April 9, 2014
6 mins read

የጃርት ጉባኤ ርደት (ሥርጉተ ሥላሴ ሲዊዘርላንድ -ዙሪክ)

ባድማ በጃርት ተሰቅዛ

በአረማሞ አራሙቻ ናውዛ

እህህን ሰንቃ ደንዝዛ

ሰቀቀን ታጥቃ አርግዛ።

ሬት ጨጎጎት ተደልዛ

መቀነት በእሾኽ ተገንዛ፣

ቁም ስቅሏን አዬች

ይህው በልዛ።

`ጃርተ ምርት እሾህ

ፍጥረተ ነገሯ ውጋት

በበቀል – ተዋቅራ

በደም – ተቋድሳ

በደጋን ታምሳ – ተደቁሳ፤

እሾህ አዘራች መልሳ፤

የጃርት ገላ መላልሳ።

ህልመ ራዕዩ ምልግልግ

የላንቁሶ ውሃ ዝልግል

ጃርተ – ልብ፤ የእሾህ ልግ

የአሜክላ የቋሳ ድግዳግ።

ጃርትስ አሰኛት የበቀል ብቅል

ቋቱ ’ማያውቅ ግል

የጃርት ህሊና የውጋት ግልል፣

ሰባራ ገል።

እሾህስ አልቦ የለም ጃርት

ከዘረ እሾህ የለም ምርት

የጠቀራ ናስ ሃሞት

ዙሪያ ገባው ማት፤

… ህልፍት የሐገር ቅብረት።

አንተ አለህና በቤትህ

ትሰማለህም ታያለህም

የጃርትን ትዕቢት፤ … የቀን ጥሰት

የበቀል አምላክ አትለፋት፤

የህዝብን ዕንባ ህማማት፤

እ!-እ!-እ!-እ!እ!-እ!-

እም – እም – አም እ——-ም!

 

ውስጥ

 

ይህን ግጥም ለመጀመሪያ ጊዜ መድረክ ላይ ያቀርብኩት የመጀመሪያዋ ሐገራዊ ፓርቲ ሊ/መንበር ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ የፓርቲያዋን የአንድነትን ዓላማና ተግባር ለማስተዋወቅ፤ እንዲሁም ደጋፊ አካላትን ለማዋቀር እ.አ.አ በ2008 በታህሳስ ወር አውሮፓ በተዘዋወረችበት ወቅት ሲዊዝ ጄኔባ  መጥታ በነበረችበት ጊዜ ነበር። ከመክፈቻ ንግግሬ በኋላ ግጥሙን አቅርቤ ስጨርስ እንዲህ አለች „አንቺ ምን አለብሽ?! እንዲህ የልብሽን በነፃነት ታቀርቢያለሽ። እኛ የግጥም ምሽት አዘጋጅተን ከቢሮችን ውስጥ በታጣቂዎች ተከበብን“ በማለት ተክዛ ቆዬችና አይኗን ወደ እኔ ላከችው።

አዬሩ ፈቅዶ ሁለታችንም አገናኘን። በመንፈስ ተቀራረብን – ተዋኽድን። አስተውላም አዬችኝ በውስጧ – እኔም ምላሹን ደረብኳት። ህልሜ ተሳክቶ ሴት አቅሟን ብቃቷን እንዳዛ በወሳኝ የኃላፊነት ቦታ በእርግጠኝነት ስታቀርብ ከማዬት በላይ ሐሴት አልነበረም። ተስፋውንም ቀጠልኩበት። ቃሌን ሳላጥፍ ከተግባር አርበኞቿ፤ ከሲዊዝ የአንድነት ድጋፍ ሰጪ አካሎቿ ጋር ጥሩ የሰመረ የሰላም ጊዜ አሳለፍን። እንዲሁም በአለም ዙሪያ ካሉ ተቆርቋሪዎቿ ጋርም የሚያስመካ የፍቅር አንድነት ገነባንበት። አቅለ ቢሱ ወያኔም ስትመለስ እግር ብረት ለእሷና ለልጇ ለሀልዬ አዘጋጅቶ ቢጠባቅታም ደጋፊዎቿ ግን በያሉበት ታጥቀውና ተግተው ታገሉ። ከአውሮፓ ወደ ቃሊት። እጅግ አስደንጋጭና መራራም ነበር። ዛሬ ደግሞ ለሴት ተቆርቋሪ ሆኖ ሙጃው ወያኔ አለሁኝ ሲል አዳመጥን።

እኔ በግሌ ከጃርት የእሾህ ፈል እንጂ ሌላ እምጠብቀው የለም። ጠንከር ያሉ ትችቶችን ላጥ አድርጎ ማስመሰሉን አቀለጠበት – አይፍር መንፈሱን በአሻቦ ያወራረደ – ግልብ። እንደዚህ ላጥ እያደረገ ቀሰማውን እንደሚያስነካው ስለምን የተባበሩት መንግስታት ድንጋጌዎች አክብሮ በሰቧዕዊ መብት ላይ የሚደልቀውን ጭፈራ አይገታም? ወኔ ካለው በሺህ የሚቆጠሩ ሴት እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፍታ። ከዚህ ከለበጣ ኮሜዲ ተግባሩ በፊት። ሲያንጎላች ይከርምና እንዲህ ይባንናል – የጉም ሽንት። ለቅብ እንዳረገደ እንዳረገረገ 23 ዓመት —– ነጎደ።

የኔዎቹ በሉ ተመራርቅን አንለያይ። የተመቼ ጊዜ እንሆ ተመኘሁላችሁ። ፍቅርና ናፍቆት በገፍም ተላከ ለእናንተ ——– — ለክብረቶቼ።

ማሳሰቢያ — 1.   ግጥሙ – ግንቦት 20 ቀን 2000 ዓ.ም ክላይነአንደልፊንገን – ሲዊዘርላንድ ተጻፈ። ከመጀመሪያው መጸሐፌ „ተስፋ“ ላይ ከገጽ 49 እስከ 50 ይገኛል።

2.  ይህቺ ምልክት ለንባብ እንዲያመች አንድ ፊደል መዋጡን ታመልካታለች – ከትህትና ጋር።

ለቅሶ የሚያበቃበት ቀን ናፈቀኝ!

እግዚአብሄር ህዝባችንና ልዕልት ኢትዮጵያን ይጠበቅ። አሜን!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop