April 29, 2014
10 mins read

በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የኦሮሞ ብሔር ተማሪዎች ባነሷቸው ጥያቄዎችና እየደረሰባቸው ያለው ጉዳይ

ከአቤኔዘር በወንጌል

በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል መካከል ይተገበራል የተባለውን ማስተር ፕላን ተከትሎ ተቃውሞ፣ ድጋፍና ገለልተኛ የሆነ አቋም እያየው ነው። መጀመሪያ ደረጃ ማንም ጤነኛ ሰው ልማትን አይጠላም። የሰው ልጅ ህይወቱን የሚለውጥለትን ነገር አይጠላም። ስለዚህ ሰዎች ልማት እንደጠሉ አድርጎ ማሰብም ማውራትም የውሸት ፕሮፓጋንዳ ነው። ወደ ጉዳዩ ስንመጣ ተማሪዎቹ ያነሱትን ጥያቄና በተማሪዎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን ነገር እንይ።

ተማሪዎቹ ማስተር ፕላሉን በመቃወም በተለያዩ ዩኒቭርሲቲዎች ውስጥ በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። ይሄ ሙሉ ለሙሉ መብታቸው ነው። አብረውም ሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ነው። ለምሳሌ: ኦሮምኛ ከአማርኛ ጋር አብሮ የፌደራል መንግስት የሥራ ቋንቋ ይሁንና የመሳሰሉት። ይሄም ሙሉ ለሙሉ መብታቸው ነው። ከዚያም አልፎ ኦሮሚያ ትገንጠል ቢሉ እንኳን ይሄም ሙሉ ለሙሉ መብታቸው ነው። ማንም ሰው ለሌላ ሰው ይሄንን ብለህ ጠይቅ ወይም አትጠይቅ ብሎ አጀንዳ ሊያዘጋጅለት አይችልም። ይሄንን ማድረግ የሚፈልጉ አምባ-ገነኖች ብቻ ናቸው። እኔ ደግሞ አምባ-ገነኖች ከየትኛውም አቅጣጫ ቢመጡ አልቀበላቸውም። ዋናው ጉዳይ ተማሪዎቹ ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ነው እያቀረቡ ያሉት ወይስ በሌላ የሚለው ነው መታየት ያለለት። እስካሁን ድረስ በሰላማዊ መንገድ ነው እያቀረቡ ያሉት። የሀይል እርምጃ እየወሰደ ያለው ኢህአዴግ ነው።

አንዳንዶች ጉዳዩ ማስተር ፕላሉን ለመቃወም ከሆነ ለምን ሌሎች አጀንዳዎችን አነሱ የሚሉና ጉዳዩን ጃዋር እያራመደው ካለው ነገር ጋር ተቀላቅሏልና ባልጠራ ነገር ላይ መደገፍ ይቸግረናል ሲሉም አይቻለው። በእኔ በኩል የሌሎችን ሰዎች መብት እስካልነኩ ድረስ ሌሎች ጥያቄዎችን አብረው ማንሳታቸው ምንም ችግር የለውም። ከዚህ በፊት ለማንሳት እድሉን ስላጡና ስለታፈኑ ነው። ስለዚህ ይሄንን አጋጣሚ ሲያገኙ በውስጣቸው ያለውን ነገር አብረው አቀረቡ። መብትህን መጠቀም በማትችልበት ሀገር ያገኘኸውን አጋጣሚ ሁሉ ትጠቀምበታለህ። ለዚህም ነው ታላቁ እሩጫ ላይ በየአመቱ ብሶታችንን ስናሰማ የነበረው። ከላይ እንዳልኩት ተማሪዎቹ ማስተር ፕላሉን ከመቃወም ጀምሮ ኦሮሚያ ተገንጥላ የራሷን ሀገርና መንግስት ትመስርት ብለው የመናገርም ሆነ የመጠየቅ መብት አላቸው። ይሄንን ማንም የሚሰጣቸው ወይም የሚነሳቸው መብት ሳይሆን ሰው በመሆናቸው በተፈጥሮ ያገኙት መብት ነው።

በእኔ እምነት ወደፊት ሊከሰት የሚችለው የገበሬዎች መፈናቀል የኦሮሞ ብሔር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮዽያዊ ጉዳይ ነው። በመሆኑም ተማሪዎቹ ሌሎቹንም ከኦሮሞ ብሔር ውጪ ያሉ ተማሪዎችን በሚያሳትፍ መልኩ ሰላማዊ ተቃውሞውን ቢያደራጁት ጥሩ መሰለኝ። ሌሎቹም ተማሪዎች ጉዳዩ የጋራ መሆኑን አውቀው ዳር ሆነው ከመመልከት አብረው ሊሆኑ ይገባል። በጋራ ችግራችን ላይ በተናጠል ተጉዘን ማናችንም የትም አንደርስም።

Photo Credit globalcement.com
በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የኦሮሞ ብሔር ተማሪዎች ባነሷቸው ጥያቄዎችና እየደረሰባቸው ያለው ጉዳይ 1

አሁን ግን ተማሪዎቹ በዋናነት እያነሱ ያሉት ጥያቄ በርካታ ገበሬዎች ከመሬታቸው የሚያፈናቅለውን ፕላን በመቃወም ነው። ይሄንን እኔም ሙሉ ለሙሉ የምቃወመው ነው። እኔ ይሄንን ዕቅድ የምቃወመው ግን የአዲስ አበባን መስፋትና አለመስፋት በሕዝብ ውሳኔ ሳይሆን በኢህአዴግ ከተመሰረተው የብሔር ፌደራሊዝም ጋር አያይዤና ተቀብዬ አይደለም። ነገር ግን ዕቅዱ ከዚህ በፊት በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብና በሌሎችም ክልሎች እንደታየው በልማት ስም እዚህ ግባ በማይባል ካሳ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ያለ አግባብ ከመሬታቸው አፈናቅሎ መሬቱን የጥቂት ግለሰቦችና ባለ ሀብቶች የሚያደርግ ስለሆነ ነው። ኢህአዴግ መሬት መሬት ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ካለፉት የ23 አመታት ተሞክሮ ማየቱ በቂ ነው። ለመሆኑ የአዲስ አበባ መስተዳድር በከተማዋ ውስጥ ያለውን መሬት በደንብ አልምቷል? መጀመሪያ ይሄ በደንብ ሊፈተሽ ይገባል።

ወደ አነሳሁት ጉዳይ ስመለስ የሀሳብ ልዩነታችንን ይዘን በማስተር ፕላኑ ጠቃሚነትና ጎጂነት ላይ፣ ተማሪዎቹ እያነሱት ባሉት ተመሳሳይና ተያያዥ ጥያቄዎች ላይ ልንወያይ ልንከራከር እንችላለን። በተማሪዎቹ ላይ ኢህአዴግ እየወሰደ ባለው ሕገ-ወጥ እርምጃ ላይ ግን ልንከራከር አንችልም። አይገባምም። በአንድ ድምጽ ልናወግዘው የሚገባ ጉዳይ ነው።

አንዳንዶች ሁለቱን ነገር በመቀላቀል ገለልተኛ መስለው እየታዩ ነው። ይሄንን አካሄድ የኢትዮዽያውያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ላይም ሲያንፀባርቁት አይቻለው። ማንም ወገን የመሰለውን ጥያቄ በሕጋዊ መንገድ እስካቀረብ ድረስ አጀንዳውን ደገፍነውም አልደገፍነውም መብቱን መጠቀሙን ልንደግፍለት ይገባል። ይንን መብቱን በመጠቀሙም የተነሳ በደል ሲደርስበትም አብረነው ልንቆም ይገባል። በመርህ የሚመራ የሰብአዊና የዲሞክራሲያዊ ብሎም የነጻነት ጥያቄ እንቅስቃሴ ይሄ ነው። አለበለዚያ አጀንዳው የኔ ካልሆነ ሌሎች ዜጎች ላይ ሕገ-ወጥ ድርጊት ቢፈጸምም አይመለከተኝም ብሎ ከዳር ቆሞ መመልክት መጀመሪያውኑም በመርህ እንደማንመራ የሚያሳይ ነው።

ከዚህ በፊት እንዳልኩት በፖለቲካ አስተሳሰባችን የተለያየ አቋም ሊኖረን ይችላል። ነገር ግን በየትም ቦታ ይሁን ዜጎችን ከመሬታቸው ላይ አላግባብ የሚያፈናቅል ዕቅድንም ሆነ ድርጊትን ልንቃወም ይገባል። መብታቸውንም በመጠየቃቸው የተነሳ በተማሪዎቹ ላይ እየተወሰደ ያለውን ሕገ-ወጥ እርምጃም በአንድነት ልንቃወመውና ከዞን 9 ከታሰሩት አባላትና ሌሎች ጋዜጠኞች ጉዳይ ባላነሰ መልኩ ድምጻችንን ልናሰማላቸው ይገባል። ያው በኢህአዴግም ከኢህአዴግ ውጪም ያሉ የተወሰኑ ሰዎች/ቡድኖች ሆን ብለው አሉታዊ ክፍፍል ለመፍጠርና ጥላቻን ለማስፋፋት ሲሞክሩም እያየው ነው። የእነሱንም አካሄድ በማውገዝ ጨዋታቸውን ወደ ጎን ትቶ እንቅስቃሴያችንን በአንድነት መቀጠሉ አማራጭ ያለው ነገር አይመስለኝም።

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop