ከሮበሌ አባቢያ፣ 5/5/2014
የአንድነት ፓርቲ ያቀረበውን እጅግ በጣም ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ፣ አይኖቼ እምባ እያቀረሩ፣ ልቤን ደስታ ፈንቅሏት ነው እኔም እንደ ሰልፈኞቹ መፈክር እያሰማሁ ከናት ሀገሬ ውጪ ከምኖርበት ከተማ በቴሌቪዥን ከመኖሪያ ቤቴ ተቀምጬ ነበር የተመለከትኩትት።
እሰይ! ድል ለወጣቱ ትውልድ!!! በማለት ይህቺን መጣጥፍ ለመክተብ ተነሳሳሁ። ከዚህ ቀደም ደጋግሜ እንደጻፍኩት ግትር ኢትዮጵያዊ ነኝ። ያ እንዳለ ሆኖ፣ አንድነት ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ የተገኙት ታዳሚዎች በኦሮሞ ተማሪዎችና በደጋፊዎቻቸው ላይ የደረሰውን ፋሺስታዊ ጭፍጨፋ አበክረው በማውገዘቸው በወገኖቼ ኢትዮጵያን ኮርቻለሁ፤ አድሮብኝ ከነበረው ጥልቅ ሀዘንም ተፅናንቻለሁ፤ ለሰብአዊ መብት ዓላማ ስኬት ለመታገል ቃልኪዳኔን አድሻለሁ።
ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ—