April 6, 2014
2 mins read

የጠበቆች ማህበር በአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ላይ የወንጀል ክስ መመስረታቸው ተሰማ

በአዲስ አበባ ታትሞ የሚወጣው ማራኪ መጽሔት እንደዘገበው በቅርቡ በሰይፉ ፋንታሁን የኢቢኤስ ሾው ላይ ቀርቦ በአዲስ ፊልሙ ላይ አደንዛዥ ዕፅ ተጠቅሞ መስራቱን ለማህበረሰቡ ያሳየው አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ የጠበቆች ህብረት በጋራ የወንጀል ክስ አቅርበውበታል።

ጠበቃ ማቲያስ ግርማ ለማራኪ መፅሄት እንዳስረዱት በክሱ ላይ ሰይፉ ፋንታሁንና አለማየሁ ታደሰ ደጋፊ ሀሳብ በመስጠታቸው ክስ ይመሰረትባቸዋል ብለዋል። አርቲስቱ ምንም እንኳ ለፊልም ግብዓት “መስለው ሳይሆን ሆነው” ለመስራት ያደረጉት ተግባር ቢሆንም ህብረተሰቡን ከወንጀል ለመጠበቅ ሲባል ክስ እንደተመሰረተባቸው የጠበቆች ተወካዩ አስረድተዋል።

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ በፊልሙ ላይ
የጠበቆች ማህበር በአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ላይ የወንጀል ክስ መመስረታቸው ተሰማ 1
“ይህንን የበለጠ ማጣራት የነበረባቸው ፖሊስና አቃቤ ህግ ቢሆኑም ፣ በግልፅ በሀገሪቱ የአየር ክልል የተላለፈውን መረጃ ዝም ማለታቸው እንዳሳዘናቸውም ገልፀዋል። በሀገሪቱ የወንጀል ህግ ስርዓት በተለይ ግሩም በክሱ ጥፋተኛ ከተባለ እስከ ሰባት አመት እንዲሁም የ50ሺ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል።

በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ 1996/97 አንቀፅ 525 ንዑስ አንቀፅ/ሀ መሰረት እስከ ” አደንዛዥ ዕፅን እራሱ ወይም ሌላ ሰው ሊጠቀምበት በማሰብ የገዛ፣የተጠቀመ፣ እንዲጠቀም ያደረገ፣,,,” ከ7 ዓመት እስከ 50ሺ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል። እነ ሰይፉ ደግሞ “ወንጀልን ባለማወቅ” ክስ ተመስርቶባቸዋል።

መጽሔቱ ዘገባውን ሲያጠናቅቅ ለግሩም በቅርብ መጥሪያ ይደርሰዋል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል።

3 Comments

  1. ድንቁርና ነው ምን አልባት ድራግ (አደንዛዥ እጽ ስለሳበ ታላላቅ የፊልም አክተሮችን የመስለ ምስሎት ሊሆን ይችላል የሚገርመግን ታላላቆቹም ይህን አያደርጉም) በጣም ነጻነት አለበት በሚባሉት ታላላቅ ሃገሮችም እንደዚህ አይነት ቅሊት ተደርጎ አያውቅም ቀሽም ነው።

  2. I was thinking is drug legal in Ethiopia? When I saw his interview with seifu and I was also so angry how they disrespect Ethiopian the show like this air. Any it to be heard the lawyer’s are stand for it!

  3. ካነበብኩት “በጣም ያስጠላኝ ወሬ”
    ከግሩም ኤልያስ ሐሺሽ በተለየ ሐገርን እያደነዘዘ ያለው ህወሀት ኢህአዴግ ሆኖ ሳለ ፈሪ ሁላ አህያውን ኢሕአዴግን ፈርቶ ዳውላውን ተወናይ እያወገዘ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
    የወያኔ ሐገር የማጥፋት ስራን ለማስቆም ሁሉም በየፊናው እየተሯሯጠ ባለበት ሠአት ስለ ግሩም የምናስብበት ትርፍ ጊዜ የለንም ብንላቸው እንዲህ አሉን ይህማ ነውር ነው ይህንን ተዋናይ አርአያ የሚያደርጉ ስላሉ ድርጊቱን ልናወግዘው ይገባል፡፡
    ማን ይሙት ኢትዮጵያዊ ተወናይ አርአያ ሊደረግ ይችላል ተለጣፊ ሁላ
    ለማንኛውም ልድገመው ሐገርን እንደ ሐሺሽ እያደነዘዛት ያለው ወያኔ እንጂ አንድ ተራ ተዋናይ አይደለም፡፡
    ግሩም ኤርሚያስን ስራው ስህተት ከሆነ ብትከሠው ፖለቲከኛ ስላልሆነ ፍርድ ቤት ደህና ውሳኔ ይሰጥሀል፡፡
    In skating over thin ice our safety is in our speed.

Comments are closed.

Previous Story

እስክንድር – ይናገር!

Next Story

ያልዘሩትን ማጨድ ከቶ አይቻልም! (ግንቦት7)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop