May 3, 2013
5 mins read

የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠ

ከነመራ ዲንሳ

ነመራ ዲንሳ
የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን አረጋገጠ 1

ከ፩፯ አመት የደርግ የጭቆና አገዛዝ ማብቂያና ስርአቱ ካበቃበት ከ፩፱፰፫ ወርሐዊ ግንቦት ጀምሮ ለ፪፪ አመታት የስርአቱን ለዉጥ ተከትሎ ስልጣንላይ በሀይል ተቆናጦ ያለዉ የህወሐት መንግስት አምባገነንነቱ ወደ አፓርታይድ ስርአት ተቀይሮዋል።
ለዚህም ማሳያዉ ላለፋት ፪፩ አመታት በሙዋቹ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መሪነት በሐገሪቱዋ ዉስጥ እጅግ ኢሰብአዊ ድርጊት ዘርንና ክልልን መሰረታዊ ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል አሁንም እየተፈፀመ ነዉ።
ለመጥቀስ ያክል ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ የህወሐት ባላስልጣናት ትእዛዝ መለስን ጨምሮ በጋምቤላ፣በኦሮሞ፣በአማራ፣በኦጋዴን እና በደቡብ ህዝቦች ላይ አስከፊ የእስራት የግርፋት እና የጅምላ ግድያ ወንጀል ተፈፅሟል አሁንም ድረስ የቀጠለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ ዜጎችን በሀገሪቱዋ በየትኛዉም አካባቢ የመኖር የሀገሪቱዋ ህገ መንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ የዘር ማፅዳት ወንጀል በህወሐት አምባገነን መሪዎች እየተፈፀመ ነዉ።
በ፩፱፰፫፣፰፬ ጋምቤላ፣ከ፩፱፰፬ እስከ ፩፱፰፮ በኦሮምያ ጅማ፣ሰጠማ፣ሲጊሞ እና ጌራ የሚባሉ አካቢዎች፣ከ፩፱፰፬ እስከ ፩፱፰፰ በአማራ ተወላጆች ላይ በበደኖ፣ወተር፣በአርሲ ባሌ፣በሐረር ጉርሱም አካባቢ፣ከ፩፱፱፱ እስከ ፪፲፻ በደግሐቡር፣በቀብሪደሐር እና በኦጋዴን በመለስ ዜናዊ ትእዛዝ በመከላከያ ሠራዊት በጦር ሄሊኮፕተር በመታገዝ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል።ከወራትም በፊት በደቡብ ኦሞ እና በጋምቤላ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል። ይህ ሁሉ በደል ሲፈፀምና አሁንም እየተፈፀመ ባለበት ወቅት በሀገሪቱ ፍርድ ቤት ማንም ተከሶ ለፍርድ የቀረበ የለም ነር ግን ይሄን ሁሉ በደል እና ግፍ የተቃወሙና የፃፋ ንፁሀን ያገሪቱ ዜጎች ለአፈና፣ለስደትና ለእስር ተዳርገዋል።
በስደት ያሉትን ባልዘረዝርም ሀገር ዉስጥ ሆነው በሀገሪቷ ህገመንግስት ተጠቅመው ስርዐቱን ስለተቃወሙና ስለፃፋ ከእድሜ ልክ እስከ ረጅም አመት እስራት ተፈርዶባቸዉ በእስር ላይ ያሉና እስርቤትም ሆነው ይግባኝ በማለትም ሆነ ባለማለት በሀገሪቷ የመጨረሻዉ ጠቅላይ ህወሐት ፍርድ ቤት ፍትህ መቀበሩን ያበሰሩንን ጀግኖች ጠቅሳለሁ፣
ሌልሴ ወዳጆ፣ርዮት አለሙ፣እስክንድር ነጋ፣በቀለ ገርባ፣አንዱአለም አራጌ፣ዉብእሼት ታዬ፣የድምፃችን ይሰማ ኮሚቴዎች>>>ወዘተ ኮራንባችሁ ያላችሁበት ህይወት የኛ ሆኖ ቢያቃጥለንም።
በአንዱአለም እና እስክንድር ነጋ ላይ የይግባኝሽ ፍርድ ቤት ያፀናዉ ፍርድ ከመለስ ሞት በውሓላም ህወሐት ፍትህን የገደለ የአፓርታይድ ስርዐት መሆኑን አሳውቆናል።
ስለሆነም ከሰሜን ኮርያ በላይ የከፋው የህወህት ስርዐት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን እየተደገሰለት ባለዉ የዉሸት ፖለቲካ ክስ እሱንም በይግባኝ ፍርድ ቤት ጭምር ከምናምን እድሜ እስር ጋር ቂሊንጦ ወይም ዝዋይ እስርቤት ማየታችን አይቀርም።
እናም የኢትዮጵያ ፌደራል ከፍተኛ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገሪቷ ፍትህ መቀበሩን አረጋግጦልናል።
ውድ አንባቢዎቼ ነገር ግን እኔም ተመስገን ደሳለኝ ነኝ እናንተስ?
ሀገራችንን እና ህዝቧን ከአፓርታይድ ስርዐት ዛሬዉኑ እንታደግ!!!
ህዝብ ያሸንፋል።

1 Comment

  1. እኔን ከሁሉ የሚያሳዝነኝ እንዲህ ዐይነት ያልተገባ ፍርድ የሚሰጡ ህሊናቸውን ለሆዳቸው የሸቀጡ ዳኞች መኖራቸው ነው። ከ1953ቱ መፈንቅለመንግስት በሁዋላ ብርጋዴር ጀነራል መንግስቱ ንዋይ፣ ኢትዮጲያ ውስጥ የፍርድ ስርዐት ስለወረደ አምርረው ማዘናቸውን ገልፀው ነበር። ዛሬም ቅንጣት ታህል የፍርድ ስነስርዐቱ አለመሻሻሉን ማየት ምንኛ ያሳዝናል።

Comments are closed.

04
Previous Story

ጽናት – ሁሉም ሊያየው የሚገባ ፊልም (Video)

abune petros
Next Story

ግርማዊነታቸው የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልት ሲያቆሙ የተናገሩት

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop