ሙሴ፣ ሱስ፣ የዓባይ፣ ሽምግልና፣ እርቅ፣ ስልቻ ቀልቀሎ በሚሉ ማታላያዎች አማራን ማጭበርበሩ ይበቃል!

እውነቱን ሲነግሩት የአማራ  ሕዝብ ማድረግ ያለበትን ያውቃል!

 

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

#image_title

እንደ ፍካሬ እየሱስ መደገም ያለባት የአርበኛውና የደራሲው የክቡር አቶ ሀዲስ አለማየሁ ትዝታ መጽሐፍ እንደምታስረዳው አምስቱ ዘመን እየተባለ በሚታወቀው የሁተኛው የጣሊያን ወረራ  ወቅት እንደ ክቡር ሀዲስ ያሉ በዘመናዊ ትምህርትም ሆነ በሃይማኖታዊ ትምህርት ፊደል የቆጠሩ ምሁራን ሕዝባቸውን በጽሑፍ፣ በትያትርና በሌሎችም መንገዶች ሌት ተቀን ያነቁ ነበር፡፡ በሕዝቡና በአገሪቱ የመጣበት ጠላት እርስቱን የሚቀማና አገር አልባ እንደሚያደርገው ተቻለም ተምድር እንደሚያጠፋው ተግተው እውነቱን ያስተምሩ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የሚታመኑትን የልጆቹን ትምህርት የሰማው ሕዝብም ሞረሽ ተጠራርቶ ጣሊያኖች ወደ ተቆጣጠሩት ትግሬ ጠቅላይ ግዛት እንደ ልማዱ ዘመተና ተዋደቀ፡፡

አማራ ትግራይ ጠቅላይ ግዛት በሚዋደቅበት ወቅት ከአድዋው ጦርነት ትምህርት የቀሰመው ፋሽሽት አማራንና የተዋህዶ ቤተክርስትያንን ለማጥፋት አማራ ጨቋኝ እንደሆነና ሌሎች የአገሪቱ ዜጎች ከጣሊያን ጋር ወግነው አማራን እንዲወጉ ሰበከ፡፡ ለዚህ የፋሽሽት ስብከት የገበሩት እነ አባ ጆቢር እንደ ዛሬው ሁሉ አማራን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ያባርሩ ነበር፡፡ እነ አባ ጆቢር የአማራን ራስ ቆርጦ ላመጣ 30 ብር እሰጣለሁ እያሉ በአማራ ላይ የዘር ፍጅት መፈጠም ጀምረው ነበር፡፡  (ትዝታ ገፅ 166-167)፡፡ የዘሩን ፍጅት ያስቆመው ከሰሜን ወደ ደቡብ ምዕራብ ስልታዊ ማፈግፈግ አድርጎ የተዛወረው የጥቁር አንበሳ ጦር ነበር፡፡

በእኛ የልጅነት ዘመንም የመንግስት መናወጥ አገር መፍረስ የመሰለው ዚያድ ባሬ ድንበር ጥሶ ሀረርጌ እንደገባ ሲነገረው በሰላም ጊዜ አራሽ በጦር ዘመን ተኳሽ የሆነው አማራ ያሳዬው መረባረብ ዛሬም ተአይምሮዬ ትኩስ  ነው፡፡  ከገበያ ዳር በድምፅ ማጉያ “አገርህ ተደፍራለች! አገርህን ጠላት ወሯታል” ተብሎ ሲነገራቸው ሊሸጡ ያመጡትን እህልና ከበት በትነው ቤተሰቦቻቸውን ሳይሰናበቱ እያቅራሩና እየፎከሩ ለመዝመት ከቀረበላቸው ክፍት መኪና በእሽቅድድም የገቡት አርበኛ ወገኖች ዛሬም ከዓይኔ ናቸው! መኪናው ሞልቶ በመቅረታቸው ጸጉራቸውን የነጩት ጎበዛዝትና “ግንባር-ግንባሩንን ብላችሁት በድል ተመለሱ” እያሉ የተንጎራደዱት ወይዛዝርት ዛሬም በህሊናዬ የሚመላለስ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  [የለንደኗ ጽዮን ቤ/ክ ጉዳይ] ወፈ ግዝት! - የምንኩስናን ሥርዐት ያጎደፉ፣ ጣምራ የቀበሮ ባኅታውያን

አማራ እውነቱ ሲነገረው የሚያድርገውን የሚያውቅ ሕዝብ ነው፡፡ አማራ እርስቱን ተነጥቆና አገር አልባ ሆኖ ዝቅዝቅ እየታዬ ከመኖር አለመኖርን የሚመርጥ ሕዝብ ነው፡፡ አማራ የመጥፋት አደጋ የተደቀነበት እውነቱ እየተደበቀ የማጭበርበርያ ቅጥፈት ሰለባ ስለሆነ ነው፡፡ አማራ የተጨፈጨፈው ህዳሴ፣ ግድብ፣ ሙሴ፣ ሱስ፣ አንድነት፣ ተዋልደን ተካብደን፣ ይቅርታ፣ ሽምግልና፣ እርቅ በሚሉ የሆዳም ምሁራን ድስኩር ስለተጭብረበረ ነው፡፡ አማራ ለጥቃት የተዳረገው እንደ አድዋውና አምስቱ ዘመን የተደቀነበትን አደጋ በትክክል የሚያስረዱ እንደ ሀዲስ አለማየሁና አስራት ወልደየስ ያሉ ምሁራን  ብዙም ስለሌሉት ነው፡፡

አማራ ዛሬ የሚያስፈልገው ድምጣቸውን አጥፍተው ሆዳቸውን ሲቆዝሩ ኖረው እንደ ቅምቡርስ ለመሞት የቆረጡ ወይም በራዲዎና በተሌቪዥን መስኮት ጣታቸውን እያፍተለተሉ እንደዚሁም ጀንዲ እሚያካክል ከንቱ ጠልሰም እየጠለሰሙ ግድብ፣ ዓባይ፣ ሙሴ፣ ሱስ፣ የይሁዳ ሽምግልና፣ የጅላንፎ እርቅና ሌላም ሌላም ቅራቅንቦ የሚሰብኩ ከርሳም ጋዜጠኞች፣ ምሁራንና ካህናት እንዳልሆነ የሃምሳ ዓመቱ የአማር እልቂት ትምህርት ነው፡፡ አማራ ዛሬ የሚያስፈልገው እንደ አድዋውና እንደ አምስቱ ዘመን የተደቀንበትን አደጋ በደንብ አስገንዝቦ እንደ ንብ ተሞና ተናድፎ ራሱን እንዲከላከልና ሌሎችንም ነጣ እንዲያወጣ  የሚነግሩ የአድዋውና የአምስቱ ዘመን ዓይነት ምሁራንና ካህናት ነው፡፡

አማራ የመንፈስ ዝቅተኝነት በሽተኞች ሰለባ የሆነው እውነቱ ስላልተነገረው ነው፡፡ እውነቱ ሲነገረው አማራ የሚያደርገውን የሚያውቅ ሕዝብ ነው፡፡ አማራ እውነቱ ሲነገረው እንኳን ራሱን ሌላውንም ነጣ ያዋጣ ሕዝብ ነው፡፡ ስለዚህ አማራ እርስትና አገር አልባ ሆኖ ተምድር እንዳይጠፋ የፈለገ ጋዜጠኛ፣ ምሁር ወይም ካህን እንደ አበያ በሬ መተኛቱና መልመጥመጡን አቁም እንደ አድዋውና እንደ አምስቱ ዘመን ምሁራንና ካህናት ድስኩር ሳያበዛ እውነቷን እቅጯን ይንገረው፡፡ አስመሳይና ሆዳም ጋዜጠኛ፣ ካህን ወይም ምሁር በዓባይ፣ በግድብ፣ በይሁዳ ሽምግልና፣ በጅላንፎ እርቅ፣ በሱሳም ሙሴና በሌሎችም ስልቻ ቀልቀሎዎች አማራን ማታለል ይብቃው፡፡ አመሰግናለሁ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የከንቲባው ፍጻሜ…!! (ከመምር ዘመድኩን በቀለ የቴሌግራም ገጽ የተወሰደ)

ግንቦት ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share