April 21, 2013
5 mins read

በኖርዌይ ስታቫንገር ከተማ የተደረገው የአባይ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ወያኔ የተከራየውን አዳራሽ ተቃዋሚዎቹ ተቆጣጥረውታል!!

Norway demo2


በኖርዌይ ስታቫንገር ከተማ የተደረገው የአባይ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ወያኔ የተከራየውን አዳራሽ ተቃዋሚዎቹ  ተቆጣጥረውታል!!

ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ጭቅጭቅ ነበር። ተቃዋሚዎች አይገቡም በማለት የተጀመረው መክፈቻ በኋላ ላይ ግን ፖሊስ ከመጣ በኋላ እንዲገቡ ተፈቀደ ። ስብሰባው በጥያቄ ተጀምሮ ነበር።  ተቃዋሚዎቹ ጥያቄውም እንዲ በማለት ጀመሩ፥

1 በመጀመሪያ እስከዛሬ እናንተ ከገባችሁ ጅምሮ ለገደላችሁት ሰዎች  የህሊና ፀሎት ይደረግ በማለት ነበር የተጠየቀው በመቀጠል

2 እስከዛሬ እናንተ ያደረጋችሁትን የዘር ማጥፋት በአማራ፣ በኦሮሞ እንዲሁም በሕዝባችን ላይ የተደረገው ነገር ሳያንስ ዛሬ ደግሞ በአማራው ላይ የዘር ማፅዳት ዘመቻ እየፈፀማችሁና እየገደላችሁ እዚህ መጣችሁ ገንዘብ መጠየቅ ለኛ ድፍረት ነው በማለት በስብሰባው አዳራሽ በጩወትና በመፈክር ተናወጠ የወያኔ የስዊዲን አገር ቆንፅላም እንዲሁም ጀሌዎቹም በመፍራት አዳራሹን ለተቃዋሚዎች  በማስረከብ ለቀው ወተዋል ! ።

ሌባ ነው ሌባ ወያኔ ሌባ በማለት የተጀመረው በመፈክር  በጭወትና በዝማሪ አዳራሹ ተደበላልቋል!

ከገንዘብ በፊት ነፃነት ይቅደም!

ከገንዘብ በፊት  ሰብኣዊነት ይቅደም!

ኢትዮጵያ አገራችን የደፈረሽ  ይውደም! በማለት ተቃዋማቸውን ሲያሰሙ ነበር።

የወያኔ/ ህውሃትና ጀሌዎች በአለም ላይ የሚያደርጉት የአባይ ገቢ ማሰባሰብያ በየአለማቱ ተቋውሞ እየደረሰበት ይገኛል።

በደቡብ አፍሪካ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰብያ ሳይሳካ እንደውም ወያኔ የተከራየውን አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት ያሳዩትን ጀግንነት ቀጥሎ በሌሎች አገርም  በአሜሪካ፣ በሳውዲ አረቢያ( ጅዳ) ፣በጀርመን ተቀጣጥሎ በቀጠለበት ሁናቴ  በኖርዌይ

ከፍተኛ የሆነ ተቋውሞ ደርሶበታል ።በኖርዌይ የተጀመረው ገቢ ማሰባሰብያ ስብሰባ በመቃወም  ወያኔ የተከራየውን ገቢ ማሰባሰብያ  አዳራሽ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር በማስወጣት የወያኔን ባንዲራ በማውረድ  የኢትዮጵያን ትክክለኛውን ባንዲራ በመስቀል በማውለብለብ ወያኔዎችንና ጀሌዎችን በማባረር አዳራሹን ተቃዋሚዎቹ ተቆጣጥረውታል ። በአለማቱ ያሉቱ የወያኔ ቅጥረኛ አምባሳደር ተብዬዎች አንገታቸውን ያስደፋና እንደ ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተራቸው አንገትን አስደፍቶ፣አስደንግጦ ወደ መጡበት ያስመለሰ ነበር።አዳራሹ ውስጥ የነበሩት ተቃዋሚዎች ሙሉ በሙሉ ይበልጣሉ።ታሪክ በውጪ ባሉ ኢትዮጵያዊያን እየተሰራ ይገኛል!

ኢትዮጵያውያን አንድነታቸው ተጠናክሯል ። የወያኔ የመገነጣጠል አላማ ስትራቴጂ የወደመበት ሆኗል።የሕዝቡም አንድነት የታየበት ነበር።ይህ በእንዲህ እንዳለ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍም ሚያዚያ 18 2013 መካሄዱ ይታወሳል።

ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ በመሆን በመዘመርና በመፍክር ብሶታቸውን አሰምተዋል።

ተቃዋሚዎቹ በአንድነት በመሆን ያሰሙት ቃል ነበር

(( ገና ይቀጥላል ሁላችንም ነፃ እስከምንወጣ ድረስ ))

ሞት ለአንባገነን!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

 

5 Comments

  1. Editors,

    You are masking the whole picture of the commotion at the meeting place. Please include the running video of the event so that readers can get the whole picture. Can you?

  2. አይ ጀግንነት!
    ሐገር ነፃ የምትወጣው የራሱን ምቾት ትቶ ከእርሷ የቆመ ልጅ ሲኖራት ነው። ታድያ በሰው ሐገር እየተሞላቀቁ ስለ ሰብዓዊ መብት ከበቂ በላይ ዕውቀት ካለው ፖሊስ ጋር እየተጋፉ ተቃውሞን መግለፅ ትግል ይሆን?
    የኖርዌይ መንግሥት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሐገራቸው እንዲመለሱ ሲወስን ከምን ተነስቶ እንደሆነ አሁን ነው የገባኝ…
    የተፈጠረውን እናንተ አጣማችሁና ቆራርጣችሁ እንዳቀረባችሁት ሳይሆን የኖርዌይ ዜና ማሰራጫ እንደዘገበው ላጫውታችሁ…
    ተቃዋሚው ዳያስፖራ ቦታውን የያዘው ቀደም ብሎ ነው። የወያኔ ተወካዮች ሲመጡ ግርግሩ ተጀመረና ፖሊስ መምጣቱ አስፈላጊ ሆነ። ፖሊስ እንደደረሰም አዳራሹን የተከራየው ማን እንደሆነ አጣርቶ ሲያበቃ ተቃዋሚ ዳያስፖራዎችን እንዲለቁ በትህትና ጠየቀ። ተቃዋሚው ዳያስፖራ ግን ወደ ኃይል የተቀላቀለበት ተቃውሞ በመግባቱ ፖሊስ ስብሰባው መቋረጥ እንዳለበት ወስኖ የወያኔ ተወካዮችን በመኪና ካሳፈረ በኋላ ተቃዋሚውንም ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ነገራቸውና ዕለቱ እንደዚያ አለቀ።
    በሌላ ዜና ኃይለማርያም ደሳለኝ አውሮፓን ዙረው ሲያበቁ ከአውሮፓ ኮሚሽን የሚፈልጉትን የትብብር ስምምነት ተፈራርመው ሐገራቸው ተመልሰዋል።
    ታድያ የተቃዋሚ ዳያስፖራ ግርግር ምንድን ነው የፈየደው?
    ኢትዮጵያውያን እንዲህ ናቸው ከማስባል ውጪ…

Comments are closed.

012
Previous Story

ኢትዮጵያውያን በኖርዌይ የወያኔን አምባሳደር አሳፍረው መለሱ (Video)

Fnote 73 pic
Next Story

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ 2ኛ ዓመት ቅጽ 2 ቁ 73

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop