April 10, 2014
6 mins read

የአሩሲና አካባቢው ተወላጅ አማሮች አስቸኯይ መልእክት ለኢትዮጲያዊው!!!

የአሩሲና አካባቢው ተወላጅ አማሮች አስቸኯይ መልእክት ለኢትዮጲያዊው!!! (መጋቢት 30፣ 2006 ዓ.ም.)

በአማራው አናት ላይ እያንዣበበ ያለውን የጅምላ እልቂት እንዴት ወገኖች ከመጤፍ እንዳልቆጠራችሁት ለኔ ትልቅ እንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ። መቼም ኢትዮጲያዊያኖች ትልቅ የግንዛቤ ችግር ነው ያለብን። ከሰሞኑ በአሩሲ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች በተገኙበት የተመረቀው በተቆረጠ እጅ ላይ የተቀመጠ ጡት የሚያሳይ ሀውልት ከፍተኛና ምናልባትም በኛ ትውልድ ያልተስተዋለ ጎሳን መሠረት ላደረገ ፍጅት ብዙ እርምጃዎችን ያንደረደረን ድርጊት መሆኑን ምን ያህላችን ያስተዋልነው ጉዳይ እንደሆነ ሳሰላስለው ብዙዎቻችን እያስገመገመ ያለውን አርማጌደን አይቀሬነት አምነን የተቀበልን ያህል እንዲሰማኝ ሆኗል። በምረቃው ቦታ የመገኘት እድል የገጠማቸው የአካባቢው ተወላጅ አማሮች በስነስርዓቱ ላይ ስለተገኘው ግዙፍ መጠን የነበረው ታዳሚ እንዲህ ላለ ታላቅ ጥፋት መሳሪያ መሆን ታሪክ የማይረሳው እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊት መሆኑን ገልፀው አሳሳቢም ነው ብለዋል።

ታዳሚው ፊት ላይ ይነበብ የነበረውም የጥላቻ ውፍረትና የበቀልተኝነት ስሜት ስለተከታዩ ነገር አመላካች መሆኑን በሀዘን ገልፀዋል። እስከ አሁን ድረስም በኦነግ እና ኦህዴድ ጭፍን ብሄርተኛ ተከታዮች ዘንድ ሲሰበክ የነበረውን የአማራ ጎሳን ከኦሮሚያ የማፅዳት ውጥን የይለፍ ምልክት የሰጠ ድርጊት አድርገን እንቆጥረዋለን ብለዋል። አክለውም ሁኔታውን ተከትሎ ሀውልቱ በቆመበት አሩሲና አካባቢው እየተስተዋለ ያለው አንዳንድ አፍራሽ እንቅስቃሴ ይህን እምነታቸውን ምክንያታዊ እንደሚያደርገው ገልፀዋል። የዚህ ሴራ አንዱና ብቸኛው አላማ አማራውን ማስፈጀት መሆኑን ገልፀው ሀውልቱም ለዚህ በአማረው ላይ ለሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ህያው ማስጠየቂያ እንደሆነ አብራርተዋል። በህዝቡ መካከል ያለመቻቻልና የጥላቻ መንፈስ ስለሌለ እንዲቀሰቀስ የታሰበው የጎሳ ግጭት የመነሳት እድሉ ጠባብ ነው የሚለው የፖለቲከኞች አስተያየት የግል የፖለቲካ አጀንዳን ለመግፋት ሲባል በዜጎች ህይወት ላይ ቁማር መጫወት መሆኑን ገልፀው የፓለቲከኞቹን በንቃት እንሳተፍበታለን ስለሚሉት የሀገሪቱ ፖለቲካና በህዝቦች ተቻችሎ እና ተሳስቦ የመኖር በሀል ላይ ስላሳረፈው አፍራሽ ተፅዕኖ ያላቸውን ዝቅተኛ መረዳትም የሚያሳጣ ነው ብለዋል። ዛሬ ይህን ከአማራ የፀዳ ኦሮሚያን ስለመመስረት የሚያቀነቅኑ እንደ ኦነግ እና ኦህዴድ ያሉ ብሄርተኛ ድርጅቶች ተከታዮች የሆኑ፣ በዚህ አውዳሚ ፍልስፍና የሰከሩና ህሊናቸው የታወረ ፤ ከዚህ በፊት በአርባጉጉ በበደኖ ወዘተ የተፈፀመውን ዘግናኝ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት አይነት ለመፈፀም ወደሗላ የማይሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ አክራሪ ብሄርተኞች መፈልፈላቸውን በማመላከት የዚህን የእልቂት ጥንስስ አውዳሚ መጨረሻ የተቀረው ኢትዮጲያዊ ተረድቶ በሰላማዊ ሰልፍና በመሳሰሉት የእሪታ ድምፁን በአስቸኯይ እንዲያሰማላቸው ጠይቀዋል። ካራ ተስሎብን ወደ ምታችን የምንነዳ በሚሊዮን የምንቆጠር ዜጎች ፖለቲካው ውስጥ በሚርመሠመሡ ጉዶች ጉዳያችን እንዲህ አትኩሮት መነፈጉ የጉዳዩ ብቻ ሳይሆን የመፍትሄውም ብቸኛ ባለቤቶች የመሆናችንን መሪር ሀቅ የጋተን አጋጣሚ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል። አያይዘውም ኢትዮጲያዊው ወገን ለጥያቄያቸው ባፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የማይችል ከሆነ ግን እነሱ የሚቻላቸውን እንደሚያደርጉና አካባቢውን በጅምላ ከመልቀቅ ጀምሮ የተቀረው የአማራ ተወላጅም አካባቢውን በመልቀቅ የራሱንና የልጆቹን ህይወት እንዲታደግ ሰፊ ቅስቀሳ ውስጥ እንደሚሰማሩም አሳስበዋል።

አምደፂዮን ዘተጉለት፤ ከአሩሲ ነገሌ

 

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop