July 28, 2024
13 mins read

የሃይማኖት መሪዎች ሃላፊነት እና የዳንኤል ክብረት አይነት የፖለቲካና የሞራል ዝቅጠት

July 28, 2024
ጠገናው ጎሹ

አሳሳቢነቱ ግልፅ የሆነን ጉዳይ ግልፅ፣ ቀጥተኛ እና ገንቢ በሆነ ሂሳዊ አስተያየት ተገቢና ወቅታዊ ትኩረት እንዲያገኝ ፣ ሊያደርሰው የሚችለው ጉዳት እንዳይደርስ እና እያደረሰም ከሆነ የሚያስከፍለው ዋጋ ይበልጥ አስከፊ እንዳይሆን  ከማድረግ ይልቅ የጉዳዩ ቀጥተኛ ባለቤት የሆነውን አካል ማንነትና ምንነት እያሰላንና በእጅጉ የተለጠጠ ሰበብ እየፈጠርን ለዘመናት በመጣንበት ፖለቲካ ወለድ የመከራና የውርደት አዙሪት ውስጥ የመጓጎጥን እኛነት ሙሉ በሙሉ ባንታደገውም እንኳ ትርጉም ባለው ሁኔታ ለማሻሻልና ቀስ በቀስም ይበል በሚያሰኝ አኳኋን ለመታደግ እልህ አስጨራሽ የጋራ ጥረትን ይጠይቀናል።

ተስፋ ለምናደርገው ሰማያዊ  ህይወት ዋስትናው በምድራዊ የህይወት ቆይታችን የምንሆነውና የምናደርገው መልካም ነገር መሆኑን ለመረዳት የተለየ የሊቅነት ችሎታን የሚጠይቅ አይመስለኝም።  ይህንን ግልፅና የተቀደሰ የህይወት  መስተጋብር ጤናማ በሆነ ሃይማኖታዊ እሴትነት ጠብቆ ለማስኬድ ይቻል ዘንድ ከየትኛውም አቅጣጫ ፣ አካል ወይም ግለሰብ የሚመጣውን እኩይ ባህሪና ተግባር ግልፅነት፣ ቀጥተኝነትና አስተማሪነት ባለው ይዘትና አቀራረብ ለመገሰፅና ከተቻለ ከስህተት ለመመለስ ፣ ካልሆነ ግን ያ አካል ወይም ግለሰብ ሃላፊነቱን መውሰድ እንዳለበት ግልፅ ለማድረግ የፅዕኑና ብልህ የሆነ የሃይማኖት መሪነትንና አገልጋይነትን ይጠይቃል። በእውነት ስለ እውነት ከተነጋገርን የሃይማኖት መሪዎች ፣ ሊቃውንትና ሊቀ ሊቃውንት ትልቁና አስቀያሚው ውድቀትም እዚህ ላይ ነው።

በሃይማኖታዊ ትርጉሙ “በጎችን ጠብቅ ሲባል” ከውጭ ከሚመጣ አደገኛ (ጎጅ) መንፈስ ወይም አካል ብቻ ሳይሆን “ዲያቆንና ሙዓዘ ጥበባት” የሚሉና እጅግ ጥልቅ ትርጉም ያላቸውን  ሃይማኖታዊ ማዕረጎች ተሸክመው በፖለቲካ ወለድ ወንጀል የበሰበሰና የከረፋ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት አማካሪ በመሆን አገርን እና  ከሃይማኖታዊ እምነት ጋር በርካታ በጎ እሴቶችን አጣምራ የያዘችውን  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካረከሱትና በማራከስ ላይ ከሚገኙት እንደ ዳንኤል ክብረት አይነት ግለሰቦች መከላከል  ይቻል ዘንድ  ግልፅ ተግሳፅ ለማሰማትና አስፈላጊውን (ተገቢውን) ሃይማኖታዊ እርምጃ ለመውሰድ  የሚገደው የሃይማኖት አመራርን  የእረኞች የበላይ አስተዳዳሪና አስተባባሪ ለማለት እንዴት እንደሚቻል ለመረዳት ይከብዳል። አዎ! ይህን እጅግ ግልፅና ቀላል ሃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ሃላፊነትንና ግዴታን ለመወጣት የሚሳነው አመራር ሌሎች በፖለቲካ ቁማርተኞች በእጅጉ የተመሰቃቀሉ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን እንዴትና በምን ሊታደግ እንደሚችል እንኳን ለማመን ለማሰብም ይከብዳል።

በእውነት ስለ እውነት ከተነጋገርን እጅግ በሚያሳዝን አኳኋን ጨካኝ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ካድሬዎች የጵጵስና ማእረግ ተለጥፎላቸው፣ የጵጵስና ዩኒፎርም ተደርቦላቸው፣ እና ክቡር መስቀሉ የአስቀያሚ ተውኔታቸው ማድመቂያ እንዲሆን ተደርጎላቸው በአባልነት የታደሙበት የሃይማኖት አመራር (ሲኖዶስ) የእኩያን ቁማርተኞች ቤተ መንግሥት አማካሪ በመሆን ቤተ ክርስቲያንን መሳለቂያ ያደረጉትን እንደ ዳንኤል ክብረት አይነት ግለሰቦች ደፍሮ ባይገስፅ እና “ዲቆንና ሙዓዘ ጥበባት”  በሚል ያሸከሟቸውን  ማእረግ በተመለከተ ተገቢውን ሃይማኖታዊ እርምጃ ባይወስዱ ፈፅሞ የሚገርም አይሆንም።

ለነገሩ የሸፍጠኞች፣ የሴረኞች ፣የፈሪዎችና የጨካኞች የጎሳ ደምና አጥንት ስሌት አገዛዝ  አገርን ምድረ ሲኦል እያደረገ ዓመታትን ሲያስቆጥር የተማፅኖ መግለጫ ከማውጣት እና የእግዚኦታ አዋጅ ከማወጅ ያለፈ እርምጃ ያልተራመደ እረኝነት መከረኛውን ህዝብና ቤተ ክርስቲያንን ከነ ዳንኤል ክብረት አይነት ተኩላዎች ይከላከላል ብሎ መጠበቅ ያስቸግራል ።

ይህ ሂሳዊ አስተያየቴ ከሚታይና ከሚጨበጥ ምክንያታዊነት የሚነሳ እንጅ ምናባዊ ጨለምተኝነት ( ideal pessimism) አይደለም። የትኛውም ስህተት በዓለማዊም ሆነ በሃይማኖታዊ እምነት አካል (መሪ/አመራር)  ሲፈፀም ትክክል አይደለምና ይታረም የሚል ሂሳዊ ትችትና አስተያየት መሰንዘርን እየሸሸን ስለ ገጠመንና እየገጠመን ስላለው አስከፊና ሁለንተናዊ ቀውስ (ውድቀት) የምሬትና የእግዚኦታ ጩኸት እየጮህንና እያስጮህን  ራሳችን ብቻ ሳይሆን መከረኛውን ህዝብ ጨምረን ግራ ማጋባት  ጨርሶ ስሜት የሚሰጥ ነገር አይደለም።   ለዘመናት ለመጣንበት እና አሁንም ይበልጥ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ራሳችንን እየሸነገልን ለቀጠልንበት ክፉ አዙሪት ማቆሚያ እንዳናበጅለት ካደረጉን  ምክንያቶች አንዱ ይኸው ነው።

የሃይማኖት መሪዎች እና ባለ ሌላ የሥልጣን ማዕረግ አገልጋዮች እንደ ሰብአዊ ፍጡርነታቸው ተሳስተው ሊያሳስቱ የሚችሉ መሆናቸውን በጥሞና እና በአግባቡ ተገንዝቦ ገንቢነትንና ከበሬታን  በተላበሰ ይዘትና አቀራረብ ወቅታዊና ገንቢ እርምት እንዲያደርጉ መጠየቅን እንደ ሃጢአት ወይም እንደ ፀረ ሃይማኖት  ወይም የፈጣሪን ቁጣዊ መዓት እንደ መጋበዝ ፣  ወዘተ አድርጎ የማየት አጉል ልማድ በአግባቡ ሊፈተሽና ተገቢ እርምት ሊደረግበት ይገባል።

በዚህ ረገድ ያለብን ጉድለት ጥልቀቱና ስፋቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቃለለ ከመሄድ ይልቅ እየባሰበት በመሄድ ላይ የመሆኑን መሪር ሃቅ በደምሳሳው ወይም በሰንካላ ሰበብ ለማስተባበል መሞከር እንኳንስ ሁሉን ነገር ለሚያውቀው እውነተኛ አምላክ ቅንና ሚዛናዊ የሆነ ህሊና ላለው ሰብአዊ ፍጡርም ፈፅሞ አይመጥንም ።

እናም አሁንም ለሰማያዊውም ሆነ ለምድራዊ ህይወት ስኬታማነት የሚበጀው ዘመን ጠገቡንና እጅግ አስቀያሚውን ደጋግሞ የመውደቅ አዙሪት በአርበኝነት ሞራል፣ በአስተሳሰብ ልዕልና እና ውጤታማ በሚሆን የተግባር ውሎ በመጋፈጥ ሃይማኖትን ጨምሮ ሁለንተናዊ መብቶች የሚረጋገጡበትንና የሚከበሩበትን ሥርዓት እውን ማድረግ ብቻ ነው።

ለዘመናት ለመጣንበትና አሁንም ተዘፍቀን ለምንገኝበት አጠቃላይ ማለትም የሃይማኖት ነፃነት ትርጉም አልባነት ፣ የፖለቲካና የሰብአዊ መብቶች እጦት ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ህይወት ዝቅጠት፣ የሞራልና የሥነ ልቦና ቀውስ፣ ወዘተ ግዙፍና መሪር እውነታ ዋና ተጠያቂዎች እኩያን የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት መሥራቾችና ጠርናፊዎች መሆናቸው ፈፅሞ የሚያጠያይቀን አይደለም።

ይህ ግን የዚሁ ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት ሰለባ የሆነውን ህዝብ አንቅቶና አደራጅቶ ወደ የነፃነት ትግል ሜዳ በማሰማራት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እውን እንዲሆን ማድረግ የሚገባው  ምሁርና ልሂቅ ነኝ ባይን የህብረተሰብ ክፍል ከሃላፊነት ውድቀት ነፃ አያደርገውም።

የሃይማኖታዊ እምነት አመራርም፣ ምሁርም፣ ሊቅና ሊቀ ሊቃውንትም ሃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት ምክንያት እንደ ዳንኤል ክብረት አይነት የአድርባይነትና የአስመሳይነት ልክፍተኞች በቤተ መንግሥት አማካሪነታቸው ሃይማኖቱን (ቤተ ክርስቲያንን) የፖለቲካ ወለድ ወንጀል ሰለባ ሲያደርጉና አደጋ ላይ ሲጥሉ በግልፅና በቀጥታ ነውር ነው ለማለት እና ለተሳሳተ ዓላማ እየዋለ ያለውን “የዲቁና እና የሙዓዘ ጥበባት” ማእረግ በይፋ ለማንሳት የሚያስችል የሃይማኖትና የሞራል   ልዕልና ማጣቱ  የሃላፊነቱን ውድቀት ከፍ ያደርገዋል እንጅ አይቀንሰውም።

እናም የገዛ ራሳችንን ግዙፍና መሪር ሃቅ መጋፈጥ ሲሳነን የሰበብ ድሪቶ እየደረትን ዙሪያውን የመዞሩን ክፉ አባዜ ትተን በተሻለ አስተሳሰብና የተግባር ውሎ የተሻለ ነገን እውን ማድረግ ይኖርብናል። ይህንን ሆነንና አድርገን ለመገኘት ደግሞ እንደ ዳንኤል ክብረት አይነት የጥራዝ ነጠቅ ፊደል ቆጣሪዎችና የአድርባይነት ልክፍተኞች ከተቻለ እንዲታረሙ እና ካልሆነ ግን ከመከረኛው ህዝብ የነፃነትና የፍትህ መንገድ  ደንቃራነታቸው ዘወር እንዲሉ በግልፅ መነጋገርና መንገር ያስፈልጋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop