ሰላማዊ ትግላችንን ከፍ አድርገን እንቀጥላለን!!!

ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ ጊዚያት በሐገራችን የሚፈፀሙ የተለያዩ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶችና ህገ ወጥ ድርጊቶች ኢንዲቆሙ ለመንግስት የተለያዩ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቢቆይም ከመንግስት የተሰጡት ምላሾች ግን ጥያቄዎቻችንን ማንቋሸሽና ማጣጣል ወይም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ማለፍ ሆኖ ቆይቷል፡፡

ፓርቲያችን ጥያቄዎችን የሚያቀርበው መንግስት አፋጣኝ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰድባቸው ቢሆንም ችግሮቹ እስካሁንም ሳይፈቱ አንዳንዶቹም እየተባባሱ ቀጥለዋል፡፡ በመሆኑም ፓርቲያችን ከዚህ በፊት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጥሪ ለመንግስት አቅርቦ መልስ ከተነፈጋቸው መካከል፤

1ኛ. ለፍትህና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና
አባላትን በአሸባሪነት ስም ማሰርና ማሰቃየትን አጥብቀን የምንቃወም መሆኑንና እስረኞችንም እንዲፈታ የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን ምንም መልስ ያልተገኘ በመሆኑ፤
2ኛ. የዜጎችን ሰብዓዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶችን በመጣስ ለዘመናት ከኖሩበት ቦታ ኢሰብዓዊ በሆነ ድርጊት በታጠቁ ኃይሎች እንዲፈናቀሉ ማድረግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመሆኑ የድርጊቱ ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና የተፈናቀሉት ዜጎችም በአስቸኳይ ወደየመኖሪያቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ በመንግስትም ሆነ በግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግላቸው የጠየቅን ቢሆንም አሁንም ገና የሚፈናቀሉ ዜጎችን ስም ዝርዝር በየማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ ተለጥፎ እያየን በመሆኑ፤
3ኛ. መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ አይግባ፣ የእምነት ስርዓታችንና የሃይማኖት መሪዎቻችንን እምነታችን
በሚፈቅደው ብቻ እናከናውን ያሉ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን በአሸባሪነት ወንጀል በመክሰስ በእስር እንዲማቅቁና ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጣስ መደረጉ እንዲቆምና ያነሷቸውም የእምነት ነፃነት ጥያቄዎቻቸው እንዲከበር የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን የተገኘ መልስ ባለመኖሩ፤
4ኛ. መንግስት የኑሮ ዉድነትን፣ የሥራ አጥነትንና በሙስና የተዘፈቁ የመንግስት ሌቦችን የሚቆጣጠርባቸውን
መንገዶችና ፖሊሲዎች በማዉጣት ሐገራችንን ከቀውስና ዜጎችንም ከሰቆቃ እንዲያወጣ በተደጋጋሚ ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ሰሚ አጥተው በመቆየታቸው እነዚህ ችግሮች እንዲፈቱ አሁንም አጥብቀን የምንጠይቅ መሆኑ እና ሌሎችም፤

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቤተ-መንግስቱ ታምሷል! | 4 ኪሎ ገብቶ የሰረቀው ሌባ

በመንግስት ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ መፈለግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሰረት ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት ድምፃችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ከላይ ያነሳናቸውና ሌሎችም ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ሰማያዊ ፓርቲ ለመጠየቅ ወስኗል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ጥያቄዎች እንዲመለሱ የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበራትና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእነዚህ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ. ም
አዲስ አበባ

3 Comments

  1. This is what a responsible party supposed to do for the last couple decades.
    Tank you Semayawwey gud

  2. Ayzon Semayawiwochu……Hulachnim kegonachuk nen…
    Zeregnaw yeweyane mengist bechkun Ethiopiayawyan tigil Ygeresesal!!
    Mot lemeles Zenawina Achafariwochu

  3. where are these old ….kalemenor yemayshalu—medrek and andnet guys the time? I think this is a critical lesson for them too. This is what a true opposition party is supposed to do. No violence, but press and expose the dictators in any form such as the AU assembly. Where is the so called Dr Negaso now, Off course i totally gave up of the prof…man neber…Meera. He has to retire like that Prof Beyene…norewem altekemunem…rather they are surving the government to systematically eat us. that is is why young has to join the current politices of Ethiopia. Without our participation, we can’t move anywhere, but the old guards has to step by step leave the leadership to the younger generation, so that the struggle witll get momentum. But we need the seniors as they have lot of experiences. Well done Semayawi. But be sure that you can’t get the permission to hold on the rally, but it is our constitutional right! Stick to that! Never forgive once you started the right way of struggling! We are fade up of starting and quitting! Be informed of that!! In case you will be trap yourself to the usual, ye enate mekenet adenakefegn….you better sleep as these in medker do…go and site in your office, simply chat…go out take your makiato…and …

Comments are closed.

Share