December 9, 2023
2 mins read

የዳንኤል ክብረት ቅኔ

danielጭራቅ አሕመድ ማለት ሥጋ ለብሶ የሚሄድ ውሸት ነው ብሎ ለጦቢያ ሕዝብ መናገር ለቀባሪው ማርዳት ነው።  ይህን ሥጋ ለብሶ የሚሄድ ውሸት የሚያማክረው ደግሞ አቶ ዳንኤል ክብረት ነው።  አቶ ዳንኤል ክብረት ደግሞ ጭራቅ አሕመድን እየሱሴ ብሎ ሞቱንም ሽረቱንም ከጭራቅ አሕመድ ሞትና ሽረት ጋር እንዳይፈታ አድርጎ በጥብቅ አቆራኝቷል።  ጭራቅ አሕመድ ደግሞ እየሞተ ስለሆነ፣ ዳንኤል ክብረትም እየሞተ ነው።  ስለዚህም ዳንኤል ክብረት እስትንፋሱ እስክትወጣ ደረስ መዋሸቱን መቀጠል ብቻ ሳይሆን፣ የውሸቱን ዓይን አውጭነት እየጨመረ ይሄዳል።  ባጭሩ ለመናገር አቶ ዳንኤል ክብረት በውሸት ዝናብ መበስበስ ብቻ ሳይሆን ስለሾቀ፣ የውሸት ፍራቻው ሙሉ በሙሉ ጠፍቶለታል።  ሲዋሽ የሚቆጠቁጠው ሕሊናው ሙቶ ስለተቀበረ፣ ለመዋሸት ገደብ የለውም።

ዳንኤል ክብረት ገደብ የሌለው ውሸታም ነው ማለት ግን ውነት አይናገርም ማለት አይደለም።  አቶ ዳንኤል ክብረት በመጠኑም ቢሆን ቅኔ ተምሯል።  ያስተማረችው ደግሞ ጭራቅ አሕመድን እየሱሱ ካደረገ በኋላ ሊያጠፋት ቆርጦ የተነሳባት ተዋሕዶ ናት።  ቅኔ ደግሞ ሰም በመጥቀስ ወርቅ መናገር ነው።  ስለዚህም አቶ ዳንኤል ክብረት “ፋኖ ባሌስትራውን ሰብሯል፣ የቀረው ምላስ ብቻ ነው” ሲል በወርቅ የተናገረው ስለ ፋኖ ሳይሆን ስለጭራቅ አሕመድ ነው።  የጭራቅ አሕመድ ጨፍጫፊ ሠራዊት ስለፈራረሰ፣ እሱ (ማለትም ዳንኤል ክብረት) እና ጭራቅ አሕመድ ጣረሞት ላይ እንደሆኑና ግብአተ መሬታቸው በቅርቡ እንደሚፈጸም መርዶውን ለመናገር የፈለገው ለጭራቅ አሕመድ ነው።  ችግሩ ግን የበሻሻው ደንቆሮ ቅኔ አለማወቁ ነው።

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

                                                         ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)                                                       ጥር 12፣ 2017(January 20, 2025) ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለማስረከብ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው በአሜሪካን ምድር በጣም አደገኛ የሆነ የኦሊጋርኪ መደብ እንደተፈጠረና፣ የአሜሪካንንም ዲሞክራሲ አደጋ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል ተናግረዋል።  ጆ ባይደን እንዳሉት በተለይም በሃይ ቴክ

አሜሪካ ወደ ኦሊጋርኪ አገዛዝ እያመራ ነው! ጆ ባይደን ስልጣን ለመልቀቅ ጥቂታ ቀናት ሲቀራቸው የተናዘዙት!!

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

Go toTop