“የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሐዊና ሕጋዊ ነው”

ሰንደቅ ጋዜጣጋዜጣው ሪፖርተር

አቶ አባዱላ ገመዳ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔ

 በአዲስአበባ ዙሪያያሉትን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚተዳደሩ ከተሞችን ከአዲስአበባ ጋር በማስተሳሰር በጋራ ለማልማት የወጣውን የተቀናጀ መሪዕ ቅድ በመቃወም ሰሞኑን በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የተካሄደው ተቃውሞ ተከትሎ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። በአዳማ፣ በድሬዳዋ፣ በጅማ፣ በመደወላቡ፣ በአምቦ፣ በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲዎችና በጠቅላላው በ11 ዩኒቨርሲቲዎች የተቀጣጠለው ተቃውሞ መነሻው የአዲስአበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ትግበራ ጉዳይ ነው። ዕቅዱ “የኦሮሚያ ከተሞችን በመቁረስ ወደአዲስአበባ ለማጠቃለል የታቀደ ነው፣ በርካታ ኦሮሞዎች ከቤት ንብረታቸው ሊፈናቀሉ ነው” የሚሉ አስተያየቶች በተለይ በማህበራዊ ድረገጾች በስፋት በመሰራጨታቸው ተማሪዎች ግራ በመጋባት የወሰዱት እርምጃ እንደሆነ ይታመናል። መንግሥታዊ አካላትም በወቅቱ ሕዝቡን በማሳተፍ ስለፕላኑ (ዕቅዱ) በቂና ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን አለማድረጋቸው ለግጭቱ መነሳት አንድ ምክንያት መሆኑ እየተነገረ ነው።

ቶ አባዱላ ገመዳ
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔ

የመንግሥት ኮምኒኬሸን ጽ/ቤት ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በመደወላቡ እና በአምቦ ዩኒቨርሲቲዎች ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ 10 ሰዎች መሞታቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ እግርኳስ በመመልከት ላይ ባሉ ተማሪዎች ላይ ባልታወቁ ሰዎች በተወረወረ ፈንጂ 70 ያህል ተማሪዎች ሲቆስሉ አንድ ተማሪ መሞቱን አስታውቋል።

ጽ/ቤቱ በዚሁ የመንግሥትም አቋም በገለጸበት መግለጫው በፌዴራልና በክልል የፀጥታ ኃይሎች ትብብር ሁከቱ በተፈጠረባቸው ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት መቻሉን ጠቅሶ እስካሁን በተደረገው ማጣራት ከበስተጀርባ በመሆን ሁከቱን በማነሳሳትና በማቀነባበር ተግባር ላይ የተሰማሩት ጥቂት ፀረ ሰላም ኃይሎች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል ብሏል። ከዚሁ ግርግር በስተጀርባ የቆሙትና ከዚህ ቀደም በነበሩ ግጭቶች እጃቸውን ሲያስገቡ የነበሩ የአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ያሉ ኃይሎች በሚቆጧጠሯቸው ሚዲያዎች እየታገዙ ይህንን የተማሪዎችን ጥያቄ ለጥፋት ዓላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ መንቀሳቀሳቸውን በመግለጫው አስታውቋል።

በተፈጠረው ሁከት ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸውና ወገኖችና ቤተሰቦቻቸው መንግስት የተሰማውን ሐዘን የገለጸ ሲሆን የጥፋቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ የነበሩትን ተከታትሎ ለፍርድ ለማቅረብ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።

በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉትን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚተዳደሩ ከተሞችን ከአዲስ አበባ ጋር በማስተሳሰር በጋራ ለማልማት የወጣውን የተቀናጀ መሪ ዕቅድ ጋር ተያይዞ በተማሪዎች ስለተነሳው ጥያቄና በመንግሥት ስለተወሰደው እርምጃ የአሜሪካ ድምጽ አማርኛ ክፍል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባዔ የሆኑትን አቶ አባዱላ ገመዳን ከትላንት በስቲያ አነጋግሯል። እንደሚከተለው ቀርቧል።

ጥያቄ፡- ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ብዙ ሰዎች ሞተዋል። ሰልፉ የተካሄደው ባልታጠቁ ተማሪዎች ነው። በሮቤ፣ በአምቦ፣ በጅማ፣ በነቀምት፣ በመዳወላቡ፣ ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። መንግሥትም ራሱ ሐሙስ ዕለት ባወጣው መግለጫ እስከ 10 ሰዎች መገደላቸውን አምኗል፣ በዚህ ላይ የሚሰጡን ምላሽ ምንድነው?

አቶ አባዱላ፡- እውነት ነው፤ በኦሮሚያ ክልል ባሉት ዩኒቨርሲቲዎች የተነሳ የተቃውሞ ጥያቄ አለ። ጥያቄው የተነሳው በኦሮሚያና የአዲስ አበባ የጋራ ማስተር ፕላን በሚመለከት የተነሳ የተቃውሞ ጥያቄ ነው። በሁሉም አካባቢ ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ ፍትሃዊና ሕጋዊ ነው። እነዚህን ፍትሃዊና ሕጋዊ ጥያቄ በየአካባቢው ያሉት፣ የዩኒቨርሲቲ አስተዳደርም ሆነ በየአካባቢው ያሉት አስተዳደሮች ለመመለስ ጥረት አድርገዋል። ጉዳዩን በቅርበት ይከታተሉ የነበሩ የመንግሥት ኃላፊዎችም በጉዳዩ ሒደት ላይ ማብራሪያ ለመስጠት ሞክረዋል። ይሁንና አንዳንድ ቦታ ተማሪዎቹ ጠየቁ፣ በቂ መልስ አላገኘንም አሉ። ለበላይ አካልም ጥያቄያቸው እንዲሄድላቸው ጠየቁ፣ ግን ደግሞ ያ-ምላሽ ከመምጣቱ በፊት ነው ሰልፍ ወጡ። እንግዲህ ሰላማዊ ሰልፍ የመውጣት ሕገ-መንግሥታዊ መብት ነው። ይህ በሕገ-መንግስቱ የተቀመጠ ነው። ይሄ እንደተጠበቀ ሆኖ ሠላማዊ ሰልፍ ሲወጣ አስቀድሞ ማሳወቅ እንደሚገባ ይደነግጋል። ይሄ የሚሆነው በአካባቢው ያለ የመንግሥት አስተዳደር ሰልፍ የወጣው ሕዝብ አንድም ጉዳት እንዳይደርስበት ለመከላከል ነው። ሁለተኛ ደግሞ በሌላው ዜጋ ንብረትና ሐብት ጉዳት እንዳይደርስ ለመጠበቅ ነው። እነዚህ ሁለቱ ካልተሟሉ ችግር ሊከሰት እንደሚችል በአገራችንም በሌሎች ዴሞክራሲያዊና ባደጉ አገራትም ይታወቃል። መጀመሪያ ተማሪዎቹ ጥያቄያቸው ፍትሐዊ ሆኖ ሠላማዊ ሰልፉ ሕጉን ተከትሎ ያለማካሄድ ችግር ያጋጠመበትና ሳያሳውቁ በኃይል ስለተወጣ ከተማ ላይ በንብረት ላይ የደረሰ ኪሣራ አለ። ይሄ ወደባሰ ችግር እንዳይሰፋ የፀጥታ ኃይሎች ለመከላከል የወሰዱት እርምጃ አለ። የፀጥታ ኃይሎች አድማ ለመበተን ጢስ እና ውሃ ተጠቅመዋል። ይህን አልፎ ለሕይወት መጥፋትና ለሌሎችም ችግሮች የተከሰቱበት ሁኔታ አለ።

ጥያቄ፡- የተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሐዊና ሕጋዊ ነው ብለዋል። ሠላማዊ ሰልፍ ደግሞ በሕገመንግሥቱ የተቀመጠ መብት ነው ብለዋል። ሠላማዊ ሰልፍ ማድረግ የሚፈልግ ለመንግሥት አካላት ማሳወቅ ነው ብለዋል። ነገር ግን የታጠቁ ኃይሎች ልጆቹ ላይ ተኩስ እንደከፈቱና በዚህም ምክንያት የማይተካ ሕይወት እንደተሰዋ ነው የሚነገረው። ጥያቄያቸው ትክክለኛ እስከሆነ ድረስ ለዚህ ግድያ ምን መልስ ይሰጡናል?

አቶ አባዱላ፡- በመጀመሪያ ይህ መምጣት የሌለበት ነው። ሕይወትም ንብረትም መጥፋት በጣም የሚያሳዝን ነው። መንግሥትም ሐዘኑን ገልጿል። እኔም በቦታው ደርሼ አይቻለሁ፣ አዝኛለሁ። መሆን የማይገባው ጉዳይ ነው። በቦታው በኃይል ለመመለስ ወይም በጥይት ለመመለስ አይደለም ዝግጅቱ። አንድ ምሳሌ ለማንሳት ልሞክር። የአድማ በታኝ የፌዴራል ፖሊስ በቦታው የደረሰው ብዙ ተሽከርካሪዎችና ንብረት ከተቃጠለ በኋላ ማታ ላይ ነው። ማምሻውን 11 ሰዓትና ከዚያ በኋላ ነው የደረሰው። ቃጠሎው እየሰፋ ሲሄድ ነው፣ የክልሉ መንግሥት ይሄ ነገር የከፋ ሕይወት ሊያጠፋ ስለሚችል የሚቆጣጠር ኃይል መግባት አለበት ብሎ ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ አቅርቧል።

ጥያቄ፡- ተማሪዎቹ መኪናዎችን ሲያቃጥሉ ነበር ነው የሚሉኝ?

አቶ አባዱላ፡- እንግዲህ በአምቦ ከተማ ቀደም ሲል ሠላማዊ ሰልፍ ሲወጣ ማሳወቅ ይገባል ያልነው ባመፈፀሙ፣ ቅድመ ዝግጅት ባለመደረጉ፣ ተማሪዎቹ በግቢያቸው ውስጥ የመጨረሻውን ዝግጅት አድርገው የወጡ ቢሆንም፤ ከውጪ ግን ተማሪዎችን የተቀላቀለ ብዙ ኃይል አለ። የዘረፋ ፍላጎት ያለው፣ የማውደም ፍላጎት ያለው ኃይል ተቀላቅሏል። ከተቀላቀለ በኋላ ለምሳሌ በአምቦ አበበች መታፈሪያ የሚባል ሆቴል ተዘርፏል። ሆቴል ውስጥ የነበሩት የቱሪሰት መኪናዎች ተቃጥለዋል። እንደዚህም የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ተቃጥሏል። የምዕራብ ሸዋ ፍ/ቤት ዶክመንቶችና ፍ/ቤቱ ራሱ ተቃጥሏል። እንዲያውም ተማሪዎች ናቸው ለማለት የማያስችለው ከጥበቃ ኃይሎች ትጥቅ በመቀበል ወደተኩስ የተገባበት ሁኔታ ነበር። ይሄ ነገር ሄዶ ሄዶ ብዙ ሕይወት፣ ብዙ ንብረት እንደሚያወድም ይታወቃል። መንግሥት ይህን የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት።

6 Comments

  1. Before they said there are peoples behind the students with hidden agenda. Now they said the students have legitimate right.

  2. If it is a peaceful protest why do they have to burn cars …..hotels and aslong as in one country the government can demarcated any reagin in what ever way it wont.

    • @defaru
      Please work on your language or write it in English. I couldn’t get what you wanted to convey in this statement.

  3. no crime is reason out in both tplf bucher and oromo narrowist olf members using poor ,innocent students let GOD rest their soul in heaven and peace and prosperity for that misearable land of ethiopia and its people death for bucherism and narrowism .

  4. Obviouslly woyane is ” wonbede, and Mafiya ” so what do we expect from the government took power by firearms, TPLF did not come to bring to Ethiopia for peace, democracy and prosperity contrary to that for people’s and our country’s disintegration. We need to unite for the fall of TPLF. TPLF is a massacre.

Comments are closed.

zone 9999
Previous Story

የማለዳ ወግ …ዞን 9 ኞችን አደግፋለሁ !አግብቷቸው ስለጦመሩ መብታቸው መገፈፍ የለበትም (ነቢዩ ሲራክ)

Next Story

ትዴኢ አንድነትና መኢአድን ለመዋሐድ እየጣረ ነው ትዴኢ አንድነትና መኢአድን ለመዋሐድ እየጣረ ነው

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር

ፋኖ ምሽጉን ደረመሰው ድል ተሰማ | ” ስልጣን እለቃለሁ ” ፕረዚዳንቷ | ህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ | “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ

-966+9-የኦህዴድ ድብቅ ስብሰባ በአዲስ አበባ “ተመስገንን በመዳፌ ስር አስገብቼዋለሁ” አብይ – ስልኩ ተጠለፈ “እኛ የምን’ዘጋጀው ለፋኖ ሳይሆን ለኤር-ትራ ነው” አበባው|”በጊዜ ቦታ አዘጋጁልኝ” አረጋ

አንድ በኢኮኖሚና በሌሎች ነገሮች ወደ ኋላ የቀረች አገር አንድን ኃያል መንግስት በመተማመንና ጥገኛ በመሆን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማምጣትና የተሟላ ነፃነትን መቀዳጀት ትችላለች ወይ?

ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር) ሰኔ 4፣ 2016 (ሰኔ 11፣ 2024)   በዚህ አርዕስት ላይ እንድጽፍ የገፋፋኝ ዋናው ምክንያት ሰሞኑኑ ዶ/ር ዮናስ ብሩ የቻይንንም ሆነ የቬትናምን በኢኮኖሚ ማደግ አስመልክቶ ሁለቱ አገሮች እዚህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ሊደርሱ የቻሉት ከአሜሪካ ጋር

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት

ፋኖ አንድ ሌሊት አያሳድረንም” የአማራ ብልፅግናየኢሳያስ ግዙፍ ጦር ወደ ወልቃይት አብይና ዳንኤል ክብረት ጉድ አሰሙ-|ጀነራሉ በቁ*ጣ ተናገሩ-‘ህዝቡ ጉድ ሰራን’-|“ብልፅግናን ራ*ቁቱን አስቀርተነዋል”-|ታዳሚው ባለስልጣናቱን አፋጠጠ
Go toTop