(ከመለሰው ጥበቡ)፦ በያዝነው የአውሮፓውያን የውድድር ዓ መ ት ጣ ሊያ ና ዊ ው የ ፊ ት መ ስመር ተጫዋች አንቶኒዮ ዲናታሊ በጣሊያን ሴሪያኤ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች ሆኖ አጠ ና ቋ ል ፡ ፡ በ28 ጐ ሎ ች ፡ ፡ ለ ዩ ዲ ኒ ዜ የሚጫወተው ዲናታሊ ክለቡ በዘንድሮው የ ው ድ ድ ር ዓመት 4ኛ ደ ረ ጃ ን ይ ዞ በማጠናቀቁ ለቀጣይ አመት በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚያሳትፈውን እድል በማግኘቱ አንቶኒዮ ዲናታሊን በአውሮፓ የውድድር መድረክ ልናየው እንችላለን፡፡
አንቶኒዮ ዲናታሊ የተወለደው ጣሊያን ኔኘልስ ከተማ እ.ኤ.አ በ1977 ነው፡፡ 10ቁጥር ለባሹ አንቶኒዮ ዲናታሊ ቁመቱ1 ሜትር ከ70 ሳንቲ ሜትር ነው፡፡ ገና በወጣትነት እድሜው ማለትም በ1996 ኢምፖሊ ለ ተ ባለው ክለ ብ በመፈረም የኘሮፌሽናል እግር ኳስ ህይወቱን ጀምሯል፡፡ በኢምፖሊ ክለብ ቆይታው 159 ጊዜ ተሰልፎ 48 ጊዜ ኳስን ከመረብ ጋር አገናኝቷል፡፡
በ1997 ደግሞ በውሰት ውል ኢሞፔዞላ ለተባለ ክለብ ተዛውሯል፡፡ በዚህ ክለብ ቆይታው 33 ጊዜ ተሰልፎ 6 ጐሎችን መረብ ላይ አዋህዷል፡፡ ከአመት በኋላ ቪያረጅዮ ለተባለ ክለብ በውሰት ቆይታው በ25 ጨዋታዎች 12 ጐሎችን ማስቆጠር ችሏል፡፡
እ.ኤ.አ ከ2004 ጀም ሮ በ ሴ ሪ ያኤ ለሚሳተፈው ክለብ ዩዲኒዜ በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡ በዩዲኒዜ 223 ጨዋታዎችን አድ ርጐ 110 ጐ ሎ ች ን መ ረ ብ ላ ይ አሳርፏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለጣሊያን ብሔራዊ ቡድን 36 ጊዜ በመሠለፍ 10 ጐሎችን አስቆጥሯል፡፡በአጨራረስ ብቃቱ የተመሠከረለት አንቶኒዮ ዲናታሊ በታላላቆቹ የሴሪአው ክለቦች ማለትም በኢንተርሚላን፣
ኤሲሚላን፣ እንዲሁም ሮማ ቢፈለግምፈቃደኛ አልሆነም፡፡
ተጫዋቹ ከሌሎች አንጋፋ የጣሊያን አጥቂዎች ጋር የሚያመሳስለው ነገር አለ፡፡ ይኸውም እድሜው 34 ደርሶ በጐል ጨራሽነቱ ምስጉን መሆኑ ነው፡፡ ከእርሱ በፊት እንኳ በ30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ሆነው በሴሪአው ከፍተኛ ግብ አግቢ በመሆን ከ200 በላይ ጐሎችን ያስቆጠሩ ጣሊናዊ አጥቂዎች በርካታ ናቸው፡፡ ከነዚህም መካከል የጁቬንቱሱ አሌክሳንድሮ ዴልፔሮ፣ የኢንተር ሚላኑ ክርስቲያን ቪየሪ፣ የሮማው ፍራንችስኮ ቶቲ፣ የኤሲሚላኑ ፊሊፖ ኢንዛጌ፣ የቦሎኛዎቹ ሮቤርቶ ባጂዮ እና ማርኮ ዲቫዮ ይገኙበታል፡፡
ከላይ የተጠቀሱት የጣሊያን ተጨዋቾች በሴሪአው ያስቆጠሯቸውን ጐሎች ብዛትና በሴሪአው የውድድር ዓመት መጨረሻ ከፍተኛ ጐል አስቆጣሪነት ክብርን ሲቀዳጁ በተደጋጋሚ የተስተዋለው እድሜያቸው ከ30 ካለፈ በኋላ መሆኑ ነው፡፡ አንቶኒዮ ዲናታሊ ባለፈው 2010 29 ጐሎችን በሴሪአው ሲያስቆጥር እድሜው 33 ዓመት ነበር፡፡
ዘንድሮ ደግሞ በ34 ዓመቱ እንዲሁ 28 ጐሎችን አስቆጥሯል፡፡
ከ2002 ዓ/ም ጀምሮ ኢሊኒያ ከተባለች ፍቅረኛው ጋር በትዳር ተጣምሮ ሁለት ልጆችን ያፈራው ዲናታሊ በዩዲኒዜ ደጋፊዎች ዘንድ በእጅጉ የሚወደድ ተጨዋች ነው፡፡ ቶቶ በሚል ቅፅል
ስም የሚጠራው ዲናታሊ በ2010 የዓመቱ ምርጥ የጣሊያን ተጨዋች ክብርን አሸንፏል፡፡
ለሀገሩና በጣሊያን ተ ዟ ዙ ሮ በ ተ ጫ ወ ተ ባ ቸ ው ክለቦች እስካሁን 499 ጊዜ ተሰልፎ 212 ጐ ሎ ች ን በ ማ ስ ቆ ጠ ር ጠ ን ካ ራ ነ ቱ ን አስመስክሯል፡፡ ወ ደ ፊ ት የመጫወት ወኔ እ ን ዳ ለ ው የ ሚ ና ገ ረ ው ዲ ናታሊ በ ዩ ሮ 2012 ዋ ን ጫ ለጣሊያን ብሔራዊ ቡ ድ ን ቢ ሰ ለ ፍ እ ን ደ ሚ ደ ሰ ት ደስተኛ መሆኑን ተናግሯል፡፡