ባሳለፍነዉ ሳምንት ወሎ ወስጥ በሚገኙ የፋኖ ብርጌድና ክፍለጦር አመራሮች መካከል በተደረገ ስብሰባ፣ አንድ የወሎ እዝ ለመመስረት ስምምነት ላይ ተደርሷል። በዚህም ስብሰባ ላይ አዲስ ለተቋቋመዉ የአማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ አመራሮች ምርጫ ተካሂዷል። አማራ ፋኖ በወሎ ዕዝ ከሁሉም በተወጣጡ ተወካዮች በአብላጫ ድምፅ የተመረጡ ዋና አዛዥ :- ኮሎኔል ፈንታው ሙሀባ ምክትል አዛዥ:- ዋርካው ምሬ ወዳጆ አስተዳደር:- አለምነህ መብራቱ ሎጂስቲክ:- ኮሎኔል ሞገስ ብርሀኔ ፖለቲካ ዘርፍ:- ሻፊ ሀብታሙ ሌሎቹም በዚሁ ዕዝ የሚዋቀሩ ይሆናል ።