June 17, 2024
30 mins read

አገራችን አሁን ያለችበት እጅግ አጣብቂኝ ሁኔታ (እውነቱ ቢሆን)

በዚህች አጭር ጽሁፌ ሁለት ነገሮች ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፤ በወልቃይትና ራያ መሬቶች ጉዳይና ስለአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ዙሪያ፡፡

ስለወልቃይትና ራያ፦ እነዚህ ቦታወች ዱሮ የማን ነበሩ? በማን ስርስ ይተዳደሩ ነበር?  አሁንስ የማን ናቸው?? ለምንስ ይህንን ያህል ደም ያፋስሣሉ… ወዘተ ወደሚለው ጥያቄ ከማምራታችን በፊት መሬቶቹ በውስጣቸው ምን ቢይዙ ነው? አቀማመጣቸውና ጠቀሜታቸውስ ምንና እንዴትስ ቢሆን ነው …ሰወችን እንደዚህ የሚያጫርሱት …ወዘተ የሚሉ የመሳሰሉ ነገሮችን እውነታ እንመልከት፡፡ በቦታወቹ ላይ የሰፈረውንና ከጥንት ጀምሮ ይኖር የነበረውን፣ አሁን እየኖረ ያለውን ህዝብ ማንነትና በተለይም ማን ነው ባለርስቱ የሚለውን ጭብጥና እውነታ ከታሪክና ከመረጃ አኳያ ወደመጨረሻው አካባቢ እንፈትሻለን፡፡

ከሁሉም በፊት በሚገርም ሁኔታ ቦታወቹ እጅግ ለም ናቸው፡  ከዱሮ ጀምሮ እስካሁን ድረስ  ኢትዮጵያ ከሰሊጥና መሰል ቅባት እህሎች ወጪ ንግድ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ታገኝ የነበረው ከወልቃይትና በዙሪያው ካሉ ሰፋፊና በተፈጥሯቸው እጅግ ለምና ምርታማ ከሆኑ እርሻዎች ነው፡፡ ይህ እውነታ ማለትም የአፈሩ ለምነት እንኳን ከተከዜ ማዶ ይኖሩ የነበሩትንና የኢትዮጵያ መስራችም አካልም የሆኑትን ትግሬወችን ቀርቶ ከውጭ አገራትም  ሱዳንንም ኤርትራንም አልፎ ተርፎም አሁን ላይ የተባበሩት አረብ ኢምሬትንም ጭምር እያጓጓ ፣ እያስጎመጀ፣ እያስከጀለ መምጣቱ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡

ታዲያ አሁን ተረኛና ባለጊዜ የሆነው ኦሮሙማ በሆነ ዘዴ ማለትም እስካሁን ብአደንን አሽከሩም ምርኩዙም አድርጎ  የመጣበትን  (convince & confuse) ስትራቴጅን ተጠቅሞ፣ ወይንም በሌላ ‘በፌደራል ስር ይተዳደሩ’ በሚል ሰበብ ወይንም ቦታወቹን ከአማራው እጅ አስወጥቶ ለጊዜውና በሸፍጥ በተጋረደ ስታራቴጅ ራሳቸውን የቻሉ ክልል ይሁኑ በማለት’ ማታለያ ወይንም  በሌሎች መሰል የእጅ አዙር አካሄዶች ሆዳም አማራወችንም ጭምር ተጠቅሞ እነዚህን መሬቶች ቢመኝና ቢከጅል ይነወርበታልን?? እዚህ ላይ ኦሮሙማ ስንል “”ሁሉም የእኛ”” እና “’ከሁሉም በላይ እኛ””  በሚል ከንቱ አስተሳሰብ ውስጥ ተዘፍቆ የሚነዳውን የኦሮሞ መንጋ እንጅ ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ አለማለት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

በራያና አካባቢው ያሉ መሬቶችስ በውስጣቸው ምን ቢኖር ነው በኦሮሙማ አራጋቢነት አማራንና ትግሬን  እንደዚህ የሚያራኩታቸው የሚለውን ጉዳይ በትንሹ እንፈትሽ፡ ራያና አካባቢው ያሉት መሬቶችም ከወልቃይት ባልተናነሰ ሁኔታ ለም አፈር ያላቸው ሰፋፊና በተለይም   ለእርሻ፣  የከብት  ሀብት  ልማትና  ኢንዱስትሪ  የተጣመረና  ተመጋጋቢ  የሆነ ልማት  (Agro Complex Development) እጅጉን ምቹ ናቸው፡፡   ይህንኑ መሰረት አድርጎ ገና ከመነሻው አማራን በጠላትነት ከመፈረጅ ጀምሮ አማራን አርቆ በመቅበር ብሎም ጭራሹኑ  ለማጥፋት ጉዞውን አንድ ብሎ ጀምሮ 27 አመት በጥፋት ጎዳናው ከተጓዘ በኋላ አሁን ላይ ነገሮች ተቀያይረው እዚህ አሳፋሪ አወዳደቅ ላይ የደረሰው ወያኔ ያኔ ሁለቱንም ለም ቦታወች በቁጥጥሩ ስር አድርጎ በነበረበት   ወቅት ስለራያና በዙሪያው ስላሉት መሬቶች ትልቅ የልማት አቅም፣ በቂና ስርነቀል ጥናትን አካሂዶ ታላቋ ትግራይን እስከሚመሰርት ድረስ ጥናቱን በጠረጴዛ መሳቢያ ውስጥ ቆልፎበታል፡፡ እንደ ጥናቱ ዳሰሳ የልማቱ እቅድ በሚገባ ከተካሄደ በራያና በአካባቢው የሚካሄደው አግሮ ኮምፕሌክስ በዉጤቱ በአፈር መሸርሸርና ለብዙ ዘመናት በግብርና ስራ ለም አፈሯ የተሟጠጠውንና መሬቷ የተራቆተውን ትግራይን ብቻ ሳይሆን መላዋ ኢትዮጵያንና አልፎ ተርፎም ምስራቅ አፍሪካን ጭምር ሊያዳርስ የሚችል በቂ ምርትና ተረፈ ምርትን ያስገኛል፡፡ ስለመሬቱ ለምነት አሁን በገሀድ  እንደሚታየውም ተጨባጭ  እውነታው ይህ ነው ፤ ወያኔ የመሬቶቹ ባለቤት እከሚሆን ድረስ  መሳቢያ ውስጥ ቆልፎ ያስመጠውም ጥናትም የሚያሳየው ይህንኑ ነው፡፡

መሬቶቹ ይህንን ያህል ለምና ምርታማ በመሆናቸው ለዘመናት በተጎሳቆለ መሬት የግብርና ምርቷ እየተመናመነ የመጣባት ትግራይ እነዚህን ለም መሬቶች በአንድም ሆነ በሌላ ዘዴ ብትመኝ፣ በወያኔ የስልጣን አመታትም ለተወስኑ ጊዜያት በሀይል አማራውን ጨፍጭፋና አፈናቅላ እንደቆየችው የትግራይ ናቸው ብትል፣ አሁንም ከኦሮሙማ ጋር ተመሳጥራ ድጋሜ መሬቶቹን ለመውረር ብትሞክር ምን ነውር አለበት?? በተለይም በወያኔው 27 አመታት አገዛዝ ወቅት “’አማራን ወክሏል”’ የተባለለት የዱሮው ኢህድን ከዚያም ስሙን ወደ ብአደን የቀየረዉና አሁን በኦሮሙማ ጊዜም ደግሞ ለመጣው ጌታ ሁሉ የአሽከርነት ግብሩ እንዳለ ሆኖ ስሙን ወደ ‘የአማራ ብልጽግና’ የቀየረው ‘የሆዳም አማራ ትርፍ አንጀቶች ጥርቅም’ “”ብአደን”’ በአማራ ህዝብ ላይ ብዙ ወንጀሎች እንዲፈጸሙበት መሳሪያ ሆኖ አገልግሏል፡  የህዝብ ብዛት ቁጥሩን ከማሳነስ ጀምሮ ለጊዜውም ቢሆን ርስቶቹን አስነጥቋል፡፡ገና ያልተመለሱት ደራና መተክልም በምሳሌነት ይጠቀሳሉ፡፡ ብአደን ስለአማራ ህዝብ ጥቅምና መጎዳት ምንም ነገር ለማለትም ሆነ ለማድረግ ፍላጎትም አቅምም አልነበረውም፡፤ አሁንም የለውም፤፡ ችግሩ በውስጡ በመሪነት ተሰግስገው የነበሩት አማራ ያልሆኑት እነ አዲሱ ለገሰ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ በረከት ስምኦንና የመሳሰሉት ጉጅሌወች በድርጅቱ የመሪነት ቦታ ላይ መኖርም ጭምር ነበር፡፡ አሁንም አብይ አህመድ አማራን እየገደለው ያለው ከአብን እነ በለጠ ሞላን ከብአደን ደግሞ በካቢኔ አባልነት እነ ተመስገን ጥሩነህንና የመሳሰሉትን “አማራ ነን”  የሚሉ አህዮችን ይዞና እነርሱኑ ተመርኩዞ ነው፡፡ ስለዚህ አማራው ገና የራሱ የሆነ ትክክለኛ ወኪል ስለሌለው የራያና ወልቃይት ለም የአማራ ርስቶች በወያኔም በኦሮሙማ ከአማራው ሊነጠቁ ቢሞከር አያስደንቅም፡፤ ይህንን ለታሪክ እንተወዉና አሁን ስለ ፖለተካዉና እጅግ አሳሳቢ ስለሆኑት የእነዚህ መሬቶች ተጨባጫ ሁኔታወች እንመለስ፡፡

በታሪክ እነዚህ መሬቶች የአማራ ርስቶች ናቸው፡፤ ለዚህም ብዙ የታሪክና የድርጊት ማረጋገጫወች አሉ፡፡አንዷን ብቻ መዝዘን እንጥቀስ፡፡ የትግራይ ገዥ የነበሩት ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም ቃለ መጠይቅ አንዱ ነው፡፡ የትግራይ ገዥ የነበሩት ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም ከመሞታቸዉና  በድምጸ ወያኔ ተገድደው እንደገና ሌላ አይነት መግለጫ እንዲሰጡ ከመደረጋቸው በፊት በነጻ አንደበታቸው ስለ ቦታወቹ የትግራይ አለመሆን ጉዳይ ቁልጭ አድርገው አስረድተዋል፡፤ያሰረዱበት ጊዜና መረጃቸውም አሉ፡፡ይህ ብቻም አይደለም፡  ቦታወቹ የአማራ አጽመ ርስቶች ስለመሆናቸው ሌሎችም አያሌ የውጭና የአገር ውስጥ የጽሁፍ፣ የታሪክ መረጃወችም አሉ፡፤ በቦታው ያለዉና በፊትም ይኖር የነረወ ህዝብም ህያው ምስክር ነው፡፡

ታዲያ ቦታወቹን ወያኔ ለምኑ ፈለጋቸው ለሚለው ጥያቄ አንድ መልስ ብቻ በቂ ነው፡  ወልቃይት ለምነቱን ብቻ ሳይሆን ወደ ሱዳን መግቢያና መውጪያ በርነቱን ወያኔ አጥብቆ ስለሚፈልገዉና በእውን ያለችው ትግራይም የአፈሯ ለምነቱ እየትሟጠጠ በመሄዱ ለም መሬቶችን የያዘች ታላቋ ትግራይን እንደ አገር መመስረት ስለፈለጉ ነበር ወያኔ ያንን ሁሉ (ከስምንት መቶ ሽህ በላይ) የትግራይ ወጣቶችን ወደ እሳት የማገደው፡፡

የአሁኑስ ወያኔወች ከኦሮሙማ ጋር ከተጣመሩ በኋላ የጀመሩት አዲሱ የወረራቸው ሙከራና ሙከራውም ባይሳካ ራሱ ክጀላቸውም ቢሆን ያስኬዳቸዋልን የሚለው ጥያቄ ግራሞትን ይጭራል፡፤ ወያኔ ጠላቱ የነበረውን ተረኛውን የኦሮሙማ የጅቦች ስርአት አሁን ራሱ ዮሮሙማ ጥገኛና ተለጣፊ አጋሩ ሆኗል፡፡ አሁን ሁለቱም በጋራ አማራን ለማዳከም ስምምነት ላይ የደረሱበት ጊዜም ነው፡፡ በስምምነታቸውም መሰረት ቀዳሚ አላማቸው አማራን ማዳከም፣ መፍጀት፣ ማስራብና በማሰቃየትም አማራው እንድዳከምላቸው ማድረግ ነው፡፡ ይህ ቀዳሚ እቅዳቸው ሲሆን አማራውን የምኞታቸውንና የእቅዳቸውን ያህል በመናበብ ካደቀቁትና ከተዳከመላቸውም በኋላ ቀጣዩ እቅዳቸውን እውን ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ በቀጣይ እቅዳቸውም ወያኔ ወልቃይትንና እንዲሁም ራያን ጨምሮ ሰሜን ወሎን ደቡብ ትግራይ ብሎ ሰይሞ ታላቋ ትግራይን እንደ አገር መመስረትና ኦሮሙማ ደግሞ ደቡብ ወሎን ሰሜን ኦሮሚያ ብሎና በኦሮሚያ አራቱም ማእዘናት በዙሪያው ያሉትን ግዛቶቹን አስፋፍቶ በኢትዮጵያ መቃብር ላይ ታላቋን የኦሮምያ ሪፐብሊክ መመስረት ነው፡፤ ይህ ነው ሁለቱ  የተስማሙበት ዋና ግባቸው፡፡

ታዲያ ምን ያደርጋል አማራን ‘ጠላት ነው’ ብለው የተጣመሩት ኦሮሙማና ወያኔ አማራን ሳይወድ በግድ ገፍተው ገፍተው ጫፍ አደረሱት፡  በዚህም ጠላቶቹ ሆን ብለው ቁጥሩን የሚክዱትና ዝቅ የሚያደርጉት 56 ሚሊዮኑ የአማራ ህዝብ ‘ሞት ወይንም ነጻነት” ብሎ የነጻነቱ ተጋድሎ አብሪ ኮከብ ከሆነው ከፋኖ ጎን በአንዲነት ቆሟል፡፡ ፋኖ ደግሞ ከጠላቶቹ በየአውደ ዉጊያው በሚማርካቸው ትጥቆች አይነኬ ሆኗል፡፡የፋኖ የተጋድሎው መንሳኤም ልኑርበት ነው፡፡አትግደሉኝ ነው፡፤ ይህ ነው ስለአማራ ህዝብ መሬት ላይ ያለው እውነታና ወቅታዊው ተጨባጭ ሁኔታ፡፤

እቅዱ ይሳካል ወይ?? እንደ አማራ የህልዉና ተጋድሎ ዉጤትና እንደተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ንቃት ወደፊት የሚታይ ይሆናል፡፡ በአንድ ነገር ላይ ግን እርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል ፤ ወልቃይትና ራያ የአማራው አጽመ ርስቶች ስለሆኑ መሬቶቹ እንደ ካሽሚርና ጋዛ ሰርጥ ጦርነት የፈለገውን ያህል ጊዜ ይወስዳሉ እንጅ አማራው ርስቶቹን መቼም ቢሆን መቼም ለማንም አሳልፎ አይሰጥም፡፡

ቆም ብለን እናስብ፡፡ ፖለቲከኖቹን ወደጎን እናድርጋቸውና ከትግራይና ከአማራ ህዝብ የሚብስበት ይብሰበታል አንጅ ባለፉት የወያኔ 27 አመታት እንደታየው አማራው ርስቶቹን በወያኔ ተነጥቆ ዝም ብሎ እንዳልተቀመጠ ሁሉ አሁንም ወደፊትም ቢሆን አማራው ርስቶቹን በማንም አስወስዶ ዝም ብሎ እንደማይቀመጥ ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው የሚገባ ሀቅ ነው፡፡ጥቃትን መቀበል የአማራ ታሪክ እንዳልሆነ ጠላትም ወዳጅም ታሪክም አይክዱትም፡፤

የአብይ አህመድ የማይሳካ ቅዠትና ህልም ፦ ይህ ሁለተኛው የጽሁፌ መነሻ ነጥብ ነው፡፡ ጮርቃው አብይ አህመድ አገሪቱን እየበተናት ነው፡ አብይ ትምህርቱን ከ4ኛ ክፍል አቋርጦ ማራገቢያ እያዞረ ሲሸጥ የነበረ የበሻሻ ጭሎ(ልጅ) ነበር፡፡ ወደ ወያኔም ተጠግቶ ሬደዮ ኦፐርቴር ሆነ፡፡  ከዚያም ዶክተር ነኝ አለና የህዝቡ ጸረ ወያኔ ትግል ፍሬ ሊያፈራ ጫፍ ደርሶ በነበረበት ሰአት ድንገት ተከሰተና በአቋራጭ ቲም ለማን ትቀላቅሎ ቲሙንም አፈር ድሜ አስበልቶ ለዚህ አሁን ላለበት የስልጣን ማማ ላይ ደረሰ፡፡ አብይ ቦቅቧቃ ቢሆንም አደገኛ ሰው ነው፡፤ በጥቅሉ አደገኝነቱ የመነጨውም ፍጹም ፈሪና እልም ያለ መሀይም ከመሆኑ ነው፡፤ መሀይምና ፈሪም የሆነ ሰው ደግሞ ጭካኔው አያድርስባችሁ፡፡አያመዛዝንማ!!!

የሰውየው እርምጃወቹ በሙሉ መርህ፣ እውቀትና ብቃት ላይ የተመሰረቱ አይደሉም፡]፤ ማንም ይጎዳ፣ ማንም ይለቅ፣ ቢፈልግ አምስት፣ አስር፣ ሀያ ወይንም ሰላሳ ሚሊዮን ህዝብ ይለቅ ..ወዝተ ማንም ይሰደድ፣ ምንም ይሁን ምንም….ወዘተ አብይ የሚያስበው ስልጣኑ ላይ መቆየት መቻሉን ብቻ ነው፡፡ ሰውየው ይህንን የዘቀጠና የተበላሸ ማንነቱን ይዞ በታሪክ አጋጣሚም በብሄር በተከፋፈለ ህብረተሰብ ውስጥ ተከስቶ የአገሪቱን በዘር መከፋፈል አስፋፍቶ በመጠቀምና የክፍፍሉም ዋና መሪ ተዋናይ ራሱ በመሆን ልዩነቱን ወደአሰቃቂ መተላለቅ እያሳደገው 6 አመታትን ተጓዘ፡፤ በዚህም አረመኔያዊ ድርጊቶቹ በአገሪቱና በህዝቧ ላይ ብዙ ጉዳቶችን አደረሰ፡፤ አሁንም እያደረሰ ነው፡፡

እንደ አድራጎቶቹ ጸረ ህዝብነትና ሰውየው ከእወቀት የጸዳ እንደመሆኑ መጠን ህዝቡ ስር በሰደደ የዘር ጥላቻ እርስ በእርሱ የተናከሰ ባይሆን ኖሮ ሰውየው ገና ዱሮ አልቆለት ነበር፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል እውነታው ይህ ነው፡፤ እንደ አለመታደል ሆኖ አሁን አገሪቱ ውስጥ ያለው ወያኔ የዘራው በዘረኝነትና በጎሳ የተከፋፈለ አስተሳሰብ ሲሆን ከ27 አመታት በኋላም ላለፉት 6 አመት ኦሮሙማ እየኮተኮተ የሚንከባከበው በዘር የተከፋፈለ ህዝብ ነው፡ ወያኔ የዘረኝነትን መርዝ በኢትዮጵያ ውስጥ መትከሉ ብቻም ሳይሆ አገሪቱንም  ወደቧን እንድታጣ ትልቁን ሚና ተጫውቷል፡፡ ከስላሳ አመታት በኋላ ያ ድርጊት ማንን ጠቀመ?? ማንንስ ይበልጥ ጎዳ? ምናልባትም ሁኔታወች በዚሁ ከቀጠሉ ከሌላ ሰላሳ አመታት በኋላ ማን ነው መውጪያ መግቢያ አጥቶ መፈናነፈኛ የማያገኘው?? አስቡት፡፡ በዚያ ላይ አገሪቱ ተመልሳ ጠንካራ አገር እንዳትሆን ተግተው የሚሰሩ የውጭም የቅርብም ጠላቶቿ ቀና እንዳትል አሰፍስፈው እየጠበቋት ነው፡፡ ይህ ነው እውነታው፡፡

የአገሪቱ ህዝብ በዚህ ፈተና ውስጥ ወድቆ ባለበት በዚህ ወቅት አብይ አህመድ አገሪቱንና ህዝቡን ወደፈለገው የቁልቁለት ጎዳና እያጣደፈው ነው ፤ በጎን ከውጭ በጌቶቹና ለአገሪቱ ጥሩ በማይመኙ ስብስቦች በታዘዘው መሰረት የብልጽግና ወንጌል (PROSPERITY GOSPEL) የሚባል እምነት እንዲስፋፋ ተግቶ እየሰራ ነው፡፡ በሌላ ጎን እናቱ ዱሮ እንደነገሩት 7ኛ ንጉስ ለመሆን ሲቃዥ ዉሎ ሲቃዝ ያድራል፡፤ ከሌላ አንጻር ደግሞ አሁን ያለው የአገሪቱ ሸንጎ የእርሱ መጠቀሚያ እቃ ቢሆንም አገሪቱን አሁን ካለችበት ፓርላሜንታራዊ አሰራር ወደ ፕሬዝዳንታዊ ስርአት ወስዶ እርሱ የእድሜ ልክ ፕሬዝዳንት ሊሆን እየዳዳው መሆኑ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ በእነዚህ ሁሉ በማይሆኑ ምኞቶቹ የተሞሉት ያብይ አህመድ ጉዞወች ውስጥ በመሀል የታከነባትና ታዋቂ የሆነበት አንዲት ነገር አለች፡፤ ያቺም ነገር መበጥረቅ፣ ደጋግሞም መበጥረቅ ትባላለች፡፡በእውንም ነች፡፤ ሰውየው ውሸትና ማስመሰል ፈጽሞ አይሰለቸውም፡፤ የህዝብ እልቂት ለእርሱ ምኑም አይደለም፡፡ የፈለገው ቁጥር ህዝብ ቢያልቅ ስልጣኑ እስካልተነካ ድረስ አገሪቱን ወደ ልማት ህዝቡንም ወደሰላምና እድገት እየወሰድኩ ነው ብሎ ከመበጥረቅ አያቆምም፡፡ ከዚህ አንጻር መርዘኛው መለስ ዜናዊ በምን ጣእሙ???  አብይ አህመድ የአገሪቱ መከላከያና ደህንነት መስሪያ ቤቶች መኖሩን የማያውቁትና የማያዙትም ከአገሪቱ በሚወጣ ገንዘብ ዘመናዊ መሳሪያን የታጠቀ የራሱ እዝ ያለው የሪፐብሊካን  ጋርድ  የሚባል ለራሱ ልዩ ጥበቃ የሚያውለው ልዩ ሰራዊት አለው፡፤ ይህ ብቻም አይደለም፡ አብይ አህመድ ራሱ ያደራጀውና የሚመራው የራሱ የሆነ የሸኔ ቡድንም አለው፡፤ ይህ ብቻም አይደለም፡፡ የሰው ደም ጠጥቶ የማይረካው ጭራቁ አብይ አህመድ “ኮሬ ነጌኛ” የሚባል ራሱ ያዘጋጀውና የሚመራው ሌላ የኦሮሙማ ገዳይና አፋኝ ስኳድም አለው፡፡

በአገሪቱ ውስጥ ከ33 ሚሊዮን ህዝብ በላይ የውጭ ምግብ እርዳታ ጠባቂ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ከ4 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተስዷል፡፡ በአማራ ፣ ትግራይና ኦሮሚያ ውስጥ ሰላም የለም ብቻ ሳይሆን አብይ የአገር መከላከያ የሚባለውን ግብስብስ ጦሩን አሰማርቶ የራሱን አገር ህዝብ በታንክ፣ በመድፍ፣ በድሮን  እያጨረሰ ነው፡፤ ጦሩ የገበሬውን የእህል ክምር ጭምር  አያቃጠለ ነው፡፡  ሴቶችን እየደፈረ ነው፡፤ አብይ አህመድ ማለት ወጣቶችን ወደ ትምህርት ቤት ሳይሆን ወደመቃብር እየላከ፣ ንጹሀንን በጅምላ እየቀበረ ያለ ስርአትን በመምራቱ ይህንኑ በድፍረትና በኩራት በመመጻደቅ ጭምር ይናገረዋል፡፡

በመላው አገሪቱ ውስጥ ህዝቡ ደም እምባ እያላቀሰ እርሱና መንጋው ኦሮሙማ በአዲስ አበባ የድሆችን ቤት ያለህግ እያፈረሱ ከሚሰሩችው የኮሪደር ልማቶች፣ መጸዳጃ ቤቶች፣ የከተማ ውስጥ መንገዶች፣ መናፈሻ ቦታወችን ..ወዘተ ከመስራት ውጭ ለህዝቡ የሚጠቅምና የህዝቡን ችግሮች የሚያቃልል ተጨባጭ ነገር አልሰሩም፡፡ አብይ አህመድ በከተማዋ ውስጥ ያሉትን የታሪክ አሻራወቿን ሆን ብሎና አቅዶ እንደልነበሩ አድርጎ አጥፍቷል፡  በከተማዋ  ህጋዊ ይዞታና ድንበር ላይም ከአዳስ አበባ ከተማ አንድ የኦሮሙማ ማከላዊ ኮሜት አባልን እንደዚሁም ከሌላው ወገን ማለትም ከኦሮምያ ክልል አንድ ሌላ ተመሳሳይ የኦሮሙማ ማእከላዊ ኮሚቴ አባልን ‘’አደራደርሁና የከተማዋን የድንበር ውል አፈራረምሁ’’ ብሎ ከተማዋን ‘እቃ እቃ’ ተጫወቶባታል፡፡ እንጭጩ አብይ አህመድ የነጻ ገበያ ኢኮኖሚን እከተላለሁ እያለ የግል ቤቶችን ያለህግ ያፈርሳል፡፡ የግል ይዞታ ባለቤቶችን ይዞታቸውን ዜሮ አድርጎ ሜዳ ላይ ይጥላቸዋል፡፡ በቦታወቹም ላይ የራሱን ምርጥ የኦሮሙማ ባለሀብቶችንና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያንም የጥቅም ተከፋዮቹን ያስፍራል፡፡ “የተኪራይና አከራይ አዋጅ” እያለም ህዝቡን እርስ በእርሱ ለማናከስ የግል ቤቶቻቸውን ያከራዩ ባለሀብቶችን መብት ይገፍፋል፡፡ ነግሸባታለሁ በሚላት አዲስ አበባ ውስጥ ዘርን መሰረት ያደረገ የመንግስት የስራ ቅጥሮችን ያከናውናል፡፡ በአገሪቱ ውጥረት ነግሶ እያለ ሰላም ያለ በማስመሰል በአገሪቱ በአራቱም ማእዘናት ማድረግ የማይችለውን በከተማው ውስጥ ‘የአገራዊ ምክክር’ አጀንዳ ቀረጽኩ ይላል፡፤ አልፎ ተርፎም ለመጭው ምርጫው ዘመቻ መስል ነገር ከአሁኑ ጀምሮ ያለፉትን 6 አመታት ዜሮ ስኬቶቹን በውሸት ታጅቦ መበጥረቅ ጀምሯል፡፡አገራዊ ምክክርና ምርጫ ዝግጅት 90 ከመቶውየቆዳ ስፋቷ ሰላም በሌለባት አገር!!!

“የሚሉሽን በሰማሽ  ገበያ ባልወታሽ” ነው ነገሩ፡፡ ስለ በጥራቃው አብይ አህመድ አንድት ቃልን ብቻ ብለን እንጭርስ፡፡ “ አጃኢብ ነው”፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ከቦታ ቦታ በነጻ ተዘዋውሮ መስራትም መኖርም አይቻልም ብቻ ሳይሆን አይታሰብም፡፤ ታዲያ ይህ በሆነበት  እውነታ ውስጥ ተሁኖ የሰውየው ቅዠትና ዝቅጠት ስንቱ ተጠቅሶ ያልቃል???

3 Comments

  1. በጽሁፉ እንደተጠቀሰው አብይ አህመድ በአገሪቱ ላይ ብዙ ወንጀሎችን እንደሰራና አሁንም በመስራት ላይ እንደሆነ በገዛኡ መድረሻ ያታው የኢትዮጵያ ህዝብም፣ መላው አለምም፣ ምእራባዊዉያን አለቆቹም፣ መሪዋ ለፍናፍንቱ አብይ አህመድ የወንድ ፍቅረኛው የሆነችዋ ትንሿ ጥጋበኛ አገር አረብ ኢምሬትም ሁሉም ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡
    የአማራው ህዝብ የህልውና ተጋድሎ መሪ ፋኖ አብይንና መንጋውን ኦሮሙማ ህዝቡን ባሳተፈ ትግል ነቃቅሎ ይጥለዋል፡፡
    ያኔ አገሪቱ ወደ እውነታዋ ተመልሳ እንደ አድስ በጋራ የእኩልነት ጉዞዋን ትጀምራለች፡፡ ድል ለፋኖ!!!

  2. የሃበሻ ፓለቲካ ውሃ ወቀጣ ነው። ላስረዳ። በየዘመናቱ የሃገሪቱን የመከላከያ ሃይል የደርግ፤ የወያኔ፤ የብልጽግና ሰራዊት እያልን ከገዢው መደብ ጋር ማዛመድ ብቻ ራሱን የቻለ ስካር ነው። ማንም ሃገር በየትም ቦታ አንድን የመከላከያ ሃይል በገዢው መደብ ስም እየጠራ አፈር አይመልስበትም። እርግጥ ነው በንጉሱም ጊዜ ሰው ሺ ዓመት መኖር እንደማይችል እየታወቀ የንጉሱ ወታደር ሺህ አመት ያንግስዎ ይል ነበር። ቆይቶ የሆነውን አይተናል።
    ሃገሪቱን አጣብቂኝ ውስጥ የከተትናት ፊደል ቆጥረናል በማለት ከስማቺን ኋላም ሆነ በፊት ዶ/ር፣ ፕሮፌሰር፤ እንጂኒየር ገለ መሌ የምንልና አፈ ጮሌ ብሄርተኞች ነን። ዘመኑ ቆዬ – አንድ ትልቅ ከተማ ውስጥ ሌሊት ላይ በድምጽ ማጉያ ” ይህ የኢህአሰ ሰራዊት ድምጽ ነው” የሚል በተኩስ የታጀበ ነገር ተሰማ፤ ቀጥሎም መዝሙር የሚመስል ነገር በአውራጎዳናው ሲዘመርና ሲጨፈር አደረ፤ እነዚያ ዘማሪዎቹ ከታገቱበት እስር ቤት የተለቀቁ ነበሩ። ሲነጋ የሚሞተው ሞቶ የሚሸሸው ሸሽቶ ከምሳ ሰአት በፊት በራሽያ ሰራሽ ካሚዪን የተጫኑ ደም የጠማቸው የመንግስት ወታድሮች ከተማዋ ገቡ ከዚያ በህዋላ የሆነውን በቃል መግለጽ ይከብዳል። ግድያው፤ እስራቱ፤ ዝርፊያ፤ ፍተሻው አፈነው.. ከሰው ልጆች ባህሪ ውጭ በሆነ መልኩ ተፈጸመ። አሁንም እንሆ ይህ ፋኖ የሚባል ቡድን በዚህም በዚያም ተኩስ ከፍቶ ገድሎና ሞቶበት ሲፈረጥጥ ሃገር ሰላም ነው ብለው የተቀመጡ ሰላማዊ ሰዎችን የሃገር ወታደር በብቀላ መንፈስ አሰፍልፎ እንዲረሽናቸው ምክንያት ይሆናሉ። ግፍ ኢትዮጵያ ምድር አባርቶ አያውቅምና ደም ጠጥታ የማትጠግበው የሃበሻ ምድር ዛሬም የንጽሃን እና የቡያንን ደም ትጋታለች። እብድ ለመሆን ጨርቅ ማውለቅ አያስፈልግም። ሙሉ ገበርዲን ተለብሶም ማበድ አለ። ጦርነት የኋላ ቀርነት ምልክት ነው። ወንድምና እህቱን እየገደለና እያስገደለ ነጻነት ብሎ ነገር የለም። በአለም ላይ ካሉ ሃገሮች ኢትዮጵያ የጦርነትን አስከፊነት ለመረዳት የኋላ ታሪኳ በቂ ነበር። በውጭ ወራሪ ተወረናል። እርስ በእርስ ተላትመናል። አሁንም የምናደርገው ይህኑ ነው። ፓለቲከኞች ልበ ቢሶች ናቸው። ካለፈ ታሪክ አይማሩም። ዛሬ በመንግስት ሃይሎችና በተፋላሚዎች የሚደረገው ውጊያ የነጻነት ሳይሆን የሰቆቃና የሞት ምንጭ ነው። ማቆሚያውም አይታይም።
    አስተሳሰባችን ከመሻገቱ የተነሳ በአንድ ሃገር ውስጥ እያለን በክልል የአፓርታይድ ፓለቲካ ታጥረን ይህ የእኔ ነው ያ የአንተ ነው ስንል አለማፈራችን። የትግራይ ህዝብ ፍጽም ኢትዮጵያዊ ነው። የወያኔን ሸንካላ ፓለቲካ ወደ ጎን ትተን ኢትዪጵያ ያለ ትግራይ ትግራይ ያለ ኢትዪጵያ ኑረው አያውቅም። ይህ ሃቅ እንጂ ከሚያልፍ ወንዝ የተጨለፈ ጉዳይ አይደለም። የአማራ ህዝብ ደግሞ በምድሪቱ በብዛት ከተበተኑት ወገኖች መካከል ቀዳሚው ነው። ታዲያ በምን ሂሳብ ነው ይህ ምድር የእኔ ያ ስፍራ ያንተ የምንለው? አሁን ማን ይሙት በእኛ ሃገር ዘርና ማንዘሩን ይቅርና 200 ዓመት ወደኋላ ተመልሶ ይቅርና የመቶ ዓመቱን የሚያሰላና እርግጠኛ የትውልድ ሃረጉን የሚነግረን ይኖራል? ጭራሽ። የብሄር ሰካራሞች እንደሚሉት ሳይሆን ህዝቡ ድብልቅ ህዝብ ነው። ቢሆንና ቢቻል ኑሮ ሁላችንም የዝሪያ የDNA ምርመራ ብናደርግ ውጤቱ አምነን ከተቀበልነው የፈጠራ የፓለቲካ ጉንጉን የራቀና የወል የሆነ ውጤትን እንደሚያሳየን ቅንጣት አልጠራጠርም። የኦሮሞን ባህልና ወግ ብሩህ የሚያደርገው ሌላው ሲቋደሰው እንጂ ቡናውን እስከ 3ኛ ለብቻ መጠጣቱ ለምርቃቱ አይመችም። በጋራ ሲኖሩ ሁሉም ደስ ያሰኛል። ይህ ለእኔ ብቻ የሚለው የጽንፈኛ ብሄርተኞች ፓለቲካ ሁሉን አስለቃሽ እንጂ ለማንም ጠቃሚ አይሆንም። አሁን ያለውን የአፓርታይድ የክልል ፓለቲካ ሳስብ አንድ ያነበብኩት መጽሃፍ ትዝ ይለኛል። ጸሃፊው Frantz Fanon የመጽሃፉ አር ዕስት Black Skin White Mask. ቁጭ ብለን አሁን ያለውንና በፊትም የተላለቅንበትን ጉዳይ ስናሰላው ውጤቱ ዜሮ ነው። መገዳደል፤ ሰው ማፈናቀል፤ መዝረፍ፤ ተመልሶ መዘረፍና መገደል የድግግሞሽ ፓለቲካ! እኔን የናፈቀኝ ለሰው ዘር በጎነት ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነትና እኩልነት እታገላለሁ የሚል እንጂ ቋንቋውንና ክልሉን ተገን አርጎ በብሄርተኝነት ተንኮል ሌላውን እያሰቃየ ለእኔ ብቻ የሚለውን ድርቡሽ ማየት አይደለም።
    ዛሬ ላይ ካለፈው የፍትጊያ እሳት ተርፈው ትዝታዬ፤ ትውስታዬ፤ አብዪቱና ገለ መሌ ወዘተ እየተባሉ ለንባብ የበቁት መጽሃፍቶች ሁሉ ራስን ከሃላፊነት ያገለሉ እውነትን የማይናገሩ እያወቁ ደብቀው ሚስጢርን እንደያዙ ዛሬ አፈር ተመልሶባቸው ምስጥ የሚበላቸው ስንቶች ናቸው? እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደር የሚለው ያ ባህላዊ አነጋገር ዛሬ ላይ እውነት ተናጋሪም የመሸበት የሚያሳድርም የማይገኝባት ምድር ሆናለች። ያኔም አሁንም የምለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡ ተው እናንተ ጠበንጃ አንጋች ሃይሎችና መንግስት ሁሉን ነገር በውይይትና በሰላም ለመፍታት ታገሉ። መገዳደሉ ይብቃ። ሃገራችን ለባሰ መከራና ሰቆቃ ለመዳረግ የሚደረገው ይህ የኦነግና የፋኖ ፍልሚያ በድርድር ይለቅ። አራት ኪሎ ስንገባ ገለ መሌ መባሉ የፓለቲካ ድንፋታ እንጂ ፍሬ ነገር የለውም። አራት ኪሎ ቢገባም ከሚሊዪን ኪሎ የሚከብድ የሃገሪቱ ችግር እላይህ ላይ ይጫናል። ኢትዮጵያውያንኖች በሰላም የሚኖሩባት ሃገር የምትመሰረተው በሰላማዊ መንገድ እንጂ በደም ማፋሰስና አንድ አንድ በማፈናቀልና በመግደል አይደለም። የትግራይ መሬት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። የአማራ መሬት የሁሉም የትግራይ ተወላጅ ነው። ምድሪቱ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የጋራ እንጂ የክልልና ያካላዪች አይደለችም። ጊዜ እያለ እንንቃ!

  3. ተስፋ የተባልከው ተስፋ ቢስ!
    አንተ ሁልጊዜም ቢሆን በጥራቃውን አብይ አህመድን ሽዕንቆጥ የምታደርግ መጣጥፍ ካገኘህ አብይን ለማዳን የማትዘባርቀው እንርቶ ፈንቶ የለም፡፡ መጀመሪያ አገሪቱ ውስጥ የፖለቲካና የዘረኝነት ችግር ስለመኖሩ እመን፡፡ይህንን ካመንክ ችግሩ ለምን ተፈጠረ፣ ማን ፈጠረው፣ ብለህ መርምር፡፤ ጠይቅ፡፡ እንዴት ይፈታ ለሚለው ጥያቄ መልስህን ስጥ፡፤
    የአንተ መፍትሄህ ውይይት አድርጉ ነው፡፤ይህ ባልከፋ፡፤ ማንና ማን ነው መፍትሄ የሚወያየው?/የሚፈልገው?/

    መንግስትህኮ ከፋኖ ጋር አልደራደርም፣ ፋኖን አላውቅም፣ የአማራን ህዝብ እጨርሳለሁ ብሎ መንጋ ጦሩን አሰማርቶ ህዝቡን እያረደው ነው፡፤ ይህንን መንግስትህ አላደረገም ካልክ ነገሩ እዚሁ ላይ ያልቃል፡፤
    በጥላቻ የ56 ሚሊዮኑ የአማራ ህዝብ ደም አፋሽና ብቸኛ አለኝታ የሆነውን ፋኖ ብትሳደብ፣ ብታንቋሽሽ ፣ብትረግም፣ ብትጠላ በፋኖ የድል በድል ጉዞ ላይ ቅንጣት ለውጥ አታመታም፡፤ ምክን ያቱም ፋኖ “”አትግደሉኝ”” የሚለውን የአማራ ህዝብ ይህልውና ጥያቄ አንግቦና ህዝቡን ከጀርባው አሰልፎ በሚማርከው መሳሪያ እየተደራጀና በድል ጎዳን እየገሰገሰ ያለ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለኢትዮያ ህዝብከተታመረው የኦሮሙማና የወያነ የሤራ አገዛዝ ነጻ መውጣት አንዱ አለኝታ ሀይል ስለሆነ ነው፡፡፤ አሁን ገባህ ወይንስ አውቀህ እንድተኛህ ነው፡፤ አረመኔው የኮሬ ነጌኛ አዛዥ አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ እንዳላዋጣት ሁሉ ለአንተም አያዋጣህም፡፡ እስከዚያው ካልክም ሳንቲምህን ልቀም!! ግን ቁርበት ነህ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

a64cb 1888482 10204388455532537 8607573277156755926 n
Previous Story

ሳሙኤልም እንደ እስጢፋኖስ!

191248
Next Story

እውነተኛ ባለቤቶች| የወልቃይት ጠገዴ አርበኞች| ጣልያን እንኳን በቋንቋ ተናጋሪዎች አገሪቱን በከፈፈለበት ውቅት ወልቃይት የአማራ ነበር

Latest from Blog

የኢሰመኮ ሪፖርት እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው። የአብይ አህመድ ሰራዊት በአማራ ክልል በሶስት ወራት ብቻ የፈፀመው ጭፍጨፋ በመንግስታዊው ኢሰመኮ ሪፖርት ይፋ ሁኗል።

©ሰኔ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ሌሊት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው የታጠቀ ቡድን (በተለምዶ “ፋኖ”) አባላት ከክልሉ አዊ ብሔረሰብ ዞን፣ ቲሊሊ ከተማ አሽፋ ቀበሌ እንደወጡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ወደ ቀበሌው በመግባት ሰኔ 3 ቀን

 የአብይ አስተዳደርና የዶ/ር ብርሃኑ አኒ-ሚኒ-ማኒሞ

የጠ/ሚ አብይን የ2017 ዓ.ም. እንኳን አደረሳችሁ መልእክትን ከፌስቡክ ገጻቸው ላይ አነበብኩት፡፡ዘመኑ ላይ ተፈላሰፉበት ወይስ ምንድን ነው ነገሩ? ዘመን እድል ነው አሉን፡፡ እድል ማለት እንደ አማርኛው መዝገበ ቃላት ትርጉም ከሆነ እጣ ክፍል፣ ግንባር
Go toTop