የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ “መንግስት ለኔና ለቤተሰቤ ጥበቃ ያድርግልኝ” ሲሉ ተማጸኑ

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሠውነት ቢሻው የተወሰኑ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በተለያዩ ጊዜዎች እያደረሱባቸው የሚገኘው ጫና ሥራቸውን በአግባቡ ለማከናወን እንዳይችሉ እንዳደረጋቸው በመግለጽ ጫናው በእርሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ ጉዳት ይደርሳል የሚል ስጋት ስለፈጠረባቸው « መንግሥት ጥበቃ ያድርግልኝ » ሲሉ መጠየቃቸውን መንግስታዊ ሚዲያዎች ዛሬ ዘገቡ።
አሰልጣኙ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፉትና ለመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፣ ለፌዴራልና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ለስፖርት ኮሚሽን ፣ ለኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እንዲሁም ለመንግሥትና ለግል የመገናኛ ብዙኃን በግልባጭ ባሳወቁት ደብዳቤያቸው ላይ እንደገለጹት የተለመደ ስራቸውን ለማከናወን ስቴዲየም በሚገኙባቸው አጋጣሚዎች ከተወሰኑ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች እየደረሰባቸው የሚገኘው ከስፖርቱ ስነ ምግባር ውጪ የሆነ ድርጊት በስራቸው ላይ ጫና ፈጥሮባቸዋል። ይህ ድርጊት በእርሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ አደጋ ሊፈጠር ይችላል የሚል ስጋት ስለፈጠረባቸው መንግሥት ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ለመጠየቅ አስገድዷቸዋል።
አሰልጣኝ ሰውነት በፊርማቸው አስደግፈው በላኩት መግለጫ ፤ እነኝህ «የተወሰኑ » ሲሉ የገለጿቸው የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የካቲት 26 ቀን 2005ዓ.ም ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከቤኒን አቻው ጋር በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተጫወተበት ወቅት የእርሳቸውንና የቡድኑን ተጫዋቾች ስብዕና የሚነካ ስድብና ዘለፋ በመሰንዘራቸው ተጫዋቾቻቸው ውጤት እንዳያስመዘግቡ እንቅፋት ሆነዋል ብለዋል።
በተመሳሳይ መጋቢት 15 ቀን 2005ዓ.ም ብሔራዊ ቡድኑ ከቦትስዋና አቻው ጋር በአዲስ አበባ ስቴዲየም ባደረገው የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ እነዚሁ ደጋፊዎች « ሠውነት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ገዳይ፤ ሠውነት ጋዳፊ » እያሉ የስራ ነጻነታቸውን ፣ ሞራላቸውንና ስብዕናቸውን የሚፈታተኑ አጸያፊ ቃላት እንደወረወሩባቸው በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።
«ይህ ድርጊት በስሜታዊነት የተሰነዘረ ነው ብዬ ለማለፍ ብሞክርም ሁኔታው ከመቆም ይልቅ ፍጹም በተደራጀ መልኩ ተከስቷል » በማለት በመግለጫቸው የጠቀሱት አሰልጣኝ ሠውነት ፤ ሚያዚያ 5 ቀን 2005 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለቦች ባደረጉት ጨዋታ ላይ ድርጊቱ ከቀድሞው በበለጠ መልኩ መከሰቱን አስታውቀዋል።
ይህ ሁኔታ በማንኛውም ጊዜ በእርሳቸውና በቤተሰባቸው ላይ አደጋ ይደርሳል የሚል ስጋት እንዲያድርባቸው እንዳደረገ በመግለጫቸው ገልጸዋል። በመሆኑም ስራቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩ መንግሥት ሁኔታውን ተከታትሎ የማያዳግም መፍትሔ እንዲሰጣቸውና ፣ ለእርሳቸውና ለቤተሰባቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው በመግለጫቸው ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ምላሽ ክለባቸው ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንደሚሰጥ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ ሚዲያዎች መዘገባቸውን የዘሐበሻ ወኪሎች አስታወቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በአመክሮ ከእስር ቤት አይፈታም

5 Comments

  1. i think if he believe he is frighten by people he must quit the job. After African cub shim full last place finished he blame the goalkeeper. now he blame the fan for the fell national time performance.

  2. It is the deeds of TPLF that it always attack insideously successful Non-Tigrians. Trust me!!!

  3. Sewnet is trying to blame others for his stark coaching weakness. unless he has french connection with woyane thugs ,he would have not stayed for a minute after registered such disastrous defeat, Now he tries to scape -goat Buna supporters for all his defects and thus appealing to woyane thugs to have them throw indiscriminately the entire Buna fans behind bar. What a sadist person he is.? He should have resigned on his own accord ,if he had the slightest feel of regret for his lowest result on African cup of nations.

  4. sewnet: in the first place you aren’t good enough to be national team coach just because you are weyane’s cadre you got the post.may be these people might tell you your mistake,but I doubt that they try to kill you and your family.why any body try to kill a man like you good for nothing.please don’t accuse innocent people.instead accept the advice that they try to offer.don’t be arrogant like your bosses.

  5. በመጀመሪያ ደረጃ ሰውነት ቢሻው ማለት የብሄረዊ ቡድን አይደለም ፕሬሚየር ሊግ የሚወዳደር ክለብ ማሰልጠን የመየገባው አሰልጣኝ ተበዬ ነው። የሀገራችንን እግር ኳስ በቅርብ የሚከታተል ሰው ሰውነትን የሚያስታውሰው ትልቅ ቡድን ይዞ ወደታች ዲቪዚዮን በማውረድ ነው።

Comments are closed.

Share