በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ በመንግስታዊ እገታ ሥር የሚገኙት እነ ክርስቲያን ታደለና ዮሐንስ ቦያለውን ጨምሮ ሌሎች የማንነት፣ የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች ከነገ ጀምሮ የርሃብ አድማ እንደሚያደርጉ ገለጹ፤

እኛ በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታግተን የምንገኝ የማንነት፣ የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች ከነገ ሰኞ መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሚከተሉት ነጥቦች ምክንያት የርሃብ አድማ አድርገናል፡፡

  1. በአማራ ሕዝብ ላይ የተከፈተውን የዘር ፍጅት፣ ጅምላ ጭፍጨፋ እና ማንነት ተኮር ጥቃት በመቃወም፤
  2. በአማራዊ ማንነታችን ምክንያት በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታግተን የሚደርስብን የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የሕክምና እጥረት፣ የምግብ እጥረት በመቃወም፤
  3. በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ከፍርድ ቤት እውቅና ውጭ ታግተን ለፍርድ ባለመቅረባችን፤ ለከፍተኛ የበሽታ ወረርሽኝ እንዲሁም ለከፋ የአየር ንብረት ሙቀት መጋለጣችንን በመቃወም፤
  4. በታገትንበት ካምፕ ውስጥ የሥርዓቱ ገዳይ ቡድን የሚያደርስብን የግድያ ዛቻ፣ አማራ ተኮር ስድብ፣ ማስፈራሪያና ማንቋሸሽ በመቃወም፤

በመሆኑም በእነዚህ ከላይ በጠቀስናቸውና ሌሎች ምክንያቶች የርሃብ አድማ እና መሰል እርምጃዎችን ተፈጥሯዊ መብታችንን ተጠቅመን የምንጀምር መሆኑን እየገለጽን የፍትሕ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ተቋማት በመንግሥት ላይ ተጽዕኖ በማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እንጠይቃለን፡፡

ግልባጭ፦

ለኢሰመኮ

ለእንባ ጠባቂ ተቋም

ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማት

ለአውሮፓ ሕብረት

ለተባበሩት መንግሥታት

 አቤት ፍርሃት: አዲሱ የኢትዮፕያ ኪም ጆንግ ኡን

ተጨማሪ ያንብቡ:  በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት አንድ አስገራሚ የሰርግ ስነስርአት ተከናውኗል

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share