April 17, 2013
3 mins read

የገዛ ሚስቱን የሚገድል የኢትዮጵያ ፖሊስ በመንግስት ትዕዛዝ ሕዝብ ጨፍጭፍ ቢባል ከማድረግ ይመለሳል?

Mistun yegedelew

(የገዛ ሚስቱን የሚገድል የኢትዮጵያ ፖሊስ በመንግስት ትዕዛዝ ሕዝብን ጨፍጭፍ ቢባል ከማድረግ ይመለሳል? – ይህን ጥያቄ ለመመለስ የሚከተለውን ዜና ያንብቡ)
በቂም በቀል ተነሳስቶ የቀድሞ ባለቤቱን ህይወት በሽጉጥ እንዲጠፋ አድርጓል ሲል፤ የፌዴራሉ ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶበት ጥፋተኛ የተባለው ኮማንደር ግርማ ሞገስ ከትናንት በስቲያ በዋለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወሰነበት።

እንደ ዐቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ከሆነ ተከሳሹ ለጊዜው ስሟን የማንገልፅላችሁ ሟች የቀድሞ ባለቤቱን የአብራኬ ክፋይ የሆነ ልጄን ማየትና መጐብኘት እንዳልችል ከልክላኛለች በሚል ቂም-በቀል ተነሳስቶ፤ ሟች መኖሪያ ቤት አካባቢ ድረስ በመሄድ በሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 2 ሰዓት 30 ሲል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/02 ልዩ ቦታው ሐግቤስ መኪና መሸጫ አካባቢ፤ ከቤት ወጥታ ወደስራዋ ታመራ የነበረችውን የቀድሞ ባለቤቱን የወግ ቁጥሩ 353348 በሆነ ሽጉጥ አንድ ጊዜ ተኩሶ ግራ ጐኗን መትቶ በመጣሉ በደረሰባት ጉዳት ህይወቷ በማለፉ በከባድ ሰው መግደል ወንጀል ተጠያቂ ነው ሲል ያትታል።

በስድስት የሰው ምስክሮች፤ ከምኒልክ ሆስፒታል የቀረበ የአስከሬን ምርመራ ውጤትና ግድያው የተፈፀመበትን ሽጉጥ ለፍርድ ቤት አቅርቦ ያስረዳው ዐቃቤ ህግ፤ ተከሳሹ በተሰጠው የመከላከል ዕድል የዐቃቤ ህግን ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ተብሏል። በመሆኑም የግራ ቀኙን ሀሳብ ሲመረምር የቆየው ፍርድ ቤቱ ከትላንት በስቲያ ውሎው ተከሳሽ ያቀረባቸውን ሦስት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ማለትም፤ መልካም ሥነ-ምግባር የነበረው መሆኑን፣ ታታሪ ሰራተኛ መሆኑንና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከቅጣቱ ሦስት እርከኖችን ዝቅ በማለት በ18 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል።n (ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ኤፕሪል 17 2013 ዕትም)

4 Comments

  1. What is up with the title? What this personal tragedy go to do with Ethiopian people? What would have the title be if the husband wasn’t a policeman? I don’t know the purpose of the writer to choose this title. I have read so many stories like that a husband killing his wife or a wife killing her husband. Let use politices when the story is related to police brutality on innocent Ethiopians or government sponsored terrorism. The title I think was purposely chosen to warn people that if you rise up our policemen will kill you. I don’t like the title at all even if the writer intention wasn’t that.

  2. በግል ኢህአዲግን አለመደገፍ ብቻ ሳይሆን እቃወማለሁ ግን የአንድን ፖሊስ ወንጀል ከመላው የፓሊስ ሃይል ጋር ማወዳደር ውሀ አያነሳም ከመንግስት በተቃራኒ የቆሙ የፓሊስ አባላት የሉም ማለትም አይቻልም ።ይህ ፓሊስ የሰራውን አይነት ወንጀል ከተቃዋሚ ጐራ ያለ ቢፈጽመውስ?ፖሊስ መሆን ሙያ ነው ሆኖም ህግን ሽሮ ወይም ጥሶ ከገዥው ፓርቲ ጋር መተባበር ለፖሊስም ሆነ ለሌላው ወንጀል ነው ወይም ስልጣንን መከታ አድርጐ በሌሎች ላይ አካላዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ጥቃት ማድረስ ከተጠያቂነት አያድንም ።
    የፖሊስ አደረጃጀቱ ከማዕረግ አሰጣጡ (አዲሱ የማዕረግ ተዋረድ )ጀምሮ ችግር እንዳለበት ተጽፎ አንብቤያለሁ ያ ማለት ሁሉም ፖሊስ በጅምላ ጸረ-ህዝብ ነው ማለት አይደለም።በግል ከሁሉም በላይ የሚያበሳጨኝ ደግሞም ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ ፖሊስ ገና ህዝባዊ አለመሆን የሚሳየን ጉቦና ሙስናው እንዳለ ሆኖ ፖሊስ ለሚጠብቀው ደሞዝ ከፋይ ህዝብ ክብር የለውም እስቲ ሰልፍ ወይም ስብሰባ ሲኖር ሀይማኖታዊ በአል ሲከበር ተመልከቱ ጨዋ ህዝብ በቆመጥ ሲደበድብ ታገኙታላችሁ እንዲህ አይነቱ ፓሊስ አሜሪካ ወም አውሮፓ ቢሆን ምን ሊደርስበት እንደሚችል ታውቃላችሁ።
    በሀገራችን ፖሊስ ህዝባዊ ያለመሆን ጉድለት ብዙ ሊባልና ሊጻፍ ሲችል በደም ፍላት ወይም በቂም ተነሳስቶ የገዛ ሚስቱን ያጠፋ ሀጢያቱ ግንባሩ ላይ የተጻፈበትን ሚስቱንም በተዘዋዋሪ ራሱንም ያጣ በወንጀሉ ሲቀጣ እንደሰው ደግሞ ሊታዘንለት የሚገባ አንድ የፓሊስ ባልደረባ የመላው ፓሊስ መገመቻ ወይም መገምገሚያ አድርጐ ለማቅረብ መሞከር የፓለቲካ ሀሁ አለመረዳት ሲሆን አሊያም እንደ ገዥው ፓርቲ የጥላቻ ፖለቲካ ማራመድ ነው።
    ሌላው ደግሞ ሰላማዊ ሰልፍ አትሞክሩ ፖሊስ አይምራችሁም የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ስውር ነገር አላትን ብዬ አሰብኩ ጠረጠርኩ ብል ይ ሻላል መጠርጠር ከብዙ መከዳዳትና አለመተማመን የተነሳ የኢትዩጵያውያን ባህሪያችን ሆኗል።
    ይህኛውን በቀልድ ቢጤ ልለፈው 97 ውሀ የሚረጭ መኪና ስላልነበረን ያ ሁሉ ሰው ሞተ፤ አሁን ግን ፖሊስ ውሀ የሚረጭ መኪና የድንጋይ መከላከያ ጋሻ፡ፕሊስቲክ ጥይትና አስለቃሽ ጢስ ታጥቋል።
    ልምምድ በማድረግ ትንሽ የግልቢያ ሙከራ አድርጐ እንደሚቁነጠነጥ ሰንጋ ፈረስ ውጤቱን ለመሞከር ከፈለገ ሰላማዊ ሰልፍ መፍቀዱ አይቀርም ማን እንደሚያሽንፍ ያኔ ይታያል።ጸሀፊ ሆይ ያለመስዋእትነት ድል የለም። ጊዜው ሲደርስ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ከፈልግ ማንንም ፈቃድ አይጠይ ቅም ህዝብ እንደ ማዕበል ይሆናል እንደ አውሎ ንፋስ በሚረጭ ወሀ እና በአስለቃሽ ጋዝ ላይ ያፏጫል በእስራትና በሞት ላይ ያሽካካል ።
    አያድርስ! ሊሆን ያለው ግን ከመሆን ማገድ የሚችል ማን ነው?

  3. It is sad to see the good guy falling by the devil work and commit this heinous crime, I know Girma since I was a child we grew together, he was an innocent boy, loved his family and his friends…. When I see this article, I am really shocked…how come Girma can do this? what I cannot answer is why a man like Girma can do such a crime? I can understand, there is that devil who always trap those like Girma.

    This title though do not belong to this man,even if he committed this crime, because anybody can be trapped too. he was a professional police man works since the Previous regime until he is caught by this tragedy. Anybody can imagine what the judges even say regarding his persona during the sentence…

    Sorry this happen to you Girma…
    AYADRES!!

  4. Menem alehonem belo yadergew new enjie endayt yfetaten set bemekenayat yegelale agebeto yersuin nuro eynore yale sewnew lemen wedefetate set bechekanay Legedelel hede? sefetate desetgha nuro yemenorewe meselot neber ahuin yemnorew tedar yezonew Nege Liju seyadege yemetale new yemlew ye ethiopia abat enjie lemayet felgo aydelem endemkeneyat tetkemobet new enjie.Kefuu sew Lejuniem enat asatwe.wey rasu alyazewe wey enaton altewelet.metfoo.

Comments are closed.

Previous Story

የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን ወቅታዊ ጽሁፍ በተኑ፤ “ትላንት ወልቃይት ጠገዴ፣ በደኖ አርባጉጉና ጋምቤላ፣ ዛሬ ጉራፈርዳና ቤንሻንጉል፣ ነገስ?”

Abrham Desta
Next Story

ተቃዋሚዎች በምርጫ ቢሳተፉ ኑሮ በትግራይና አዲስ አበባ ያለ ጥርጥር ያሸንፉ ነበር

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop