ይድረስ ለብልፅግና ፈረሶች!

እርግጥ ነው እንስሳው ፈረስ ባለቤቱ ካዘዘው የተፈጥሮ የማገናዘብ ብቃት እና ችሎታ ስለሌለው የተጫነውን ተሸክሞ የመሄድ ግዴታ አለበት ፣ ሰው ሆነ ዕቃ። በስነ-ፅሁፍ ክትብ “አንተ ሰው እንደ ፈረስ ዝም ብለህ አትጋለብ” ሲባል  የፈረሱ እና የሰው የባህሪ ማንነት ሲነፃፀር (Personified) ሲሆን ለየት ያለ ትርጉም ይኖረዋል።

ፈረስ ጨው ከላሰ እና የግብስ ፍታጊ ካገኘ ለባለቤቱ ታዛዥ መሆን የግድ ይለዋልና ጋልቦ ወይም አሸክሞ “ቸ -ፈረሴ” ካሉት  ሳይቅማማ ይጓዛል።

የብልፅግና ተላላኪ እና ጋሻ ጃግሪዎች ደግሞ ገንዘብ እና ጥቅማ ጥቅም ከተሰፈረላቸው አዙሮ ማሰቢያቸው ነውልሎ “ሰዋዊ እንስሳ (ፈረስ ፣ አጋስስ)” ይሆኑና ቀልብ የሚሰፍርላቸው ብልፅግና የሚላቸውን ብቻ በመስማት እና በመቀበል “ ይጎዳናል ፣ አይጎዳንም ፣ አዋጭ ነው አይደለም ፣ ሃገርን ያጠፋል አያጠፋም ፣ ነገ ተጠያቂ እንሆናለን ፣ አንሆንም የሚለውን ቀሊለ ሃሳብ ሳይገናዝቡ በዘፈቀደ ይነጉዳሉ።

“አያ በሬ ሆይ ሳሩነን አይተህ ገደሉን ሳታይ” እንዲሉ የብልፅግና ፈረሶች ወደፊት በሃገር ሆነ በእነሱ ላይ የሚደርሰውን ፈተና ፣ ውድቀት እና መከራ ሳያገናዝቡ የአለቆቻቸው የነብልፅግናን የስልጣን ዘመን ተራዝሞ ፣ የሚወረወርላቸውን ዳረንጎት እና ጥቅማ ጥቅም ብቻ በማሰብ  ሲራወጡ ላየ “ሰው ስው የማይሸቱ” የሰው ቅራሪዎች መሆናቸውን ያሳያል።

የነ ብልፅግና ግፈኛ ላህላይ መሪዎች ውሳኔያችንን ፣ ፍላጎታችንን ወደ ህዝብ አውርዱ ፣ አስተጋቡ ፣ ተደናግራችሁ አደናግሩ ፣ ሰይጣናዊ የሆነውን  እስከ መግደል ማስገደል ፣ ማሳስር እና ማሰቃየት ጥግ ድረሰ ያለውን ህሳቤያቸውን” አስነግበው እንደ እንስሳ ሲናዷቸውና ይህን እኩይ ዓላማቸውን ተጋላቢዎቹ ፈረሶች ለማስፈፀም የሚሄዱበት ጥግ እና “ተፍ -ግፍ” ሲሉ ላየ ስባሃዊ ማንነታቸው እንደመከነ ያሳያል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ - ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

እንግዲህ በአሁኑ ሰዓት በሚታየው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ሃገር “ከድጡ ወደ ማጡ” እየነጎደች በሕግ አውጭው ፣ ሕግ አርቃቂው ፣ ሕግ አስፈፃሚው እና ሕግ ተርጓሚው የተሰገሰጉ ስግብግቦች አስተሳሰባቸው ተሰልቦ እና ማውጣት ማውረድ ተስኗቸው ተቯሚዎች የአለቆቻቸውን እንቶ ፈንቶ ንግግር ፣ ውሳኔ እና አካሄድ “እንደገደል ማሚቶ” በየመድረኩ ሲያስተጋቡ ሲታይ እና ሲሰማ ከማስገረም አልፎ የተጋቱት “አሺሽ አለ ወይ” የሚያሰኝ ነው።

እንደዚህ አይነት ተጋላቢ “ባዶ ገረወይናዎች እና አጨብጫቢዎች” ለሆዳቸው ያደሩ ከመሆናቸው የተነሳ መሪዎቻቸው መድረክ ላይ ወጥተው ማንም የሚረዳውን ተራ ልፈፋ ፣ ተቀድቶ የመጣን መነባንብ እና የወረደ ህሳቤ በመስማት ይደመማሉ ፣ በተመስጦ ይሰማሉ ፣ ይጋታሉ።  “ከዕወቀት ነፃ” መሆናቸው ጥያቄ አይጠይቁም ፣ አይመረምሩም።

መማር ፋይዳ በራስ ላይ “የባህሪ ለውጥ” ማምጣት ፣ እውነታን ለይቶ መገንዘብ፣ ማመዛዘንን እና መፂሃ ችግሮችን አንጥሮ በማውጣት አብዛኛው ሕዝብ ከያዘው አቋም እና ህሳቤ ጎን መሰለፍ ቢሆንም እነዚህ ነፍስ ያላቸው ፈረሶች ግን ከዚህ ሁሉ የራቁ በደመነፍስ የሚንቀሳቀሱ ሙተው የሚራመድ ( A walking dead body) አይነት ሰው ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም

በመንግስት ስልጣን ቁንጮ ላይ የተቀመጠ መሪ እና ቡድን “ያውም ታላቁን የአማራን ሕዝብ አጠፋለው “ ብሎ ሲነሳ እና ሲያውጅ “ግፋ ወደፊት” ብሎ ጦርነት አብሮ መጎሰም በደመ ነፍስ የተቆሰቆሰ ጦርነት በአግባቡ ሳያገባድዱ እና ሳይቋጭ “ቀይ ባሕር ነው የኛ መዳረሻ” ተብሎ በብልፅግና የጦርነት ህሳቤ ሲታወጅ ተጋላቢዎቹ የብልፅግና አሽቃባጬች አብረን ቀይ ባህር ላይ መዋኘት አማረን” ማለታቸው ዘይገርም የሚያስኝ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ገዢ ቢሰባ ለመሬት አህያ ቢሰባ ላራዊት

“ጋኖች አለቁና ምቸቶች ጋን ሆኑ” እንዲሉ እና አንድ ድምፀ መረዋ ዘፋኝ “አገሬ ሰው አጣሽ” ብሎ” እንዳቀነቀነው “ሰው ጠፋ ሆይ” ብለን ተስፋ እንዳንቆርጥ በአሀኑ ሰዓት ይህን የጠነዛ ፣ የገለማ ፣ እሚይዘውን እና የሚጨብጠውን ያጣውን የብልፅግና መንግስት የሚፋለሙ ባለ-ምጡቅ አዕምሮ ያላቸው እና ቆራጥ ወንድሞች በየዱር ገደሉ ፣ በርሃው እና ጣሻው እየተፋለሙ ፣ በድል እየገሰገሱ ፣ በለውጥ ማእዛ የሽታ ወላፈን እያስደመሙን እና “መጣን ፣ መጣን እና ደረስንላችሁ” እያሉ በመሆኑ ፣ ለታላቁ አምላክ ምስጋና ይግባውና የወደፊት ተስፋችን ብሩህ እና የድል እሸታችን የምንናጭድበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን ጥርጥር የለውም።

ይህ የብሩህ ተስፋ ህሳቤ እውን ሁኖ የድሉ ነጋሪት ሲጎሰም ያኔ እናንተን አያርገን ፣ መግቢያችሁ የት ይሆን ፣ በሰራችሁት ትርኪ ምርኪ ህሳቤ ፣ ተለጣፊነት እና አጨብጫቢነት ምድር እንቅራ ስትተፋችሁ” አየታየን በመሆኑ ሳይረፍድ “የማይረባን ጭድ ተሸክማችሁ መጋለቡን ወደ ጎን በማድረግ ከተገፋው ሕዝብ ጎን ተሰለፉ ዘንድ” በአፅንኦት እንጠይቃችዋለን።  

የሰው ልጅ ካለፈው ይማራል ፣ ደርግ ስርዓት ከብልፅግና ስርዓት የከፋ ባይሆንም ፣ በህውሃት ባለስልጣኖች ፣ ፍርፋሪ ለቃሚዎች እና አጨብጫቢዎች የደረሰው ዕጣ ፈንታ እንዳይደርስባችሁ እናሳስባለን።

የመዋጋት አቅም የሌለውን ፣ በቅጡ ስልጠና ያልወሰደ እና በእውር ድንብር የጠብመንጃ ምላጭ የሚስብ የአንድ ቡድን ሰራዊት እየላካችሁ የዋሁን ፣ አቃፊውን ፣ ሃገር ወዳዱን እና ሰላማዊውን የአማራ ሕዝብ ማስጨረሱ እና ማንገላታቱ  በብልፅግና ፈረሶች እና አሽቃባጮች የሚደርሰው ምላሽ የከፋ ስለሚሆን ከወዲሁ እስቡበት እያልን  “ምከረው ምከረው ካልሆነ መከራ ይምከረው” እንዲሉ የእናንተ ጦስ ሌላ መከራ ፣ፍዳ እና ፍጅት ሳያስከትል” እጃችሁን ከወዲሁ አጣጥፋችሁ ትቀመጡ ዘንድ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ብልጽግና ከወያኔ ጋር ቢደራደር ምንድን ነው የሚኮነው ? - ግርማ ካሳ

የአማራ ሕዝብ ያሸንፋል!!

የፋኖ ትግል በቅርቡ በድል ፋና ያሸበርቃል!!

ተዘራ አሰጉ

ከምድረ እንግሊዝ።  

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share