April 15, 2014
11 mins read

ሰማያዊ ፓርቲ የሚታገለው ማንን ነው ? (ግርማ ካሳ)

ግርማ ካሳ

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ እንደጠራ አነበብኩ። ገረመኝ። መጋቢት 28 ቀን በአንድነት ፓርቲ ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። የአዲስ አበባ አስተዳደር ሕጉን ባፈረሰ መልኩ በመጋቢት 28 ቀን ሰልፍ ማድረግ እንደማይቻል ገለጸ። የሰልፉ ቀን ወይንም ቦታ እንዲቀየር የመጠየቅ እንጂ በጥቅሉ ለቀረቡት የሰልፍ ጥያቄዎች እውቅና አንሰጥም የማለት መብት አስተዳደሩ እንደሌለው በመጥቀስ፣ በአስተዳደሩ የተላከዉን ሕገ ወጥ ደብዳቤ አንድነት እንደማይቀበል አሳወቀ። አንድነት ተለዋጭ ቀን እንዲያቀርብ የሚጠይቅ፣ ሕጉን የተከተለ ሁለተኛ ደብዳቤ፣ አስተዳደሩ፣  ላከ። የአንድነት ፓርቲ መጋቢት 28 ቀን ሊደረግ የታሰበውን ሰልፍ ወደ ሚያዚያ 5 ቀን ለማድረግ እንደሚፈልግ አሳወቀ። በሚያዚያ 5 ቀን፣ የሩጫ ዝግጅት ስላለ፣  ቅዳሜ ሚያዚያ 4 ቀን ሰልፉን ማድረግ እንደሚቻል፣ አስተዳደሩ በደብዳቤ  ገለጸ። ግምሽ ቀን የሚሰራበት እንደመሆኑ፣ ቅዳሜ ቀን ሰልፉን ማድረግ እንደማይስማማው የአንድነት ፓርቲ ገልጸ። በሳምንቱ እሁድ ፋሲካ፣ በአስራ አምስት ቀኑ ደግሞ ዳግማይ ትንሳኤ በመሆኑ ፣ ለክርስትና እምነት ተከታዮች አክብሮቱን በመግለጽ፣ ሁለት እሁዶችን (ሚያዚያ  12 እና 19) አልፎ በሚያዚያ 26 ቀን ሰልፉን ለማድረግ ወሰነ።

 

ምንም እንኳን የአዲስ አበባ አስተዳደር መጀመሪያ ላይ የጻፋቸው ሕግ ወጥ ደብዳቤዎች አሳዛኝ የነበሩ ቢሆንም፣ የአንድነት ፓርቲ ሕግ ወጥ ደብዳቤዎችን እንደማይቀበል ካሳወቀበት ጊዜ በኋላ ግን፣ በአንድነት እና በአስተዳደሩ መካከል ሲደረጉ የነበሩት የደብዳቤ ልዉዉጦች ጤናማ መሰሉኝ። ያሉ ልዩነቶችን በሰለጠነ መልኩ ለመፍታት መሞከር ሊበረታታ የሚገባዉ ነው።

 

የአንድነት ፓርቲ ከአስተዳደሩ ጋር በዚህ ሁኔታ እየተነጋገረ ባለበት ሁኔታ፣ ሳይታሰብ የሰማያዊ ፓርቲ ፣ የተለየ ጥያቄዎች ቢኖሩት እሺ፣ ግን አንድነት ባቀረባቸው ጥያቄዎች ዙሪያ፣ ሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ ጠራ።  ይሄም ሰማያዊ ፓርቲን በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎችን እንድጠይቅ አደረገኝ።

 

የአንድነት ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀንን ያለፈው ዳግማይ ትንሳኤ ስለሆነ ነው። ሰማያዊ ፓርቲ እንደ አብዛኞቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግስት በሙስሊሙ ማህበረሰብ አካባቢ እየወሰደ ስላለው አቋም ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ፣ የታሰሩ ሙስሊም እስረኞች እንዲፈቱ፣ ጠይቋል። በዚህ ሁኔታ ለሙስሊሙ ማህብረሰብ ከበሬታ መሰጠቱ ተገቢ ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ለክርስትና እምነት ተከታዮችም ከበሬታ ማሳየት አልነበረበትምን?  በክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ አመት በዓል በሆነበት፣ በዳግማይ ትንሳኤ ቀን፣  ሰልፍ መጥራት ተገቢ ነዉን ?  ፈረንጆች እንደሚሉት «ሴንሲቲቭ» መሆን አልነበረበትምን ?  ሁሉም እምነቶች መከበር አለባቸው ባይ ነኝ። ሰማያዊ በዚህ ረገድ ትክክል አደረገ አልልም። ይሄ የመጀመሪዉ ነጥቤ ነው።

 

ሰማያዊ ፓርቲ ያነሳቸው ጉዳዮች፣ የአንድነት ፓርቲም ያነሳቸው ጉዳዮች ናቸው። የሕዝቡ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው። ሰማያዊና አንድነት ቢዋሃዱ ጥሩ ነበር። ግን ሰማያዊ ለብቻው መጋለብ የሚፈልግ በመሆኑ፣ ተመሳሳይ የፖለቲካ ፕሮግራም ቢኖርምም፣ መዋሃድ አልተቻለም። ነገር ግን የቀረቡ ጥያቄዎች ተመሳሳይ በሆኑበት ሁኔታ፣ ሰማያዊ የራሱን ሰልፍ፣ አንድነት ሊጠራ ባሰበበት ወቅት ለማድረግ ከሚሞክር፣ ከአንድነት ጋር ተነጋግሮ፣  ቢያንስ በጋራ ሰልፍ ቢጠራ መልካም ነበር። ለምን ያ እንዳለሆነ አለገባኝም። ሰልፍ ሲጠራ እኮ አላማ ሊኖረውና ዉጤት ሊያስመዘግብ ይገባል። እንደው ዝም ብሎ ሰልፍ ማድረግ በራሱ የትም አያደርስም። ሰልፍ የሚደረገው ትልቅ መልእክት ለማስተላለፍ ነው። ሰልፉ የተሳካ የሚሆነውም በተቻለ መጠን ብዙ ሕዝብ ሲገኝ ነው።

 

ሰልፉ በጋራ በመጠራቱ፣ እርግጥ ነው ሰማያዊ ለብቻው የተለየ ክሬድት አያስገኝለትም። አንድነትም የተለየ ክሬድት አያገኝም። ክሬድቱን የሚወስዱት በጋራ ነው የሚሆነው። ያ ደግሞ ችግር አለው ብዬ አላስብም። ለሕዝብ የሚያስብ ድርጅት፣  «ድርጅቴ ብቻ ለምን አልተጠቀመም ?» የሚለውን ሳይሆን «ሕዝብን ይጠቅማል ወይ ?» የሚለዉን ጥያቄ ነው የሚያቀርበው። ከድርጅት በላይ የአገርን ጥቅም ያስቀድማል። በዚህ ረገድ ሰማያዊ መጠይቅ አለበት። ይሄ ሁለተኛ ነጥቤ ነው።

 

ሌላው ያስገረምኝ ነገር ቢኖር፣ ሶስተኛ ነጥቤ የማደርገው፣ የአንድነት ፓርቲ በባህር ዳር ሲያደርግ በነበረ ጊዜ፣ ማለት  ሁለት ወራት ገደማ በፊት፣ ለምን ሰማያዊ  በአዲስ አበባ ሰልፍ እንዳልጠራ ነው። ወይንም ደግሞ አንድነት በአዋሳ፣ ድረደዋ በመሳሰሉት ከተሞች ወደፊት ሰልፎች ለማድረግ ባሰበበት ወቅት፣ በአዲስ አበባ ሌላ ሰልፍ ስለማይኖር፣ ያኔ ለምን ሰልፍ እንደማይጠራ ነው።  ለምን ቢያንስ ፣ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተላበሰ፣ ፕሮፌሽናል፣ አክብሮት፣ ለአንድነት ፓርቲ አሳይም ? ለምን አንድነት ሊያደርግ ባሰበበት ወቅት  ሰልፍ ይጠራል ? ባልጠፋ ጊዜ ለምን በዚህ ወቅት ሰማያዊ ጣልቃ ይገባል ? ይህ በአንድነት ፓርቲ ላይ፣ በአገር ዉስጥም ሆነ በአገር ዉጭ ባሉ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ንቀት እንዳላቸው አያሳይምን ? «ሰማያዊዎች የሚታገሉት አገዛዙን ሳይሆን አንድነትን ነው» የሚል ስሜትስ ሰዎች ቢኖራቸው ያስገርማልን ?

 

እንግዲህ ለማጠቃለል ይሄን እላለሁ። ሰማያዊዎች በዚህ ረገድ ትልቅ ስህተት እየሰሩ በመሆናቸው ልብ ይገዙና ቆም ብለው ያስቡ ዘንድ እመክራለሁ። እላለሁ። የአንድነት ፓርቲ ትልቅ መሰረትና ድጋፍ ያለው ድርጅት ነው። አንድነትን ለመደፍጠጥ አስብው ከሆነ፣ የራሳቸው እግር ላይ እንደሚተኩሱ ማወቅ አለባቸው። የአንድነት ፓርቲ የሚያራምደው የሰለጠነ ፖለቲካ የማይመቻቸው፣ «የአገርን ችግር ለመፍታት፣ አንድነት ከኢሕአዴግ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ» ማለቱ ያበሳጫቸው፣  በዉጭ ያሉ ጥቂት ጽኝፈኞችና አክራሪዎች ፣ አንድነት ፓርቲ ተዳክሞ፣  ሰማያዊ ፓርቲ አይሎ እንዲወጣ ከመፈለጋቸው የተነሳ፣ ሆይ ሆይ ፣ እንደሚሏቸው ይገባኛል። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ አገራችን የምትፈልገው እንዲሁ በስሜት የመጋለብ ፖለቲካን ሳይሆን፣ ሕዝቡን በአራቱም ማእዘናት የሚያደራጁ፣ ብስለትና እርጋታ የተሞሉ አመራሮች ያሏቸው፣ በሚስማሙባቸው ጉዳዮች አብሮ ለመስራት የተዘጋጁ፣ የሚከባበሩና የሚቻቻሉ ድርጅቶችን ነው። የጀብደኝነት ፖለቲካን ሕዝቡ አይፈልግም። «እኔ ብቻ ነኝ የማወቀዉ» የሚል ግትር ፖለቲካ ቦታ አይኖረዉም።

 

 

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop