አቡነ ዘካሪያስ ካህናቱን ያወገዙበት ደብዳቤዎችን ይዘናል

ከአዘጋጁ፡ በሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ያለው ጉዳይን እየተከታተልን በስፋት የሚደርሱንን አስተያየቶች በማስተናገድ ላይ እንገኛለን። አንዳንድ የዘ-ሐበሻ ወዳጆች በገለልተኛው ወገን ያለውን ብቻ እያቀረባችሁ ነው፤ ይህ ደግሞ ሚዛናዊነታችሁን ሊያሳጣችሁ ይችላል ሲሉ አስተያየት ሰጥተውናል። ዘ-ሐበሻ እንደ ነፃ ሚዲያነቷ የሁሉንም ሃሳብ ታስተናግዳለች። የተላኩላትን አስተያየቶችን ዘ-ሐበሻ ሳታስተናገድ የቀረችባቸው ጊዜያት የሉም። ሆኖም ግን አንዳንዶች የዘ-ሐበሻን በር ሳያንኳኩና ለዘ-ሐበሻ ሳይጽፉ ዘ-ሐበሻን ሊወቅሱ ቢሞክሩ አስተያየታቸው ሚዛን አይደፋም። ልንወቀስ የሚገባው የተላከልንን ጽሁፍ አናወጣም ስንል ብቻ ነው። ዘ-ሐበሻ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አትገባም፤ ሆኖም ግን ዜና የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ታስተናግዳለች። አሁንም ቢሆን በየትኛውም ቦታ አቋማቸውን ያደረጉ ሰዎች በድረገጻችን ሊገለገሉበት ይችላሉ። በግልጽ በዘ-ሐበሻ ኤዲቶሪያል ላይ እንደተቀመጠው በድረገጹ ላይ የሚቀርቡ አስተያየቶች ሁሉ የጸሐፊው እንጂ የዘ-ሐበሻ አቋሞች አይደሉም።

ለዛሬው አቡነ ዘካሪያስ ካህናቱን ያወገዙበትን ደብዳቤዎች ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ አስተናግደናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያ፤ የአባይ ወንዝ ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ፤ - ኪዳኔ ዓለማየሁ ፤

3 Comments

  1. እኔን እስከሰማሁት ድረስ የሚናሶታው መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን በአካባቢው ባሉ በተለያየ ስራ ተሰማርተው እና ላባቸውን አንጠፍጥፈው እሚኖሩ ኢትዩጵያውያን ካፈሩት ገንዘብ እያዋጡ ያቋቋሙት ቤተክርስቲያን ነው። ከዚህም በተጨማሪ እንደሰማሁት በሃገር ውስጥ ያለው ሲኖዶስ እና በስደት ያለው ሲኖዶስ ችግራቸው እስኪፈቱ ድረስ ከየትኛውም ወገን ሳንሆን በገለልተኝነት ሃይማኖታችን እያከበርን እንቆያለን፣ ሁለቱ ሲኖዶሶች መስማማት እና አንድ መሆን ሲችሉ ለሚፈጠረው የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ጋር እንቀላቀላለን ብለው ከ12 ዓመታት በላይ ቆይተዋል። እናም የሚችል ካለ ከዚህ በታች የሚከተሉትን ጥያቄወች መልሶ በርቀት ለምንከታተል ወገኖች ባሁኑ ወቅት ያለው ችግር ከምን እንደመጣ ቢያስረዳን። እኔ ግልጽ ካልሆኑልኝ ጥያቄወች መሃከል የሚከተሉት ይገኛሉ።

    1) የሚኖሶታዋ መድሃኒት አለም በአስተዳደር በሃገር ውስጥ ካለው ሆነ በስደት ካለው ሳትወግን እራሷን እያስተዳደረች እንደቆየት የታወቀ ነው። እና መቼ የቤተክርሲያኑ አባላት በጠቅላላ ጉባኤ ባጸደቁት ውሳኔ ነው አቡነ ዘካሪያስ የሚባሉት እና በኢትዩጵያ ያለው ሲኖዶስ የተሾሙ ጳጳስ የቤተክርስቲያኑ የበላይ ሆነው እንዲህ አትቀድሱ እንዲያ ቀድሱ ብለው ለማዘዝ መብት የሰጣቸው? በጠቅላላ ጉባኤው ህዝቡ ከሃገር ውስጥ ሲኖዶስ ጋር እቀላቀላለሁ ብሎ ባላለበት ሁኔታ እኒህ ጳጳስ ምን አስተዳደራዊ ስልጣን ይኖራቸዋል? ህዝቡ ሳይወስን በሃገር ውስጥ ባለስ ሲኖዶስ የተሾሙ ጳጳሱ ብቻ ተነስተው ካህናቱን እና ዳይቆናትን የማውገዝ መብት ካላቸው ነገስ በስደት ያለው ሲኖዶስ የሾማቸው ጳጳስ በተቃራኒው ካላደረጋችሁ ብለው ከማውገዝ እና በቤተክርሲቲያኗ ገለልተኝነት አቋም ላይ በቀጥታ ያለ ህዝብ ውሳኔ ተጽዕኖ ለማድረግ ምን ያግዳቸዋል?

    2) በተጨማሪ እንደሰማነው የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪን ጨምሮ የተወሰኑ ካህናት ከተወሰኑ መዕመናን ጋር በመሆን በዚህ ቤተክርስቲያን እንዳንቀድስ ተወግዘናል በሚል ሰበብ በትንሳዒው በዓል እለት በቤተክርሲትያኑ የሚደረገውን ቅዳሴ አንቀድስም በማለት ሌላ (ታቦት የሌለበት እና የኦሮቶዶክስ ቤተክርሲትያን ያልሆነ) የኪራይ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ማድረጋቸውን ሰምተናል። እናም ደሞዛቸውን ከፍሎ፣ የሚኖሩበትን ቤት ገዝቶ፣የስልክ ቢል ሳይቀር እየከፈለ ቀጥሮ ከሃገር ውስጥ ያስመጣቸው አብዛኛው ምዕመናንን ቁጭ አድርገው ሌላ ቦታ ሄደው መቀደሳቸው ምን እንደምታ አለው? ማን በሚከፍለው ቤት እየተኖረ፣ ማን የገዛቸውን የቤተክርሲያን አልባሳት እና ከበሮ በማስወጣት ባልተባረከ እና ታቦት በሌለበት ቦታ ቅዳሴ ማድረጉ ትርጉሙ ምንድነው?
    3) የቤተክርስቲያኑ ሃላፊ እና ሌሎች ካህናት ለዚህ ስራ ተቀጥረው የፈሩሙት ሰነድ እና እስከዛሬ የሰሩበት አሰራር የጳጳስን ስም በቅዳሴ ላይ በማንሳት እና በገለልተኝነት ላይ ያለውን አቋም ቁልጭ አድርገው ያውቁታል። እናስ እስከዛሬ የሰሩበትን ቤተክርሲቲያን “የአህያ እና የአሳማ ማሰሪያ” ብሎ ከሚል ጳጳስ ዛሬ እገዳ ደረሰን በሚል ጥለው የወጡት የቤተክርስቲያኗ ህጋዊ ባለቤት እና አስተዳዳሪ ላቡን አንጠፍጥፎ የሰራት ሰፊው የከተማው ነዋሪ/አባላቶቹ እንጂ ሌላ ማንም አካል እንዳልሆነ እንዴት ማወቅ ተሳናቸው? እንዲህ ያለው ህዝብን ዝም አፈህን ዝጋ እና እኛ ባልነው እንደበግ እየመራን እንውሰድህ አሰራር የሰው ልጅ መብት በተከበረበት ሃገር የሚቀበል ዜጋ እንደሌለ እየተወቀ ቀጥሮ ያመጣን ህዝብ “ አለቃችን አንተ ሳትሆን ሌላ አካል ወይም እኛው እራሳችን ነን” የሚል እብሪት እና ልበ ድፍንነት እንኳን ከካህን ከተራ ግለሰብም የማይጠበቅ መሆኑን እንዴት አላስተዋሉትም?የቤተክርስቲያኒቱ ባለቤት ከሆኑ አባላት ውስጥ ከሁለት ሶስተኛው በፔቲሽን ”ከስራችሁ ታቀቡ“ “አካሄዳችሁን አልደገፍንም” ብሎ ባለበት ሁኔታ እንዲህ ያዙኝ ልቀቁኝ ትርጉሙ ምንድነው?

    እርግጥ ነው ካህናቱ በግል እስካሁን የሰሩበት የገለልተኛ አቋምን መርምረው ከኢትዩጵያ ሲኖዶስ ፈቃድ ውጭ መስራት እና የሚከተለው ውግዘት ሊያስፈራቸው ይችላል።እነሱም በዚያ ሊያምኑ የግል መብታቸው ነው። እንዲያ ከሆነ ግን ህዝብን በግልጽ “እኔ እስካሁን በሚሰራበት መንገድ መቀጠል አልችልም። የሃገር ውስጥ ሲኖዶስ የሾማቸውን ጳጳስ ስም ካልጠራህ ልሰራ አልችልም” ብሎ ስራን መልቀቅ ሲቀል እኔ ባመንኩት ከልተከተላችሁኝ ቤተክርስቲያኗን ውዝግብ ውስጥ ከትቼ፣ ምዕመናኑን አበጣብጬ አፈርሳለሁ“ የሚል አካሄድ መከተሉን ምን አመጣው? በኢትዩጵያ ሲኖዶስ ስር ያሉ ቤተክርስቲያኖች በውጭ ካልተገኙ እኮ እኒህ ለነፍሳቸው ያደሩ ካህና ሃገር ቤት ተመልሰው ከገጠር እስከተተማ የሚያገለግሉበት ቤተክርስቲያን ሞልቶላቸዋል።

    4)የቤተክርስቲያኑ አባላት የመዕመናኑን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመር እና የተሻለ እና ተለቅ ያለ ቤተክርስቲያን ማቋቋም አስፈላጊነቱን አምነው በከፍተኛ ደረጃ እየተረባረቡ እና የገንዘብ ማሰባሰቡ ሂደት በአመርቂ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ባለበት ባሁኑ ሰዓት እንዲህ ያለው መዕመናኑን የሚያበጣብጥ እና
    የቤተክርስቲያኗን እጣ ፈንታ አጠያያቂ የሚያደርግ ግርግር ለምን መፍጠር አስፈለገ?

    እባካቹሁ ለእነዚህ እና ለሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄወች ማብራሪያ ልትሰጡን የምትችሉ ወገኖች ድምጻችሁን አሰሙን።

  2. Enante sewoch blachew blachew yekehneten seltan yemensetew wey yemenshrew engna nen blachew keleba endataskugn.

  3. According to “Feteha Negest” Abune Zecharias Would not be a bishop now. We tried became very nice and good christian. But everything has limit. Now it is beyond our limit. In the near futre we will post every detail of Feteha Negest’s law which is violated by Abune Zecharias with concrete evidence. Ofcourse all Orthodox christians know the fact. But it should be post for future reference.

Comments are closed.

Share