ጃዋር ነበር የሚለው፣ አሁን ግን የኦሮሞ ተማሪዎችም ደገሙት – ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት (ናኦሚን በጋሻዉ)

ናኦሚን በጋሻዉ
naomibegashaw@gmail.com

 

በዉጭ አገር የሚኖሩ የኦሮሞ ብሄረተኖች፣ በዶር መራር ጉዲና የሚመራዉን ኦፌኮ ጨምሮ በርካታ የኦሮሞ ድርጅቶች እና አንዳንድ የኦሮሞ ሜዲያዎች ያቀረቡትን ጥሪ በመቀበልና አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም ፣ የኦሮሞ ተማሪዎች በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ተቃዉሞ ማሰማታቸው በስፋት ተዘግቧል።

መቅደም ያለበትን ላስቀድም። ተማሪዎቹ ጥያቄዎቻቸዉን ያነሱት ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ነው። በፌደራል ፖሊስ የደረሰባቸው ድብደባ ልብን የሚያቆስል ከመሆኑም ባሻገር  መወገዝ አለበት። በዚህ ጉድያ ላይ፣  ሌላ አቋም ይዞ የሚከርከር ካለ፣ ለሰብአዊነት ደንታ የሌለው ሰዉ ነው ብዬ ከማለፍ ዉጭ ብዙ የምለው አይኖረኝም።

የኦሮሞ ድርጅቶች ሆነ ተማሪዎች አዲሱን ማስተር ፕላን የተቃወሙበት ሁለት ጥንድ ምክንያቶች ሊኖሯቸው ይችላል ብዬ አስባለሁ። አንደኛው፣ በልማት ስም የኦሮሞ ገበሬዎች አግባብ በሌለው መልኩ መፈናቀል የለባቸውም የሚል ነው።

በልማት ስም፣ ወይንም የአንድ ቋንቋ ተናገሪ በመሆናቸው ምክንያት ሰላማዊ ዜጎችን የማፈናቀሉ ተግባር፣  ላለፉት ሃያ አመታት በአገራችን በስፋት ሲታይ የነበረ አሳዛኝ ክስተት ነው። እነዚህ የኦሮሞ ድርጅቶች፣  የኦሮሞ ገበሬዎች ለምን ተፈናቀሉ በሚል አሁን እየተከራከሩና እየጻፉ እንዳሉት፣ በኦሮሚያ ዉስጥ «ይሄ አገራችሁ አይደለም እየተባሉ» ዜጎች ሲባረሩና የዘር ማጽዳት ወንጀል ሲፈጸምባቸው፣ በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች በልማት ስም ቤቶች ሲፈርሱ»  ለምን ብለው ድምጻቸውን አሰምተውን ቢሆን ኖሮ ለነርሱ የበለጠ ከበሬታ ይኖረን ነበር።

የኦሮሞ ገበሬዎች በኦሮሚያ ዉስጥ በጂማ፣ በኢሊባቡር፣ በወለጋና  በመሳሰሉት   በኦሮሚያ ክልል መንግስት ተፈናቅለው መሬታቸው ለባለ ሃብቶች የተሰጠበት ሁኔታ  እንዳለ እናውቃለን። ገበሬዎቹን ሆነ ሌሎች ዜጎችን የማፈናቀል ተግባር፣ ከኦሮሞነት ጋር፣ ወይንም በአዲስ አበባ ስር ከመሆን ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። ዜጎችን በቅያቸው የማፈናቀሉ ጉዳይ መንግስት ከሚከተለው የመሬት ፖሊሲ ጋር የተገናኘ ነው። መሬት የመንግስት እስከሆነ ድረስ በኦሮሚያ ክልል አስተዳደሪ ትእዛዝ ይሁን፣ በአዲስ አበባ ከንቲባ ትእዛዝ ፣ ዜጎች በግፍ ፣ በቂ ካሳ ሳይከፈላቸው እንዳይፈናቀሉ የሚገታ ምንም ነገር የለም። ስለዚህ የሚበጀው ፣ የኦሮሞ ገበሬዎችን ጨምሮ ማንኛዉም ዜጋ የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ መታገሉ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለወዳጄ....

ሁለተኛው ተቃዉሞ የተሰማበት ምክንያት፣  በቀጥታ ተቃዉሞ እያሰሙ ካሉ የኦሮሞ ተማሪዎች ጋር በሃሳብ የሚያላትመኝ ጉዳይ ሆኖ ነው ያገኝሁት። «ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት። ፊንፊኔ የኦሮሞዎች ናት»  የሚለው መፈክራቸው ፣ እጅግ በጣም መርዛማ ከመሆኑም የተነሳ አገሪቷን ወደ ከፋ የዘር ጦርነት የመዉሰድ አቅም ያለው ነው። ይህ አይነቱ ፖለቲካ ከዉጭ በነጃዋር ሞሃመድ እየተጠነሰሰ ሲሠራበት የነበረና፣ በየድህረ ገጹና ሶሻል ሜዲያዉ የተረጨ  ሲሆን  ይኸው ዉጤቱም በመጠኑም ቢሆን በአንዳንድ የኦሮሞ ተማሪዎች ሲንጸባረቅ ለማየት እየቻልን ነው። ይህ መርዝ በአስቸኳይ እንዲመክን ካልተደረገ፣ በኦሮሞዎች እና በአማራዎች፣ በኦሮሞዎች እና በጉሙዞች፣ በኦሮሞዎችና በሶማሌዎች፣ በኦሮሞዎች እና ከፊቾዎች …መካከል የዘር ግጭት በስፋት ሊሰራጭ ይችላል። ይህም ደግሞ በዋናነት የኦሮሞ ማህበረሰብን ከሌላው ጋር በማጋጀት ፣ በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያመጣል።

ይህ አይነቱን ፖለቲካ ፊት ለፊት መጋፈጥና መቃወም ያስፈልጋል። ከአሁን ለአሁን የተቃወሙት አገዛዙን  ነው በሚል፣ ዝም ተብለው ሊታለፉ አይገባም።

«ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ብቻ ናት። ኦሮሚያ እየተወረረች ነው ! ፊንፊኔ የኦሮሚያ ናት…» የመሳሰሉትን  ከፋፋይና ጠባብ መፈክሮች ሲያሰሙ የሰማናቸው እነዚህ የኦሮሞ ተማሪዎችና በዉጭ ያሉ የኦሮሞ አክራሪዎች፣ ከገበሬዉ የሰብአዊ መብት ይልቅ፣  ከሃያ አመታት በፊት በኦነግ እና በሕወሃት በኃይል በሕዝቡ ላይ የተጫነዉን የኦሮሚያ ካርታ፣ መለወጡ ያሳሰባቸው ነው የሚመስለኝ። ከአሁን ለአሁን አዲስ አበባ ከሰፋች፣ ማስተር ፕላኑ ከጸደቀ፣ ኦሮሚያ ለሁለት ትከፈላለች የሚል ፍርሃት ሳይገባባቸው እንዳልቀረ ነው። ምናልባትም ኦሮሚያ ሬፑብሊክን የመመስረት እድላችንን ያጨልምብናል የሚልም ስጋት ሊኖራቸውም ይችላል።

ነገር ግን አንድ የዘነጉት ነገር አለ። አብዛኞቻችን ዝም ስንልላቸው፣ እነርሱ የሚጩኹት ጩኸት የበለጠ ተሰሚነት ያገኝ እየመሰላቸው ነው። አዲስ አበባ ዋና ከተማችን ናት። ማስተር ፕላን ኖረም አልኖረም አዲስ አበባ ትሰፋለች። እስከአሁንም የሰፋችው ማስተር ፕላን ኖሮ አይደለም። አዲስ አበባ ኦሮሞዉ፣ ሱማሌዉ፣ ትግሬው፣ አማራዉም ፣ ድብልቁም ..ሁሉም ያለ ፍርሃትና ያለ ሰቀቀን የሚኖሩባት ከተማ ናት። አዲስ አበባ በኦሮሚያ እንዳሉሌሎች ከተሞች፣ ኦሮሞዎች ብቻ የሚመረጡበትና የሚመርጡባት፣ ሌሎች በሰቀቀን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የሚኖሩባት፣ አፓርታይድ የሰፈነባት ከተማ አይደለችም። አዲስ አበባ የሁሉም ናት። ሕዝቡ ከሁሉም አቅጣጫ በአዲስ አበባ መኖር ይፈልጋል። በዘረኝነት አጥር መታጠር አይፈልግም። መሻሻል ይፈልጋል። ወደ አዲስ አበባም ይጎርፋል። በዚህም ምክንያት አዲስ አበባ አደገች። የሕዝቧም ቁጥር ጨመረ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጎሕ መንፈስ (በየነ ሞገስ)

በቅርብ ጊዜ ዉጥ ናዝሬት እና አዲስ አበባ ፣ አዲስ አበባ እና ደብረ ብርሃን፣ አዲስ አበባና ወሊሶ፣ አዲስ አበባና አምቦ ይገጥማሉ ተቦ ይጠበቃል። ከአዲስ አበባ ናዝሬት ያለው ሰፊ መንገድ ተጠናቋል። በኢኮኖሚና በሕዝብ ለሕዝብ ትስስር አኳያ ካየነው ፣ አዲስ አበባ እና አዳማ ገጥመዋል ማለት ይቻላል።  አዲስ አበአ እየኖሩ ናዝሬት የሚሰሩ፣ ናዝሬት እየኖሩ አዲስ አበባ የሚሰሩ ቁጥራቸው እየበዛ ነው። በቦሌ ያለው ኤርፖርት ብቃት ስለሌለው ፣ አዲስ አይሮፕላን ማረፊያ በቴሲ ከተማ ሊሰራ ነው። ቴሲ፣ ሰበታን አልፎ በአዲስ አበባ እና በወሊሶ መሃከል ያለች ናት። ኤርፖርቱ ሲጠናቀቅ ፣ የዚያኑ ያህል የኢኮኖሚክ እንቅስቃሴውም ያድጋል። አካባቢዉ ከአዲስ አበባ ጋር ትስስሩ የበለጠ እየጨመረ ይመጣል። ይሄም ደግሞ የሆነው በማስተር ፕላኑ ምክንያት አይደለም። የሕዝብ እንቅስቃሴ ነው። የሕዝብ እንቅስቃሴን ደግሞ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንደ በርሊን ግንብ አይነት ፣ ካልተሰራ ማቆም አይቻልም። እነርሱ የሕዝብን እድገት ማፈን፣ ህዝቡን በዘር አጥር አሸገው ማስቀመጥ ቢፈልጉም፣ ህዝቡ ግን አይሰማቸው። ተሸናፊ የሚሆኑት እነርሱ እርሳቸው ናቸው። (በነገራችን ላይ የዉሸት አፈታሪክ ላይ ተመርኩዘው የአኖሌን የጥላቻ ሃዉልት የገነቡ፣ ነገ የአዲስ አበባን ግንብ እንገባ ቢሉ የሚያስደንቅ አይሆንም)

እንግዲህ «አዲስ አበባ ለምን አደገች፣ ተወረርን» የሚለውን ጠባብ አመለካከት መያዝ ሳይሆን  የሚያዋጣዉ፣ «አዲስ አበባ በምታድግበት ጊዜ ሁሉንም በጠቀመና ፍትሃዊነት ባለዉ መልኩ ይሁን» በሎ መከራከሩ ነው። በተለይም ከላይ እንደገለጽኩት መሬት የመንግስት ነው በሚል ዜጎችን በኃይል የማፈናቀል  ተግባር እንዲቆም አስፈላጊዉን ግፊትና ጫና ማሳደሩ በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። ይህ የዘር ወይንም የጎሳ ጉዳይ ሳይሆን የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እያመመን መጣ! - በቦቆቅሳ ሉባክ

የኦሮሞ ተማሪዎችንም ሆነ ድርጅቶች የኦሮሚያ የዘር ጠባብ ጥያቄዎችን ማንገብ አቁመው፣ የሰብአዊ መብት ጥያቄዎች ያንግቡ እላለሁ። ያኔ እኛም ከጎናቸው እንቆማለን። አሁን ግን «ኦሮሚያ ለኦሮሞዎች» ካሉ መንገዱን ጨርቅ ያርግላቸው። እነርሱን ከማንም በላይ  የምንታገልና የምንቃወም እንጂ የምንደግፍ አንሆንም። አዲስ አበባ የሁላችንም ናት። ቡራዪ፣ ሰበታ፣ ለገጣፎ፣ አምቦ፣ ወለጋ፣ ኢሊባቡር የሁላችንም ናቸው።

 

 

23 Comments

  1. Full of nonsense . If u have the attitude”mengedun cherk yargelachew” u dont need to write this article and act as a syphtasier in ur first pharagraph. I dont agree oromia for oromos stuff but I agree with the terriotorial integrity of the region. What the hell u talking about? Aren’t we living in the fedaralism era of Ethiopia? For your arguinent to work we have tove a centralized leadership with no regions and thats not how it is in Ethiopia today sadly. So when it is the Oromis that raise the question dont raise your Ethiopianism card and label them as racist. U have the right no to support them or talk about it but please leave them alone they already have enougn from current regime. What? We were shouting about the eviction of 20 farmers from around ambo before months than we r talking noe for millions of poor farmers being evicted from their land. Tell me how those 29 farmers were more human for you to cry for them and not these millions.I know the answer but eanted to hear from you. Sorry for misspelling ir whatsoever im using ma phone.

  2. ጃዋር ብቻ የሚል ከመሰለህ ተሳስተሀል ድፍን የኦሮሞ ህዝብ አንተ እንዳልከው ሳይሆን ኦሮሚያ የኦሮሞ ብቻ ናት ሳይሆን የሚለው ኦሮሚያ የኦሮሞ ናት ነው ያንን ደግሞ ልክ ጎንደር የጎንደሬዎች መቀሌ የትግሬዎች ወዘተ እንደሆነው ማለት ነው። ወዳጄ ኦሮሞ ያቀጣጠለው ትግል አንተ እንዳሰብከው ያንተን እገዛ አይፈልግም ብታግዝ ለኦሮሞ ብለህ ሳይሆን ነጻነትህን ፈልገህ መሆን አለበት። የኦሮሞን ትግል ኦሮሞ ይወጣዋል፣ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል። ግን የታሪክ ተወቃሽ እንዳትሆኑ የበኩላችሁን ድርሻ ብትወጡ ለምትመኙት አብሮነት ይጠቅም ይሆናል። ካልሆነ ነቀምት ላይ እያደረጉ ያሉትን ፊንፊኔ ላይ የማደግሙበት ምንም ምክያት አይኖርም ።
    ዘሀበሻ ፌር ብትሆኑ እንናተንም ከወቀሳ ያድናችኀል ሃሳብን በሃሳብ ማሸነፍ ሲሳናችሁና የምትመልሱትን ስታጡ ሰውን ማፈን ይህ የምትመኙዋትን ኢትዮጵያ ለመፍጠር ያዳግታችኃል የሚላክላችሁን ፖስት (ፓብሊሽ) አድርጉ

    • @Obsa
      Just trash talk, what u gone do.To start ethnic cleansing like Rwanda.You better spend your time for good cause than harming other, U retarded.

  3. May be the author is from ‘One religion, One country, One language’ oppressive group. Any ways:
    1. Burayu, Sabata,… is Oromia does not mean Only Oromos live or allowed to live in. Oromos are by far advanced than you think. The Oromos who are currently protesting the assimilation project are those who already accepted federalism and co-existence. They have been and are living with the people in and out of the region. They themselves also live in other regions and also families with other people especially with the southern people the author mentioned above. The question of Oromos is justice and transparency. Sabata is Oromia, Burayu is Oromia means it is Oromia region but does not mean Only Oromos live or allowed to live in.It is region freed out of the past oppressors(may be like the amharic author of this article). Do not misdirect the question, It is clear for any rational people of Ethiopia that the region is Oromia region agreed up on in the federal system in which every society enjoy their culture, identity, and language while enjoying co-existence and the beauty of diversity. The past oppressor of one country, one religion, one language does not accept federalism and dreaming the re-happening of past tragedies which was very poisonous and buried for ever by the cooperative arm of nations and nationalities of the country.
    2. The reason why Oromo is for front on this issue is clear, majority victim of this plan is Oromos, but any neighbor who accept democracy, justice, and transparency is welcomed to support the question. Oromo knows addisabeba is common on the base of federalism. I think no one can be fooled with the ethenic cleansing plan by the politically siding government and the articles of past oppressor! It should be understood that the question is respect the federal constitution and rule of law.

    • Where have you been when farmers are displaced in large areas in OROMIA region.are you allergiic to ADDIS Ababa only.By the way who gave you a right to decide who live where, I am Ethiopian I can live where ever i want.It is not your good will,damn.

  4. Great Article Naomi.

    Let me tell you aboput what surprises most with regard to oromos living in the USA. They came as “political” refeugees and subsequently settled here. I can say that most of them, either through hard work or thanks to the American tax payer, live comofortably, being part of the melting pot. Although they are differnet from the local population in many aspects including sklin color, language, psychological make up etc, no body dares to say that they do not belong here. Now, these same people, under the cover of computer creeen, say “oromia for oromos”. “Non oromos out from oromo land” etc. Is it not double standard? This question surprises me a lot and would be glad if one explains me in a civilized manner.

    Hager

  5. Few points:
    1. The right of any farmer should be respected.
    2. EPRDF should have discussion with the farmers and OPDO representatives
    3. If the videos of the protest posted on internet are the correct footage, slogans of the students are total different , in this case, EPRDF will definitely get support from non oromos. A person from Hawassa, Arba Minch, Jiiga, Gondar, Mekele, Asosa, Semira,,, has the same right to live, own property, participate in the capital’s policies as a person from Nekemte, Ambo, Roba, Negele Boran. It has to be remember that Oromos themselves are settlers.

  6. ስሚኝ ወ/ሮ ኖኣሚ …. በመጀመሪያ እንኳን ደስ አለሸ! ….. እጅግ በጣም የምትጠያቸውን የኦሮሞ ወጣቶችን ግዳይ … የአጎትሽ ልጅ የትግሬ አጋዚ ሰለጣለልሽ! …. ሆኖም አንቺም ሆንሽ የትግሬው አጋዚ ፈሪ አውሬ እንጂ ጀግና አይደላችሁም፡፡ ጀግና እላችሁ የነበረው እነኝህን እጃቸው ከብዕርና ከወረቀት ውጪ ሽመል እንኳ ይዞ የማያውቀውን ምስኪን ወጣት ተማሪዎች ሳይሆን የሰለጠኑና የታጠቁ ወታደሮችን ገድላችሁ ቢሆን ነበር፡፡ ለነገሩ…..ይህን አይነቱን ቁም ነገር በታሪካችሁ ሰርታቸሁ አታውቁም፡፡ ያልታጠቀን ምስኪን መፍጀት ግን አዲሳችሁ አይደለም፡፡ ደጋግማችሁ ያልታጠቀን ምስኪን ግዳይ በመጣል የማይረሳ ታሪክ ሰርታችኋል፡፡ የአኖሌ ኃውልትም የዚሁ ዓይነት ታሪክ ማስታወሻ ነው እንጂ አንቺና መሰሎችሽ እንደምትሉት ፈጠራ አይደለም፡፡ ትላንት…. በምኒልክ ሰራዊት (በራስ ዳርጌ ፊታውራሪነት) አኖሌ ላይ የተፈጁትም ሆነ ….. ዛሬ በግፍ በአውሬዎቹ የትግሬ አጋዚዎችሽ ጥይት የወደቁት …. ለናንተ (ላንቺና ለመሰሎችሽ) ጀግኖቻችሁ የጣሉላችሁ የጠላት ግዳዮች ናቸው…. ወይም….ተስፋዬ ገ/አብ በምናቡ የፈጠራቸው ቀልዶች ናቸው…. ለኛ ግን ሠማዕታቶቻችን ናቸው፡፡ ታጋይ ይወድቃል …. ትግሉ ግን ይቀጥላል!!! አሁንም ጦርነቱ አልቆመም! አይቆምም፡፡ ማን ያውቃል ….አንድ ቀን…..ዛሬ ያንቺ አጋዚ አውሬዎች የታጠቁትንና የጀገኑበትን ብረት…. እኛም እንታጠቅና በጦር ሜዳ ዋን-ቱ-ዋን እንጋጠም ይሆናል …ያኔ ማን ጀግና …ማን የሴት ልጅ…ማን የወንድ ልጅ…. እንደሆነ ታያለሽ!!!
    አሁንም ይለይልሽ….. አዎ! ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት! ….. የፊንፊኔ ዙሪያ ወረዳ ብቻ ሳይሆን…..ፊንፊኔም ጭምር የኦሮሞ ህዝብ እንብርት ናት!!!! ያኔ በሃገር ማቅናቱ ዘመን ….አያቶችሽ የየካን…..የጉለሌንና…. የገላንን ኦሮሞዎች በግፍ ጨፍጭፈውና ከመሬታቸው አፈናቅለው… ወታደሮቻቸውን በፊንፊኔ ካሰፈሩ በኋላ…አዲስ-አበባ የሚል የዳቦ ስም እንዳወጡለት ረሳሽው ወይስ አታውቂውም??…እንግዲህ እውነታው እንደዚያ ነው፡፡ ዋጭው!…..ቢመርሽም…. በበደሌ … በሜታ …. በጊዮርጊስ …..ወይም በሄንኬን አወራርጅው!!
    በዚህ አጋጣሚ…..አንችም ሆንሽ መሰሎችሽ እንድትረዱልን የምንፈልገው…..እኛ ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት ስንል…..ሌሎች ህዝቦች ኦሮሚያ ውስጥ መኖር አይችሉም ማለታችን አይደለም!…እመኚኝ!…(ካለመንሽም የራስሽ ጉዳይ)…..ሌሎች ህዝቦች ኦሮሚያ ውስጥ መኖር አይችሉም ማለታችን አይደለም!!! በኦሮሚያ ውስጥ አማራም …..ትግሬም…..ሌሎችም ህዝቦች ከዚህ በፊትም ይኖሩ ነበር …. ወደፊትም ይኖራሉ!! የኦሮሞን ህዝብ አክብረው …በእኩልነት …በመረዳዳት ….በጋራ መኖር እስከቻሉ ድረስ ! …. አይደለም የኢትዮጵያ ህዝቦች … ለምን ኤርትራዊ …… ወይም ከዩሮፕ …ወይም ከዩ.ኤስ. አይሆንም…ኦሮሚያ ውስጥ መጥቶ መኖር… ቤት መስራት…. ፋብሪካ መትከል…ኃብት ማካበት ይችላል! … አሁንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡ እኛ በዚህ በኩል ችግር የለብንም፡፡ ከዚህ በፊትም ከጥንት ጀምሮም ቢሆን አባቶቻች ከበዳችሁን ብለው አያውቁም፡፡ እነርሱን ብሎ…እነርሱን አምኖ ለመጣ ምስኪን እንግዳ…ባህሉን ፣ሃይማኖቱን፣ቋንቋውን ሳያንቋሽሹበት …በማክበር … መሬታቸውን አካፍለው በሰላም አብረው ኖረዋል…አሁንም እየኖሩ ነው፡፡
    አሁን ትልቁ ጥያቄ….ከዚህ በፊት ያንቺ አያቶች በሃገር ማቅናት ስም መጥተው… ኃብትና መሬት በመቆጣጠር (ሲመቻቸው በጉልበት…ካልሆነም በማጭበርበር ለቤተ-ክርስቲያን…ለቀዳሽ በቅላድ….ላስቀዳሽ በቅላድ እያሉ)….አነሱ ባለፀጋ …እኛ የበይ-ተመልካች የተደረግንበት ስርዓት መቼም አይፈጠርም!!!
    አይደለም ትላንት አጎቶችሽ አጋዚዎች ወደ አምቦ ይዘው የመጡትን ስናይፐር ጠብመንጃ…..ቢ.ኤም. ሮኬትና ጀት ይዛችሁ ብትመጡም…. በጥርሳችንም ቢሆን እየታገልን …እንደዛሬዎቹ ታጋዮቻችን …. ከነክብራችን እንወድቃለን እንጂ…ዳግም በቁም አንሞትም!
    ከላይ እንዳልኩት … አሁንም ኦሮሚያም ሆነ ፊንፊኔ የኦሮሞዎች ናት!!! በእኩል አብረን ተባብረን…ተከባብረን ለመኖር ኦሮሚያ ለሁላችንም ትበቃለች…. ግን በብልጣብልጥነት …ትላንት በሃገር ማቅናት ስም…. ዛሬ ደግሞ በማስተር ፕላን ስም መሬትና ኃብት ለመቀማትና ተጨማሪ የትግራይ ግዛት በፊንፊኔ ዙሪያ ለመመስረት የምታደርጉትን ሩጫ በቁማችን እያለን አንቀበልም!…. ህርምሽን አውጭ…አንቀበልም፡፡
    እነ ገብረዋህድን የመሳሰሉ ብዙ ሺህ የትግሬ አጎቶችሽ …. ላለፉት አስር አመታት በፊንፊኔ ዙሪያ የሚኖረውን ምስኪኑን የኦሮሞ አርሶአደር ወገናችንን በጥቂት ገንዘብ አያታለሉ …. እያንዳንዳቸው እሰከ 15 ቪላ-ቤትና ፋብሪካ ሲገነቡ እኮ … ሳናውቅ ቀርተን አልነበረም ዝም ብለን በትዕግስት ስንከታተል የነበረው…. ካገራችሁ ትግራይ ኦሮሚያ ለመኖርና ለመስራት ይሻለናል ብለው ሊሆን ይችላልና …. አዚህ መጥተው ይሄን ግንባታ የሚገነቡት(ሃብቱን ከየት እንዳገኙት ግራ ቢገባንም)፤…ኦሮሚያን ህዝቧን እስካከበሩና ተሰማምተው በጋራ ለመኖር ወደው እስከመጡ ድረስ…ኢትዮጵያዊ ናቸውና መብታቸው ነው…… በማለት ነው!….. እንጂ…..እንዲህ እንደ ዛሬ ቀስ ብለው እንደ ሸለምጥማጥ እየተሽሎከለኩ….በተቀናጀ ማስተር ፕላን ስም …. የኦሮሚያ መሬት ላይ ሌላ የትግራይ ግዛት ለመመስረት ማሰባቸውን ብናውቅማ…. እስከዚህም ደርሰው …. አናታችን ላይ እንዲሸኑ ባላደረግናቸው!!!
    ለማንኛውም ዛሬ ድሃ ተማሪዎችን በመረሸን በተጎናፀፋችሁት ድል … ከትግሬ አጋዚ አራዊቶች በተጨማሪ…አንቺና ሌሎችም ደስታቸውን በገደምዳሜውም ቢሆን በፌስ-ቡክም … በሌላ መንገድ እየገለፁ የሚገኙ …. ወይም ደግሞ …. ለወትሮው ያዞ እንባ አንቢ የነበሩ ዛሬ ግን በሃገር ላይ ምንም እንዳልተፈጠረ ጆሮ ዳባ በማለት(ለምሳሌ የኤልያስ ኢትዮጵያን ሪቪው ልብይሏል)ለኛ ለአሮሞ ልጆች ያላቸውን ቦታ ያሳወቁን….እንኳንም አቋማችሁን በግልፅና በማያሻማ ሁኔታ….በግዜ አሳወቃችሁን፡፡ እናመሰግናለን!!!
    በድጋሜ…ዛሬ ባስመዘገባችሁት አንፀባራቂ ድል እንኳን ደስ ያላችሁ……….ጦርነቱ ይቀጥላል !!!

    • Mr. tadyalehu gudisa think twice before you write nobody fears nobody am oromo and amhara but Idonot support narrow minded oromos like you look am wolloye but we peoples like to live in harmony we donot proud being oromo or what ever leave the damn OLF agenda Ioppose the students oromiya for oromos every ethiopian has the right to live any where as far as respect and accept aregions culture and langue ,with anole or agazi that is your problem you guys are colliding with all ethiopians except oromos ,we know you kind of guys are selfish and hatered narrow minded specially Islamic oromos like Jawar, all peoples of ethiopia knows the plan of OLF and we are stand by it will be worse so called narrow oromos ,Iswear am 75% oromo ND 25% Amhara be open minded and peace harmony love people ,past is past OLF kills amharas in 21st century while you talk about anole ,better to live in peace no body is feared other you know what amhara means even if they are under tigres domination ,but if alion once out nothing stops beteer live in peace same also for genuine ,GODa fearing kind ,humble lencho oromos not like you and yours take care brother think twice.

  7. ይህ ፅሁፍ በጣም ሁሉንም ሁኔታ በደንብ ተመልክቶአል።
    ኦሮሚያ ለኦሮሞዎች ለሚሉ ሁሉ።
    1ኛ፣ኦሮሞ ነን ባዮቹ፣ኦሮሞ መሆናቸውን ምንም የሚያውቁት ነገር አልነበረም፣በደርግ ዘመን ኦሮሞ እንዲባሉ ታዘዘ፣ከዛ የአሁኑ ገዢው ቡድን ኦሮምያ ክልል ብሎ አወጀ።
    2ኛ፣ከዛ እየቆየ ኦሮሞ የሚለውን ቡድን ከፈጠሩ በሁዋላ ማጆሪቲይ ነን ማለት ጀመሩ።በመጀመሪያ ከተፈለገ ከነሱ በቁጥር የሚበልጥ ቡድን በኢትዮጵያ ሞልቶአል። ጉራጌውም፣ከምባታውም፣ወላይታውም፣ ከተቡዋደነ ከነሱ አያንስም።
    በመጀመሪያ ማጆሪቲ ስለሆኑ ምን ይሁን፣ከማይኖሪቲይ የበለጠ መብት እንዲኖራቸው ነው?
    3ኛ፣ኦሮሚያ የሚለውን በአዋጅ የሰጣቸው ቡድን፣ ቢገባቸው ምን ችግር አለ መልሶ ይነጥቃቸዋል።
    4ኛ፣አዲስ አበባ ድሮ ፊንፊኔ አትባልም ነበር።ምናልባት በዛን ዘመን ፊንፊኔ የተባለችው ቦታ 6 ቤተሰቦች ይኖሩባተት ይሆናል። አሁን ግን በአዲስ አበባ 6 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ይኖራል። ስለዚህ የ6 ቤተሰቦችን ታሪክ አምጥቶ ከ6 ሚሊዮን ጋር ማገናኘት ፍሬቢስ ነው።
    5ኛ፣አንድ ቡድን፣ ምንም አይደለም፣ኦሮሞ ነኝ ብሎ ይደራጅ፣ ግን ለራሱ መብት ማስከበር እንጂ መታገል ያለበት፣የሌላውን መብት ለመርገጥ መታገል የለበትም፣ ወይም የሌለ የግዛት ጥያቄ ለመጠየቅ መሆን የለበትም። ኦሮሞ የሚል ግዛት በታሪክም በምንም ስለማይታወቅ።
    6ኛ፣ኦሮምያ የኦሮሞዎች እንጂ የሌላው አይደለም ብሎ ነገር የለም። የጀርመን ኒዎ ፋሺሽቶች “ጀርመን የጀርመን ናት የውጭ ሀገር ሰዎች ይውጡ” ከሚለው ጋር ይመሳሰልብኛል። የጀርመን ፋሺሽቶች ይሄን የሚሉት እኛ የተለየን ዘር ነን ብለው ስለሚያምኑ ነው። የጀርመን ህግ ግን እነዚህን ቡድኖች በአይነ ቁራኛ ነው የሚጠብቃቸው።
    7ኛ፣የጡት ሀውልት ሰርቶ ሲያስጨፍራቸው ቆይቶ፣እንደገና ከመሬት ሲያፈናቅላቸው ነገሩ አይገባቸውም እንዴ?ለምንስ ቀድሞውንስ በጡት ሀውልት ለመጨፈር ተሞከረ።
    8ኛ፣ለምን ከሚመጣው መንግስት ጋር ሁሉ ማሽቃበጥ አስፈለገ፣በተለይ በደርግ ዘመን ማነው ያስቸገረው?ይሄው ኦሮሞ ነኝ የሚል ቡድን ነው።
    9ኛ፣ደርግ ሲመጣ ፊውዳል ብሎ መሬታቸውን የወረሰው የነዚሁን የኦሮሞ ነኝ ባዮችን አባቶችን ነው። ለግል የመሬት ባለቤትነት ከመታገል ይልቅ ለግዛት መታገል ” ቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ በሬውን ተከትላ በረት ስትገባ ባለቤቱ በጥይት የገደላት” አይነት ነገር ነው።
    10ኛ፣የኦሮሞ ዘረኝነት ስሜት ያለባቸው በኢትዮጵያ ውስጥ ማይኖሪቲ ናቸው።እነሱም ያለ ሀቅማቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ለመፈታተን ይሞክራሉ።
    11ኛ፣የወለጋ፣የኢሊባቦር፣ የምእራብ ሸዋ ጠቅላይ ግዛቶች በጎጃሞችና በጎንደሮች የተሞሉ ናቸው። ሌሎቹም ጠቅላይ ግዛቶችም እንዲሁ በሌላው።

  8. በመጀመሪያ እኔ ንጹህ አማራ ንኝ ነገርግን እርስ በርሳችን ስንወቃቀስ የወያኔ እድሜ አራዘምነዉ ወያኔንለመጣል በማነኛዉም መንገድ በመደገፍ እኛም ችግራችንን ይዘን ልክ እንደነሱ ወደአደባባይ መዉጣት እንጅ አዝንባይ መስለህ ልክ እንደአባመላ የእባብ ወይንም እስት መልክ አትያዝ ታዉቆብሀል ደበሎ ለባሽ ወያኔ ነህ እኔ የምፈልገዉ ወያኔ ወድቆ አገሬ ሰላምና ፍትህ የሰፈነበት በጎሳ ያልተከፋፈለ ሀገር ሆና ማየት እንጅ ስስ ብልት በመንካት ለወያኔ እድሜ የሚያራዝም ሰንካላ ሃሳብ ማቅረብ አያስፈልግም፡ አሁን ሁላችንም በየቦታዉ ችግራችንን ይዘን ከወጣን የወያኔን እድሜ የትንኝ እድሜ ይሆናል ከዜ ሁሉንም ያማከለ መንግስት በመመስረት አይደለም ኣሮሞ ሊገነጠል ይቅርና ኤርትራም ትመጣለች

  9. These protests should have been staged long time ago when the farmers were evicted from their lands by OPDO tugs. Most of the lands in the contested areas have already been sold out at cheap prices. The slogan of the students should have been about the farmers and other poor residents of the area future fate not about the land to be included in Addiss or Oromia. Both are parts of Ethiopia. The question should have been were the people consulted? How they are going to be integrated? How the integration will benefit the people?? IT SHOULD BE ALL ABOUT THE PEOPLE NOT LAND OR IDENTITY!!

    More than 50% of the land in those areas has already been tranesfered to non-Oromos and foreigners. The farmers have already lost their land and property with out proper compensation and these protests should have been staged back then when the farmers where in need of support.

    The way out is to consult with the residents of the areas if they want to be part of Addiss Ababa. Who doesn’t wantto be? That is why thousends flee to Addis every year. It is much better for the residents to be part of Addiss than administered by the incompetent OPDO officials.

    What surprises me is those people in OPDO contesting the plan and ruling the area are the same people who send their childern to Addiss for better education.

    If the protest is about the future fate of the farmers we all support it. But if it is about keeping the area in Oromiya, THEN yes ‘mengedun cherk yargelachehu’.

    It is a historical fact that cities will expand and near by rural areas will be part of the city. The question is how well it is planned so that the people in the expansion areas will be better off in the new arrangement??? Yes we need the government to answer this vital question. We also demand justice served for those farmers who has lost their land with out reasonable compensation by the corrupt OPDO local officials and TPLF cliques who have taken most of the land in those areas.

    HUMANITY BEFORE ETHNICITY
    NO ONE IS FREE UNLESS WE ALL ARE FREE

  10. Very interesting point Naomi. We need more people who think beyond racism. It is a shame if I am University student in the 21st century and still think ONLY about Oromo. What is the point of spending 12 years of school if I don’t think more critical than our ancestors? who were actually better than us.
    People please, don’t listen to those who have seated their ass in America and ONLy talk about Ethiopia. They haven’t got the ball to come to Ethiopia and fight.

    You are the only person who can change Ethiopia.
    May Peace be with you

  11. The saddest part is:Oromians slather their fellow eEthiopia listening TPLFwho does not care about anybody except their own race.
    Still you don’t learn your lesson, your land??? History will bring the whole truth is that is the only way you want to look or you better come to your seance and work with the rest of the nation to get rid off these rotten government and bring justice for the people of Ethiopia.
    You watched when others displaced not only that you killed, took their belonging as if it will remain for ever, now it is your turn and no one will take notice about your idiot attitude about the country

  12. ስሚኝ ወ/ሮ ኖኣሚን …. በመጀመሪያ እንኳን ደስ አለሸ! ….. እጅግ በጣም የምትጠያቸውን የኦሮሞ ወጣቶችን ግዳይ … የአጎትሽ ልጅ የትግሬ አጋዚ ሰለጣለልሽ! …. ሆኖም አንቺም ሆንሽ የትግሬው አጋዚ ፈሪ አውሬ እንጂ ጀግና አይደላችሁም፡፡ ጀግና እላችሁ የነበረው እነኝህን እጃቸው ከብዕርና ከወረቀት ውጪ ሽመል እንኳ ይዞ የማያውቀውን ምስኪን ወጣት ተማሪዎች ሳይሆን የሰለጠኑና የታጠቁ ወታደሮችን ገድላችሁ ቢሆን ነበር፡፡ ለነገሩ…..ይህን አይነቱን ቁም ነገር በታሪካችሁ ሰርታቸሁ አታውቁም፡፡ ያልታጠቀን ምስኪን መፍጀት ግን አዲሳችሁ አይደለም፡፡ ደጋግማችሁ ያልታጠቀን ምስኪን ግዳይ በመጣል የማይረሳ ታሪክ ሰርታችኋል፡፡ የአኖሌ ኃውልትም የዚሁ ዓይነት ታሪክ ማስታወሻ ነው እንጂ አንቺና መሰሎችሽ እንደምትሉት ፈጠራ አይደለም፡፡ ትላንት…. በምኒልክ ሰራዊት (በራስ ዳርጌ ፊታውራሪነት) አኖሌ ላይ የተፈጁትም ሆነ ….. ዛሬ በግፍ በአውሬዎቹ የትግሬ አጋዚዎችሽ ጥይት የወደቁት …. ለናንተ (ላንቺና ለመሰሎችሽ) ጀግኖቻችሁ የጣሉላችሁ የጠላት ግዳዮች ናቸው…. ወይም….ተስፋዬ ገ/አብ በምናቡ የፈጠራቸው ቀልዶች ናቸው…. ለኛ ግን ሠማዕታቶቻችን ናቸው፡፡ ታጋይ ይወድቃል …. ትግሉ ግን ይቀጥላል!!! አሁንም ጦርነቱ አልቆመም! አይቆምም፡፡ ማን ያውቃል ….አንድ ቀን…..ዛሬ ያንቺ አጋዚ አውሬዎች የታጠቁትንና የጀገኑበትን ብረት…. እኛም እንታጠቅና በጦር ሜዳ ዋን-ቱ-ዋን እንጋጠም ይሆናል …ያኔ ማን ጀግና …ማን የሴት ልጅ…ማን የወንድ ልጅ…. እንደሆነ ታያለሽ!!!
    አሁንም ይለይልሽ….. አዎ! ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት! ….. የፊንፊኔ ዙሪያ ወረዳ ብቻ ሳይሆን…..ፊንፊኔም ጭምር የኦሮሞ ህዝብ እንብርት ናት!!!! ያኔ በሃገር ማቅናቱ ዘመን ….አያቶችሽ የየካን…..የጉለሌንና…. የገላንን ኦሮሞዎች በግፍ ጨፍጭፈውና ከመሬታቸው አፈናቅለው… ወታደሮቻቸውን በፊንፊኔ ካሰፈሩ በኋላ…አዲስ-አበባ የሚል የዳቦ ስም እንዳወጡለት ረሳሽው ወይስ አታውቂውም??…እንግዲህ እውነታው እንደዚያ ነው፡፡ ዋጭው!…..ቢመርሽም…. በበደሌ … በሜታ …. በጊዮርጊስ …..ወይም በሄንኬን አወራርጅው!!
    በዚህ አጋጣሚ…..አንችም ሆንሽ መሰሎችሽ እንድትረዱልን የምንፈልገው…..እኛ ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት ስንል…..ሌሎች ህዝቦች ኦሮሚያ ውስጥ መኖር አይችሉም ማለታችን አይደለም!…እመኚኝ!…(ካለመንሽም የራስሽ ጉዳይ)…..ሌሎች ህዝቦች ኦሮሚያ ውስጥ መኖር አይችሉም ማለታችን አይደለም!!! በኦሮሚያ ውስጥ አማራም …..ትግሬም…..ሌሎችም ህዝቦች ከዚህ በፊትም ይኖሩ ነበር …. ወደፊትም ይኖራሉ!! የኦሮሞን ህዝብ አክብረው …በእኩልነት …በመረዳዳት ….በጋራ መኖር እስከቻሉ ድረስ ! …. አይደለም የኢትዮጵያ ህዝቦች … ለምን ኤርትራዊ …… ወይም ከዩሮፕ …ወይም ከዩ.ኤስ. አይሆንም…ኦሮሚያ ውስጥ መጥቶ መኖር… ቤት መስራት…. ፋብሪካ መትከል…ኃብት ማካበት ይችላል! … አሁንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡ እኛ በዚህ በኩል ችግር የለብንም፡፡ ከዚህ በፊትም ከጥንት ጀምሮም ቢሆን አባቶቻች ከበዳችሁን ብለው አያውቁም፡፡ እነርሱን ብሎ…እነርሱን አምኖ ለመጣ ምስኪን እንግዳ…ባህሉን ፣ሃይማኖቱን፣ቋንቋውን ሳያንቋሽሹበት …በማክበር … መሬታቸውን አካፍለው በሰላም አብረው ኖረዋል…አሁንም እየኖሩ ነው፡፡
    አሁን ትልቁ ጥያቄ….ከዚህ በፊት ያንቺ አያቶች በሃገር ማቅናት ስም መጥተው… ኃብትና መሬት በመቆጣጠር (ሲመቻቸው በጉልበት…ካልሆነም በማጭበርበር ለቤተ-ክርስቲያን…ለቀዳሽ በቅላድ….ላስቀዳሽ በቅላድ እያሉ)….አነሱ ባለፀጋ …እኛ የበይ-ተመልካች የተደረግንበት ስርዓት መቼም አይፈጠርም!!!
    አይደለም ትላንት አጎቶችሽ አጋዚዎች ወደ አምቦ ይዘው የመጡትን ስናይፐር ጠብመንጃ…..ቢ.ኤም. ሮኬትና ጀት ይዛችሁ ብትመጡም…. በጥርሳችንም ቢሆን እየታገልን …እንደዛሬዎቹ ታጋዮቻችን …. ከነክብራችን እንወድቃለን እንጂ…ዳግም በቁም አንሞትም!
    ከላይ እንዳልኩት … አሁንም ኦሮሚያም ሆነ ፊንፊኔ የኦሮሞዎች ናት!!! በእኩል አብረን ተባብረን…ተከባብረን ለመኖር ኦሮሚያ ለሁላችንም ትበቃለች…. ግን በብልጣብልጥነት …ትላንት በሃገር ማቅናት ስም…. ዛሬ ደግሞ በማስተር ፕላን ስም መሬትና ኃብት ለመቀማትና ተጨማሪ የትግራይ ግዛት በፊንፊኔ ዙሪያ ለመመስረት የምታደርጉትን ሩጫ በቁማችን እያለን አንቀበልም!…. ህርምሽን አውጭ…አንቀበልም፡፡
    እነ ገብረዋህድን የመሳሰሉ ብዙ ሺህ የትግሬ አጎቶችሽ …. ላለፉት አስር አመታት በፊንፊኔ ዙሪያ የሚኖረውን ምስኪኑን የኦሮሞ አርሶአደር ወገናችንን በጥቂት ገንዘብ አያታለሉ …. እያንዳንዳቸው እሰከ 15 ቪላ-ቤትና ፋብሪካ ሲገነቡ እኮ … ሳናውቅ ቀርተን አልነበረም ዝም ብለን በትዕግስት ስንከታተል የነበረው…. ካገራችሁ ትግራይ ኦሮሚያ ለመኖርና ለመስራት ይሻለናል ብለው ሊሆን ይችላልና …. አዚህ መጥተው ይሄን ግንባታ የሚገነቡት(ሃብቱን ከየት እንዳገኙት ግራ ቢገባንም)፤…ኦሮሚያን ህዝቧን እስካከበሩና ተሰማምተው በጋራ ለመኖር ወደው እስከመጡ ድረስ…ኢትዮጵያዊ ናቸውና መብታቸው ነው…… በማለት ነው!….. እንጂ…..እንዲህ እንደ ዛሬ ቀስ ብለው እንደ ሸለምጥማጥ እየተሽሎከለኩ….በተቀናጀ ማስተር ፕላን ስም …. የኦሮሚያ መሬት ላይ ሌላ የትግራይ ግዛት ለመመስረት ማሰባቸውን ብናውቅማ…. እስከዚህም ደርሰው …. አናታችን ላይ እንዲሸኑ ባላደረግናቸው!!!
    ለማንኛውም ዛሬ ድሃ ተማሪዎችን በመረሸን በተጎናፀፋችሁት ድል … ከትግሬ አጋዚ አራዊቶች በተጨማሪ…አንቺና ሌሎችም ደስታቸውን በገደምዳሜውም ቢሆን በፌስ-ቡክም … በሌላ መንገድ እየገለፁ የሚገኙ … እንኳን ደስ ያላችሁ……….ጦርነቱ ይቀጥላል !!!

  13. ናኦሚን ተብዬዋ ሴትዮ የኦሮሞ ጥላቻ ያሳበዳት ይመስላል:: “የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል” እንደሚባለው “የተነቃነቀ ጥርስ መውለቁ አይቀርምና” የወለቀን ጥርስ መመለስ ወይም የፈሰሰን ውሃ ማፈስ አይቻልምና ተረጋጊ:: አለበለዚያ ጨርቅሽን ጥለሽ ታብጃለሽ:: የኦሮሞ ፖለቲካ እንዲህ በቃላት ድርደራ ብቻ የሚመለስ አይደለም:: የጎሳ ወይም የዘር ፖለቲካ ብላችሁ ዘወትር የምትዘበዝቡት እንደምትሉት ሳይሆን በመላው የሰው ዘርና ህብረተብ የነበረ አሁንም ያለ ለወደፊቱም የሚኖር ጉዳይ ነው:: ስለጠላሽው የሚቀር ስለወደድሽው የሚመጣ አይደለም:: በአፍሪካ; አውሮፓና አሜሪካም ያለ ነው:: ወደ ኦሮሞ ሲመጣ አንቺና መሰሎችሽ ለምን ደማችሁ እንደሚፈላ ግራ ይገባኛል:: 6% ትግሬዎች 40% ኦሮሞን ለ23 ዓመታት በግፍ ሲገዙ ኦሮሞነት ይበልጥ እየገዘፈ እንደሚሄድ አስበሽው ታውቂያለሽ? ሁላችንም በቁመታችን ልክ የአገሪቱ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ቢሰፋልን እኮ ከኦሮሞነት ኢትዮጵያዊነታችንን እናስቀድም ነበር:: የኦሮሞ ተማሪዎች ተለይተው ከዩኒቨርቲ ሲባረሩ ኦሮሞዎች በእስር ቤት በኦሮሞነታቸው ብቻ ሲማቅቁ ኢትዮጵያዊነታውን እንዴት ሊየያስቀድሙ ይችላሉ? እንዳንቺ ያሉ ጋጠ ወጥ አላቂ ሳሚዎች ብዕራቸውን ኦሮሞ ላይ ሲደቅኑ እንዴት አድርገው ነው ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያስቀድሙት? ሻቢያ ተገንጣይ የእናት ጡት ነካሽ ብላችሁ ስታላዝኑ ኤርትራውያን እንዴት Eritrean Identity Develop እንዳደረጉ አስበሽው ታውቂያለሽ? አካሄዳችሁ ሁሉ አብሮ ለመኖር ሳይሆን እንድንለያይ የሚያደርግ ነው:: በበኩሌ fair ለመሆን ብሞክርም ድርጊታችሁ ተቃራኒውን መንገድ እንድመርጥ ያደርገኛል:: መማር fairness ካላመጣ ባትማሪ ይሻልሽ ነበር:: ለማንኛውም ረጋ ብለሽ አስቢ:: ብዙ ከመጻፍ ብዙ ማንበብና መስማት ጥሩ ነው ባይ ነኝ:: ጠላሽም ወደድሽም የኦሮሞ ጉዳይ ካለተፈተታ ኢትዮጵያ የምትባለው ሃገር አሁን ባለው ሁኔታ በአጭር ጊዜ ትበታተናለች:: የ Qubee Generation መጥቶ በር ላይ ነው:: ንቂ !!!ወደፊት እንጂ የድሮውን ያረጃ ያፈጀውን እየደረማመሰ የሚሄድ ትውልድ!!!!!

    • ወዳጄ ገመዳ ገና የፖለቲካ ሀ ሁ ያልገባቸው ናቸው በዚህ እንቅስቃሴአቸው የኦሮሞን ትግል የሚያቆሙ ከመሰላቸው ተሳስተዋል ብሶት የማይወልደው ነገር የለም ልክ እንዳልከው አንድ ቀን ነገሮች እነርሱ ወደ ማይፈልጉት አቅጣጫ ከሐደ መፈራገጥ ዋጋ አይኖረዉም። ወያኔ የአንድነቱ መንገድ በከፍተኛ መንገድ አዳክሞታል እንዳልከው አንድ ትውልድ በር ላይ ቆሞ እየተጠባበቀ ነው በማንኛውም አጋጣሚ የሚፈጠር ነገር ተቀምጦ ማየት ነው

  14. Selam..T
    Le sisay….bezi zemen endezi aynet astesasebe mantebarek denkurena new!!!!
    Lenegeru enante setmaru yabesebachuhali…..Zara lay komeki minilikin setewekisu tenesh ayakebedachun?esu bekefelew mesewatenet meselegn benetanet komek emetelefelifew!!lemehonu yetgnaw yetarik metehef new minilik ejie korete waym tut korete yemelew?sema tutena belite minamin mekuret eko yenante goji baheli new enji ye Amarame hone ye lalaw behar aydelem………demos Addis Ababa betadge minachu yakenesali?ketema me to betena faberika lemeserat yanten waym yezerochekin fekad meteyek yalebet yameselikali??manim Ethiopian yefelegew kilili had meseratm hone mentor yachelali……wededikim telakim akimu kalek tigray hadek megenebat techililek……ena emegermegn ezi enkan beseletenew Hager eyenoru (UK)oromiya ye promo nat eyalu yakebatralu ……..lemehonu enante ene man nachu? Yeti gr new tarikachu??tarik alachu enda ??left Ethiopia yeserachut??……oromo manew? manachu??eski tarikachun wede hala meles belachu lemayet mokiru….midere tulutula…arfachu kalitekemetachu weyana endehone lik yasegebachuhali….zeregnoch……..tuuuuuu…..asafariwoch!!!”

  15. They Amhara and Tigre elites develop Oromo identity from nowhere. I had never had much relation with Hararghe Oromo before, but when I know that they target me for being an Oromo in Shewa, I saw myself more related to Oromo of Harar 1000 Km away than my neighbours of Tigre whom I grew up with.

    Well come to the new world. Oromo nationalism will never stop as long as you kill, isolate exploit them and there are a potential of 40 million people which will believe all the propaganda that how Oromo were a loser in Ethiopia. If you don’t stop tiny Eritrea from what they believe, you can stop giant oromo. Just a matter of time until Oromo awareness in local/illiterate population gets 3% of the population. With independent media owned by Oromo intellectual that will not last long even.

  16. ወንድሜ አሁንም ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ኦሮሚያ የኦሮሞ ትግራይ የትግራዮች አማራም የአማራዎች መሆኑን መቀበል ማንም ላይ ምንም ነገር አያመጣም ይሄ ነገር መርዛማ ሆኖ ሳ ይሆን ወያኔ ለ 25 አመታት የረጨው የፍርሀት መርዝ ጭንቅላትህ ውስጥ ምቹ ቦታ ስላገኘ ነው

Comments are closed.

Share