት አቤት አቤት ወሬ ብቻ አንገት የሌው የወሬ ስልቻ ይልቅስ አንተ ለራስህ ኢትዮጵያዊ ነኝ ባዮ አይን ሲመቱ አፍንጫ ማለትን እወቅ ወይም ተማር።ኢትዮጵያዊነት ፍቅር ነው ስብእና ማጣት አይደለም ።

  11. You are the brightest young writer Ethiopians have. I have read so many articles of yours and listened to many poems from you. None can much this one! The so called “Oromo” liberator will scrim and die by themthelves. That is why Weyane will servive for a much longer years to come. The only compatible force to challenge Weyane is that a visionary united party led by non-selfish leader. We still did not have that and Weyane will continue until then. Henok brother, I love you so much for being my inner voice.
    From Canada

  12. Those with green, yellow red color loving Ethiopian. If you call yourself Ethiopian, it means you don’t have moral.

  13. Yalefe tarikn eyanesu kemechefchef kalefew tarik memar new miyawataw yemil merih alegn.Yetignawim mengist Ethiopian bedlual silezih yalefewin kemawra na alama yelelewn kemeketel zimta yawatal.Tiru eyita nea berta.

Comments are closed.

Share