እንድረስላቸው!
አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 3 (በተለምዶ ዋናው ንግድ ባንክ) በር ላይ በእግረኛ መንገድ ስር ከተቀበረ ቱቦ ውስጥ የፊጥኝ ታስረው የታገቱ ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠናል። ከንግድ ባንኩ ፊት ለፊት የፖሊስ ጣቢያ ያለ ሲሆን ፖሊሶች ሌሊት ላይ ሰዎችን ከተለያዬ ቦታ እያፈኑ ቱቦው ውስጥ እንደሚከቱ ተረጋግጧል።
ATM የሚጠቀሙ ሰዎች “ውሃ … ውሃ” የሚል ድምፅ ሰምተው የቱቦውን በር ሲከፍቱ በርካታ ሰዎች የፊጥኝ ታስረው ተመልክተዋል። የዓይን ምስክሩ “የተጎሳቆሉና ለሞት የሚያጣጥሩ እጅና እግራቸው የታሠሩ ሰዎችን አይቻለሁ፤ ውሃ ገዝተን ስናቀብል ፖሊስ መጥቶ አባረረን” ብሎኛል። ATM የሚጠቀሙ እናቶች እያለቀሱ ቢያንስ ምግብ እንስጣቸው ቢሉም ፖሊሶች እየደበደቡ በትነዋቸዋል።
በአቅራቢያው ያላችሁ ወገኖች ሂዳችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።
ህዝብ ያሸንፋል!