April 11, 2014
2 mins read

የገመና ድራማው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ የፍርድ ቤት ማዘዣ ደረሰው (ማዘዣውን ይዘናል)

(ዘ-ሐበሻ) በከሳሽ የፊልም አሰሪ ወ/ሮ ቤተልሄም አበበ እና በተከሳሽ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ይተላለፍ በነበረው ገመና ድራማ የዶ/ር ምስክርን ገፀ ባህርይ ወክሎ የተወነውና በተለያዩ ፊልሞች ላይ የተወነው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ መካከል ያለው የፍርድ ሂደት መታየቱን ቀጥሎ አርቲስቱ የፍርድ ቤት ማዘዣ እንደደረሰው ለዘ-ሐበሻ እስከነ ማስረጃው የደረሰው መረጃ አመለከተ።

ከዚህ በፊት በዚሁ ክስ የተነሳ በካራማራ አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የተለቀቀው አርቲስት ዳንኤል በወ/ሮ ቤተልሄም የቀረበበት አቤቱታ ለፊልም ሥራ 662 ሺህ 120 ብር ከተቀበለ በኋላ ፊልሙን ሳይሰራ ቀርቷል በሚል “የማጭበርበር” ክስ እንደሆነ ተገልጿል።

ከሳሽ ወ/ሮ ቤተልሄም አበበ የካቲት 6 ቀን 2006 ዓ.ም ጽፋ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበችው ባለ 5 ገጽ የክስ ማመልከቻ፣ 2 ገጽ የማስረጃ ዝርዝር፣ 2 ገጽ ልዩ ልዩ ማስረጃዎች በድምሩ 9 ገጽ ክሱን የሚያስረዱ ወረቀቶች ከፍርድ ቤት ማዘዣ ጋር ለአርቲስት ዳንኤል የደረሰው ሲሆን አርቲስቱም መጋቢት 22 ቀን 2006 ዓ.ም በጠበቃው በኩል መረከቡን በፊርማ አረጋግጧል።

በዚህም መሠረት ዳንኤል ለቀረበበት ክስ ሚያዝያ 3 ቀን 2006 ዓ.ም ለከፍተኛው ፍርድ ቤት በሬጅስራር ጽህፈት ቤት በኩል ማስረጃውን እንዲያቀርብና እንዲሁም ግንቦት 12 ቀን 2006 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጉዳዩ በችሎት እንዲታይ ፍርድ ቤቱ አዟል።

ዘ-ሐበሻ ይህን ጉዳይ ተከታትላ ትዘግባለች።

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop