April 24, 2013
3 mins read

ስለ ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም የሚወራው ምንድን ነው?

እንደፌስቡክ ያሉ የማህበራዊ ድረገጾች ማጥፊያም ማልሚያም ከሆነ ሰነባብቷል። ከአንድ አመት በፊት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሞቱ ተብሎ በሰፊው በየማህበራዊ ድረገጾች ከተወራ በኋላ ህዝቡ ‘ሞቱ አልሞቱም በሚል ሲወዛብ ቆትሮ በኋላም ፕሬዚዳንቱ በቲቪ ቀርበው ለረዥም ሰዓታት ተኝቼ ብነሳ ይህ እንዲህ ተወራብኝ ብለው ነበር።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ በኢትዮጵያ የስነጽሁፍ ታሪክ ግዙፍ ታሪክ ካላቸው ጸሐፊያን መካከል በዓሉ ግርማ በጣና ሀይቅ ላይ ከሚገኙት  ደሴቶች ካሉ በአንዱ ገዳም በሕይወት አለ ተብሎ እንዲሁ በሰፊው በማህበራዊ ድረገጾች ከተወራ በኋላ መጨረሻው ምን እንደሆነ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው። (በዚህ ዙሪያ በውስጥ ገጻችን ሰፋ ያለ ዘገባ ይዘናል – ይመልከቱት)

ሸሽተው በስደት ዘምባብዌ የሚገኙት የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት መንግስቱ ሃይለማርያምም ሞተዋል የሚለው ዜና መወራት የጀመረው ከሳምንታት በፊት ነበር። የኢሳት ራድዮ ይህ ወሬ ሲዛመት ወደ ዙምባዌ ደውሎ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ባለቤት ወ/ሮ ውባንቺ ቢሻውን አግኝቶ አነጋግሯቸው ነበር። ወ/ሮ ውባንቺም መንግስቱ በመልካም ሁኔታ በሕይወት እንዳሉ ሲናገሩ ጋዜጠኛው እርሳቸውን አገናኙን ሲል ቢጠይቃቸውም እርሷቸው ግን ፈቃደኛ አለመሆናቸው ይታወሳል።

ዘ-ሐበሻን ይዘን ወደ ማተሚያ ቤት ለመግባት በዝግጅት ላይ እንዳለን ደግሞ ማንም ሰው ተንስቶ የፈለገውን ነገር ሊጽፍ በሚችልበት topix.com (የመወያያ ፎረም ነው) ላይ በሰበር ዜና መንግስቱ ኃይለማርያም በልብ በሽታ በተወለዱ በ75 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተጽፏል። ወዲያው ወሬው እንደፌስቡክን በመሳሰሉ የማህበራዊ ድረገጾች ላይ ተሰራጭቶ በሰፊው ህዝብን እያወያየ ሲሆን መሞታቸውን ያመነ፣ መሞታቸውን ያላመነ እና በጥኑ ህመም ላይ እንዳሉ ያመነ እንዳሉ ከሚሰጡ አስተያየቶች ለመረዳት ይችላል።

ዘ-ሐበሻ ይህን ዜና ወደ ህትመት እስከገባችበት ጊዜ ድረስ የተከታተለች ሲሆን የቀድሞውን ፕሬዚዳንት መሞት ግን ልታረጋግጥ አልቻለችም። የትኛውም ትላልቅ ሚዲያም ይህን ጉዳይ አልዘገበም።
“ሰውን ማመን ቀብሮ” የሚባለው አባባል “ፌስቡክን ማመን ቀብሮ” ወደሚለው ቢስተካከል ምን ይመስላችኋል?

 

 

1 Comment

  1. I know one thing mengistu is way better than meles,but I am not concerned whether he is sick or dead I don’t have a bit sympathy for mengistu. in fact for both dictators.

Comments are closed.

Asrat Tassie
Previous Story

“በሀገሪቱ የተደረገው ምርጫ የቧልትና የቀልድ ምርጫ መሆኑን ለህዝብ አሳውቀናል”

Next Story

የኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ዜና ምንጭ ወያኔ ነው

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop