June 15, 2014
18 mins read

የጨጓራና የአንጀት ቁስለት – (አልሰር)

በሀገራችንም ሆነ በመላው ዓለም በዚህ በሽታ የሚጠቁ ህሙማን ቁጥር ከፍ ያለ ነው፡፡ በዚህ ህመም የጨጓራው የተለያዩ ክፍሎች ወይም የትንሹ አንጀት የመጀመሪያው ክፍል (ዱዮድነም) ሊጠቃ ይችላል፡፡ ቁስለቱ ጨጓራ ውስጥ ከተፈጠረ ጋስትሪክ አልሰር ሲባል በትንሹ አንጀት ውስጥ ሲከሰት ደግሞ ‹ዱዮድናል አልሰር› ተብሎ ይጠራል፡፡
የጨጓራና የአንጀት ቁስለት ፆታና ዕድሜ ለይቶ የሚከሰት በሽታ አይደለም፡፡
የበሽታው መንስኤዎች ምን ይመስላሉ?
1. የጨጓራና የአንጀት ቁስለት 90% መንስኤው ሔሊኮ ባክተር ፓይሎሪ ተብሎ የሚጠራ ባክቴሪያ ነው፡፡ ይህ ባክቴሪያ በተለይ የጨጓራው የመጨረሻ ክፍል ‹አንትረም› አካባቢ በከፍተኛ ደረጃ በመራባት የዚህን አካባቢ መቆጣት አንትረል ጋስትራይተስ ይፈጥራል፡፡ ይህም ሁኔታ በቀጣይነት ከፍተኛ የጨጓራ አሲድ ማመንጨትን ያመጣል፡፡ ከመጠን በላይ የሚመነጨው አሲድ የጨጓራ ወይም የትንስራ አንጀት የመጀመሪያ ክፍል ዱዮድናም መቆጣት ወይም መቁሰል (አልሰር) ያስከትላል፡፡
2. የተቀሩት 10% የበሽታው መነሻዎች
ሀ/ ሲጋራ፣
ለ/ የተለያዩ መድኃኒቶች ለምሳሌ ለቁርጥማትና ለራስ ምታት የሚወሰድ እንደ አስፕሪንና የመሳሰሉ ክኒኖች፣ ለአስምና ሌሎችም ህመሞች ሊሰጥ የሚችሉ የአስቴሮይድ (ፕሬድኒዛሎን) ኪኒኖች
ሐ/ ብዙ አልኮል መጠጣት
መ/ ከፍተኛ የጭንቀት ስሜት ውስጥ መግባት ናቸው፡፡
ከሀ-መ የተጠቀሱት የጨጓራውን የውስጥ ሽፋን በቀጥታ በመቦርቦር ወይም የአሲድ ማመንጨት በማብዛት ሂደት የጨጓራ መላላጥ ወይም መቁሰል ያስከትላሉ፡፡

የበሽታው ምልክቶች ምን አይነት ናቸው
1. የጨጓራ አልሰር ያለባቸው ህሙማን ምግብ እንደተመገቡ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በተለይ እርግብግቢት አካባቢ የማቃጠል ወይም የመቁረጥ፣ ሆድ ክብድ የማለትና የምግብ አለመፈ ጨት ስሜቶች ይከሰቱባቸዋል፡፡ ይህ የሚፈጠ ረው የተቆጣ ወይም የቆሰለ ጨጓራ የተመገብነ ውን ምግብ ለመፍጨት ስለሚቸገር ነው፡፡
2. ቁስሉ በትንሹ አንጀት ዱዮድነም ውስጥ ከሆነ ያለው የበሽታው ምልክቶች የሚከሰቱት በባዶ ሆድ ወቅት ነው፡፡ ማለትም የሚቀጥለው መመገቢያ ሰዓት ሲቃረብ እና ሌሊት ወይም ሊነጋጋ ሲል ይሆናል፡፡ እነዚህ ህሙማን እርግብግቢት አካባቢ የመቁረጥና የማቃጠል ስሜት ይኖራቸዋል፡፡ አንዳንዶች ማቃጠል ወደ ጀርባቸው ያስተጋባል፡፡
3. ቁስለቱ ጨጓራም አንጀትም ውስጥ ካለ ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች ተደባልቀው ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
በሽታውን ለማወቅ የሚደረጉ ምርመራዎች ምን ይመስላሉ?
ህመምተኛ የሚናገራቸው ምልክቶች ጠቋሚ ከሆኑ ከዚህ በታች የሚዘረዘሩ የምርመራ ዘዴዎችን መጠቀም ይቻላል፡፡
1. የደም፣ የሰገራ ወይም የትንፋሽ የሒሊኮባክተር ባክቴሪያ ምርመራ አዞ የባክቴሪያ መኖር ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
2. ኢንዶስኮፒ ምርመራ በማድረግ ጨጓራና አንጀቱን በመፈተሽ
ሀ/ የመቁሰል ሁኔታ መኖሩን ማጣራት
ለ/ ከጨጓራ ላይ ናሙና ወስዶ የሒሊኮ ባክተር ባክቴሪያ መኖር ማጣራት ይቻላል፡፡ ኢንዶስኮፒ ተመራጩ ዘዴ ነው፡፡
3. የ‹ባሪየም› ኤክስሬይ በተለይ የጨጓራ መጥበብን ለማጣራት ይረዳል፡፡
የጨጓራ የአንጀት ቁስለት ካለ በምን ዘዴ ይታከማል?
1. የበሽታው መነሻ 90% አካባቢ ባክቴረያ ስለሆነ ህክምናውም ይህን ባክቴሪያ የሚያጠፋ አንቲባዮቲክ መስጠት ነው፡፡ በተጨማሪ ባክቴሪያው የፈጠረው ከፍተኛ አሲድ ማመንጨትን ለማቆም የሚሰጥ መድኃኒት አለ፡፡ ብዙውን ጊዜ ሁለት አንቲባዮቲኮችና አንድ አሲድ የሚቀንስ መድኃኒት በጣምራ ከ7-14 ቀናት እንዲወሰዱ ይደረጋል፡፡ በዚህ ዘዴ ከ90-95% ህሙማን ከፍተኛ መሻሻል ያገኛሉ፡፡
2. በተለያዩ ሌሎች ምክንያቶች የሚመጣው ህመም አንደኛ እንደ ሲጋራ፣ ክኒኖች፣ አልኮል የመሳሰሉትን ማቆምና አንቲአሲድ ሽሮፕ እና አሲድ መቀነሻ መድኃኒቶች መውሰድ ይጠቅማል፡፡ ጥሩ የጤና መሻሻል ከታየ በኋላ ጥቂቶች የህመም ማገርሸት ሊታይባቸው ይችላል፡፡ ስለዚህ ለቀጣይ ህክምና ወደ ሐኪም መመለስና ማማከር ያስፈልጋል፡፡ በጊዜውና በአግባቡ ያልታከሙ ህሙማን ዘንድ በሽታው ሊወሳሰብና ወደ ከባድ የጤና ችግር ሊያመራ ይችላል፡፡ ከነዚህም መሀል
ሀ. የጨጓራ መድማት (ቡና አተላ የመሰለ ትውከት ወይም ሬንጅ የመሰለ ሰገራ ማየት)
ለ. የጨጓራ ወይም አንጀት መበሳት
ሐ. የጨጓራ መጥበብ
መ. የቁስሉ ወደ ሌላ አካባቢ መዝለቅ
በተለይ የጨጓራ አልሰር ወደ ካንሰር መለወጥ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት እንዳይከሰቱ የበሽታው ምልክቶች ሲከሰቱ ወደ ጨጓራና የአንጀት በሽታዎች እስፔሻሊስት ቀርቦ በአግባቡ መመርመርና ትክክለኛ ህክምና ማግኘት የግድ ይላል፡፡
በተለይ ለዚህ መሰል የጤና ችግሮች ዋንኛው የምግብ መመረዝ አለመስማማት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ የጤና ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ለዚህ ችግር መነሻ የሚሆነው በቀላሉ ለብልሽት ከሚዳረጉ ምግቦች ጋር ተያይዞ ነው፡፡ የሥጋ፣ የወተትና የእንቁላል ተዋፅኦዎች ሳልሞኔላ በሚባል ባክቴሪያ የመበከል እድላቸው በጣም ከፍተኛ ነው፡፡
ስለዚህ በአግባቡ ባልተያዙና በቆዩ በተለይ በደንብ ሞቀው በማይበሉ ምግቦች ውስጥ ባክቴሪያው በጣም ይራባል፡፡ ጤነኛ ያልሆነ ምግብ የተመገበ ሰው በቀላሉ ይታመማል፡፡ የመመረዝ ምልክቶች ከ12-24 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ይከሰታሉ፡፡ ከዚህ ባጠረ ጊዜ ምልክቶች ከታዩ ከባድ መመረዝ ተከስቷል ማለት ነው፡፡
ከምልክቶቹ መሀል ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ተቅማጥና ትኩሳት የመሳሰሉት ናቸው፡፡ በአብዛኛው ችግሩ በራሱ ይቆማል፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ ትውከት፣ ተቅማጥ ያጋጠማቸው ህሙማን የሐኪም እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህም በደም ስር የሚሰጡ ፈሳሾችና አንቲባዮቲክ መረዳት ይገባቸዋል፡፡
በሽታው በህፃናትና አዛውንቶች በተለያዩ በሽታዎች (ስኳር፣ ኤች.አይ.ቪ ካንሰር የመሳሰሉ) የተጠቁና የሰውነት የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ላይ በጣም ይጠነክራል፡፡ ለከፍተኛ ጤና መቃወስና ለሞትም ሊዳርግ ይችላል፡፡ በአጠቃላይ በበዓል ዙሪያ ምግብና መጠጦችን ከገደብ በላይ መውሰድ ወትሮውንም እንዳይጠቀሙ የተከለከሉትን ነገር ተዘናግቶ ወይም ደፍሮ መጠቀም ከፍተኛ የጤና መታወክ ሊያስከትል ይችላልና መቆጠብና መጠንቀቅ በጣም ይበጃል፡፡
በሌላ በኩል በእንቁላል፣ በሥጋ፣ በመጠጥ ውስጥ በቀላሉ ሊራባ የሚችል ሳልሞኔላ የሚባል ባክቴሪያ ስለሚኖር ሰዎች በሚመገቡበት ወቅት ወደ ሰውነታቸው ይገባል፡፡ ሰዎች እነዚህን ምግቦች በንፅህና መያዝ በተለይም በንፅህና ውስጥ ማስቀመጥ ያስፈልጋል፡፡ ተቀናንሰው ከሚቀርቡ ምግቦች የተረፈ ምግብ ለዚህ ሁኔታ በጣም የተመቻቸ ነው፡፡ ከተማ ውስጥ አይብ፣ ቅቤ የወተት ተዋፅኦዎች አይስክሬም እና ሳንድዊቾች ከፍተኛ የባክቴሪያ መራቢያ ናቸው፡፡ በጥንቃቄ ይዞ በጊዜ ተጠቅሞ መጨረስ ያስፈልጋል፡፡ በተለይ የሰውነት አቅማቸው የተዳከመ በተለያዩ በሽታዎች የታመሙ እንደ ኤች.አይ.ቪ ህሙማን ስኳር፣ ካንሰር፣ ጉበት በዕድሜ በጣም ትንንሽ ወይም በዕድሜ የገፉ ከሆኑ በቀላሉ ይጎዳሉ፡፡ ሰውነታችን ውስጥ ይህ ባክቴሪያ ሲገባ ሰውነት ጥሩ የመከላከል ሁኔታ ላይ ካለ ባክቴሪያው ይሞ ታል፡፡ ነገር ግን ደካማ በሆነ አካል ውስጥ የመመ ረዝ አጋጣሚው ከፍተኛ በመሆኑ ከመጠን በላይ የተመረቀው አሲድን በሽሮፕ እንዲቀንስ በማድረ ግ ፀረ-ባክቴሪያ መስጠት፡፡ በተለይ በሳልሞኔላ አማካይነት በአልን ተከትሎ ይመጣል፡፡
ለስላሳ፣ ኬክ፣ ሳንድዊች፣ ወተት፣ አይብ፣ እንቁላል፣ ሥጋ በሚገባ በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው፡፡ እነዚህ ምግቦች ለረጅም ጊዜ ሳይበላሹ የመቆየት ባህሪ ያላቸውም በተለይ ሳንድዊች፣ አይስክሬም በአጭር ጊዜ መበላት አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ለመሞቅ አይችሉም፡፡ ቢቻልም ምግባዊ ለዛቸው አይኖርም፡፡ ቶሎ መጠቀምና የተረፈውን ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ከሀገራችን ሁኔታ አንፃር ወጥ ነገሮች በደንብ ፈልገው (ሞቀውና ተንተክትከው) የሚቀርቡ ምግቦች ባክቴሪያውን የመግደል አቅም ስለሚፈጥሩ መጠቀም ይቻላል፡፡ አይብ ግን ብዙ ጊዜ ተቀናንሶ ነው የሚቀርበው፡፡ ማሞቅም አይቻልም በመሆኑም በትኩሱ አንደተሰራ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ከምግብ መመረዝ ጋር ብዙ ጊዜ የሚያጋጥሙት ችግሮች አንደኛ ከምግብ መመረዙ ጋር ተያይዞ ምልክቶቹ በፍጥነት ይታያሉ፡፡ የተመገበው ሰው በአማካይ ከ24 ሰዓት እስከ 48 ሰዓት ሊቋቋም ጊዜ ውስጥ ሊታመም ይችላል ከፍተኛ መመረዝ ካለ በተመገበ ከ2-6 ሰዓት ውስጥ ምልክቶችን ሊያሳይ ይችላል፡፡ ከላይ ከሆነ ጊዜ ይሰጣል፡፡ አብዛኛው ጊዜ የሚሰጠው ምልክት ማቅለሽለሽ በተለያየ ደረጃ ውሃ መሰል ተቅማጥ እና የምግብ ማስመለስ ትኩሳት ከነዚህ ጋር ተያይዞ ምን ያህል ጉዳት መጠን ላይ እንዳለ ማወቅ መዳከምና መዝለፍለፍ ከፍተኛ መጠን ላይ መድረሱን ያመላክታል፡፡ በጥቂቱ ቁርጠት እና የመሳሰሉት ከታየ ግን ቀስ በቀስ በራሱ ጊዜ ይጠፋል ስለዚህ የባክቴሪያው መጠን ምን ያህል እንደሆነ መለየት፡፡

የጥንቃቄ እርምጃዎች
እራስን ማዳመጥ በተለምዶ የማቅለሽለሽ የመቁረጥና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ሲኖሩ ሰዎች ‹‹የበላሁት ምግብ አልተስማማኝም›› ይላሉ፡፡ ይሄ ነገር በመጠኑ ምልክት ካሳየ ቀላል ሊሆን ስለሚችል ሰውነት ሊከላከለው ይችላል፡፡ በዚህ ወቅት እንደ ቡና፤ የወተት ተዋፅኦ እና የመሳሰሉት ያንጀት እንቅስቃሴ ስለሚያፈጥኑ ተቅማጥ ያመጣሉ፡፡ ከነዚህ ለተወሰነ ቀናት መቆጠብ፡፡ ብዙ ፍሳሽ እንደ ኦ አር ኤስ መውሰድ እረፍት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በከፍተኛ ደረጃ የተመረዘ ከሆነ ተቅማጥ ከፍተኛ ትውከትና ቁርጠት ስለሚያዳክመው እርዳታው ጠንከር ያለ መሆን አለበት ትኩሳትም ካለ በሆስፒታልና ክሊንኮች ሄዶ ግልኮስ ሊያገኝ ይገባዋል፡፡ ጠንካራ ምልክቶች ስላሉም ፀረ ባክቴሪያ መድኃኒቶችም ሊሰጡት ይገባል፡፡ ይሄ የህክምና ባለሞያ እርዳታ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ህመሙ በራሱ ጊዜ ይቆማል፡፡ በተዳከሙ ሰዎች ላይ ግን ወዲያው ሊጥላቸው ስለሚችል ህክምናዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል፡፡ ፈሳሽን በምግብ መልክ በመድኃኒት መልክ እያዘጋጁ መስጠት ከሶስት እስከ አምስት ቀን ከተሰጡ ህመሙን በመቀልበስ ወደ ጤናማ ሁኔታ መመለስ ያስችላል፡፡
ማንኛውም የበዛ ነገር ሁሉ ከሰውነታችን የማስተናገድ አቅም በላይ በመሆኑ የበዙ ነገሮችን መቀነስና በመጠኑ መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ የመፍጨት ሂደቱ የመዛባት ሁኔታ እንዲኖረው ስለሚያደርግ የህመም መንስኤ ይሆናል፡፡ ቅባት በብዛት ከተወሰደ በተለይ ቅባት የመፍጨት ችግር ለምሳሌ እንደ የሐሞት ከረጢት ባለባቸው ሰዎች ላይ በተለይም አንድ ኩላሊታቸው በቀዶ ጥገና የወጣ ሰዎች ትንንሽ ቅባት አልፎ አልፎ ካልሆነ በብዛት ስመጣ ስለማይፈጭ የተቅማጥ በሽታ ያስከትላል፡፡ በመሆኑም አደጋውን ለመቀነስ መሞከር ያስፈልጋል፡፡µ

 

Source: zehabesha Newspaper

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

ትላንት አንድ ወዳጀ ደውሎ “አሳየ ደርቤን” ታውቀዋለህ ወይ” አለኝ፡፡ እኔም አላውቀውም አልኩት፡፡ ኢንጅኔር “ኡሉፍ” የተባለ ሰው የዛሬ ሰባት ዓመት ያሰራረውን ጥልቀትና ስፋት ያለውን ዘገብ አቅርቦታልና አዳምጠው አለኝ፡፡ እኔም “ጉድሺን ስሚ ኢትዮጵያ–ከባድ አደጋ

ተቆርቋሪ የሌላት ኢትዮጵያ – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

ወገኖቸ፤ ለጊዜው ትችቱን እናቁምና ለወገኖቻችን እንድረስላቸው፡፡፡ በቤተ አማራ ወሎ ቡግና የተከሰተው ርሃብ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ለወገን ደራXኡ ወገን ስለሆነ እባካችሁ ህሻናትን እናድን፤ ለግሱ፡፡ ጦርነት ያመክናል፤ ተከታታይ ጦርነት አረመኒያዊነት ነው፡፡ ጦርነት ካልቆመ የረሃቡ

እግዚኣብሔር ግን ወዴት አለ?

Go toTop