ኢትዮጵያ ወደ ነበር ታሪካዊ ታላቅነት እና የከበረ ብሄራዊ ስም እና ጥቅም ማስከበር እና ለማንበር የኁሉም ኢትዮጵያዉያን ምኞት እና ፍላጎት ነበር ነዉ ፡፡
ዛሬ ላይ ኢትዮጵያዉያን ከሶስት አሰርተ ዓመታት አስቀድሞ አስከ ዛሬ ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያ ሲባል ትምክህተኛ ፣ ኤርትራ ከእናት አገር ኢትዮጵያ መለየት የለባትም መሆን ከነበረበት ህዝበ ዉሳኔ ይኑር ሲባል ነፍጠኛ ፣ የቀደመ ስርዓት ናፋቂ ፤ እንዲሁም ኢትዮጵያ ያለ ወደብ እንድትኖር ለምን ሲባል ወደብ የሚል መንገዱን ጨርቅ ያድርግልህ የተባለዉ የዓማራ ህዝብ በዋናኘነት የሚጠቀስ ነዉ ፡፡
ለዚህም በሽግግር መንግስት ምስረታ አገር ለማጥፋት ሳይሆነር አገር ለመታደግ ነዉ በዚህ የሽግግር መንግስት ጉባኤ የተገኘሁት ሲሉ ፕ/ር አስራት ወ/የስ ተናግዋል ፤ ተንብየዋል ፡፡
በርግጠኝነት በጊዜዉ የኢትዮጵያን ህዝብ እና ምሁራን ወክየ የተገኘሁት አገር ለማፍረስ እና የኢትዮጵያዉያን የአብሮነት ትስስር ለማደፍረስ ከተሰበሰቡት የጥፋት ኃይሎች ጋር በጉባኤ ለመሳተፍ መገኘቴ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና የህዝቦችን የሉዓላዊነት ለማስከበር በመሆኑ ከዚህ በተቃራኒ ለመስማማት የራሴም ሆነ የወከለኝ ኢትዮጵያዊ ፍላጎትና አቋም ባለመሆኑ የጥፋት ጉባዔዉ አካል ላለመሆን በመወሰን ራሳቸዉን አግልለዋል ፡፡
ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ እንዲህ ዓይነት ታሪካዊ እና ትንቢታዊ የዕድሜ ልክ ለትዉልድ እና አገር ወርቃማ ዘመን ተሻጋሪ ዉሳኔ የወሰኑ እረሳቸዉ ብቻ መሆኑ የዘመናችን አኩሪ የህዝብ ልጂ ፤የግንባር ስጋ የዕዉነት እና የሠዉነት ልዕልና የነበራቸዉ መሪ ፤አስተማሪ ነበሩ ፤ናቸዉ ፡፡
እንግዲህ ዛሬ ላይ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት ፤ ስለህዝቦች አብሮነት ፣ ስለ ሠላም ፣ ፍትህ ፣ ዕርቅ…….የሚወተዉቱ በኢትዮጵያዊነት ስም የሚምሉ የሚገዘቱ ያኔ ከሽግግር (ኢህአዴግ) መስረታ ጀምሮ እና ከዚያ በፊት አስከ ዛሬ በኢትዮጵያ እና ህዝቦች ላይ ከፋፋይ እና አግላይ ሴራ ሲጎነጉኑ የነበሩ ናቸዉ ፡፡
ለአብነት አንዱን ዜጋ ወይም ማህበረሰብ ከሌላዉ በጠላትነት መፈረጂ ማለትም ጨቋኝ፤ ተጨቋኝ፣ ስለ አገር እና ብሄራዊ ጥቅም መናገር ትምክህተኛነት፣ ድሮን ናፋቂነት ፣ጦረኝነት /ነፍጠኝነት…እየተባለ ብዙኃን ኢትዮጵያዉያንን (ዓማራ) ከሁሉም በሁሉም ነገር መንቀል እና ባዕድ ነገር መትከል የተጀመረዉ ከሽግግር መንግስት ምስረታ ማግስት እንደነበር ከትናንት ያስታዉሷል፡፡
ይህም ኢትዮጵያዊነትን እና ኢትዮጵያ የምትባል አገር ከነስሟ ለመንቀል የሚደረግ የጥላቻ ሴራ ኢትዮጵያ የምትባል አገር በጥቂቶች ወርድ እና ቁመት የምናብ ምድር ማድረግ ፣ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ጨርቅ ማለት፤ ትምክህተንነት (በራስ መተማመን) ከምድር ለማጥፋት ዓማራ የሚባል ህዝብ በየትኛዉም ረገድ ማክሰም ከ18ኛዉ ክ/ዘመን መባቻ ቢነሳም በተግባር ዕዉን የሖነበት የኢህአዴግ ሽግግር ጉባዔ እና የዚህ የበኩር ልጂ ህገ -ኢህአዴግ ነበር ነዉ ፡፡
ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ላይ በኢህአዴግ እና በኢትዮጵያዉያን መካከል በተለይም የዓማራ ህዝብ እያነሳ ያለዉ የማንነት እና የህልዉና ጥያቄ እና ትግል ዛሬ ላይ እንደ ደራሽ ዉኃ እንደሆነ አድረገዉ ሊያደናግሩ የሚፈልጉ የዚያን ዘመን የሽግግር ጊዜ እና የህገ ኢህአዴግ ተገልጋዮች እና አገልጋዮች ናቸዉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ዓማራ ህዝብ በ1ኛዉ ሆነ በ2ኛዉ የአርባ ዓመታት ልዩነት ጊዜ ዉስጥ ወራሪዉ እና ዕብሪተኛዉ የኢጣሊ ቀኝ ገዥ ስርዓት ናፋቂ ኢትዮጵያን ምድሯን ለመርገጥ ፤ ግዛት ለማስፋፋት የዕግር ዕሳት የሆነበት የዓማራ ህዝብ የጠለያየ ስያሜ የተሰጠዉ ያንጊዜ በነበሩ የዉጭ እና የዉስጥ አድር ባይ ከኃዲ ጠላቶች ነበር ፡፡
የዓማራ ህዝብ የነፃነት እና የአንድነት የትግል ሜዳ መጠሪያ የሆነዉ የዕምቢተኝነት ማግ እና ድር “ ፋኖ ” የሚል የአርበኝነት ተጋድሎ መጠሪያ በስፋት መዋሉን ልብ ማለት ያስፈልጋል ፡፡
ይህ ማለት ፋኖ የሚለዉ የትግል ዓርማ ስያሜ ከ18ኛወዉ ክ/ዘመን ቀድሞ አልነበረም ማለት እንዳልሆነ ተጨባጭ ሁነቶችን ከዚያ በፊት መኖራቸዉ ህያዉ ማስረጃዎች ናቸዉ ፡፡
ይኸዉም ኢትዮጵያ የ፭ ሽ ፭፻ ዘመን ዕድሜ ያላት አገር መሆኗን አስካልተካደ በዚህ ዘመን የነበሯት ግዛቶች መጠሪያ እና አስካሁንም የሚገኙት ባለቤትነታቸዉ የኢትዮጵያ የሆኑ የሚያሳዩት የኢትዮጵያዉያን የግዛት እና አንድነት ፣ ነፃነት እና ህልዉና ትግል መጠሪያ የሆነዉ ፋኖ ከኢትዮጵያዊነት ዉጭ ሌላ ትርጉም ወይም ታሪክ ሊኖረዉ እንደማይችል ከበቂ በላይ ምስክርነት ሊኖር አይችልም ፡፡
ኢትዮጵያ ዉስጥም በስነቃል ፣ በብሄራዊ ቅስቀሳ….ስለ ፋኖ የነበረዉ የቀደመ ዘመን ከሚያስታዉሱን በተጨማሪ ኢትዮጵያ እንደ አገር ከኖረችበት ጊዜ አስካሁን ፋኖ በሚል የሚጠራ መንደር ኢትዮጵያ ዉስጥ ስለመኖሩ መጠራጠር የለብንም ፡፡ እዚህ ላይ ስለዚህም ሆነ ስ ኢትዮጵያ ታሪክ ያሳስበናል የሚል የታሪክ ሊቅ ካለ ቦታዉን ለማወቅ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለአካባቢዉ ኗሪ ትተናል፡፡
በመጨረሻም ኢትዮጵያ ወደነበር ገናናቷ ተመልሳ ፣ በመላዉ ኢትዮጵያ ፍቅር እና መከባበር ነግሶ ፣ ሠላም እና ወንድማማችነት እንዲሰራፋ ስንፈልግ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ጥላቻን ነቅለን የዕዉነት እና የአንድነት ቡቃያ ለማየት ከመራር ዕዉነት መነሳት አለብን ፡፡
ለዚህ መራር ሀቅ ፋኖ ከሌላ ዓለም የተከሰተ ፍጡር አለመሆኑን መረዳት እና ማስረዳት አለብን ፡፡ ፋኖ የትግል ፋና ወጊዎች የሚከተሉት የነፃነት ፣ አንድነት እና ህልዉና የተጋድሎ ዓርማ /መጠሪያ/ብራንድ እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጂ እና በኢትዮጵያ ምድር ከጥንት አስከ ዛሬ የነበር ፤ ያለ ነዉ ፡፡
ይህ ከሆነ ትንቅንቁ ያለዉ በኢትዮጵያዉያን እና ኢትዮጵያዉያን መካከል ሳይሆን በኢትዮጵያዉያን በተለይም ዓማራ ኅዝብ እና እንዳለፉት የግፍ እና የመከራ ዘመናት ሁሉን ዓሜን በል በሚለዉ ድርጂት ኢህአዴግ መካከል ነዉ ፡፡
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘላቂ እና ዕዉነተኛ ፍትህ፣ሠላም ፣ አንድነት እና ብሄራዊ ጥቀም እንዲመጣ ከተፈለገ ችግሩን ከነስሩ ማወቅ ወደን ሳይሆን ተገደን የምንቀበል መሆን አለብን ፡፡
የኢትዮጵያ ህዘውብ ማለት በኢትዮጵያ የግዛት ዳር ድንበር የሚኖር እና ኢትዮጵያዊ ትዉልድ ያለዉ የሰዉ ልጂ ሁሉ ከሆነ ኢትዮጵያ የከዉድቀት የምትድነዉ የኢትዮጵያዉያን ችግር እና ህመም መረዳት እና ማዳን ሺቻል ብቻ ነዉ፡፡
ዕዉነቱን ማወቅ ራሳን እና አገርን ብቻ ሳይሆን ጠላትንም ያድናል ፡፡ ዛሬ ላይ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ -በዓማራ ህዝብ -ላይ ዕየተካሄደ ያለዉ ጦርነት አበዉ በማር ጠብታ አገር ተመታ እንዲሉ በጥቁር ጠበመንጃ ይገባናል ባይነት ይሁን እንጂ የረጂም ዘመናት የነበር የመኖር እና ያለመኖር “ ህይወት ወይም ሞት” የህልዉና ጉዳይ ነዉ ፡፡
ይህ ከሩቁ ትተን ከግንቦት ሀያ አስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ ሶስት ማግስት ጀምሮ በዓማራ ህዝብ እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች ላይ የተገመደ የጥፋት ሴራ እና ያስከተለዉ መዘዝ ብዙ የትግል እና ለዉጥ ጥያቄወችን አስከትሎ ስንቶች መስዋዕት ሆነዉ ማለፋቸዉን ማስታወስ ዛሬ ኢትዮጵያ እንደ አገር የምትገኝበትን የጥፋት ወጥመድ እንድታልፍ ለመፍትሄ ስለሚበጂ ነዉ ፡፡
ኢትዮጵያ አገራችን የሁላችን መጠጊያ እና መከለያ አስከሆነች ከምትገኝበት የዉድቀት እና የጥፋት ወጥመድ ታልፍ ዘንድ ኢትዮጵያን ለማዳን የኢትዮጵያዉያን አንድነት እና ህብረት ወሳኝ ነዉ ሲባል የአንድን አካል ብልት ለያይቶ መመልከት ሆነ ለመለያየት እና ለማጥፋት መሞከር የማይነጠለዉን ለመንጠል የማይቆም ተላላፊ በሽታ ለማባዛት እና ይህም ሁሉንም የሚያጠፋ ነዉ ፡፡
በዓማራ ህዝብ የሚነሱ እና የተነሱ የማንነት ፣ የነፃነት ፣ የአንድነት ፣ የዕድገት እና የህልዉና ጥያቄ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድነት እና ሉዓላዊነት ረብ ያለዉ ወቅታዊ እና ዘመኑን የዋጀ መሆኑን መረዳት ኢትጦጵያን እና ህዝቧን ብቻ ሳይሆን ጠላቶቻቸዉንም ከዳግም ጥፋት የሚታደግ በመሆኑ ፋኖ እና ኢትዮጵያዊነትን ለያይቶ ከማሳየት ጭራ ስንጠቃ ወጥን በሚበጂ እና በሚያረጂ ነገር ላይ እናተኩር ዘንድ ማስተዋል ይስጠን፡፡
ከዕዉነት መሸሽ መዳረሻ የለዉም እና እኛ ስንድን የአገራችን መዳን በመሆኑ በዕዉነት ስንስማማ ሁላችንም በጋራ ወደ ዕድገት ማማ መዉጣት እንችላለን ፡፡ ይህ አስካልሆነ በመማል ከሆነ ላሟ የዕኛ ናት የሚለዉ ተረት ለማንም አይጠቅምም፡፡
“አንድነት ኃይል ነዉ !”
Allen!