ሰኔ 29 2016 ዓ/ም
ዮናስ ብሩ
ዶክተር ዮናስ ብሩ “The Imperative Comparative: Lessons from the EOTC and Fano” በሚል ርዕስ የዘመናችንን ሲኖዶስ ከፋኖ ጋራ፡ ፖለቲከኞችን ከነፈንታሁን ዋቄ ጋራ በማነጻጸር፡ ሲኖዶሱን እያደነቁ ባቀረቧት ጦማር፦ “Fanno can benefit from two recent experiences: The successful experience of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (EOTC) በማለት ኖኖ ከሲኖዶሱ ጠቃሚ ትምህርት ማግኘት እንደሚችል ለፋኖ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ለፋኖ ያቀረቡት ጥሪ ከልጅነት እስከ እውቀት እያስተማረች ያሳደገችኝን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ማእከል ስላደረገ ወቃሺ መንፈስ በህሊናየ ተፈጠረብኝ፡፡ ሰውነቴን ለወቃሽ ሕሊናየ መቃብር ላለማድረግ ከዚህ በታች በዘረዘርኳቸው አንቀጾች ከህሊናየ አውጥቼ ሕሊናየን ነጻ እንዳወጣው ተገደድኩ፡፡
1ኛ የሲኖዶሱን ዝቅጠት፤
2ኛ የፋኖን አቋም፡
3ኛ የነፈንታሁን ዋቄን አቋም
4ኛ የቤተ ክርስቲያናችን መመዘኛ፡፡
5ኛ ለዶክተር ዮናስ ያቀረብኩላቸው ጥሪ
የተገደድኩበትን ስሜት በቅድሚያ ካቀረብኩ በኋላ በዘረዘርኳቸው አንቀጾች ወደ ምገልጻቸው ዝርዝር ሀተታየ እገባለሁ፡፡
ምንድነው ያስገደደኝ
ከቤተ ክርስቲያን ጋራ በመያያዙ ከዚህ ቀደም ባሳለፍኩ ትዝታየ ላይ የዶክተር ዮናስ *ምህር ፈንታሁንን ከ18 ክፍለ ዘመን ጫካ ተፈንጥሮ የወጣና የ21ኛውን ዘመን ፖለቲካ የደበላለቀ ነው” እያሉ ከሰዋል፡፡
ዶክተር ዮናስ የሲኖዶሱን ብቃትና ጥሩ ምሳሌነት የፈንታሁን ዋቄን አቋም በጎጅነት ወስደን እንድንማርበት አድርገው ያቀረቡት 60 ሚሊዮን ህዝብ የምትመራው ቤተ ክርስቲያኔ ካስተማረችኝ ቀኖናዋና ነገረ መለኮቱ ጋራ መቃረኑን ለማሳየት ብቻ እሞክራለሁ፡፡
የገለጹበት መንገድ ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዊ መርሆ ጋራ የተቃረነ ቢሆንም፡ ባነጋጋሪነቱና በቀስቃሽነቱ አእምሮየን ቀስቅሶ የሲኖዶሱን ዝቅጠት በትኩረት እንድመለከተው አድርጎኛል፡፡
እነ ፋንታሁን ዋቄን የተበላሸው ባህል ውጤቶች ለማድረግ “The problem with our nation’s politics is our culture” ብለው የተናገሩት የሚገልጸው እነ ፈንታሁንን አይመስለኝም፡፡ በዝሙት ወድቀው ማፈር ሲገባቸው አይናቸውን አጥበው በሲኖዶሱና በየቤተመቅደሱ የተሰገሰጉ የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት ዩቱብ ከፍተው ጠልቀው ባልተረዱት ስለ ቤተ ክርስቲያን የሚናገሩትን የሚመለክት ይመስለኛል፡፡ ዶክተር ዮናስ እነ ፈንታሁን ዋቄን በዚህ መንገድ ለምግለጽ ግን የቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ አይፈቅድላቸውም፡፡
እነ መምህር ፈንታሁን ዋቄ አሁን በቆሙበት አቋም ይዝለቁበት አይዘለቁበት እርግጠኛ ባልሆንም አሁን የሚመሩበት መንገድ ቀዳሜ ሰማእት የምንለው ቅዱስ እስጢፋኖስ የሄደበትን ሐዋርያዊ ትውፊት እንዳይ አድርጎኛልና አመሰግናቸዋለሁ፡፡
እነ ፈንታሁን ዋቄም የዶክተር ዮናስን ሀሳብ እኔ በተረዳሁበት ተረድተው “የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ” በሚለው ሐዋርያዊ ትውፊት ካሉበት እርከን ዝቅ እንዳይሉ እያሳሰብኳቸው፡ ዶክተር ዮናስ ለመልካም ነገር መለኪያ አድርገው የጠቀሱት ሲኖዶስም ዶክተር ዮናስ ባቀረቡት ከንቱ ውዳሴ ራሱን ሳይደልል ጽሑፋቸውን መስታዋት አድርጎ ራሱን ቢመለከትበት ከነ መምህር ፈንታሁን ሐዋርያዊ ትውፊት ትምህርት እንደሚያገኝ አልጠራጠርም፡፡
ዶክተር ዮናስን “Fanno can benefit from two recent experiences: The successful experience of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (EOTC) እንዲሉ ያደረጋቸው፡፡ ከቤተ ክርስቲያን በመራቃቸው ይመስለኛል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ “The same screwed up culture” ያሉት እርሳቸውንም ጠልፎ እንደከተታቸው ተገነዘብኩ፡፡
ሲኖዶሱም እነፈንታሁንም የሚመዘኑበት መድሎት “እለ ተንሥኡ በምኩራብ እንተ ስማ ሊበርጢኖን እምቀሬኒወን ወእምክስንድሬዎን ወእምቂልቅዮን ወእምእስያ” (የሐ 6፡9) በምትለው አረፍተ ነገር አካታ የያዘችው ሐዋርያዊት ትውፊት መሆኖን ዶክተር ዮናስ የተገነዘቡ አይመስሉም፡፡
ከዚህ በላይ መድሎት ብየ በጠቀስኳት አረፍተ ነገር የተገለጹት ሰወች በዘመናቸው የተከሰተባቸው ፖለቲካ ከተወለዱባቸው ቦታወች አሳዷቸው ሊበርጢኖን በምትባለው ቤተ ምኩራብ እየተሰበሰቡ ስለነጻነት የሚወያዩ ልሒቃን ነበሩ፡፡ በነዚህ ልሂቃን ቅዱስ እስጢፋኖስ የገጠመው ተግዳሮት አሁን በዘመናችን እነ ዲያቆን ፈንታሁን ከገጠማቸው ተግዳሮት ጋራ የሚመሳሰል እንደሆነ ግልጽልጽ አድርጎ ያሳያል፡፡
ዶክተር ዮናስ ብዙወች የቤተ ክርስቲያን አባላት እኔም ጭምር ተበላሽቷል እያልን የምንቃወመውን ሲኖዶስ እንደ መልካም ምሳሌ በመጥቀስ ይስተካከል የሚሉትን እነ ፈንታሁን ዋቄን እንደጥፋት በመቁጠራቸው ከቆምኩለት አላማ ስለተጋጨብኝ አላማየን ለመከላከል እንጅ እርሳቸውን ለምንቀፍ እነ ፈንታሁንን ለመደገፍ እንዳልሆነ ሁሉም እንደሚረዳልኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ከዚህ በመቀጠል ዶክተር ዮናስ ለመልካም ምሳሌነት የጠቀሱት የሲኖዶሱን ዝቅጠት መድሎት ባልኩት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡
1ኛ የሲኖዶሱ ዝቅጠት
ዶክተር ዮናስ እንዳሉት ሲኖዶሱ ለምሳሌነት የሚጠቀስ ሳይሆን ከማይወጣበት አዘቅት እንደገባ አባላቱ በስፋት እየተነጋገረበት ነው፡፡ የሲኖዶሱን ዝቅጠት ለማሳየት ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጦማሮቼ ደጋግሜ የገለጽኩትን እደግማለሁ፡፡ “ደሙ ለእኁከ በጽሐ ኀቤዬ እምድር ርግምተ ትኩን ምድር እንተ አብቀወት አፉሃ ከመ ትስተይ ደሞ ለእኁከ” (ዘፍ 4፡
10_11) እንዳለው ባንድ በቃኤል የተገደለው ያንድ የአቤል የደም ድምጽ ከእግዚአብሔር ደርሶ ከከሰሰ፡ በኢትዮጵያ አገራችን እየፈሰሰ ያለው የብዙ ሚልዮኖችን የደም ክስ ተሸካሚው ማን ይሆን? ሸክሙስ ምንኛ ይከብድ ይሆን? እጅግ ያስፈራል! ያንድ የአቤል ደም መሬትን እንድትጮህ ካስገደደ፡፡ መሬትም እንድትረገም ካስደረገ፡፡ መሬትንም ካስጮኸ ለ30 አመታት ሲፈስ የነበረው የአማራው ደም፡፡ ይልቁንም በብልጽግናው መግሥት የፈሰሰው የአማራውና የትግራይ በጥቅሉ የሕዝበ ክርስቲያን ደም የሚያስከትለው ምድራዊ ጩኸት በመሬት ላይ ያለ የሰው ዘር ይቅርና ፕላኔቶች ሊሸከሙ የሚችሉት ይመስለወታል? ለዚህስ ዘግናኝ እልቂት በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ እርሰዎ በምሳሌነት ከሚጠቅሱት ከሲኖዶሱ ሌላ አካል ተጠያቂ የሚኖር ይመስለወታል?
“ወሶበ አእመረ አውናን ከመ ኢኮነ ሎቱ ዘርዕ ሶበ ቦአ ኀበ ብእሲተ እኁኁ ከዐወ ዘር ዲበ ምድር ወኮነ እኩየ ቅድመ እግዚአእብሔር ወቀተሎ” ዘፍ 38፡10_11 እንዳለው መጽሐፍ አውናን የሚባል ሰው ዘሩ ወደ ትዕማር ማሕጸን ተቀድቶ ትውልድ እንዳይቀጥል ዘሩን በመሬት ላይ በመድፋቱ እግዚአብሔር ቀሰፈው፡፡
ያላገባብ የሰው ዘር ጠብታ የሚያስከትለው መቅሰፍት እግዚአብሔርን ካስቆጣና የሞት ፍዳ ካስከተለ የአማራ ዘር ዘሬ አይደለም፡፡ ካማራ ጋራ የደም ንክኪ የለኝም በማለት ከኢትዮጵያ ገጸ ምድር እንዲጠፋ እየታረደ ያለቀው የአማራው ደም በኢትዮጵያ ላይ ሚያስከትለው ተከታታይ ፍዳ በደሙ ፍንጣቂ የተበከለው ራሱ ሲኖዶሱ የህይወት መስዋዕት የሚጠይቅም ቢሆን ከፍሎ በንስሀ ራሱን አጽድቶ በምሳሌነቱ ሁሉም የሚጸዳበትን እቅድ ካልዘረጋ በቀር የእልቂቱ ቀጣይነት እርሰዎ በምሳሌነት የጠቀሱት ሲኖዶስ ጾምና ጸሎት የሚገታው ይመስለወታል?
“ኦ ዘታወጽኦ ለሕጻን እምሐቄ ብእሲ ወትፌንዎ ውስተ ከርሠ ብእሲት ወትጠበልሎ በሰፋድል ረቂቅ ወእንዘ ማይ ውእቱ ታረግኦ በጥበብከ ወትነፍህ ላዕሌሁ መንፈሰ ሕይወት ወበ አርባ እለት ትሰይም ዲቤሁ በዘኮነ ከዊኖ” (አትናቴዎስ ቁ 114፡) ማለትም፦በማህጸን ሳለ በ40 ቀኑ ሰባዊ ቅርጹን የጨረስው ጽንሱ ሙሉ ሰውነቱን አሟልቷል፡፡ ሰው መሆንን ጀምሯልና ማስወረድ መግደል ነው” ብላ የምታስተምረውን ቤተ ክርስቲያን እመራለሁ ከሚለው ሲኖዶስ ሌላ ማነው ተጠያቂው?
“ርዑደ ወድንጉጸ ወሕውከ ኩን ላዕለ ምድር” እንዲል፦ ቃኤል ያንድ የአቤልን ደም በማፍሰሱ ተቅበዝባዥ፡ ተሸባሪና ስኩረ መንፈስ ካስደረገው፡ በሚሊዮን የሚቆጠርውን የሰው ደም ካስፈሰሰና ካፋሰሰ ጋራ የተሰለፈው ሲኖዶስ ይቅርና በዓለም ያለውን ሁሉ የአዳም ዘር ተቅበዝባዥ ተሸባሪና አሸባሪ አያደርገውም ብለው ይገምታሉ?
ኢትዮጵያዊት ቤተ ክርስቲያናችን በራሷ ምድር ከዚህ ቀደም በወረሯት ጠላቶቿ በልጆቿ ላይ ከተፈጸመው የከፋ ግድያ ከዚህ በታች በዘረዘርኳቸው በአራት ማንነቶቻቸው ምክንያቶች በመልካም ምሳሌ በጠቀሱት ሲኖዶስ ተባባሪነት ጭፍጨፋ እየተፈጸመባቸው መሆኑን አያውቁምን?
1ኛ፦በኦርቶዶክስ እምነታቸው
2ኛ፦ ባማራነታቸው
3ኛ፦ባመረኛ ተናጋሪነያቸው
4ኛ፦በኢትዮጵያዊነታቸው
ከአማራው ሕብረተ ሰብ ውጭ ያለው ህዝብ በአማራው ላይ ቀጥታ ከተሰነዘረበት ሰይፍ ቢያመልጥም አማራኛ በመናገሩና በኢትዮጵያውነቱ ሙስሊሙም ከመገደል እንዳላመለጠ ሳይሰሙ ሳያውቁ ቀርተው ነው? አማራ ሳይሆን በኦርቶዶክስ ክርስትናው ከአማራው ጋራ ንክኪ ያለው ሁሉ ከግዳያው እንዳላመለጠ በተደጋጋሚ ተነግሯል፡፡ በትግራይ የሚኖረው ኦርቶዶክሱም በወያኔወች ዘመን በአማራው ላይ ሲፈጸም የነበረው እልቂት በትግሬንቱ ሳይነካው ቢቆይም፡፡ የወያኔ መንግሥት ከፈረሰ በኋላ የደረሰበት እልቂት በኢትዮጵያውነቱና በኦርቶድክስ እምነቱ እስካሁን እያለቀ ነው፡፡ ለዚህስ በተቀዳሚ ሊጠየቅ የሚገባው ማነው?
በሚካሄደው ጭፍጨፋ የኢትዮጵያ ምድር ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በኢትዮጵያውያን ሬሳ ተሸፍኗል፡፡ አፈሩ
በኢትዮጵያውያን ሥጋ ደምና አጥንት ወደ ጭቃነት ተለውጧል፡፡ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚፈሱት ወንዞች ሳያቋርጥ ከሚጎርፈው ኢትዮጵያውያን ደም ጋራ ተቀላቅለዋል፡
- ሲኖዶስም ጭምር ህዝቡ የሚጠጣው ውሀ ከወገን ደም ጋራ የተቀላቀለውን ነው፡፡ የሚነፍሰውም አየር ከደም ጋራ የተቀላቀለውን አፈር እየጋፈ የሲኖዶሱን አባል ሁሉ ባፍንጫው እየጋተው ነው፡፡ መጋት ብቻ አይደለም፡፡ ከወገን አጥንትና ሥጋ የተቀላቀለውን አፈር እየጋፈ በሲኖዶሱ ላይ በመበተን ሲኖዶሱን በቁሙ እየቀበረው ነው፡፡
በመንግሥት አልባነት ይኖራል ተብሎ በማይገመት ሕብርተሰብ ላይ ይፈጸማል ተብሎ የማይገመት ይህ ሁሉ ድርብርብ ግፍና በደል በህዝበ ክርስቲያኑና በኢትዮጵያዊው ሁሉ ዜጋ ሲፈጸም ግፈኛውን መንግሥት በመተባበር ያደፈጠውን ሲኖዶስ እኮ ነው ለመከላከል በመታገል ላይ ላለው ፋኖ ምሳሌ ይሁንልህ የሚሉት፡፡
የሚጨፈጨፈው ሕዝበ ክርስቲያን ከደረሰበት መከራ አምላኩ እንዲያወጣው እየተሳለ የሚሰጠውን የስለት ገንዘብ እየበላ በትረ ምንግሥቱን እየተቀባበሉ ከሚፈጁት አረመኔወች ጋራ በመተባበር ያደፈጠውን ሲኖዶስ ለፋኖ “Fanno can benefit from two recent experiences: ብለው ሲጠቅሱ እጽፍ ድርብ በደል እይመስለወትምን? ከዚህ በመቀጠል ስለቱን እየበላ እንደ ድልብ በሬ ሰውነቱን አወፍሮ ከብልጽግ ጋራ ከሚያናፋው ሲኖዶሱ ይልቅ ፋኖ እጅግ በተሻለ ሞራላዊ እርከን ላይ እንዳለ ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡
2ኛ ከሲኖዶሱ አቋም የፋኖ አቋም በእጅጉ የተሻለ ነው፡፡
ከዚህ ቀደም በተለያዩ ዘመናት የወረሩን የተለያዩ ጠላቶች ከሰነዘሩበን የአመጽ ብትር የከፋውን ብትር ከዚህ በታች በምገልጻቸው በአራት ማንነቶቻቸው በኢትዮጵያውያን ላይ ሰንዝሯል፡፡
1ኛ፦በኦርቶዶክስ እምነታቸው
2ኛ፦ ባማራነታቸው
3ኛ፦ባመረኛ ተናጋሪነያቸው
4ኛ፦በኢትዮጵያዊነታቸው
የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይም አማራውን ለመስበር አረመኔወች የሚቀባበሉትን ብትር ለመስበር ፋኖ እንደ ዳዊት የጽድቅ ብትሩን አንስቷል፡፡
ጽድቅ የአመጽ ተቃራኒ ነው፡፡ አመጽ በደል ነው፡፡ አመጸኛ በደለኛ ነው፡፡ አመጽ ፈጻሚው በደለኛ መንግሥት ሲሆን፡፡ መንግሥት ብትሩን የሰነዘረበት ተበዳይ ሕዝብ ነው፡
- መንግሥት በህዝብ ላይ የሰነዘረው ብትር የአመጽ ብትር ነው፡፡
ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ሕዝብ በተወለደበት ምንደር ምንግሥት እየተከታተለ እየጨፈጨፈው ነው፡፡ አሁን ደግሞ ተሰዶ በሰፈረበት መንደር ጠላትን ለመከላከል የተሰለፈውን ሠራዊት አዘመተበት፡፡ መንግሥት የሠራዊቱን ብትር ወደ አመጻ ብትርነት ቀየረው፡፡ ሠራዊቱንም በራሱ ሕዝብ ላይ በማዝመት አመጸኛ አደረገው፡፡
ዳዊት “አፍቅርከ ጽድቀ ወአመጻ ጸላእከ በትረ ጽድቅ ወበትረ መንግሥትከ” ማለትም፦ ጽድቅን ወደድክ አመጽን ጠላህ ብሎ በገለጸበት ስንመዝነው የአመጽን ብትር በወገን ላይ ያነሳው ማነው? በወገን ላይ የተሰነዘረውን የአመጽ ብትር ለመከላክል ለዘለቄታውም ለምስበር የጽድቅንስ ብትር ያነሳው ማነው? መቼም ዶክተር ዮናስ የፋኖን ብትር ወደ አመጽ የብልጽግናን ብትር ወደ ጽድቅ እንደማይለውጡት እርግጠኛ ነኝ፡፡
ዶክተር ዮናስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን 151ኛ አድርጋ ደምራ የያዘችውን መዝሙረ ዳዊት ከነ ማህደሩ ወርውረው ብልጽግና የተሸከመውን 150ኛ ማህደር አልባ መዝሙረ ዳዊት እንደማይሸከሙ እርግጠኛ ባልሆንም፡ እነ ፈንታሁንና ፋኖ በደረታቸው ከተሸከሙት ከግእዙ 151ኛ ላይ የተቀደሰውን የዳዊትን መፈክር ከዚህ በታች እጠቅሳለሁ፡፡
“ወቀብዐኒ ቅብዐ ቅዱሰ፡፡
አኅውየሰ ሠናያን ወልሂቃን፡፡
ወኢሠምረ ቦሙ እግዚአብሔር ፡፡
ወወጻእኩ ለተእኅዞቱ ለሕዝብ ነኪር፡፡
ወረገመኒ በአማልክቲሁ ርኩሳን፡፡
ወአንሰ ነሣእኩ አእባነ እምውስተ ፈለግ
ወወጸፍክዎ ውስተ ፍጽሙ፡፡
አሜሃ ወድቀ በኃይለ እግዚአብሔር ፡፡
ወአንሰ ነሣእኩ ዘእምላዕሌሁ ሰይፈ፡፡
ወመተርኩ ርእሶ ለጎልያድ፡፡
ወአሰሰልኩ ጽእለተ እምደቂቀ እስራኤልለ”(መዝ 151)
እርሰዎ በመልካም ምሳሌነት የሚጠቅሱልን የብልጽግናን ጎደሎ መዝሙረዳዊት አንግቦ በወገን ላይ የዘመተውን ሲኖዶስ ነው፡፡ ከዚህ ቀጥየ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያኔ በግዕዙ ቋንቋ አፌን ባሰፈታችኝ በዳዊት መፈክር ላይ የተመሠረተውን የነፈንታሁን ዋቄን አቋም ለመግለጽ እሞክራለሁ፡፡
3ኛ የነፈንታሁን ዋቄ አቋም
የነፈንታሁን ዋቄ አቋም ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያናችን ባሸከመቻቸው በ151ኛ በተመዘገበው ዳዊት በተናገረው መርሆ ላይ የተመሠረተ ሆኖ ከፋኖ መፈክር ጋራ ተቀራራቢ ቢመስልም፦ እነ ፈንታሁን ይዘው የተነሱት ከፋኖው ለየት ያለ ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ሰይፍ ብሎ የገለጸው ረቂቅ ትጥቅ ነው፡፡ ይህ ረቂቅ ትጥቅ በ149 ነኛው መዝሙረ ዳዊት ላይ እንደሚከተለው የሰፈረው ነው፡፡
“ወከመ ይእሥሮሙ ለነግስቶሙ በመዋቅህት ፡፡ ወለክብራኒሆሙኒ በእደ ሰናስለ ሐጺን፡፡
ከመ ይግበር ኩነኔ ዘጽሑፍ ላዕሌሆሙ፡፡
ክብር ይእቲ ዛቲ ለኩሉ ጻድቃኑ” የሚለው ቃል ነው፡፡ ይህም ማለት፦ “መሪወቻቸው ሞራለ ቢሶች ሲሆኑ እግሮቻቸውን በእግር ብረት እጆቻቸውን በዛንጅር አስረው በተጻፈው ሕጋቸው ይቀጧቸው ዘንድ ለተመረጡት እድል ተሰጣቸው” ይህን የዳዊትን ሀሳብ ክርስቶስ ለዮሐንስ በራእይ “ወዘሰ በመጥባሕት ይቀትል ሀለዎ ይሙት በመጥባህት፡ ወዘሂ ውእቱ ትዕግስቶሙ ወብጽዕት ሃማኖቶሙ ለቅዱሳን፡ ወኢአንክሮቱ ለሰይጣን” ብሎ ገለጸው ፡፡ (ራእየ ዮሐንስ 13፡ 10)፡፡ እነ ፈንታሁን ብዙወቹ ከሚከሰሱበት ከሰይጣን ወጥመዶች ከዝሙት ከስለት ገንዘብ ከዘረፋና ከመወላወል ገለል ያሉ እንደ ቀዳሜ ሰማእቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ “እናንት አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ እውነቱን የምትቃወሙ” (የሐዋ 7፡51) እያሉ ከቀኖናው ከነገረ መለኮቱ ርቀው ያሉትን ለመገሰጽ እግዚአብሔር ያደላቸው በልዕለ አእሞሮ ላይ ያሉ ናቸው፡፡
4ኛ ዶክተር ዮናስ ለሲኖዶሱ የሰጡትን ከንቱ ውዳሴ የቤተ ክርስቲያንችን አስተምህሮ አንኮታኩቶ ሲጥለው ከዚህ በታች የሰፈረውን እንመልከት፡፡
“ወኤጲስ ቆጶስሰ ዘነሥአ ክህነተ እምእግዚአብሔር ከመ የዐቀብ ሥጋ ውሰነፍስ እምኀጉል በከመ ነፍስ ትከብር እምሥጋ ከማሁ ክህነትኒ ትትሌዓል በክብር እመንግሥት ወይእቲ ተ አሥሮ ለዘይደልዎ ኩነኔ ወትፈትሖ ለዘይደልወ ፋትሐ፡፡ ወበከመ ክህነት ትትሌዐል እመንግሥት ወከማሁኬ ትትሌዐል ኩነኔሁ ለዘይትቃረና ለክህነት ይፈደፍድ እምኩነኔሁ ለዘይትቃወሞ ለንጉሥ”(ፍ አ 9፡289_290) ፡፡
ማለትም፦በእግዚአብሔር ፈቃድ ላይ የተመሠረተ ክህነት በምዳራዊ ፈቃድ ጉስቁላና በቅድስና ተዐቅቦ የተለየ ስልሆነ በምድራዊ ፈቅድ ላይ ከተጻፈው ሕግ በላይ ነው፡፡
በብጽዕናውና በቅድስናው ከምድራዊው መንግሥት በላይ ስለሆነ ከምድራዊውም ሕግ በላይ ነው፡፡ ምድራዊውንም ሰማያዊውንም ሕግ በምሳሌነት አክብሮ በማስከበር ከመንግሥት የላቀ ከፍተኛ ልዕለ አእምሮ አለው፡፡
ሲኖዶሱ በዚህ ሁሉ ድርብርብ ተቀብዖቱ ከመንግሥት የላቀ ሥልጣንና ሀላፊነት አለበት፡፡ ምድራዊው መንግሥት በሥጋዊ ፍላጎት ተፈትኖ ሀላፊነቱን ረስቶ ራሱ ከሰራውና አስፈጽመዋለሁ ብሎ ከማለለት ህግ በታች ሲወድቅ ፦ ሲኖዶሱ የመገሰጽ ብሎም ህዝብ የካደው መንግስት የተሰነዘረበትን የአመጽ ዱላ ሰባብሮ እንዲጥለው የማስተማር ግዴታ አለበት፡፡ ህዝብ የተሰነዘረበትን የአመጽ ብትር ሰባብሮ እንዲጥለው የተቀደሰው ሲኖዶስ በሚያደርገው ቅስቀሳ፡ ከሀዲው መንግሥት ከሚሰነዘረበት የአመጽ በትር ሲኖዶሱ ሳያፈገፍግ ከህዝብ በፊት ድብደባውን የመቀበል ግዴታ አለበት፡፡
ዶክተር ዮናስ ለዘመናችን ሲኖዶስ የሰጡት ከንቱ ውዳሴ ተንኮታኩቶ እንደወደቀና እነ ፈንታሁን ዋቄ በቀኖናችን ላይ መቆማቸውን ከዚህ በላይ ክ 1 እስከ 4 በዘረዘርኳቸው አንቀጾች ካሳየሁ በኋላ ለዶክተር ዮናስና ለመሰሎቻቸው ከዚህ በታች በማቀርባት በ5ኛዋ አንቀጽ የተማኅጽኖ ጥሪ በማቅረብ ሀሳቤን እቋጫለሁ፡፡
5ኛ ለዶክተር ዮናስና ለመሰሎቻቸው የቀረበ የተማሕጽኖ ጥሪ፦
ዶክተር ዮናስ ብሩ ሆይ! ለጽሑፈዎ መነሻ አድርገው ለፋኖና ለነ መመምህር ፋንታሁን ለሰጡት ምክር ራሰዎ “The Imperative Comparative: Lessons from the EOTC and Fano” ያሏትን እኔም ሐሳበዎን ለመቃወም “The Imperative Comparative: Lessons from the EOTC and Fano” ያሏትን እንደመግቢያ አድርጌ ተጠቅሜአታለሁ፡፡
የተቃውሞ ጽሑፌን በገባሁባት ለመውጣት ብቻ ሳይሆን ለማቀርብለዎ ጥሪ መገቢያ ካደረኳት ሌላ የተሻለ ሀሳብ
ስላላገኘሁ ጭምር እንደ መግቢያ ያደረኩትን ለመጥሪያነት ተጠቅሜ መደምደሚያ ባደርጋት ስነጽሑፍ ነውር አያደርግብኝምና በመግቢያየ የጀመርከበትን የተቃውሞ ሐሳብ የጥሪየ ተማኅጽኖ አድርጌ ሳቀርብለዎ በደጊመ ቃልነት እንዳይሰለቹ አደራየ ጥብቅ ነው ፡፡
የዘመናችንን ሲኖዶስ ከፋኖ ጋራ ፖለቲከኞችን ከነፈንታሁን ዋቄ ጋራ በማነጻጸር ሲኖዶሱን እያደነቁ፦ ፋኖንና የፋኖ ደጋፊወችን ከፈንታሁን ዋቄ ጋራ ደምረው የነቀፉበት ሀሳብ እንድንማርበት ያቀረቡልንና በመቀጠለም “The same screwed up culture is what has allowed መምህር Fantahun Waqe to jump out of the woods of the 18 th century and cacophonize the 21 st century” ብለው ያቀረቡትን ከቤተ ክርስቲያናችን መርሆ ጋራ መጋጨቱን አሳይቻለሁ፡፡
የገለጹበት መንገድ ከቤተ ክርስቲያናችን ቀኖናዊ መርሆ ጋራ የተቃረነ ቢሆንም፡ ባነጋጋሪነቱና በቀስቃሽነቱ አእምሮየን ቀስቅሶ የሲኖዶሱን ዝቅጠት በትኩረት እንድመለከተው አድርጎኛል፡፡ ይዝለቁበት አይዘለቁበት እርግጠኛ ባልሆንም የዘመናችን ዲያቆናት እነ ፈንታሁን ዋቄ አሁን የሚመሩበት መንገድ ቀዳሜ ሰማእት የምንለው ቅዱስ እስጢፋኖስ የሄደበትን ሐዋርያዊ ትውፊት እንዳይ አድርጎኛልና አመሰግነወታለሁ፡፡
ይሁን እንጅ እንደ መልካም ምሳሌ አድርገው ያቀረቡት ሲኖዶስ በቀኖናችን ሲመዘን መወገዝ መወገድ የሚገባው እንጅ ለመልካም ምሳሌነት መጠቀስ እንደማይገባው ራሱ ሲኖዶሱ በራሱ ይመስክራል፡፡ እርሰዎ የሲኖዶሱን ስህተት እንደ መልካም ምሳሌ አርገው ማቅረበዎ እኔ አይደለሁም ቀኖናችን ይቃወመወታል፡፡
ታዲያ ይህን ቀኖናዊ ተቃውሞ በአኮቴት ተቀብለው አመለካከተወን አስተካክለው፡ ለቤተ ክርስቲይናችንም የሚጠቅመው ቀኖናውን መከተል መሆኑን ተገንዝበው ፡ ሲኖዶሱ ብልጽግናን መከተሉን እርግፍ አርጎ ትቶ ቀኖናችንና ዶክትሪናችንን በመከተል እነ ፋንታሁን ጸንተው የቆሙበትን የቅዱስ እስጢፋኖስን ምሳሌ ይከተል ዘንድ በነካ እጀዎ በጽሑፍ የጥሪ መልእክት እንዲያቀርቡለት በትህትና እጠይቀወታለሁ ፡፡ ይህን ቢያደርጉ ለቆሙላት አገረዎም ለቤተ ክርስቲያናችንም እንደሚበጅ እርግጠኛ ሆኜ ልገልጽለወ እወዳለሁ፡፡
እግዚአብሔር መልካም መሪወችን ለኢትዮጵያ ይፍ