ግናው የዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የእህት ልጅ!
/
የዛሬ አስር አመት ገደማ ነው። ደቡብ ኮርያ እንደነበርኩ ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ወደ ደቡብ ኮርያ ይመጣል። ይህ ሰው በወቅቱ የተወሰን ሰዎች ሳንሰማ ኮርያ ውስጥ ከሚኖሩ ከአንዳንድ ኢትዮጵያውያንን ጋር ስብሰባ ለማድረግ ወስኖ ስብሰባው በታሰበው ሰዓትና ቦታ ይጀመራል። ከፍ ሲል እንዳልኳችሁ ይህንን ስብሰባ እኔ አልሰማሁም። ለግል ጉዳይ ስብሰባው ከሚካሄድበት አካባቢ እሄዳለሁ። በዚያ አንድ ኢትዮጵያዊ ወንድሜን አገኘሁ።
ይህ ወንድም ወደ ኮርያ ከመጣ ገና ጥቂት ጊዜው ነውና በደንብ አንተዋወቅም።
የሆነ ሆኖ ሰላም ከተባባልን በኋላ
” ዛሬ ስብሰባ እንዳለ ታውቃለህ?” ይለኛል
እኔ አላውቅም። የምን ስብሰባ? ብየ ጠየኩት
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የሆነ ሆቴል ተከራይቶ ኢትዮጵያውያንን ሊያነጋግር ነው። ስለዚህ እንሂድና ለህዝባችን ድምጽ እንሁን….. ለሃገራችን ድምጽ እንሁን…… የዚህ አገር ሚዲያዎችም ስለሚኖሩ ጉዳዩ ትኩረት ያገኛል። ለታሰሩ ወገኖች ድምጽ እንሁን…. እንሂድ ….. እንሂድ……እንሂድ…… አለኝ።
እኔም እንዲህ አይነት አክቲቪስት ሳገኝ ደስ አለኝና ሁለታችንም ተነስተን እየበረርን ከስብሰባው ቦታ ደረስን። ቀስ ብለን ከስብሰባው አዳራሽ ተቀመጥንና ስብሰባው ሲጀምር ድምጽ ማሰማት ጀመርን።
ለውጥ እንሻለን….. ለውጥ…ለውጥ …… እያልን ጮህን። የነበቀለ ገርባንና የነ እስክንድርን ስም እየጠራን ይፈቱ…… ይፈቱ…… ኢትዮጵያውያን ነጻ ይሁኑ….. የሚል ድምጽ አስተጋባን። የጸጥታ ሰዎች ከስብሰባው አስወጥተው እሲኪያሰናብቱን ጮህን።
ወደ ውጪ በፖሊሶች አማካኝነት ከወጣን በኋላ። የሆቴሉን ጊቢ ለቀን እንድንወጣ ተነገረን። በዚሁ መሰረት ጉዞ ወደ ሰፈራችን ጀመርን……
እዚህ ቪዲዮ ላይ ከእኔ ጎን ቆሞ ከፍ ባለ ድምጽ ወያኔ ዘረኛ ነው……. ዘረኛ ነው….. ዘረኛ ነው….. እያለ የሚጨኸው ትንታግ ወጣት ጋር ተያይዘን ጉዞ ቀጠልን። ከስብሰባ ስንወጣ አንድ አብሮን የነበረ ሰው አብሮን ነበርና ይህንን ትንታግ ወጣት እያየ
“ቤተሰብ ምን ይል ይሆን? አጎትህን…. ” እያለ ያወራል።
ፈጠን ብዬ ይህንን ወደ ስብሰባ እንድሄድና ተቃውሞ እንዳሰማ የቀሰቀሰኝን ከጎኔ ሆኖ ወያኔ ዘረኛ….. እያለ ይጮህ የነበረውን ወጣት አየሁት
ምንህ ነው ዶክተር ቴድሮስ? አልኩት
አጎቴ ነው። የእናቴ ታላቅ ወንድም ነው……. ።
የውነትህን ነው?
“አዎ ትናንትናም በግል ሊያገኘኝ ልኮብኝ እምቢ ብዬው ነው። አገር እያፈረሰ ለእኔ አጎት ቢሆን ምን ይሰራልኛል ብለህ ነው? የእሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርነት ለእኔ ምኔም አይደለም” አለኝ። ወጣቱ ትንታጉ የቴድሮስ አድሃኖም የእህት ልጅ…………….ታሪኩ….ታሪክ ሰራ።
እምቢ ዘረኝነት ማለት አለብን ጎበዝ። የብሄር ፖለቲካ በቃ! ኢትዮጵያውያን ልክ እንደዚህ ወጣት ዘርና ብሄር ሳይገድበን ለፍትህ ከተነሳን በርግጥ ሀገራዊ ህብረታችንን እንጠብቃለን!
# Ethiopia
ገለታው ዘለቀ