April 17, 2013
1 min read

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት ተወሰደ

Woubshet-Taye-Deputy-Editor-In-Chief-Awramba-Newspaper
ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት ተወሰደ 1

ፍኖተ ነፃነት

አውራምባ   ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት ተወሰደ፡፡

የአውራምባ   ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በፌደራል  አቃቤ ህግ በሽብርተኝነት ተከሶ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኛ በሚል 14 ዓመት ተፈርዶበት ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስሮ ይገኝ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ ሚያዚያ 8 ቀን 2005ዓ.ም. ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከአዲስ አበባ ከ170 ኪሎ ሜትር አካባቢ በደቡብ ምስራቅ ርቀት በሚገኘው ዝዋይ ወህኒ ቤት መወሰዱ ታውቋል፡፡

የጋዜጠኛው ባለቤት እና ልጁ በሁኔታው ከፍተኛ መደናገጥ እንደፈጠረባቸው ተጠቁሟል፡፡ በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስት ጋዜጠኞችን በማሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተወገዘና ያሰራቸውን ጋዜጠኞችንም እንዲፈታ በተደጋጋሚ ጫና እየተደረገበት መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም መንግስት ግን ጋዜጠኛ  ውብሸት ታዬ፣ ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እስካሁንም ለመፍታት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡

Previous Story

የመለስ ሌጋሲ አስፈጻሚዎች ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን በእስር ቤት ቢያሰቃዩም ዩኔስኮ ጋዜጠኛዋን ሸለመ

Next Story

ለኢትዮጵያ መንግሥት ከኢትዮጵያ የተላከ ደብዳቤ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop