ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

መጠላለፍ ወደየትኛው ገደል እየመራን ነው?

የአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው “እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!” በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ ይገባበዙ ነበር! ይህ ባህል በጠንካራ የሥልጣኔ ላጲስ ተደምስሶ ጠፍቶ በምትኩ እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም መንገዱን ሁሉ መቆላለፍ አዲስ የመጠላለፍ ባህል እየተተከለ ነው፤ የመጠላለፍ ባህል የሚታየው በባቡር መንገዶች ላይ ብቻ አይደለም፤ በብዙ ነገር መጠላለፍ ባህል እየሆነ ነው! የዚህ ዝንባሌ መጨረሻው አሸናፊ የሌለበት ሙሉ ጥፋት ነው።

በመንገዶች ላይ ጥቂት በጫት የሚነዱ መኪናዎች በመቶ የሚቆጠሩ መኪናዎች እንዳይንቀሳቀሱ ለማድረግ ይችላሉ፤ ሲያደርጉም በየቀኑ እየታየ ነው፤ በማኅበረሰባዊና በፖሊቲካ ግንኙነትም አንድ ሰው የሚዘራው መርዝ የጊዜው ሁኔታ በሚፈቅድለት ፍጥነት የማኅበረሰቡን አባላት ያዳርሳል፤ እንቆቅልሹ እንደሚለው ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! ማለት መርዝ፣ እሳት፣ ተላላፊ በሽታ በሕዝቡ ላይ ማሰራጨት ከአምስትና ከአሥር ዓመታት በኋላ ውጤቱ ምን እንደሚሆን መገመት አያቅትም።

ድብብቆሽ አይጠቅምም፤ሁለት ነገሮችን በግልጽ ማውጣት አለብን፤አንደኛ በአሜሪካና በአውሮፓ መሽጎ ፍርሃቱንና ሽቁጥቁጥነቱን ለመሸሸግ መርዙን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚረጨው ለምንድን ነው? አገዛዙ ይህንን የሚያደርግበት ምክንያት ግልጽ ነው፤ ከፋፍሎ የመግዛት ዘዴ ነው፤ ከአገዛዙ ጋር በሚደረግ ትግል ከታች ሆነው ከሥልጣን ውጭ የሆኑ ዜጎች በሥልጣን ላይ ከተቀመጡት ጋር እየተቆራቆዙና እየተጋጩ ናቸው፤ ይህንን እኔ የላይና-የታች ግጭት (vertical conflict) የምለው ነው፤ ከወያኔ/ኢሕአዴግ ጋር የሚደረገው ትግል ይህ ነው፤ ይህንን ለማክሸፍ ወያኔ/ኢሕአዴግ ትግሉን ከላይና-ታች አውጥቶ ወደጎን-ለጎን ግጭት (horizontal conflict) ሊለውጠው ይፈልጋል፤ ከወያኔ/ኢሕአዴግም ውጭ በጎሠኛነትና በሃይማኖት አክራሪነት የደነዘዙ ሰዎችም ትግሉን ጎን-ለጎን ሊያደርጉት እየሞከሩ ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያዊነት ሰዎች በፈቃዳቸዉ ሊለዉጡት የማይችሉት ማንነት ነዉን ? (በሸንቁጥ አየለ) 

የፖሊቲካ ትግልን የሚመሩ ሰዎች በጎሠኛነትና በሃይማኖት አክራሪነት ስሜት እየተሳቡ ትግሉን የላይና-የታችነቱን ጠብቀው በተደራቢነት የጎን-ለጎን ትግሉን ይጨምሩበታል፤ ይህ ሲሆን ሀሳብ፣ ጉልበትና ሀብት ይከፋፈላል፤ ይበታተናል፤ ወደዓላማ ለመድረስም ያስቸግራል፤ ወያኔ ወደመጨረሻው ላይ ኢሕአዴግ ብሎ የሰየመውን ቀፎ አስቲፈጥር ድረስ በስሙ ውስጥ ኢትዮጵያን የሚያነሣ ነገር አልነበረውም፤ ወያኔን ለድል ያበቃው የማታለያ ስሙ እንደሆነ በበኩሌ አልጠራጠርም፤ ከሃያ ሁለት ዓመታት የጎሣ ሥርዓት በኋላ ኢትዮጵያ ቆስላለች እንጂ አልሞተችም፤ የአሐዝ ማስረጃ ለማቅረብ ባልችልም በብዙ ጎሣዎች መሀከል ጋብቻ እንደዱሮው እየቀጠለ ነው፤ ይህንን የቆየ የዝምድና ሰንሰለት ለመበጠስ የሚጥሩም አሉ።

ኒው ዮርክ ተቀምጦ ትኩስ ውሻ (ሆት ዶግ!) እየበላ ለእስላም ኦሮሞዎች የመገዳደያ መመሪያ የሚሰጥ ሰው የመንፈስ ጤንነቱን እጠራጠራለሁ፤ ይህንን የኒው ዮርክ ቀረርቶ ተከትሎ ሌላ የመጠላለፍ አዋጅ ሰማን፤ ቴዎድሮስ ካሣሁን ለአጼ ምኒልክ ስለዘፈነ ከበዴሌ ቢራ ፋብሪካ ጋር ለማስታወቂያ የገባው ውል ሥራ ላይ ከዋለ የበዴሌን ቢራ አንጠጣም ተባለና ማስታወቂያው ተሰረዘ ይመስለኛል፤ ማን እንዳሸነፈ ወደፊት ጊዜ ይነግረናል፤ አሁን ደግሞ ሌላ ማዘዣ ሰማሁ፤ “የስ” በሚለው ውሀ ጠርሙስ ላይ እንስራ የተሸከመችው ኮረዳ መስቀል አድርጋ ነበር፤ ልጅቱ ከነመስቀልዋ የምትታይበትን ውሀ እስላሞች አንገዛም ስላሉ ነጋዴዎቹ መስቀሉን አወለቁባት! ይህንን ማዘዣ ላወጣው አክራሪ እስላም ወረባቦ ቅዳሜ ገበያ ሄዶ እንዲጎበኝ አሳስበዋለሁ፤ ዛሬ ተለውጦ እንደሆነ አላውቅም እንጂ እኔ ብዙ ጊዜ ተመላልሼ እንዳየሁት የወረባቦ ኮረዶች ሁሉ ትልልቅ መስቀል በአንገታቸው ላይ ይታይ ነበር፤ መስቀል የእምነት መግለጫ ይሆናል፤ አያጠራጥርም፤ ግን መስቀል ጌጥም ይሆናል! መስቀል የናዚ ምልክትም ሆኖ ነበር! ለማናቸውም የዚህ ዓይነቱን መጠላለፊያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገምዱ ሰዎች ዓላማቸው ማንንም ለመጥቀም ሳይሆን ፍቅርንና ሰላምን ለማደፍረስ ነው፤ የኢየሱስ ክርስቶስ መሠረታዊ ትምህርት ክፉን በክፉ አትመልሱ ነውና ለተበጠሰው መስቀል አጸፋውን ለመመለስ ማሰብ አይገባም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቅዱስ ፓትርያርኩና የማኅበረ ቅዱሳን ልዩነት ወደ ሃይማኖት አደገ

ከኒው ዮርክ የተሰማው ቀረርቶም ሆነ የመስቀል ማስወለቁ ጉዳይ የተከሰተበትን ጊዜ ልብ ልንለው ይገባል፤ እስላሞች ስለነጻነት የሚያደርጉት ንቅናቄ በጣም እየጋለ በመሄድ ላይ እያለ ክርስቲያኖችም የዜግነት ግዳጃቸው አድርገውት ድጋፋቸውን በሚሰጡበት ጊዜ ነበር፤ ይህ መሆኑ ጥርጣሬን ይጋብዛል፤ የገጠመውን የእስላሞችና የክርስቲያኖች ሰልፍ በማደፍረስ ወይም በመክፈል የሚጠቀም ማን ነው? የሚጎዳውስ ማን ነው? ሁሉም የትግል አጋፋሪዎች ለዚህ ጉዳይ የሚያስፈልገውን ክብደት ቢሰጡት ትግሉ በጎን-ለጎን እንዳይሄድና እንዳይዳከም ይረዳል፤ ከዚያም በላይ አክራሪነት የሚባለውና የሚያስከትለውም ሽብርተኛነት የሚመጣው እንዲህ እያለ ነው፤ እግዚአብሔር ከዚያ ያውጣን!

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
መጋቢት 2006

(ምንጭ: Mesfin Woldemariam Blog)

6 Comments

  1. >>> ታላቅ የምሥራች ለትውልዱ ሁሉ..”አዲስ የመጠላለፍ ባህል እየተተከለ ነው” ምን ያልተተከለብን አለ? ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ አዲስ ሊተከል ግን ብዙ ነባር ነገሮች ተነቅለው ጠፍተው ነው። ያው እንግዲህ የማፍረስ አባዜ መሆኑ ነው።

    >>ከወያኔ/ኢሕአዴግም ውጭ በጎሠኛነትና በሃይማኖት አክራሪነት የደነዘዙ የፖሊቲካ ትግልን የሚመሩ እየተሳቡ ትግሉን የላይና-የታችነቱን ጠብቀው በተደራቢነት የጎን-ለጎን ትግሉን ይጨምሩበታል፤(የአራት ማዕዘን ታጋዮች) አዲስ ባሕል!
    ህወአት/ወያኔ ወደመጨረሻው ላይ ኢሕአዴግ ብሎ የሰየመውን ቀፎ አስኪፈጥር ድረስ በስሙ ውስጥ ኢትዮጵያን የሚያነሣ ነገር አልነበረውም!አሁንም የብሄር ብሄረሰብ ሕዝቦች ሆኑ የኢትዮጵያ ህዝቦች ይልና ለነጻነት በበረሃ በገባባት ክፍለ ሀገርና ህዝብ መካከል ከልሎና ከፍሎ የጎሳና የብሔር ተዋረድ በመፍጠር “የአፓርታይድ መንደርን” ሲፈጥር ለየት ለማለትም ያንኑ ነጻ ያወጣውን ሞትንለት የሚሉትን ድሃ የትግራይ ህዝብ ብሄራዊ ቋንቋህ አንግሊዘኛ ካልሆነ ብለው ሲያደናቁሩት ይታያሉ…ትግሬ እንግሊዛዊ ሊሆን ደደቢት በረሃ ገባ? ለመሆኑ እራሱን መሆን ያስጠላው ህወአት ታላቋንና ሰፊዋን ኢትዮጵያ እንዴት ሊሆን ይችላል!? ይልቁንም በድሮ አለቆቻቸው ሻቢያ የደነቆሩ ህወአት ኦነግና ኦብነግን ይዞ ዙሪያውን ያጯጩሃል። ግን ሁሉም ዳር ይዘው አንዱ ሌላውን እየወነጀለ የውስጥ በጋራ የማፍረስ የቤት ሥራቸውን እየሰሩና እየሰረሰሩ ፶ዓመት ተልመው፣ ፳ዓመት መሽገው፣ ፳፪ ዓመት የቁራ ጩኽት የአዞ እንባ ያነባሉ። የሚተዳደሩበትና የሚሰሩበት ግን በአንድ ማኒፌስቶ ነው።ሆኖም ከሃያ ሁለት ዓመታት የጎሣ ሥርዓት በኋላ ኢትዮጵያ ቆስላለች እንጂ አልሞተችም፤

    **እርግጥ ይህ የሆት ዶግ በል(የሞቀ ውሻ መር!) የዲያስፖራ ቡልጠቃ…የሙስሊም ኦሮሞ የሜንጫ አብዮት የኢትዮጵያውያንን ደካማ ጎን ሁሉ እያጠኑ በየዋህ ዜጎች ትከሻ ላይ ተንጠላጥሎም ይሁን ተሸጉጦ የሀገር ሉዓላዊነትን ታሪክ እያጠፉ…ወጣቱን በተሳሳተ አመለካካት እያተራመሱ.. የህዝብ ሰላምና አብሮ መኖርን የሚያደፈረሱ ..ትውልድ አምካኝና አባካኝ የጠላት መልዕክተኖች…የሀገር ፖለቲካል ኢኮኖሚና መከላከያ ይገባለናል…ሰፊ መሬት ተሰጥቶናል ቋንቋችንን ተናግረናል መሄድ ይገባናል ይላሉ። ያው ልዩ በደል ደርሶበታል ተጨቆነ የሚሉት ድሃ የኦሮሞ ሕዝብ ድሮም ዛሬም አላለፈለትም ሰላሙን አጥቶ ሲያዋጉት ብዙ ዘመን አለፈበት። እነሱ በባዕዳን ገንዘብ አልፎላቸው በድሃ ልጅ ደም ኖረዋል፣ ወደፊትም የዋህና ሞኝ እርሃብ ያንገላታውን በዘር በቋንቋ አቧድነው እርስ በእርስ አጫርሰው በሰላም ለመኖር አቅደዋል።ግን እስልምና እጅ፣ እግርና አንገት በሜንጫ ቁረጥና ፅደቅ ይላልን!?

    ***ፖለቲካ ቁማርተኞች የተለያዩ የሽብር ካርታን ይስባሉ…በግብፅ ኢትዮጵያዊ አደለንም የአባይን ግድብ አንደግፍም! በሳውዲ ኣረቢያ እኛ ኦሮሞዎች ኢትዮጵያዊም ክርስቲያንም አደለንም!የቀድሞው ኦፒዲዮ የኢህአዴግ ፕሬዘዳንት በኋላም የአድነት ፓርቲ መሪ የሆኑት የአጼ የምኒልክ ሀውልት እንዲፈርስ ፊርማ አሰባስበዋል ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ነበር አሁን ከፓለቲካም ከቤታቸውም ወጥተው መንገድ ላይ ናቸው፡፡ ቴዎድሮስ ካሣሁን ለአጼ ምኒልክ ስለዘፈነ የበዴሌ ቢራ እዳትጠጡ ተባለ ህወአት አብሮ አዳመቀ…አይ የድሃ ነገር ይህ ጠግበው በሚደፉ ሀገር እንጂ ተርበው በሚደፉ ያፍሪካን ፳፭ ከመቶ ድራጎት ለሚቦጭቁ ሀገር አይሰራም እኮ! ፲፩ከመቶ የደነቆረ ቦልጥቀኛ…ወግ ወጉ እንደ አህዮቹ አሉ። ለግራዚያኒ ሀውልት መቆምና በሳውዲ ዓረቢያ ኤምባሲ በወገናችን ለደረሰ ግፍ ተቃውሞን የሚያስከለክሉትም የኢህአዴግ ክንፍ አባላት የዚሁ የሆት ዶግ መር ቡልጠቃ አቀንቃኝ ተንታኝና በታኝ ኅይሎች ናቸው። በቤተ መንግስት አጥር ላይ መሰቀል አየን! የባንዲራው አንበሳ ላይ መስቀል አለው!…‹‹የስ›› በሚለው ውሀ ጠርሙስ ላይ እንስራ የተሸከመችው ኮረዳ መስቀል አድርጋ ነበር፤ ልጅቱ ከነመስቀልዋ የምትታይበትን ውሀ እስላሞች አንገዛም ስላሉ ነጋዴዎቹ መስቀሉን አወለቁባት!የዚህ ዓይነቱን መጠላለፊያ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገምዱ ሰዎች ዓላማቸው ማንንም ለመጥቀም ሳይሆን ፍቅርንና ሰላምን ለማደፍረስ ነው፤ይህን የሚያስብ ኢትዮጵያዊ እስላም አልነበረም! አይኖርም! ለረጅም ግዜ ተካሔደው የተቃውሞ ሰልፋቸው እንኳን በሜንጫ አብዮተኞች ከመጠለፉ በፊት..ድንቅ ግሩም እንኳንም እኛን ዓለምን አስደምሟል…የጥንታዊ አብሮ መኖርን ትሩፋትን አስቀጥሏል ግን “በጥበጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል?”

    **የእስላሞችና የክርስቲያኖች ሰልፍ በማደፍረስ ወይም በመክፈል የሚጠቀም ማን ነው? የሀገርን ሉዓላዊነት ለባዕድ አሳልፎ በመስጠት ተጠቃሚው ማነው? የሃይማኖት አክራሪነት ስንል በዐላማ ጸንቶ፣ ሕገመፅሀፍ-ቅዱሱንም ይሁን ሕገ-ቁራዓንን ለማስከበር ተግቶ መሥራትና መልካም ትሩፋትን ለትውልድ ማውረስ እንጂ በሰው ሀገር ተቀምጦ በቀን አሥር ግዜ እየበሉ፣ እየጨፈሩና፣ እያስጨበጨቡ፣በአመፅና ሽብር ሽቀላ መተዳዳር የሃይማኖት አክራሪ ሳይሆን ሃይማኖትን እራሱን ማሸበር፣ማርከስም፣ማክሰርም ነው። ፪፻ሺህ የዓይን (ክላኮማና ትራኮማ) በበሽታ በሚሰቃዩ የኦሮሞ ሕዝቦች መንደር ፳ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድንጋይ መካብ!?ለመሆኑ ይህንን ማውጣት የቻለ ክልል ሁልግዜ ለምን ያለቅሳል?ለነገሩ ሳይሞቱ ሐውልት የቀረፁ ታጋይ ፓትሪያክና የጦር ሀይል ባለሥልጣናት አሉን አደለምን!?እንግዲህ የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል…ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል…ትውልድ ነቅቶ እራሱን ካልጠበቀ ከሄደው እየሄደ ሰፊውም ጎዳና አጣብቂኝ አለው።የላጭን ልጅ ቅማል በላው! ሠራዊታችን ሀገር የመታደግ ኀላፊነት እንዳለበት መዘንጋት የለበትም! እግዝሐብሄር ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን በቸርነቱና በቃል ኪዳኑ መሠረት ይጠብቃት ይህንንም የዋህ ሕዝብ ከብልጦች፣ ከአስመሳይ፣ ምንደኞች፣ አመፅ ሽብርና ውንብድና ይጠብቀው።አሜን! ሰላም ለሁሉም ይሁን በቸር ይግጠመን>>>

  2. Here we go! Professor Mesfin is now joining the choir of extremism sector of the Amhara society. Even though he is not mentioning Oromo by name, he is covertly talking about the Oromo in the issues related to Tewodros Kassahun. Professor Mesfin’s erroneous view about Oromo people is not really a secrete issue. He started to negatively express himself about Oromo people some decades back. His hateful expression about the Oromo was clearly visible in one of his early books. When I was a junior high school I read his book on “Geography”. The book was really not fully a geography book. Even though the book as written in English, it is not uncommon to find hateful expressions about Oromo in Saba script on some of its pages. The expressions portray Oromo people as cruel and people who came from unknown place.

    For the professor it would have been the best not to go back to the era of blindness to deny the right of other group of people who express their disappointments on denial of their true history and what happen to them in in the past. Those decades when elites try to treat non-habesha Ethiopian as sub-human is gone and we have left those behind us at least three decades ago. Any person can worship Menilik if s/he wants to do it. But no one has a right to have concerts in Oromo cities and towns to justify Menilik’s wrong deeds to Oromo people. Professor Mesifin is also not expected to defend this act at this age after learning more about the pain of mistreating others in the last 22 years.

  3. I share Professor’s concern. Instead of having a collective struggle aginst WOYANE the side struggle intiated by various groups for for diffent agenda is/will weaken our collective effort to get rid of WOYANE. Let our effort be to clean the house from Woyane and then have a National agenda to go forward from their.

  4. From GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay)

    Thanks my dear professor Mesfin Weldemariam. I still pray for your healthy and energy. The God of Ethiopia already showed you before you die my enemy and your enemy mercenary Meles Zenawi who is responsible for all these ethnic and religious conflict to occur in our country has been removed once for all by the God of Ethiopia.

    What you stated on your commentary is clearly right on the mark. These Ethiopian Islamic Mujahedeen trained in Saudi Arabia, Pakistan are many of them followers of radical Wuhabee. Not only the Wuhabist group lost their rational mind for such backward ideology, but the young Muslim Oromos, Hararee, Ogadenee, Afar and others are obsessed with the faith for radical Islam . They are pathetic to say the least.

    Last time a friend who visited Ethiopia a region with Muslim majority saw the population getting high and intoxicated almost in every corner of the street he walked, and saw young Muslims tuned their mind to a lunatic sate by a the leaf of hallucinating drug called ‘Katt’. At one moment, he said “I saw a man urinating in a standing position and beaten up by the surrounding Muslims for violating Islamic code”. Can you believe that? The Muslim regardless a man, must urinate in a sitting position and for that he is considered in violation of Islamic code. While surprisingly, even their Sheikkes are intoxicated with this highly hallucinating drug called Kaat considered acceptable.

    Can someone explain to me how on earth a man is beaten and forbidden to urinate in standing position for not sitting like a woman when urinate is a violation of Islamic code, not millions and millions of Ethiopian Muslim getting high and intoxicated by a toxic drug? Are these not and the likes who are now demanding do not want to see a picture of women wearing a cross on any commercial trade mark. It made me think deep, how far these lunatic and drug addicts are going crazy with a hate for Christian women photo posted with cross wearing for commercial.

    I can see why these lunatic are getting more savagery and lost in the modern world of rational thinking every day, because their mind is highly poisoned by Katt, and nicotine /tobacco. Shockingly, they want to beat someone for urinating in a standing position when they failed to learn the elementary knowledge of Islamic code that, “getting high with any hallucinating drug” is considered as ‘ a code of prohibition’ told by their leader Mohammed. Yet, they claimed they are Islam or hate to see women wearing cross on her neck? Nerve! How about cleaning their mind from hallucination chewing drugs before talking about picture of a woman with cross wearing crap

    You are right that in Ethiopia, many Muslim women wear cross on their neck and forehead. We know that many of them were converted by the Jihadist and terrorist Grang Ahmed. Therefore, is hard for their culture to leave it even after 300 years.
    This is not new only in Ethiopia. Muslim women in Mali the “Tuwareg” wears multiple cross symbols on their neck and forehead. These fanatic Muslims in Ethiopia and in Somalia are worst than the Boko Haram in Nijeria. Their mind is completely bankrupted and taken away by outsiders psychological subversion and by CKatt chewing habit. These lunatics still are the first to oppose cross symbol in any Christian products and the first to go to the Mosque being intoxicated by Ckatt. Nerve! What an ignorance!

    Can’t they see the symbol in Microsoft windows? Or do they know what reads in the mighty Dollar their masters in Saudi Arabai in love with? Why can’t these fanatic Muslim in Ethiopia refuse to touch any money that was touched by Christians hands? ha!

    I am telling you the Muslim fanatics and Oromo fanatics are pushing the Amhara and Christian followers too hard and too far. I have no idea where it is heading, but if the pushers keeps pushing the envelop too far, it wont be as smooth and easy road when the other side is running out its patience. The result could be, cruel and unpredictable response when a victim is cornered for so long and all sides will be a victim.

    The scenario seemed to continue unchallenged for now, and spoiled too much, this is because, there is a lunatic group in power that is ready to destroy the country including its own population, using fanatic Islam and fanatic ethniQos a road for destruction.

    There are groups in Diaspora like the fellow called Sadik Mohammed interviewed in ESAT who claimed there is no “fanatic/extreme/terrorist Islam in Ethiopia”. There is also a fellow in Washington (forgot his name;- he is the chair person of the Ethiopian Muslim community in DC claiming “there is no different in Islam. All Muslim are one and followed one faith called Islam”. But that is not the case. He is a liar! All dozens of different Islam preaches different. That is why he and his likes and the wuhabists hate Alhabash. Yet, Alhabash claimed also it is the right Islam. The Wuabist also claimed it is not the Suni but, the Salaffi version of Islam as right. So and so and so…

    This all religious players are the product of TPLF Ethnic federalism which produces conflict by giving religious ethnic groups material incentives to perform their dirty job. Sad!

Comments are closed.

Share