በቤንች ማጂ በተነሳ ግጭት ሶስት ተማሪዎች ቆሰሉ

በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በሚገኘው ሚዛን 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት በተነሳው ግጭት ሶስት ተማሪዎች መቁሰላቸውና ከሚያዚያ 10 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ትምህርት መቋረጡን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ጠቆሙ ፡፡ እንደ ፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፃ ከሆነ ከሚያዚያ 7 ቀን 2005ዓ.ም. ጀምሮ
በትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና አስተዳደር አካላት በተነሳ አለመግባባት ከፍተኛ እረብሻ በመፈጠሩ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ለረብሻው መንስኤው ለትምህርት ቤቱ ከአሜሪካ በተሰጠው የትምህርት ዕድል የ12ኛ ክፍል የመሰናዶ ተማሪዎች መካከል በተደረገው ውድድር ከሴቶች ተማሪ መድኃኒት ስታሸንፍ ከወንዶች ደግሞ በጀመሪያ
ተማሪ ጌታመሳይ ማሸነፉ ከተጠቆመ በኋዋላ በተደረገ የውጤት ማጣራት ሂደት ተማሪ ዮሐንስ ማለፉ መለጠፉ ነው፡፡
ይህንንም ተከትሎ በተለይ የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ በወንዶች ተማሪ ዮሐንስና ተማሪ ጌታመሳይ ውድድር ላይ የውጤት አሰራር ስህተት በመኖሩን በተማሪዎችና በትምህርት ቤቱ መምህራንና አስተዳደር አካላት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መማር ማስተማሩ ሂደት መቋረጡ ተጠቁሟል፡፡
በመጨረሻም በተደረገው የውጤት ማጣራት መሰረት በውድድሩ ያለፈው ተማሪ ዮሐንስ መሆኑንም ምንጮቻችን አስታውሰዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio፡ በኢትዮጵያ መንግስት በሚዲያ የጦርነት ቅስቀሳ ጀመረ፣የጋሞ ብሄረሰብ አገዛዙ በቃን ራሳችንን በራሳችን እናስተዳድራለን አሉ፣ኤርትራ በማንኛውም ሰዓት ኢትዮጵያ ልትወረኝ ትችላለች አለች፣በአርባ ምንጭ ወንድሙ የነጻነት ትግሉን በመቀላቀሉ አንድ ወጣት በደህነቶች ተይዞ ከፍተኛ ማሰቃየት ተፈጸመበት ብገደል ሀላፊነቱ የመንግስት ነው ብሏል፣የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች ለእንግሊዝ መንግስት በምሬት ተማጽኖ አቀረቡ፣የጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ እና የኤድዋርዶ ቃለ መጠይቅ እና ሎሎችም
Share