እስክንድር – ይናገር!

ከሥርጉተ ሥላሴ 06.04.2014 (ሲወዘርላንድ – ዙሪክ)

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ

ይመስክር – ይናገር
ያ —– አርበኛ ፍቅር
የእናቱን ነገር።
የአቅም – አንደበት፤
የመሆንም – ችሎት።

እስክንድር ይናገር
የአዬር አልቦሽ ኑሮ ——- ይዘርዝር
——————— ይመንዝር።
ትርጉሙ – ለእናቱ
ቅኔውም –  ለአዳራው፣
የማግዶ – ውሎው።
ያስቀደመ – እማን
የድጓውም – ዳን
ዓይነታ – የኪዳን።
ሩ———ቁ፤ ——- አሳቢ
አስቀድሞ – አላሚ
ማግስትን – አቅላሚ
ትንቢትን – ተላሚ።

እስክንድር ይናገር
የእናቱን ነገር።

ተሰራ በእስክንድር
የነፃነት – ቀመር፤
በተግባሩ – ንጥር።
ተበጀ – በእስክንድር
መንፈሳዊ – መስመር
የብራና – ህብር።

የቃና —– አባቱ
ረ ለባቱ።

ዝማሬ ማህሌት
ቀኑ ቀናያለት።

ሚስጥር ተ —— ዚያ፤ ማዶ
ቀራንዮን —— ወዶ፤
እራሱን – ዬሰጠ
ትዳሩን – ዬሰጠ
ናፍቆቱን – ዬሰጠ
ኑሮውን – ዬሰጠ
ምቾቱን – ዬሰጠ
እንግልት – መረጠ
ነገነን ——– ያማጠ።

እስክንድር ይናገር
የእናቱን ነገር።

አለሁልሽ ያለ
ያላወላወለ ————
ብዕር ወለወለ
ለሃቅም አደረ
አብነት —- ሰመረ።
የጽናት አድባሩ
የተቋሙ —-  ድሉ
የወርቅ እሸት ጓሉ
እሱን አሉ አሉ!

ብቃቱ – መካሪ
ኮንፓሱ – መ
ራዕይ – አሳማሪ!

                                  ሥጦታ ለአባ ትርጉም – ለጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ።

 

 

 

 

ተጨማሪ ያንብቡ:  የለውጥ-ሀይሉ የጅብ እራት እንዳይሆን!!! - አማኑኤል ታደሰ (ከድሬዳዋ)

1 Comment

  1. ብዙ እስክንድሮች ብዙ ሪዮቶች ይፈጠራሉ አሁንም አሉ እዉነት ትመነምናለች እንጂ አትበጠስም

Comments are closed.

Share