ዶ/ር ነጋሶ ኢንጂነር ዘለቀ ረዲን ከአንድነት ያባረርነው በብቃት ማነስ ነው አሉ

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ አቶ ትግስቱ አወሉ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት እንደተናገሩት የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚሁም መሰረት የአንድነት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ በመጪው አመት መስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ላይ እንዲደረግ በፓርቲው ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት አድርጎ እንደሚያካሂድ አስረድተዋል፡፡ በፓርቲው ደንብ ለሊቀመንበሩ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበሩትን ኢ/ር ዘለቀ ረዲን በስራ አፈፃፀም ብቃት ማነስ ምክንያት አንስተው በቦታው አቶ ስዩም መንገሻን መተካታቸውን ለምክር ቤቱ አሳውቀዋል፡፡ ምክር ቤቱም ሹመቱን አፅድቋል፡፡ አቶ ትግስቱ ጨምረውም ባለፈው ረቡዕ በሰንደቅ ጋዜጣ ለአንድነት ፓርቲ አሉታዊ አመለካካት ባለቸው አካላት የወጣውን መሰረተ ቢስ ውንጀላና በፓርቲው ስራአስፈፃሚ አባል በነበሩት ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ በተሰጠው የሀሰት መረጃ ዙሪያ ኢንጅነር ዘለቀ በተገኙበት ሰፊውይይት መደረጉን አብራርተዋል፡፡
ምክር ቤቱ በሰጠው ውሳኔ መሰረትም ነገ ሰኞ ሰንደቅ ጋዜጣ ያወጣውን ሀሰተኛ መረጃ የሚያስተካክል መግለጫ እንዲሰጥ ኢ/ር ዘለቀን በሚመለከትም ጉዳዩ ለብሔራዊ ዲሲፕሊን ኮሚቴ እንዲመራ መወሰኑን የምክር ቤቱ ጸሀፊ ገልፀዋል፡፡

የሰንደቅ ጋዜጣ ዘገባን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ከጥቂት ወራት በፊት በኢሳት ላይ ቀርበው “መለስ ዘረኛ አልነበረም” ሲሉ የካዱት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በቅርቡ ከወያኔው የራድዮ ጣቢያ ፋና ጋር አድርገውት የነበረውን አወዛጋቢ ቃለ ምልልስ ካላደመጡት እንዲያዳምጡት ለትዝብት እዚህ አቅርበነዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በደብረ ኤልያስ ገዳም ልትሞሸር የነበረች ልጃቸው ለፀበል ሄዳ በአብይ አህመድ ሰራዊት በግፍ የተገደለችባቸው ወጣት ቤተሰቦች መሪር ሀዘን የእንባ ዥረት-

2 Comments

  1. What kind of opposition do we have in Ethiopia. They are not even allowed to hire a place to conduct their party meetings, the are not allowed to have a meeting with the public, they cannot hold mass rallies.

    Every time the fascist woayane threatens, the so called opposition roll down and just go away. I think these people are a disgrace to themselves and to the public.

    If you call yourself an opposition party and you cannot do such things what are you there to perform? what is your purpose?

    It is no point complaining about the woyane, if you are not courageous enough to exercise your basic rights, such as calling meetings with the public and if you cannot even hold your own party meetings without being threatened and harrassed by the fascist woyane.

  2. DR..what did you do so far as a party and yet you fired another doctor claiming he is not capable of doing his share.you are just a big rock sitting on the same place.nothing else.you did no matter what, this wasn’t the right time to get rid off someone.

Comments are closed.

Share