July 27, 2024
14 mins read

የዳንል ክብረት መጽሐፍ ምረቃ እና የትውልድ ማፈሪያነት የማይሰለቻቸው ታዳሚዎቹ

July 27, 2024
ጠገናውጎሹ

Danile 2ሰሞኑን  የሴራ፣ የሸፍጥና የእኩይ ተግባር  ማምረቻና ማከፋፈያ የሆነው የቤተ መንግሥት ፖለቲካ  ጨካኝ  ጠርናፊ የሆነው እና የፖለቲካ ብቻ ሳይሆን እጅግ አደገኛ የሆነ   የሰብዕና  ቀውስ የተጠናወተው አብይ አህመድ አማካሪ የሆነው”ዲያቆንና ሙዓዘ ጥበባት”(  ሰይጣነ ጥበባት ተብሎ ቢጠራ ትክክል ነው ) ዳንኤል ክብረት 35ኛው እንደሆነ የተነገረለትንና “የትርክት ዕዳና በረከት” የሚል ርዕስ የለጥፈለትን መጽሐፍ ተብየ ያስመረቀበትን መድረከ ተውኔት ተከታተልኩት።

በመሠረቱ ዳንኤልም ሆነ ማነኛውም ግለሰብ የቆጠረውን ፊደል እና በህይወት ያገኘውን ተሞክሮ  ተጠቅሞ አቅሙና ችሎታው በፈቀደለት መጠን እንኳንስ 35 በየዓመቱ   መፅሐፍ  ቢፅፍና ቢያስጠርዝ በደምሳሳው ጥያቄ የሚያነሳ ምክንያታዊና ሚዛናዊ ህሊና ያለው የአገሬ ሰው የሚኖር አይመስለኝም። የዳንኤልን ደራሲነት በተመለከተ ሊነነሳ የሚገባው ጥያቄም ከዚህ አይነት ደምሳሳ ጥያቄ የሚነሳ መሆን የለበትም።

አንድ መሠረታዊ ጉዳይ ግን ግልፅ መሆን አለበት። እርሱም የአደገኛው ትርክት ማምረቻና ማከፋፈያ የሆነው የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ  ቁማርተኞች ሥርዓት ጉልቾቹን እየቀያየረ እንደ ሥርዓት እንዳይቀጥል ካልተደረገ በስተቀር እንደ ዳንኤል ክብረት አይነት ወራዳና ህሊና ቢስ እኖር ባዮች/አድርባዮች እያስጠረዙ ገበያ ላይ ለሚያውሉት  የሸፍጥ ሥራ (hypocritical work) ሰለባነት ራስን አሳልፎ እየሰጡ ማቆሚያ የሌለው ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት አዙሪት ውስጥ መርመጥመጡ ይቀጥላል።

አዎ! ይህ ትውልድ እንደ ዳንኤል አይነቶችን የፖለቲካ ቁማርተኞችና (ነጋዴዎችና) የሞራል ዝቅጠት ምሳሌዎች ከዘቀጠ ሰብእናቸው እና ከተሰማሩበት ርካሽና አደገኛ ተግባራቸው ጋር የሚላተም የትንታኔ ድሪቶ ፅፈውና አስጠርዘው “ሙዓዘ ጥበባትነታችን ልታደንቅ ካልቻልክ የትርክት ባለ እዳ ነህ “ ሊሉት ሲዳዳቸው ካልተፀየፋቸውና ከፍኖተ ነፃነትና ፍትህ ተጋድሎው ላይ ዘወር እንዲሉ አስፈላጊና ገንቢ በሆነ የጋራ ተጋድሎ ቁርጡን ካላሳወቃቸው በእጅጉ አሳሳቢና አስፈሪ ነው።

ምንም እንኳ የዳንኤል ክብረት የአድርባይነትና የአስመሳይነት ሰብዕና በእጅጉ ሥር የሰደደ (deeply chronical) መሆኑን ለማወቅ ብዙም ባያስቸግርም በተለይ ከስድስት ዓመታት ወዲህ ዕዳ ነው የሚለውን ትርክት በመሣሪያነት ተጠቅመው አገርን ምድረ ሲኦል ያደረጉትና  እያደረጉ ያሉት ተረኛ የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ቁማርተኞች አማካሪነት ቦታ ላይ ተቀምጦ ስለ ትርክት ዕዳነትና በረከትነት  ሰብአዊ ህሊናቸውን ለከርሳቸው ርካታ በሸጡ ቢጤዎቹ  አጃቢነት ሲሰብከን (ቅርሻቱን ሲያቀረሽብን) ማየትና መስማት የእውነተኛ ነፃነትና ፍትህ ፈላጊ የአገሬን ሰው ህሊና በእጅጉ ያቆስላል።

በእጅጉ አሳዛኝና አደገኛ የሆነውን የዳንኤልን የሰብዕና ቀውስ ለማስረዳት በብልፅግና እና በህወሃት መካከል በተካሄደ ጦርነት ወቅት ለመናገር እንኳ የሚከብድ “የበሏቸውና የጨርሷቸው”  የአማካሪነት ዘመቻውን እና ከአንድ ዓመት ወዲህ ደግሞ እንኳንስ ካለፈው እብደቱ ሊማር የውስጥ ችግሮች መኖራቸው እንደ ተጠበቀ ሆኖ የአማራ  ማህበረሰብ እርሱ (ዳንኤል) በሚያማክረው ወንጀለኛ ቤተ መንግሥት አዛዥነትና ውሳኔ ሰጭነት የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ የተገደዱትን የፋኖ ሃይሎች የስድብና የውንጀላ ውርጅብኝ የማውረዱንና እያወረደ የመሆኑን መሪር ሃቅ ልብ ማለት ብቻ በቂ ነው።

በዘመን ጠገብ  ፖለቲካ ወለድ መከራና ውርደት አረንቋ ውስጥ ከመጓጎጥና ከመርመጥመጥ ሰብሮ ለመውጣት የሚያስችለውን ንቃተ ህሊና እና ድርጅታዊ ቁመና  አምጦ ለመውለድ  ገና ያልተሳካለትን  የአገሬ ህዝብ  እንደ ዳንኤል ክብረት አይነቶች ሃይማኖታዊ እምነትንና የእኩያን ገዥዎች ጨካኝ የፖለቲካ ሰይፍን እየቀላቀሉ ጥርሳቸውን ነቅለው ላደጉበትና ለጎለመሱበት እጅግ ሥር የሰደደ የአድርባይነትና የቅጥፈት ሰብዕናቸው ማርኪያ ቢያደርጉት ከቶ የሚገርም አይሆንም።

በምረቃው ተውኔት አስተናጋጅነት ፣ በመፅሐፍ ተብየው ላይ የሙገሳ ዲስኩር ደስኳሪነት እና በአጃቢነት (በአጨብጫቢነት) አለባበሳቸውን (ቅርፃቸውን) አሳምረው የተገኙ ካድሬ ምሁራን ባለ ሥልጣናት ፣ የዩኒበርሲቲ ዶ/ሮች እና ፕ ሮች ተብየዎች ፣አንጋፋ  የኪነ ጥበብ ባለሙያ ተብየዎች እና የእድሜ ባለ ፀጋነታቸው ፈፅሞ ያላስተማራቸው ባለ ነጭ ፀጉሮች “ለመሆኑ ዳንኤል በየትኛው ሰብእናው እና የተግባር ማንነቱ  ነው ስለ ትርክት እዳነትና በረከትነት የሚደሰኩርልን? “ የሚል ጥያቄ ህሊናቸውን ሲያልፍም እንኳ አልነካውም።

እንግዲህ ይህንን ትውልድ የሚያስተምሩት፣ የሚገዙት፣ ለኪነ ጥበብ እድገትና መስፋፋት አርአያዎችህ ነን የሚሉት እና እድሜ ቁጥር ብቻ ሳይሆን ከህይወት የመማርና የማስተማር ፀጋ መሆኑን ከእነርሱ እንዲማር የሚሰብኩት ፣ ወዘተ እንዲህ አይነት ትውልድ አሳፋሪና ገዳይ ወገኖች ናቸው።

አብይ አህመድም ለማታለያና ለርካሽ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድ የመፅሐፉ ፀሐፊ ሆኖ ከቀረበው አማካሪው (ዳንኤል ክብረት) ጋር እየተናበበ ለጥረዛና ለምረቃ ያበቃው መፅሐፍ የታለመለትን ዓላማ ሊያሳካ እንደሚችል የተሰማውን ርካታ (ደስታ) ለመደበቅ ተስኖት ሲቁነጠነጥና በአድናቆት ቃላትና ሐረጎች መረጣ ሲቸገር ታዝበናል ። አዎ! በእርሱና በካምፓኒው (በፓርቲው) መርዘኛ የትርክት ስርጭት ምክንያት የግፍ አሟሟትና የቁም ሞት ሰለባዎች የሆኑትና እየሆኑ ያሉት ንፁሃን ዜጎች ጉዳይ ከመፅሐፍ ምረቃ፣ ከችግኝ ተከላ፣ መናፈሻ ከማስዋብ፣ ከኮሪደር “ልማት” ፣ ከጥርጊያ መንገድ አስጎብኝነት፣ ወዘተ  በላይ ፈፅሞ አይበልጥበትምና (አያሳስበውምና) በዚህ መፅሐፍ ምረቃ ላይም ይህንኑ እጅግ ሸፍጠኛና ጨካኝ የፖለቲካ ማንነቱን ለመደበቅ ቢሳነው የሚያሳዝን ቢሆንም የሚገርም ግን አይደለም።

ይህ ቀጥተኛና ግልፅ ሂሳዊ አስተያየቴ የሚመራቸው ወገኖች ከሚሰነዝሩት የውግዘት ውርጅብኝ በተጨማሪ ለመሆኑ መፅሐፉን ሳታነብ …? የሚል ጥያቄ እንደሚያነሱ የምጠብቀው ነው።  ዳንኤል በመፅሃፍ አስጠረዘው እንጅ ፖለቲካ ወለድና መራሽ የትርክት ሴራና ሸፍጥ የእለት ከለት ወጋችን (መነጋገሪያችን) ከሆነ ዘመናት ተቆጥረዋል።

ገንቢና ዘላቂ መፍትሄ ከመፍጠሩ ላይ ነው አይወድቁ ውድቀት የወደቅነው።  ለዚህም ነው ዳንኤል ክብረት እኩይ ትርክትን በሥርዓተ ትምህርት እና በቀጥታና በተዘዋዋሪ በፖለቲካ  መመሪያወቻቸውና በፖሊሲዎቻቸው አማካኝነት የእኩይ ፖለቲካ ማስፈፀሚያ ባደረጉትና እያደርጉ ባሉ የጎሳ አጥንት ስሌት ቁማርተኞች የቤተ መንግሥት አማካሪነት ወንበር   ላይ ተኮፍሶ የትርክት የትንታኔ ድሪቶውን በመፅሐፍ መልክ በማስጠረዝ  ወደር የሌለው እኩይ ጮሌነቱን እንድናደንቅለት የሚሰብከን።

ዳንኤል ክብረት የእኩይ ትርክት አምራችና አከፋፋይ የሆነውና እየሆነ ያለው የፖለቲካ ሥርዓት እንደ ሥርዓት መሠረታዊ የሥርዓት ለውጥ ያስፈልገዋል የሚል ትርጉም ያለው አንዳችም ቃል ወይም አባባል ፈፅሞ ሊጠቀም አይችልም። ለዚህ ነው ፈፅሞ ሊድን በማይችል የእኩይ  ፖለቲካ ትርክት  ካንሰር የተመረዘን ሥርዓት  እንደ ሥርዓት የትርክቱ  ማስተካከያ አካል የሚያደርግ የትንታኔ ድሪቶ አዲስ ነገር ስለሌለው ቢነበብም የፀሐፊውን ሸፍጥ ከማሳየት ያለፈ አዲስ ነገር ፈፅሞ አይኖረውም ብሎ መሞገት ትክክል የሚሆነው።

አለመታደል ሆኖብን ሳይሆን በገዛ ራሳችን እጅግ አስቀያሚና ተደጋጋሚ የውድቀት አባዜ ምክንያት በአንፃራዊነትም እንኳ ቢሆን ትክክለኛና ገንቢ የሆነ የትርክት ይዘትና አቀራረብ  እውን  ሊሆን የሚችልበትን ሥርዓት እውን  ለማድረግ ባለመቻላችን ምክንያት  ይኸውና ዛሬም ወደር በሌለው ፖለቲካ ወለድ ወንጀል የበሰበሰውና የከረፋው የጎሳ አጥንት ስሌት ፖለቲካ ሥርዓት ቁማርተኞች  አማካሪዎች እና ህሊና ቢስ ባለሟሎች መሳለቂያ ሆነን ቀጥለናል።

ከዚህ ዘመን ጠገብ ፣ እጅግ አስከፊ እና አስፈሪ ሁኔታ ሰብረን መውጣት ካለብን የእንዲህ አይነት ወገኖችን የፖለቲካና የሞራል ዝቅጠት መፀየፍ እና ቢቻል ወደ ህሊናቸው እንዲመለሱ፣ ካልሆነ ግን ከመከረኛው ሀዝብ የነፃነትና የፍትህ መንገድ ላይ ዘወር እንዲሉ ማድረግ ለነገ የማይባል  የትግል አካል መሆን አለበት!!!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ “ይድረስ ለእገሌ” ማለቱ ሰለቸኝና ተውኩት እንጂ ዛሬም መጻፍ የፈለግሁት የአማራን ዕልቂት ለመታደግና የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማብሰር እየተዋደቁ ላሉት ወገኖቼ ነው – በፋኖም ይሁን በሌላ ስም፡፡ ኢትዮጵያን ወደቀደመ ክብሯ ለመመለስ የነገድና

ጀልባዋ አትሰምጥም፤ የሚሰምጥ ግን አለ!

[ማስታወሻ ከፍል አንድ፣ በዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ ኦፍ ጃዋር አንድ ኢትዮጵያ ተብሎ በእንግልዝኛ ወጥቷል] (https://zehabesha.com/of-jawar-and-ethiopia/) ባለፈው ሰሞን፣ ጃዋር መሐመድ ከደረጀ ኃይሌ ጋር  በነገራችን ላይ ክፍል ሁለት ባደረገው ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቼ ገንቢ አስተያየት ጽፌ በኢንግሊዝኛው ዘሐበሻ ድረ ገጽ ላይ አሳትሜ ነበር። አስተያየቴ በዚህ ቃለ ምልልስ

ስለ ጃዋርና ኢትዮጵያ (ክፍል ሁለት)

January 20, 2025 ጠገናው ጎሹ የአቤ ጎበኛው አልወለድም ለወገኖቹ መብት መከበር ሲል ባደረገው ጥረት ምክንያት እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ይሙት በቃ በፈረዱበት ጊዜ በምላሳቸው መልካም  አድርጎ ስለ መገኘት እያወሩ በድርጊት ግን ተቃራኔውን የሚያደርጉ ሁሉ

ወዮ ለመከረኛው የአገሬ ህዝብ እንጅ  ታየማ ታየ ነው

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ “ ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ”   — መክብብ 7፥5 እስቲ ቆም ብለን በማሰብ  ራሳችንን እንፈትሽ ።  እንደ ሰው ፣ የምንጓዝበት መንገድ ትክክል ነውን ? ከቶስ ሰው መሆናችንን እናምናለንን ? እያንዳንዳችን ሰው መሆናችንን እስካላመንን ጊዜ ድረስ ጥላቻችን እየገዘፈ

 ለሀገር ክብርና ብልፅግና ብለን ፤ ቆም ብለን በማሰብ ፤ ህሊናችንን ከጥላቻ እናፅዳ

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

Go toTop